ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#አረ ደሴ ደሴ
ገራዶ ገራዶ
አለቀልሽ ልቤ ተንዶ ተንዶ

       የደሴ አዝማሪ ጎበዝ ባለቅኔ
       ልቡን ከናደችው መሰስ ብሎ ገባ
      ደሴ ደሴ እያለ ልቧን እየባባ

እኔ ጅል አዝማሪ ድንቄም ባለቅኔ
ልቤን የናደችው ብታንፍቀኝ ዛሬ
ደሴ ደሴ እል ጀመር በናፍቆት ታስሬ

    መገን ደሴ ደጉ ሀይቅ ነው ባህሩ
    ባህሬ ናፍቃኝ ነው ከዚ ከሀገሩ
    መገን የኔ ባህር አቦ ናፍቀሺኛል
   አይኔም እርቦሻል ከዚ ከመንደሩ

አዝማሪው ባህሩ ቃኜ የወለደው
እሹሩሩ ብሎ ፍቅሩን የወሰደው
የኔን ባህር አምጣ እሹሩሩ ብለህ
ባህሬን አምጣልኝ አካሌ ሳይሳሳ
ወዲህ አስገባልኝ ናፍቆቴኔም ልርሳ

      መጀን የኔ ባህር
      ከአይኔ ማጠፋው
     ከልቤም ማትርቀው
    ያቺ መወከሌ የልቤም ምላት ሰው
 
ዛሬ ልቤን ንዳ እንዲህ ብትናፍቀው
 ዜማውን ወዲያ ከቶ ብታስረሳው
ብዕሩን አነሳ ያ ጅሉ አዝማሪው
ለአፍ የተሾመው ድንቄም ባለቅኔው

                             በብላቴናው (ለባህሩ)

@getem
@getem
@getem
👍1
#ምንሼ #ነው #ጋሼ
ባለፈው ተዘርፈን ~ ስንደነባበር
አራዳ ነኝ ብለህ ~ ነግረኸን አልነበር
ታዲያስ ያራዳ ልጅ
እኛ ነጋ ስንሞት ~ ጠባ ስንገደል
እዛ እናንተ ግቢ ~ ሁሉ ፒስ ነው አይደል?
አረ ረ ረ …………… ሼ
ያራዳ ልጅ ብዬ ~ እኔ ራሴ አንግሼ
ጀለስካ ነው ብዬ ~ ዙፋኑን ለግሼ
ሞተን አለቅን እኮ ~ ምንሼ ነው ጋሼ
#አረ #ምንሼ #ነው
ያራዳ ልጅ ብለን ~ ፈቅደን እንድትመራን
ቆጥበን ቆጥበን
በጠራራ ፀሀይ ~ ጨቡ ምታሰራን ?
አረ ምንሼ ነው
ባላየ ላሽ እያልክ ~ ምታስጨፈልቀን
ካለፈ በኋላ
ፍሉካ ከች ብለህ ~ በወሬ ምትጨምቀን
#ምንሼ
ያራዳ ልጅ ሆነህ ~ ፋራን ምትወክለው
መቃብራችን ላይ ~ አበባ ም‘ተክለው
#ምንሸት #ነው
መለኛ ነህ ስንል ~ በተስፋ ትንበያ
አረ አታወዛግበን ~ አትሰክሰን በያ

አምነን እንዳንተኛ ~ አራዳ ነው ብለን
ወይ ከተነቃቃን ~ አልባንንም በለን

የአራዳ ልጅ ጭዌ ~ ላራዳ ባይጠፋም
እንዲህ መጨካከን ~ ጨርቆስን አይነፋም
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
@getem
@getem
@getem
👍1