ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ነው_እንዴ?



በ እንጀራ ከሞላ ሌማቱ፤
ወጡም ካለ በየዓይነቱ፤
የቱን ልብላ ቢል እንጂ ሰው፤
ሳይጓጓ ነዉ የሚጎርሰው።


ከጎደለ ግን መሀዱ፤
ኩርማን ሲቀር ከመሶቡ፤
ወጡም ባይጥም የተብላላው፤
ሰው ጣፍጦት ነው የሚበላው።


ሞልቶ ተርፎ ንቆት ኖሮ፤
ችላ ያለው ተደርድሮ፤
ብላ ሲባል ትዝ ያላለው ተለምኖት ባለመዋል ፤
እፍኝ ሲቀር ከጎተራው ማለቁን ሲያይ ይጥመዋል።


ሰሞኑን ...
ከወትሮ ገነነ ፍቅርሽ በጣም ጣፈጥሺኝ ውዴ፤
ሊያልቅ ነው መሰለኝ ልንለያይ ነው እንዴ?

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
40👍34😁11🔥4😱4😢3
#ነው_እንዴ?



በ እንጀራ ከሞላ ሌማቱ፤
ወጡም ካለ በየዓይነቱ፤
የቱን ልብላ ቢል እንጂ ሰው፤
ሳይጓጓ ነዉ የሚጎርሰው።


ከጎደለ ግን መዓዱ፤
ኩርማን ሲቀር ከመሶቡ፤
ወጡም ባይጥም የተብላላው፤
ሰው ጣፍጦት ነው የሚበላው።


ሞልቶ ተርፎ ንቆት ኖሮ፤
ችላ ያለው ተደርድሮ፤
ብላ ሲባል ትዝ ያላለው
ተለምኖት ባለሟል ፤
እፍኝ ሲቀር ከጎተራው
ማለቁን ሲያይ ይጥመዋል።


ሰሞኑን ...
ከወትሮ ገነነ ፍቅርሽ
በጣም ጣፈጥሺኝ ውዴ፤
ሊያልቅ ነው መሰለኝ
ልንለያይ ነው እንዴ?

#ሄኖክ_ብርሃኑ (@yeneeyita)
@getem
@getem
@getem
👍6217😁5😱3🤩3👎2🎉2