ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#በቅንነት__በኩል
#ትንሽ__እንቸኩል

እንኳን መ'ረንበት
_ እሬት ሆነን ለሰው . . .
ለመክሰል ለመቁሰል
____ ኑሮ መች አነሰው ?

ለዕለት ጉርስ
ለዓመት ጨርቅ ____ ለአንዲት ቁራጭ ታዛ
ደም እየገበረ
ላብ እየሠፈረ ____ ተስፋ ለሚገዛ

ያለ'ድሜ
ለሚጎብጥ ____ ለመልካችን አምሣል
ለመክሰል
ለመቁሰል ____ ሕይወት መቼ ያንሳል ?

ምናለበት ታድያ
__ ከሁሉ ዓይኖች ጋራ __ በቅን መተያየት ?
ሸክም ላለ'በት ሰው
__ ውለታ ሳይቆጥሩ _ ትንሽ ይቅር ማለት ?


°°
ትንሽ : ለፈገግታ
ምክንያት : ማፈላለግ
በደግነት : ማከም
የሕመምን : ፈለግ
ቃል : አለማ'ራገብ
የምላስን : እሳት
እየሰሙ : ማለፍ
ቶሎ : ቶሎ : መርሳት

ከአፍ : እየቀደሙ ____ ፍቅር : ብቻ : መልቀም
ሰውን : በዚህ : መውደድ
ሰውን : በዚህ : ማከም
በሰዎች : ድካም : ውስጥ ___ እራስን : ማየት : መቻል
ለእግዜርም _ ለእራስም __ ለሰውም : ይመቻል

°°

መውቀስ
መክሰስ
መርገም
የሳቱትን : መድገም
እንኳን : ድኩም : ገላን ____ነፍስን : ያሰለቻል !

ዓለምም
ፍጥረትም
ዘመንም
ሕይወትም
እውነትም
እምነትም
___ ሳይደርሱበት : ያልቃል ፤
አንድ : ሰው
አንድ : ልብ
አንድ : ዕድሜ
አንድ : አካል
እንኳንስ : ለክፋት ____ ለፍቅር : መች : ይበቃል ?

°°
ታዲያ . . .

ለዚህ : ሁሉ : መግቻ
ለዚህ : ሁሉ : መፍቻ
ለዚህ : ሁሉ : መርቻ

| ቶሎ : ቶሎ : መውደድ ____ ይቅር : ማለት : ብቻ |

••
የበለዙ ልቦች
___ በተስፋ እንድንኩል
በቅንነት በኩል
___ ትንሽ እንቸኩል
••
°°
Seifu Worku

@getem
@getem
👍8245🔥6🎉3👎1😱1