ወደድኩሽ .....ጅል እስክሆን
ሄድሽ ደሞ .......ያንን ሰሞን
አንቺዬ
የተነሳሽበት ማልደርስበት መንገድ
ናፍቆትሽን ይዤ ዘላለም ል'ራመድ
ከበደኝ
ቀድሞውንስ መች ቀለለኝ።
ታድያ ይሄን እየሰማሽ
እንደምን ነህ አልሺኝ
እኔማ...
አለው እንደምንም ምንም ባለመሆን
ታውቂው የለ አፍቃሪን ያፈቀረ ሰሞን
አንዲያ ነኝ....
አዎን
የናፍቆቴን መራብ ትውስታ ላይገታው
ዝምብዬ ምኳትን ህመሜን ላይረታው
መጣው ስላልሺኝ ነው አሁንም ምበረታው።
አንቺዬ
ውዬ አድሪያለው እና እስክትመጪ በፆም
ባክሽ ብቅ በዪ እስትንፋሴ እንዳትቆም።
✍️#በረከት_ሐ(@berii34)
@getem
@getem
@getem
ሄድሽ ደሞ .......ያንን ሰሞን
አንቺዬ
የተነሳሽበት ማልደርስበት መንገድ
ናፍቆትሽን ይዤ ዘላለም ል'ራመድ
ከበደኝ
ቀድሞውንስ መች ቀለለኝ።
ታድያ ይሄን እየሰማሽ
እንደምን ነህ አልሺኝ
እኔማ...
አለው እንደምንም ምንም ባለመሆን
ታውቂው የለ አፍቃሪን ያፈቀረ ሰሞን
አንዲያ ነኝ....
አዎን
የናፍቆቴን መራብ ትውስታ ላይገታው
ዝምብዬ ምኳትን ህመሜን ላይረታው
መጣው ስላልሺኝ ነው አሁንም ምበረታው።
አንቺዬ
ውዬ አድሪያለው እና እስክትመጪ በፆም
ባክሽ ብቅ በዪ እስትንፋሴ እንዳትቆም።
✍️#በረከት_ሐ(@berii34)
@getem
@getem
@getem
👍41❤22👎5
ልብህ ከታወረ ......ፅልመት ከወረሰው
እንደምን ቆጠርከው እራስህን እንደሰው?
እንደምን?
እንደማን?
ሰው መሆን ከባድ ነው መሸንገል ህሊናን ።
ይልቅ
ከጠቆረው ቤትህ ሰው መሆንን አስስ
አልያም ከቻልክበት መኖሪያህን አፍርስ
ወዳጄ
የነገሩን ሁሉ ሀቅ እርቆታል ከእውነት አይዋደድ
ዘር......... ከእህል እንጂ ........ከሰው አይዛመድ
ታድያ
ከዚህ ...እግዜሩን ከረሳ ከባከነ ዘመን
ያዩልህን ሳይሆን ያየኸውን እመን
በል ንቃ
በል አሁን ውጣ ጫጫታውን ትተህ
ብራንህን ፈልግ ሽንቁር አበጃጅተህ
በል አሁን ተነስ
ስንኩል ልብህን አቅና
ሰው መምሰል አደለም ሰው መሆን ነው ደህና
ይቅናህ.....።
#በረከት_ሐ
(@berii34)
@getem
@getem
@getem
እንደምን ቆጠርከው እራስህን እንደሰው?
እንደምን?
እንደማን?
ሰው መሆን ከባድ ነው መሸንገል ህሊናን ።
ይልቅ
ከጠቆረው ቤትህ ሰው መሆንን አስስ
አልያም ከቻልክበት መኖሪያህን አፍርስ
ወዳጄ
የነገሩን ሁሉ ሀቅ እርቆታል ከእውነት አይዋደድ
ዘር......... ከእህል እንጂ ........ከሰው አይዛመድ
ታድያ
ከዚህ ...እግዜሩን ከረሳ ከባከነ ዘመን
ያዩልህን ሳይሆን ያየኸውን እመን
በል ንቃ
በል አሁን ውጣ ጫጫታውን ትተህ
ብራንህን ፈልግ ሽንቁር አበጃጅተህ
በል አሁን ተነስ
ስንኩል ልብህን አቅና
ሰው መምሰል አደለም ሰው መሆን ነው ደህና
ይቅናህ.....።
#በረከት_ሐ
(@berii34)
@getem
@getem
@getem
👍44❤19
.
(@berii34)
@getem
@getem
@getem
ናፍቆት ያለ ፍቅር
ገጣሚ ያለ ብእር ፣ እንደምን ይውላሉ
ባንዳች ነገር ታስረው እስከተፈጠሩ።
አየሽ
እንዲያ ነበርን እኛ፣ ምንም ያልጎደለን
አንዳች ነገር ቀልሞ ፣ አንድ ለይ የሳለን
አንድ ለይ ያዋለን።
ደግሞም እንደ ንፋስ ፣ ባህር ውቅያኖሱን
ተራራ እና የብሱን ፣ ነፍሰን እንዳላለፍነው
በነበር እንዲቀር ፣ እግዜር አስኪፅፈው።
እንቺዬ
እንዴት ነበርን ብልሽ
ምን ይሆን ግን መልስሽ?።
እንዳልተዋደድን ፣ እንዳልተፋቀርን
በእግዜርሽ ፣ በሞቴ እንዳልተማማልን
እንዴት ግማሽ ጣዖት
እንዴት ግማሽ ጽላት ሆንን?።
እንዴት?....
#በረከት_ሐ(@berii34)
@getem
@getem
@getem
👍28😢3🔥2😱2😁1
ረሀብ አምጦት ፣ ማጣት የወለደው
ከሐበሻ ሰማይ ስር ፣ ለቅሶ በዛ ምነው?
ጩኸት በዛ ፣ ረሀብ እና እንባ
ክፋትም አየለ ፣ ቅናት እና ደባ።
እግዜሩም ዝም አለ
ተማፅኖን ዝም አለ ፣ ወይ አይሰጠን ፍቅር
ምስኪኑ አለቀሰ ፣ ከጥቁር ሰማይ ስር።
አስኪ ጠይቋቸው
እስኪ ጠይቋቸው ፣ የጦቢያዬን ልጆች
ዳቦ ሚለምኑ እነዛን ፣ ውብ አይኖች
እንደምን ውለዋል ፣ እንደምን አድረዋል
የዛሬን ባያውቁም ፣ ትናንት አልቅሰዋል።
ነገስ?
#በረከት_ሐ
(@berii34)
@getem
@getem
@getem
ከሐበሻ ሰማይ ስር ፣ ለቅሶ በዛ ምነው?
ጩኸት በዛ ፣ ረሀብ እና እንባ
ክፋትም አየለ ፣ ቅናት እና ደባ።
እግዜሩም ዝም አለ
ተማፅኖን ዝም አለ ፣ ወይ አይሰጠን ፍቅር
ምስኪኑ አለቀሰ ፣ ከጥቁር ሰማይ ስር።
አስኪ ጠይቋቸው
እስኪ ጠይቋቸው ፣ የጦቢያዬን ልጆች
ዳቦ ሚለምኑ እነዛን ፣ ውብ አይኖች
እንደምን ውለዋል ፣ እንደምን አድረዋል
የዛሬን ባያውቁም ፣ ትናንት አልቅሰዋል።
ነገስ?
#በረከት_ሐ
(@berii34)
@getem
@getem
@getem
👍38😢11❤10👎3
"እንቆቅልሽ ፣ ምን አው...ህ/ሽ"
ሰከን ያለ ልብ ፣ በለሆሳስ ሚጓዝ
ደግሞም
ፀጥ ያለች ነብስ ፣ ወደራስ የምትፈስ
ሁካታን የጠላች ፣ ጫጫታን የቀጣች
ከዚህ ሁሉ ፍጡር ፣ ፍጥረት ላለመባል ብቻዋን የከሳች ፣ ብቻዋን የወዛች።
ሁሉን የምታክል ፣ ሁሉን የምትስል
በፊደል ምትደማ ፣ በቃል የምትቆስል
ከውብ ግጥሞች ስንኝ ፣ አንዷን የምትመስል::
ማንናት ?
ማነች ?
በራስ ክራር ስልቷ ትዝታን የቃኘች...
ማነች ?
ካላወቃቹ እንግዲህ ሀገር ስጡኝ...
#በረከት_ሐ
@getem (@berii34)
@getem
@getem
ሰከን ያለ ልብ ፣ በለሆሳስ ሚጓዝ
ደግሞም
ፀጥ ያለች ነብስ ፣ ወደራስ የምትፈስ
ሁካታን የጠላች ፣ ጫጫታን የቀጣች
ከዚህ ሁሉ ፍጡር ፣ ፍጥረት ላለመባል ብቻዋን የከሳች ፣ ብቻዋን የወዛች።
ሁሉን የምታክል ፣ ሁሉን የምትስል
በፊደል ምትደማ ፣ በቃል የምትቆስል
ከውብ ግጥሞች ስንኝ ፣ አንዷን የምትመስል::
ማንናት ?
ማነች ?
በራስ ክራር ስልቷ ትዝታን የቃኘች...
ማነች ?
ካላወቃቹ እንግዲህ ሀገር ስጡኝ...
#በረከት_ሐ
@getem (@berii34)
@getem
@getem
👍31❤12👎1🔥1