፡፡፡፡፡፡ፍካት ናፋቂዎች፡፡፡፡፡፡
~~~~~~~~~~~~~~~
የዘመን እጣፋታ እኛን ባንቺ ላይ ጥሎ
የተስፋ ጽገሬዳ በከርስሽ ውስጥ አጎንቅሎ
ዘላለማዊ እንቡጥ በልቦናችን ሸብልሎ
አላበበ አልረገፈ
ፈክቶ አልተቀጠፈ
ቅጠል ብቻ ሰዶ ስሩን
ተስፋ ብቻ አንቡጦ እንቡጡን
ነቅለን አንወረውረው
ማንነት ከአስኳልሽ ቋጥሮን
ግብር ሆነን ጊዜ አቅምን ሰልቦን
እንቡጥ አምላኪ አደረገን የነገን ተስፋ ናፋቂ
ያልተቀደደ ጎህ ልጆች ሁሌ በተስፋ ታጣቂ፡፡
ምን ታረጊዋለሽ
©በድሉ ዋቅጅራ
#ቅኔ_አድባር
@getem
@getem
@gebriel_19
~~~~~~~~~~~~~~~
የዘመን እጣፋታ እኛን ባንቺ ላይ ጥሎ
የተስፋ ጽገሬዳ በከርስሽ ውስጥ አጎንቅሎ
ዘላለማዊ እንቡጥ በልቦናችን ሸብልሎ
አላበበ አልረገፈ
ፈክቶ አልተቀጠፈ
ቅጠል ብቻ ሰዶ ስሩን
ተስፋ ብቻ አንቡጦ እንቡጡን
ነቅለን አንወረውረው
ማንነት ከአስኳልሽ ቋጥሮን
ግብር ሆነን ጊዜ አቅምን ሰልቦን
እንቡጥ አምላኪ አደረገን የነገን ተስፋ ናፋቂ
ያልተቀደደ ጎህ ልጆች ሁሌ በተስፋ ታጣቂ፡፡
ምን ታረጊዋለሽ
©በድሉ ዋቅጅራ
#ቅኔ_አድባር
@getem
@getem
@gebriel_19