ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ቃል_ፈጠርኩ

እንደ ጨቅላ ህፃን ቃላት እንደሚያጥረው
ቢጨንቀው ቢጠበው ቃል እንደሚፈጥረው
የሚኮለታተፍ ማውራት እያማረው

እኔም እንዲያ ሆንኩኝ.....

ልክ አንቺን እንዳየው ዲዳ እሆናለሁ
ላወራሽ ፈልጌ ቃላትን አጣለሁ

ወይም እንደ ጨቅላው....
ፊደል ሰባብሬ ልነግርሽ እሻለው

ግ ና......አልችልም....

ሆዱ ባዶ ሲሆን ረሀቡ ሲሰማው አርፎ እንደማይተኛ
ልቤም ያንቺ ሆኖ ያምረዋል ቁራኛ

ልክ እንደህፃኑ...

ቃላትን ፈጠርኩኝ ፊደል ደራርቤ
ልቤን አጋብቼ ፍቅርሽን ተርቤ

ለአንድ አፍታ እንኳን እናቱ እምዬ ብትሰወር ከሱ
እማ የምትልን አንድ የሚያቃትን ቃል ይዟል በምላሱ።

እኔም ያንቺ ጨቅላ አኔ ያንቺ ህፃን
ከጆሮ ቆራጩ ከስውር በቀቀን

ከሚያስፈራው ጭራቅ ከትልቅዬው ጅብ
አንቺን ነው ምፈራ አንቺን ነው የማስብ

እናም እናቴዋ.....

ቃላት መራርጬ ፊደል ገጣጥሜ
አይንሽን አይቼ በሳቅሽ ታምሜ
አንድ ፊደል ፈጠርኩ
"ናፈቅሽኝ" አለሜ

OB'☀️(ja)

@Jadmasse25
@getem
@getem
@getem
👍45🔥62😢1🎉1