ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
የለሽም
   
የለ_ሽም
ሌቱ ሚቀድምላት
መቅረዝ ቢሷ ቤቴ_
     እበር አልባው ሙክራብ
ከሰው ተለይቶ ለጠሀይ ሚቀርብ፤
የነብሴ መመነን ስጋዬ ብትፈቅድም
ካንካሣ ሀሳቤ አንቺንስ ከማሰብ ዛሬም አልታቀብኩም።
              ለምን????
      ምኩራብ ያልኩሽ ቤቴ
       ያቺን ወናዋን ነው።
ሽውታ ጠቅ አርጎት ንፋስ እንዳመጣው
ከሩቅ አጥናፍ ምጥቀት ሀይል እንዳ_ከነፈው፤
የናፍቆትሽ እስትንፋስ ውስጤን አስታወሰው።
          ////ደግሞ////
ትፋቴን እምልስ መማርን ማልሻ
         ከመሀል ላይ ቆሜ...
እያልኩ ተርካለው ይብቃን አይገታንም እስከመጨረሻ።
ግና ባስብሽም...
   የለሽም
   የለ_ሽም
           <<ምናልባት>>
ማለም ካ'ንተ ቢኖር
የስሜን ስያሜ
አውጥተህ ባትሰድር እንደ ጠጋ ጠበል፤
የሚወደኝ ልብህ ከጦት ባይዳቀል
ይገባህ ነበረ
ትመጣም ነበረ..
በሚያስገመግመው
ድካም በማይቃኘው የፍቅራችን ፈረስ
......ትይኝ እኮ ይሆናል.....
  ቢገባሽ!!!!!
ካንቺ ዘንድ ባልገኝ ፀብ ፈንታችን ሆኖ
ግን...
እጠብቅሻለው ላፍታ እንኳን ሳልሰለች በይ_ቅርታ ተማፅኖ።
ያነከሰው ልቤ ስብራት የደቃው
ማጣት አመካኝቶት...
ከናፍቆት ምርኩዝ ላይ ላያነሳ የጣለው።
ካልቀናው ቤቴ ውስጥ ጥለሽ መሆድሽ ነው።
   ቢሆንም
.
.
.
የለሽም!!!!
#ሊዮ_ማክ
#ከባሌ_ጎባ

@getem
@getem
@getem
👍28😁1
እንጃ...
ጡት እንዳጣ ህፃን
ሆድ ብሶኝ ማለቅሰው
የልቤን ለማውጣት ከቃሌ ማልደርሰው
ለምን ይሆን???
እንጃ...

እንዲህ በሴትነት ግብርሽ
እንዲያ በ'ህትነት ልኬት ቀርበሽ
ሳንስ ከወንድምነት ሚዛን ጎድዬ
በፍርሀት ገደብ ተከልዬ
ባይንሽ ዱላ ምስኪን እኔ ስወገር፤
ናፍቆት ጥሎኝ በማጣት ጦስ ስሰክር።
  ግን ለምን ይሆን???
ዝብርቅርቁ  አንቺነትሽ የማይጠራ
ልሳንሽ ቃልን ሽቶ ማያወራ
እንጃ...
እንጃ...
በጨረቃ ውበት በምሽቱ እንዳልደመቅን፤
ከዋክብትን ለትዝብት ዙሪያችንን አቁመን፤
ፍቺ አልባ በሆነ ቅርበት ሰጥመን
የዝናብ ግርፍ ዜማ ሆኖ እንዳልቃኘን፤

ይህ ከሆነ...

ታዲያ ለምን ይሆን???
መሀላችን የልዪነት  መስመር የሚሰመር
ከፍቅራችን ያ'ድማስ ደሴት የምንቀር...?
ለምን ይሆን...?

እንጃ...
#ሊዮ_ማክ
#ከባሌ_ጎባ


@getem
@getem
@getem
👍25😢21
ከሚላ
የት እንደምንደርስ ባይገኝም ተንባይ
ፍቅራችን ግልፅ ነው በአፅኖት ለሚያይ።
ትናንት...
  ብዙ ገጥሚያለው
  ብዙንም ፅፌያለው ስለመለያየት
ሕልሜ እየተናደ አንቺ የሔድሽ 'ለት
ምስክር ስትሰጠኝ ባብሮነት ጊዜያችን
ዛሬ ቃሏን ሽራ ብትል አንድ ያልነበርን
ጨረቃን ታዘብኳት።
ብዬ እንኳን ቢገባት
እጅ ለእጅ ተያይዘን እንደደመቅንባት
ብዙውን ባዋያት፤
ግን አንዱም አልገባት።
ቃል እንደጠፋበት ጀማሪ ገጣሚ...
እኔ አልኩኝ እንጂ
አልኩኝ ገባኝ ገባኝ
እንኳንስ ያልገባኝ
የገባኝ መች ገባኝ
ያልገባኝ ሲገባኝ
የገባኝ መች ገባኝ
እያልኩ አወራለው
የገባኝን ቅኔ ባልገባኝ ሽራለው።
ሐዘን ውስጤን ሰብሮት ተንኮታኩቶ ልቤ
ሀሳብ ሲያዋልለኝ ስነጠቅ ከቀልቤ
የሆንኩኝ መሰለኝ የረከስኩ ቆርቤ።
አንቺን በማጣቴ...
ለወራቶች በርተሽ ላ'መት ብትጠፊ
ከህልሜ ባነንኩኝ እንደመታኝ ጥፊ።
መምጣትሽን ሳስብ...
ፍቅራችን ተጥሶ በጥላቻ ማዕበል
መለየት ሲዳኘን ልባችን ለየቅል
ሆኖ እያደረ፤
መድረሻችን ታውቆ በሩቅ ታይቶ ቀረ።
ግና ይሄ ሁሉ የትናንት ታሪክ ነው።
የጥላቻ አምድ!!!!!
በልዩነት መሀል ፍቅራችን የሚነድ
ዛሬ.....ነገር ተቀይሯል
የፍቅራችን ማህተም ቅሩ ተጎንጉኗል
በመምጣትሽ ፋና ውስጤ ተጠግኗል።
መራራቅ የዳኘው ሰባራው ልባችን የተንኮታኮተው
በእውነተኛ ስሜት ፍቅርን...ማደሪያ አደረገው።
እልሽ እንደነበር...
   ታግሶ ለኖረ ጊዜ መልስ ይሰጣል
  ህመም የትም ቢገኝ ሳቅ ግን ያስከፍላል።
  እጁን ካ'ፋ ገቶ
በለሱን ያቆየ ፍሬዋን ይበላል።
እልሽ እንደነበር...
  የፃፈ በሙሉ ገጣሚ ካይደለ
  ጦር ሜዳ ያለ ሁሉ ጀግናን አይወክልም፤
  የወደደሽ ሁሉ አፍቃሪሽ አይደለም።
ግን አንተስ ብትዪኝ...
   መሔድ አንድ ስም ነው፤
   አጠገቤ ሆነሽ ትናፍቂኛለሽ...እናፍቅሻለው።
  ባፈቀርኩሽ ዘዬ ቃላት አልከሽንም
  ከሌላ አኑሬሽ በሌላ አልመዝንም።
አሁን ግን...
ከልቤ ፅላት ላይ ስያሜ ተፅፏል።
የፍቅርሽ ክያኔ ማንነቴን ገዝቷል።
በማይገልፅሽ ቃላት ሰኝቼሽ ከሚላ
ከ'ቅፌ ስለሆንሽ አልታትርም ሌላ።

#ሊዮ_ማክ
#ባሌ_ጎባ
ተፃፈ፦04/02/2013ዓ.ም

@getem
@getem
@getem
👍327🔥1🎉1