"ወርቅ ቅብ"
#ሚካኤል ኤርሚያስ
***
እኔማ.......
ወርቅ መምሰያ ቅብሽ
ጥቂት አየለና አይኔን ቢጋርደው
በቀይ እንቁው ሚዛን
አንቺን ቅባቅቧን እመዝንሻለው
ከዛ.....
ላላፊ አግዳሚው
እሳቱን ይመስል ወርቅ ናት እላለው
ምንም ቢገዝፋ ቅባቅብሽ
ወርቅ እማ ወርቅ ነሽ ለኔለአፍቃሪሽ
እስኪ አስቢው .....አሁን ምን ይሉታል......?
በቀይ እንቁ ሚዛን ቅባ ቅብ መመዘን
በይሁንታ ምኞት
ወርቅ ናት እያሉ በአንደበት ማላዘን
ልብን እያራዱ በልበ ኦና ማዘን
ንፍገተ ክብርሽን በላይሽ ላይ መድፍት
በፍቅርሽ ታፍሮ
ሀሰትሽን ታቅፎ ሀቅ ላይ መደንፍት
እኮ ይሄን ምን ይሉታል......?
በእሳቤ ጥጋጎት ወደላይ ማንጋጠጥ
የፈጠረሽ ጌታን
ወርቅ አድርግልኝ ብሎ ዘውትር መለማመጥ
እስኪሰማኝ ድረስ ሌላ አለማዳመጥ
በህላዌ አንድምታ
በጥቀርሻ ጥፍር አይምሮንመቧጠጥ
ወርቀ ቅባ ቅብነትሽ ታጥቦ እንዲለቅሽ
ማሳበቅ ላምላኬ ማሳበቅ ላምላክሽ
እሱ..ምንም ማይሳነው ..
ወርቁን እንዲያደርግሽ
መማፀን በእግዜሩ ቤት ስምሽ
:
ይሄ ብቻ መስሎሽ........
:
የኔ የልብ መሻት....
ከምመዝንበት
ከቀይ እንቁ አክብሬሽ በጥበብ ሰውሬሽ
እስከ ዐለም እጥፍት ነበር ፍላጎቴ በልቤ ላኖርሽ
ይሄ የኔ መሻት ነው .........
እሷ ግን ......
አሁን ያልኩት ሁሉ ለሷ እንዲሆንላት
ማንጋጠጤን አይቶ እንዲፈፅምላት
ቅባቅቧን ነስቶ ወርቁን እንዲያለብሳት
በጥበብ ሞሽሮ ከልቤ እንዲያውላት
ምለምንበትን ልብ ምልበትን
እኔነቴን ሰልባህቃቆቴን ነስታ
ቀልበ ቢስ ትላለች ማረሻ ስለቴን
አቀቀርቅራ እያየች ከጎኔ ተኝታ።
@getem
@getem
@getem
#ሚካኤል ኤርሚያስ
***
እኔማ.......
ወርቅ መምሰያ ቅብሽ
ጥቂት አየለና አይኔን ቢጋርደው
በቀይ እንቁው ሚዛን
አንቺን ቅባቅቧን እመዝንሻለው
ከዛ.....
ላላፊ አግዳሚው
እሳቱን ይመስል ወርቅ ናት እላለው
ምንም ቢገዝፋ ቅባቅብሽ
ወርቅ እማ ወርቅ ነሽ ለኔለአፍቃሪሽ
እስኪ አስቢው .....አሁን ምን ይሉታል......?
በቀይ እንቁ ሚዛን ቅባ ቅብ መመዘን
በይሁንታ ምኞት
ወርቅ ናት እያሉ በአንደበት ማላዘን
ልብን እያራዱ በልበ ኦና ማዘን
ንፍገተ ክብርሽን በላይሽ ላይ መድፍት
በፍቅርሽ ታፍሮ
ሀሰትሽን ታቅፎ ሀቅ ላይ መደንፍት
እኮ ይሄን ምን ይሉታል......?
በእሳቤ ጥጋጎት ወደላይ ማንጋጠጥ
የፈጠረሽ ጌታን
ወርቅ አድርግልኝ ብሎ ዘውትር መለማመጥ
እስኪሰማኝ ድረስ ሌላ አለማዳመጥ
በህላዌ አንድምታ
በጥቀርሻ ጥፍር አይምሮንመቧጠጥ
ወርቀ ቅባ ቅብነትሽ ታጥቦ እንዲለቅሽ
ማሳበቅ ላምላኬ ማሳበቅ ላምላክሽ
እሱ..ምንም ማይሳነው ..
ወርቁን እንዲያደርግሽ
መማፀን በእግዜሩ ቤት ስምሽ
:
ይሄ ብቻ መስሎሽ........
:
የኔ የልብ መሻት....
ከምመዝንበት
ከቀይ እንቁ አክብሬሽ በጥበብ ሰውሬሽ
እስከ ዐለም እጥፍት ነበር ፍላጎቴ በልቤ ላኖርሽ
ይሄ የኔ መሻት ነው .........
እሷ ግን ......
አሁን ያልኩት ሁሉ ለሷ እንዲሆንላት
ማንጋጠጤን አይቶ እንዲፈፅምላት
ቅባቅቧን ነስቶ ወርቁን እንዲያለብሳት
በጥበብ ሞሽሮ ከልቤ እንዲያውላት
ምለምንበትን ልብ ምልበትን
እኔነቴን ሰልባህቃቆቴን ነስታ
ቀልበ ቢስ ትላለች ማረሻ ስለቴን
አቀቀርቅራ እያየች ከጎኔ ተኝታ።
@getem
@getem
@getem
ምስጋና ቢስ ፀሎት!
#ሚካኤል አስጨናቂ
።።።።።።።።።።።።።።።።።
#እዛ ጎዳናው ላይ ...
ስንኩል ሽባነቱን ለሰማይ የሚያሳይ
"እጅ ከሰጠኸኝ ልመና አቆማለሁ" ብሎ እየማለ
አብዝቶ የሚያለቅስ ፥ አንድ ለማኝ አለ።
እናም የዛ ለማኝ!
የኔ ቢጤን ጠሎት...
እግዜር ኖሮ ሰምቶት...
በጥልቅ እንቅልፍ ጥሎ ~ እጅ አበጃጀለት
ላፈሰሰው እንባ ፣ ለጠለየው ጠሎት መልሱ ተላከለት።
ግን እርሱ ሲነቃ...
እጅ አገኘሁ ብሎ አላመሰገነም
ለገባው ቃልኪዳን
ለተሳለው ስለት ~ምላሽ አላኖረም
ዛሬም እንደ ፊቱ...
ዛሬም እንደ ትናንት ~ ማልቀሱን አልተውም።
እንዲህ ሲል ቀጠለ...
"መንገድ ላይ ወድቄ
ተዘከሩኝ እያልሁ ~ በስምህ ስጣራ
ጤነኛ ነው ብለው...
ፈራንካ ለመስጠት ~ ሰው እንዳይኮራ
ይህን አስብበት ~ ጌታ ሆይ አደራ!!
@getem
@getem
@getem
#ሚካኤል አስጨናቂ
።።።።።።።።።።።።።።።።።
#እዛ ጎዳናው ላይ ...
ስንኩል ሽባነቱን ለሰማይ የሚያሳይ
"እጅ ከሰጠኸኝ ልመና አቆማለሁ" ብሎ እየማለ
አብዝቶ የሚያለቅስ ፥ አንድ ለማኝ አለ።
እናም የዛ ለማኝ!
የኔ ቢጤን ጠሎት...
እግዜር ኖሮ ሰምቶት...
በጥልቅ እንቅልፍ ጥሎ ~ እጅ አበጃጀለት
ላፈሰሰው እንባ ፣ ለጠለየው ጠሎት መልሱ ተላከለት።
ግን እርሱ ሲነቃ...
እጅ አገኘሁ ብሎ አላመሰገነም
ለገባው ቃልኪዳን
ለተሳለው ስለት ~ምላሽ አላኖረም
ዛሬም እንደ ፊቱ...
ዛሬም እንደ ትናንት ~ ማልቀሱን አልተውም።
እንዲህ ሲል ቀጠለ...
"መንገድ ላይ ወድቄ
ተዘከሩኝ እያልሁ ~ በስምህ ስጣራ
ጤነኛ ነው ብለው...
ፈራንካ ለመስጠት ~ ሰው እንዳይኮራ
ይህን አስብበት ~ ጌታ ሆይ አደራ!!
@getem
@getem
@getem