ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ስሜ_ተላወሰ

ሞገደኛው ሽፍታ !!
ሀገር ያሸበረ
ስንቱን ያኮላሸ
ስንቱን ያነፈረ
ሀገር ተይዞለት ፥ እግሬ ሳይሄድ ከርሱ
ሚሽትክን ጠብቆ ፥ ጭኗት በፈረሱ
ባዘዘው ሰው ጤፉ !!
ያለ መኮነኑ
ያለ መጠየፉ
ደርሶ ሰው እንዳጣች ፥ አጋደማት ቢሉ
ባንቺ እጁን ማንሳት ፥ በኔ መታበሉ
እሺም
እንቢም ጠፍቶኝ ፥ አጡዞኝ ነገሩ
ገፍቶኝ ...እንዳልገፋው !!
አንቺ ከበስሩ
ይድላሽ ብዬ እንዳልሰድ ፥ አልጋና ጠፍሩ
ሽሙጦ በኔው ነው ፥ አድባርና አውጋሩ
ሲበደል ለኖረ ፥ አልፎም ገፈት ቀማሽ
ብሩክ ማንነቱ ፥ እሬት ግንባር ሲታሽ
ምንም አለ ምንም
ደግም ሰራ ክፉ ፥ እሱው ነው ተወቃሽ !
በልክ የለሽ ትግስት
ወንድነት ሲፈተን ፥ በፍቅር ፣ በክብሩ
ስንቱ ስሙ ጠፋ
በተጓደለ ፍርድ ፥ የእውነቱ ጅማት ፥ ተበጥሶ ክሩ።

#አብርሀም_ተክሉ

@getem
@getem
@getem