ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ጥማት

በኮርማ ፣ በርችት ፣ ከምንቀበለው የዘመን መባቻ
ባርቲ ቡርቲ ወሬ ፥ በወገን ጥላቻ
እንደ ሀገር ኖሮ ፥ መሞት ለየብቻ
ምን አውቅልሽ በዝቶ.....
ውሎ ማደር ፈርተን ፥ በማጀት ጉልቻ
ቀናችንን ሳናምን
ጠጥተን ሳንረካ ፥ ጎርሰን ሳንጠግብ
ዛሬ ሳያከትም ፥ ለነገ ስናስብ
የሰቀቀን ጉርሻ ፥ ደጋግሞ እያነቀን
የኑሮ ውድነት ፥ በጠኔ እየናጠን
ዝም ባለ ሰፈር ፥ በፍርሀት ተጣብቀን
በጠራራ ፀሀይ ፥ ጨለማ አውሮን ፥ ምርኩዝ ተስፋ እያጣን
በልተን እንዳልበላ ፥ ስጋት እያከሳን
ካዲስ አመት በላይ ፥ ሰላም ነው የጠማን።
እንጂ!!
አሻፈረን ብንል ፥ ዘመን መች ይቆማል
ሲሻው የሳት እራት ፥ አልያ ዶሴ ገድል
የምንከትብበት
ባለ ሶስት መቶ ገፅ ፥ ብራና ያበጃል።

#ሰላማችን_ይብዛ

#አብርሀም_ተክሉ

@getem
@getem
@lula_al_greeko