ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ያምና ናፍቆት !!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።
እሷን አስብና !
የቀድሞዋ ፍቅሬን፦
ያምናዋ ወዳጄን...
እኔ ባጠፋሁት ፥ በበደልሁት በደል
ይቅርታ ማለቷን ፥ ከኔ እንዳትነጠል
ደግሞ አንቺን አይቼ ...
በምትምሽው ገደል ፥ በለኮስሽው እሳት
ሳለ ያንቺው ጥፋት!
እኔው ይቅር ብዬ ...
ደጅሽ ላይ ተጥዬ ...
በተማጥኖ እንባ ፥ ወራት ባስቆጥርም
ፍቅሬን ስትገፊ ፥ ልብሽ እንዲለግም
አገኘሁ እላለሁ!
ያምና ብድራቴን
እሷ ላይ የቆየኝ
የሐጥያት ውርሴን ።
ይኸው ዛሬም ድረስ!
እሷ ባቀናችው ፥ ጎጆ በማይበቁ
ለሷ በቀለድሁት ፥ ቀልድ በማይስቁ
እሷን ባስለቀሳት ፥ መርዶ በማያዝኑ
እሷን በማረካት ፥ ቦታ 'ማይዝናኑ
ከክፍቱ ጎኔ ፥ መሙላት በማይችሉ
አንዴ በሚረዝሙ ፥ አንዴ በሚጎድሉ
በግዑዛን ሴቶች ፥ መንደር ተሰልፌ
አምናን እራባለሁ ፥ ዘንድሮን ታቅፌ።

@getem
@getem
@getem