ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ሰላም ጤና ይስጥልኝ እንደምን አላችሁ። #ተመስገን_አብይ እባላለሁ። በ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ #የስነልቦና ተማሪ ነኝ። ሰዎችን ሊሚያነቃቁ እና ሊለውጡ የሚችሉ የህይወት ክህሎት ስልጠናዎችን እሰጣለሁ። የተለያዩ መልዕክት አዘል ሀሳቦችን የማካፍልበት ቻናልም አለኝ። እንድትቀላቀሉኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ።


@temuabiy
@temuabiy
@temuabiy
እናቴም እህቴም ፤
እርካብ ላይ ትውጣና ፤
እንደ እቴጌ መነን ዛሬም ትንገስልኝ ፤
እንኳን በእግሬ ሂጄ ፤
በእጄ ማልጨርሰው ፤
ተከፍሎ የማያልቅ ብዙ ሺህ እዳ አለብኝ


((( ጃ ኖ )))💚💛

ሸጋ ጁምኣ!!💚

@getem
@getem
@balmbaras
በግራ እጄ የፃፍኩት ግጥም(ልዑል ሀይሌ)
.
የምፅፈው ግጥም ይወለጋገዳል፤
ቁርጥ ቀን ላይ ቆሞ
ቀኜ እየተማረ ግራ እጄን ያለምዳል፤
.
(እየፃፍኩልሽ ነው...)
በክፉ ቀን ስንቄ
ምን ቢያዳግተኝ በግራ ቤት መምታት፤
ምን ቢወለጋገድ በማያምር ፅሁፍ
በስንኝ ሰድሮ አንዲት ግጥም ማውጣት፤
ቀን አይታገሉት
ያልፉታል እንዳለ ያልፋል እንደመጣ፤
ግራን ያለምዱታል ቀኝ እጅ ሲታጣ፤
.
(እየፃፍኩልሽ ነው...)
ሕመሜን ለምዳለሁ የመለያየቱን፤
ቀን አስተምሮኛል
በጨለማ እያሉ አሻግሮ ማየቱን፤
እስኪያልፍ የሚያለፋ አንድ ዕድል ሲታደል፤
እንዴት እነሳለሁ?
ስለዛሬ ብዬ ነገዬን ለመግደል፤
.
የምፅፈው ግጥም ይወለጋገዳል፤
ቁርጥ ቀን ላይ ቆሞ
ቀኜ እየተማረ ግራ እጄን ያለምዳል፤
.
(እየፃፍኩልሽ ነው...)
ይሄን ሁሉ ዘመን
ሳነብሽ ቆይቼ
ሳሰፍርሽ አልፌ ከፊደል ገበታ፤
ቀኜን ሳጣ ገባኝ
ዕውቀቴን ስነጠቅ ካስቀመጥኹት ቦታ፤
.
በይ አትታበዪ
ባለማወቄ ላይ አትመፃደቂ፤
ይልቅ ተነሺና
አለማወቅሽን መርምረሽ እወቂ፤
ተነሺና ለኪ የማፍቀሬን ጥልቀት፤
ከማፍቀር ጀምሮ
እስከ መጥላቴ ነው የመውደዴ ርቀት፤
.
የምፅፈው ግጥም ይወለጋገዳል፤
ቁርጥ ቀን ላይ ቆሞ
ቀኜ እየተማረ ግራ እጄን ያለምዳል፤
.
.
.
(እየፃፍኩልሽ ነው....)
.
4/11/2011 ዓ.ም.
መቐለ
11 July at 12:03 ·

@getem
@getem
@gebriel_19
"ቀና በል ቀን አለ ወዳጄ አታቀርቅር፣
ጀምበር አዝቅዝዝቃ ማታ ሆና አትቀር፣
ትዋጣለች ጠዋት
በሸህ ሀሴን ትንቢት በሸህ ሁሴን ንገር፣ "
አብሽር መጀን ብሎ ሸህ ኑር መረቀኝ፣
እንደ ልጅነቴ ፀጉሬን እየነካ በዱኣ ፈወሰኝ።
መገን የጁማኣ ቀን ዋካታው ናፈቀኝ፣
ቤተሰብ ከልጁ፣
ቤቱን አጫጭሶ ተቀምጦ ደጁ፣
ሲጨዋወት ሲወል፣
ምርቃት እንደ ጭስ ሺቅብ ሲንፎለፎል፣
ጨዋታው ሲደራ....
አቦል ቶና ሲባል
ቁርሱ ሲቀራርብ ሲቆረስ እንጀራ፣
ሁሉም ቢናፍቀኝ በተራ በተራ፣
ጎዳናውን ይዤ መንገድ ተከትዬ፣
ሄድኩኝ ከሸሁ ቤት ለጁምዓ ቀን ብየ።


"ወላሂ ለአርሴማ ሳልረጥብ አላልፍም" ከሚል ደጋግ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ጋር በአንድ ምድር በቅየ ጁምኣን አለማስታወስ አልችልም። እኛ ጋ ምንም የሚለየን ነገር የለም።

" ፍቅር፣ እምነት፣ እውነት፣ ታሪክ " ያለባት ሀገር ኢትዮጵያ!!!!

አምባዬ ጌታነህ

መልካም የጁምኣ ቀን!!!!

@getem
@getem
@amba88
ፍቅር - ልብ - ሀይቅ
የፍቅርሽ ማዕበል እንደ ጣና ሲበረታ
ወጨፎ ያገኘዋል ልቤን በጨረፍታ
#
የእይታሽ ፍንጣሪ መንፈሴን እያራሰ
ባልጠበኩት መንገድ ልቤ በሰበሰ
#
የሚያምረው ስብዕናሽ በፍቅር ሲንሳፈፍ
ልቤ ሰመጠ ልብሽ ላይ ለማረፍ
የፍቅሬ ይዘቱ እጅግ ስለጠጠረ
በፍቅር ሀይቅ ውስጥ እንደሰጠመ ቀረ
የሰጠመ ፍቅሬን
ምንም ችግር አያወጣውም
ምንም ስቃይ አይፈነቅለውም
ፍቅርሽ በልቤ እስካለ
ሞገድ አይመታውም
ማዕበል አያናውፀውም
ልቤ በልቡ እስከማለ
ይኸው በጣና ልማልልሽ
የፍቅሬ ፅናት ልቤ ላይ አለ
ማየት ትችያለሽ በፍቅር እንደተኳለ
በልቤ ሀይቅ ላይ ገፅሽ ስለተሳለ

@getem
@GETEM
@GETEM
Audio
ሳሙኤል (zemas)

ከህይወት ገፅ #02
ልጅነት (ህሊና) የተሰኘው ግጥሜን እጋበዛቹሀለው::

music by Kidus

@getem
@getem
@getem
የምስኪኑ መፅናኛ

(ቡሩክ ካሳሁን)

ደሀ ቢሉኝ እንኳን ቤሳ ቤስቲ የሌለው
ለሁለት ብር ዳቦ ሶስት ብር የጎደለው
በህይወት ዘመኔ ያሻኝ ባልበላ
ያሻቸውን በልተው እሱን ለማቃጠል ሲቸገሩ መላ
ቆሜ ተመልክቼ
ላመስግነው እንጂ ሁሉን ባይሰጠኝም
ካሻኮር ነው እንጂ ኮሌስትሮል የለብኝም!


26/06/2011

@getem
@getem
@burukassahunc
ነብይ የኔ ምርጥ❤️❤️

ፍቅርና ወሊድ

ነቢይ መኮንን

ፍቅርና ወሲብ፣ በድመቶች ዓለም
አለው አንዳች ነገር፣ እጅግ የሚያስደምም፡፡
ወሲብ የሠሩ እለት፣ አይጣል ነው ምጣቸው
አገር ያዳርሳል፣ ጩኸት እሪታቸው ፦


የወለዱ ለት ግን ፣ ምጥም የለባቸው
አንዲት ጠብታ ድምጽ ፣ ቃል አትወጣቸውም።


የእኛ ግን ሌላ ነው ፡-
ለፍቅርም ማማጥ ነው
ለአንድነት ማማጥ ነው
ለወሊድ ማማጥ ነው
ለሞትም ማማጥ ነው
ጣር ነው ጅምራችን፣ ጣር ነው መጨረሻው
ለምንድን ነው አልኩኝ፣ ከድመት ያነስነው?!

ስውር ስፌት (ቁጥር 2

@getem
@getem
@getem
///አፈቅርሻለው///

በጦርነት አለም በትንቢቱ መምጫ:
በዚህች ምድረ ዛቻ
በጥፋት መርቀቅ ውስጥ:
ሚሳኤል ሲመረት ጠላት ድባቅ መምቻ

ለአንድ ግዑዝ ብረት:
ነፍስ ሊዘሩለት
ፍጡር ፍጥሩን ሊፈጥር ሊሰራ ሮቦት
ሌት ከቀን ሲባዝን ጠዋት ማታ ልፋት
ከኛ ዘንድም ለውጡ ነውጥን አፍልቆበት
የሀገሬን ሰማይ ክፋት አንዣቦበት:
ደመና ጠልሎት
የፀሀይም ብርሀን:
ከየት መጣ ተብሎ ሰው ተለይቶበት
አዘቅዝቆ ጉዜ አዘቅዝቆ ምጥቀት
ገበሬውም ሳይቀር የእህል ዘር እረስቶ
የሰው ዘር አስልቶ

እውቀትን ፍርሀት
ስልጣኔን ሽሽት
ሰለጠን ያሉትም ስይጥንናን መውረስ:
ሞኝነት መቀባት
.
.
.
ይህ ሁሉ ሲሆን ግን
እኔ አንችን አፍቅሬ
የእንትናን ዘር ሳላውቅ ስለራሴም ሳለይ:
ወደኔ ቀስሬ
:
ሮቦት ቢሰራ ሚሳኤል ቢመረት
ወደማርስ ቢጓዙ ምድርን ቢንቋት
ቅንጣት ሳልጨነቅ አንችን ብቻ ሳስብ
ፍቅሬን ልገልፅልሽ ሀረጋትን ብመርጥ:
ቃላት ብሰበስብ
በፅሁፍ ላቀርበው ብዕሬን አንስቸ
ላንች የሚመጥኑ ቃላትን አጥቸ
ከሚሳኤል ብልጭታ ከዘር ከሀይማኖት:
ያንች ውበት በልጦ ፍቅርን አይቸ
እሄው እስካሁን አለው አፈቅርሻለሁኝ
እያልኩኝ በርትቸ ።

እስጢፋ ተስፋየ


@getem
@getem
@getem
ፍቅርሽ የኔ ጀብዱ!!

Fekadu Getachew

:

<<የፈራ ይመለስ >>

የሚል ጥቅስ አንግበው ጥለውኝ ሲሔዱ 

ዘራፍ ሳልል ቀረሁ ከወንዶች እንዳንዱ።



አጠገቤ ሆነሽ ሰጥተሺኝ ውብ ዓለም 

ለማን ነው የምዘምት? ለማን ነው ምፋለም?



ኮረዶች በዘፈን 

እየሸነቆጡሽ ስቀሽ ስታልፊያቸው

እረኞች በቅኔ

በወንድነቴ ላይ ተረብ ሲተርፋቸው

ንቀቱ ሳይገፋን

ተረቡ ሳይደፋን

ስንቱ ጀብድ አውሮት ሲያጨን ለስላቁ

ኗሪ ናቸው ብለን ፍቅርን የታጠቁ

ኖርን ስለሐቁ።



ከድል አጥቢያ ማግስት ቀረ ስንቱ ጀግና 

የሟች ሚስቶች ቀሩ በባል ፍልሚያ ዝና።



ስንቱ እግርና እጁን ዓይኑን አጥቶ መጣ

አስታማሚ ሆነ የጀግና ሚስት እጣ።



ተመልሶ የመጣ ሙሉ አካሉ ያለ

ፈለጥነው ቆረጥነው የደም ግብሩን ኳለ።



ወንድም ከወንድሙ ለተተኳኮሰ

በመሔድ በመቅረት ማን ከማን አነሰ

ዘመን ሸርተት ሲል

እርቅ ተፈፀመ አየሽ ተቃቀፉ

ለማን ቀረ ጀግና ?

ለማን ድል ጉብሎች ማልደው ረገፉ ?



አየሽ ልክ ነበርን 

ስሜታዊነቱ ዝቅ ብለን አለፈ

ንቀት በቀን ያልፋል ፍቅራችን ተረፈ።



ባል ያጡት ለመኑኝ

ለበዓል የገዙትን ዶሮ እንዳርድላቸው

እዚህ ድረስ ነበር ያሽሙር ዘፈናቸው

ታቀፉ ባዶ ቤት ተረፋቸው ኦና

በሞተ ባል ጀብዱ ጎጆ አይሞቅምና።



ስላንቺ እንደምዘምት ይነግርሻል ፍቅሬ

አንቺው ነሽ አገሬ ፍፃሜ ድንበሬ

የነኩሽ እንደሆን ያደርጉኛል አውሬ።



መሳሪያ ወልውዬ ሆ ሲባል አልዘምትም

ጥዬሽ አልጀግንም ከየትም ወደየትም 

ጀብዱ አንቺን ማቀፍ ነው 

ያጡት አያጡትም።

@getem
@getem
@paappii
1
የአርነት ጥያቄ?!

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።።።።።።።።።።።።

እኔም አንድ ሰሞን !

እንደ ክፉው ሳዖል

እልፍ አንገት ለመቁረጥ 

ሰይፍ ይዤ ስሮጥ

በቃላትህ በትር ፥ በድምፅህ ድንፋታ

መሬት ላይ ወድቄ ...

ልቤን አስማረክሁኝ ፥ መንፈሴ ተረታ ።

ከዛ ካህን ፈለግሁ ...

በደሌን ተናዘዝሁ ...

ደግሞም ያንተ ካህን ፥ መጥሀፍ አዋቂ 

የስምህ ቀዳሽ ሰው ፥ ቃላትን አርቃቂ

ሰይፍ እንዳነሳ ፥ ሰይጣን በኔ አድሮ 

እልፍ አንገት ለመቁረጥ ፥ እንደቆየ አሲሮ 

ስህተቱን ጠቅሰው 

እንደነበር አርገው 

ከቃልህ ቀንጭበው

መክረው አስተማሩኝ

ይሄን ባሉኝ ማግስት 

እኔም ያንተ ፍጥረት....

ጲላጦስን ሆኜ እጄን እያነፃሁ

ንሰሐዬን ሻርኩኝ ።

አንተም ይሄን ስታይ!

በአርያም ደንፍተህ ...

አይደረግም ብለህ.. .

ለምን ? እንዳትለኝ!

.

ሰይጣን በኔ አድሮ ፥ ለሚቀላው አንገት 

ለሚያቆየው በደል ...

በኔ ነፍስ ፈንታ ፥ ራሱ ይወንጀል ።

እኔ ምን ተዳዬ ???

@getem
@getem
@paappii
ቃል
""""

ቃልም ሲዘናበል
እሱም ቃል ነውና መምከሪያም ይጠፋል
ውሸትን በውሸት
ለማጥፋት ቢሞከር ውሸትን ያገዝፋል
አንደበትም የለ
አልታዘዝ ይላል ቃላት ቢደረደር
ለቃል መገሰጫ
ከቃል የከበደ ቃልም ስላልነበር
ይከብዳል እውነት ነው
ያ ቃል ያጠፋ ቀን በቃላቶች መምከር።

አብርሃም
@Run_Viva_Run

@getem
@getem
@GETEM
ሞጣ ቀራኒዮ፤
ሞልቶ ካህናቱ ቅዳሴ ሚቆመው በተራ በተራ ፤
ምነው በስተማታ ወይ የሚል ቄስ ጠፋ ለፍታት ሲጠራ ፤
ብለን ተማሮቹ ድንቅንቅ ብሎን ገርሞን ስናወራ ፤
ፍቅር ሚያስተምር ዋና ሊቅ ተገኘ ኡጋዴን ጅጅጋ ጎዴ ካራማራ።
ኧረ በዚያ መንደር ፤
ወንበዴ የዘራው ፤
የክፋት አዝመራ ስሩ ተመንግሎ ፤ ጠፋ አሉ መጋኛ ፤
ሙስጠፋ ደግ ሰው ሙስጠፋ ሰውኛ ፤
ከብላክ ቦርዱ ስር ፤ ሲያስተምረኝ ዋለ ፍቅር በአማርኛ ።

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

መልካም የረፍት ቀን💚!

@getem
@getem
@balmbaras
ፍልቅልቁ አምባቸው!!!!!


ከጉግሳ ወሌ ሃገር ፤
ያውም በጌምድር ፤ጋይንትና ጉና ፤
እንደፈረደብኝ ፤
ደግሞ ሃዘን መጣ ፤
ደግሞ ለቅሶ ልድረስ እንዳምና ካቻምና ።
እነዚህ ጋይንቶች ፤
ሸለቆና ጅረት ወንዝና ተረተር ሞልቷል በደጃቸው ፤
ባይሆን ፤
በየበራበሩ ቀየ እየጠበቁ ፤
ሃገር እያቀኑ ቁመው የሚያድሩበት ይበዛል አምባቸው ።
አቄቶ ስማዳ፤
እስቴ ክምር ድንጋይ አንቺምና ጋሳይ ፤
ታቦርና ጋይንት ፤
እንደምን ይቻለው፤
ይህን ያገር ህመም ፤ይህን ያገር ስቃይ ።
ከመይሳው ሃገር ፤
ከካሳ ሃይሉ ቤት ጎንደር ተወልዳችሁ ፤
እንደጉና ዳገት ፤
ቀጥ ብሎ የቆመ ሰንደቅ ተሰጥቷችሁ ፤
ሃገር እንስራ እንጅ ፤
ጎጆ እናፍርስ ማለት አያውቅም ልባችሁ ።
እንደ ገብርየ ልብ ፤
እንደ ገልሞ ኪዳን ፤
በወንድምነት ልክ ፈርጆት ነው እንጅ ፤
ኧረ እነዚያ ሰዎች ፤
አይደፍሩትም ነበር ፤
የጋይንቶችን ቤት፤ የነ አጅሬን ደጅ ።
ያኔ በዚያ ሰሞን ፤
እነዚያ ሸፍጠኞች፤
የጀግኖቹን ጎጆ ፤
የአርበኞቹን ድካ ፤ ቅብቅቡን ሲያፈርሱ ፤
አማራን በሃሰት በፈጠራ ታሪክ በውሸት ሲከስሱ ፤
የወገኖቹ ጣር፤
እምባና መከራ እየኮሰኮሰው ብሶት አሳራቸው ፤
አትንኩት ይበቃል ፤
ቁስሉን አታቁስሉ በሚል አማርኛ ሰርክ የሞገታቸው ፤
ተረታ አሉኝ ዛሬ የጉናው ስር ጀግና ጋይንቴው አምባቸው ።
ከጨለማ አውጥቶ ፤
ከጉድጓድ አውጥቶ ፤
ሰው ያደረገውን ባለውለታውን ሸምጥጦ ሚከዳ ፤
ለካ በዚህ ዘመን ፤
አለ ሺህ አርዮስ አለ ሺህ ይሁዳ።
እነ ሞት አይፈሬ ፤
አምባቸው መኮንን ፤
ጀግናው እዘዝ ዋሴ ፤ ተስፋየ ጌታቸው፤
በመይሳው ካሳ ፤
በሹርባው ገመድ የተጎነጎነ ቃል ኪዳን አላቸው ፤
አትጠራጠረኝ ፤
እስከመጨረሻው ከጉና ተራራ ይገዝፋል ስማቸው ።
አንዱ እግሩን ከጋይንት ፤
አንዱ እግሩን ከጎጃም ፤
በነ በላይ ዝናር
በመይሳው ቤልጅግ ፤
በየበራበሩ በአጀብ በከራማ እየተራመደ ፤
ኧረ የዚያ ጎበዝ፤
እንኳን አንደበቱ ስራው ቁምነገሩ ምግባሩ ከበደ ።
ፋርጣ የጁየ ነው፤
ስረ መሰረቱ ፤
አይወድም ጭቆና አይወድም አሽከላ ፤
ጦም ማደር ይመርጣል ፤
በካልቾ እየመቱት ፤ ሆዱን ከሚሞላ ።
ተኳሹ ጋይንቴ፤
ጠበንጃው አይን አለው፤
ያያል ባሻጋሪ ከአዝመራው መሃከል ይነቅላል አረሙን ፤
ሰላቶውን እንጅ ፤
ሃገር ሻጩን እንጅ መች ይዳፈርና አብሮ አደግ ወንድሙን ።
ልክ እንደዚያ መስሎት ፤
ነው እንጅ ዘንድሮ ፤
ሳተናው አምባቸው ደርሶ መሸነፉ ፤
እስቴና ስማዳን መች ይደፍረው ነበር ቡልሃና እንከፉ ።
እስክብርቶ ይዞ ፤
ወረቀቱን ይዞ አግኝተውት እንጅ ዘንድሮ በድንገት ፤
የዚያን አጋሚዶ ፤
የእዘዝ ዋሴን ገድል ፤
የባሩዱን ሽፍታ ታች ጋይንት ያውራለት ።
ጉና ልብስ አጥቶ፤
ጎን አጥንቱ ገጥጦ ፤ ሲበርደው ጧት ማታ ፤
እዘዝ አይደለም ወይ ያገር ዛፍ አልብሶ ቆፈን የሚረታ ።
ጉና ተረተሩ ተሸረሸረ አሉ ፤ የበረዶ ጅራፍ ራሱን ገረፈው ፤
አይኑ ጉድ አየ አሉ ፤
እንዳምና ካቻምና፤
ወንድም በወንድሙ፤ ወንድሙን ሲጠልፈው ፤
ጠበንጃ ሲደግን ፤
ክፉ ቀን ትዝ ብሎት ፤
ወንድሜን እያለ ፤ደግሞ አንዘፈዘፈው ።
አማራነት እውነት ፤
አማራነት ክብር ፤
አማራነት ኪዳን ፤
የሰውነት ሚዛን ቢሆንም መንገዱ ፤
አሉ ይሁዳዎች፤
ጉንጩን እየሳሙ ወጪቱን ሰባብረው ውለታ ሚክዱ።
በአፍ ዲስኩር ተሳክረው ፤
በወንድማቸው ላይ ዝመት ተነስ የሚል ጩኸት የሚዘሩ ፤
አማራን ሳያውቁት በአማራነት ሽፋን ሰርክ የሚፎክሩ ፤
ዝመት ግፋ እያሉ በየሰርጣ ሰርጡ እሳት እያስጫሩ ፤
የወሬ ተኳሾች ወንድምን በወንድም አቀባብረው ቀሩ ።
ግን በዚህም መሃል ፤
ይሁዳ ቢኖርም፤ ሰላቶና ባንዳ ፤
ጴጥሮስም ቢመጣ፤
ገና ዶሮ ሳይጮህ ሶስት ጊዜ ሚከዳ ፤
ለአማሮች ነፃነት ፤
እስከቀራንዮ ይከፈላል ግብር ይከፈላል እዳ ፤
እስኪደረማመስ፤
ወያኔ ያቆመው ያ የክፋት ሃውልት ያ የጥል ግድግዳ ።
ጠላቴ ሆይ ስማ ፤
ከበሮ አትደልቅ ፤
ፌሽታህን አትደርድር እንዳሻህ አትዝለል ፤
ካንተ ነው ያየሁት ፤
በትግል በረሃ እንታገል ብለህ ወንድሞችን መግደል ።
ታሟል አሉ ሃገሬ ፤
በሸራችሁ ሾተል በሴራችሁ ጥይት አንገቱን ተቀልቶ ፤
ጉድ አየ ይህ አይኔ ፤
ትልቁ ሰው ገዳይ በትንሹ ገዳይ ሲስቅ ጥርስ አውጥቶ ።
አማራነት ሚዛን ፤
አማራነት ድካ ፤
አማራነት ልኬት ፤ የለው ግብር ይውጣ ፤
ከእኩሌታው ቀለም ፤
ባዘን የማይጎድል ፤ በሳቅ የማይወጣ ፤
ይህንን የማያውቅ፤
የማለዳ ጤዛ ፤ የጀምበር ምስለኔ ፤
ወደቁ አሉ እያለ፤
አስግጎ ይመኛል ሳርና ገደሉን ልክ እንደ ቀጭኔ ።
በምንጫችን ግርጌ ፤
ውሃ እንጠጣ ብለን፤
ኩልል ያለ ውሃ፤
መጠጣት ስንጀምር አለቅትና ጉድፉን አጥልለን በእጃችን ፤
ዛሬም አለ ለካ እናደፍርስ የሚል ሞልቷል በቀያችን ፤
ግን ደግሞ ግን ደግሞ ፤
ከጨለማው መሃል፤
ይወለዳል ገና ላገር የሚበቃ ቀንዲል ብርሃናችን ።
የከዳችን ጀምበር፤
የራቀውን አድማስ ፤ በፍቅር ያደመቁ ፤
በውበት ሞሽረው ፤
የማለዳን ጠሃይ በፍቅራቸው ጠርተው ማምጣት የናፈቁ ፤
የጨለማን ገደል ፤
ሊንዱ ሲያስቡ ፅልመቱን ሊገፉ ፤
በበላኤ ሰብ እጅ ፤
ከወንዙ ጎደሉ ከመልካው ተገፉ ።
ጅረትን ቢሰብሩት ፤
ከወዲያ ከወዲህ ፤ ዘለላውን ከፍለው እየቀናነሱ ፤
ክረምቱ ሲመጣ ከወንዙ መልካ ላይ አይቀርም መፍሰሱ፤
ወንዙ ደረቀ አትበል ጅረት ቀረ ብለህ ከቴም አትፅናና ፤
እንደ ሃምሌ ሰማይ ፤
ጀግና ሲያስገመግም መገንፈሉ አይቀርም ወንዝና ጉተና ።
እኒያ ወንድሞቼ ፤
በደማቸው ፅፈው፤
ሰማይ ሙሉ ህልሞች ፤በክዋክብት ልክ የተከፈከፉ ፤
ምን ጣይ ቢበላቸው ፤
ታምር ህልሞቻቸው እንደ በጋ አበባ ጠንዝለው አይረግፉ ፤
ይልቅ ፤
በጨለማው መሃል ፤
ያበራሉ ሁሌም እንደ ግብር ችቦ በተራ በተራ እየተሰለፉ ።
ህልመኛውን ገድለው ህልምን ገደልን ያሉ ነበሩ ባገሩ ፤
ሲሞቱ ታይተዋል ፤
በሞተው ህልመኛ አኑሮት በሄደው ራይና ምኞት እየተባረሩ ።
ገደልኩ እንዳትለኝ ፤
አበቃ አከተመ እንዳትለኝ ዘራፍ ፤
ሲቆርጡት ሺህ ሁኖ ፤ሲበቅል አይቻለሁ ጀግናና ባህር ዛፍ ።
እናም አንተ ሆየ ፤
እኒያ ወንድሞቼን ፤
ገደልኳቸው ብለህ ተወኝ አታቅራራ ፤
ወድቆ የማይወድቀው ፤
ጠፍቶ የማይጠፋው ዝንፍልፍሉ ወይራ፤
ጠፋ አሉ ሞተ አሉ ብለህ ስታወራ ፤
እንደ ባህር ዛፍ ነው ፤
በቆረጡት ቁጥር አስር ሃያ ሆኖ መልሶ ሚያፈራ ፤
ደመንማኔ እያለ ድንገት ብቅ ሚለው ከበልጅጉ ጋራ ፤
ትንሳኤው ብዙ ነው፤
ትንሳኤው እልፍ ነው አትጠራጠረኝ አይሞትም አማራ።

((( ጃ ኖ )))💚💛❤️

@getem
@getem
@balmbaras
Audio
ሳሙኤል (ዜማስ)
ከህይወት ገፅ #27
ዛፌ (የፍቅር ፍሬ) የተሰኘው ግጥሜን እጋበዛቹሀለው::

piano:- Dagm

@getem
@getem
@getem
ኢትዮጵያዊ ነኝ
ለጠየቅሽኝ እንቆቅልሽ ፣ ሲጠፋብኝ እኔ መልሱ
ሀገር ስጠኝ የምትይኝ ፣ ደንቆሮ ነሽ አንቺ ራሱ!
።።
ሁሉ ሀገሩን ተከፋፍሎ፣ ክልልሎችን እያጠረ
ኬት አምጥቼ ሀገር ልስጥሽ ?፣ ሀገር ማለት ሰው ነበረ
ሰውም በዘር ተደራጅቶ ፣ ሀገር መሆን አቅቶታል
ገድሎ ሚኖር ተበራክቶ ፣ ሞቶ ሚያኖር ከሀገር ጠፍቷል
ይህን እውነት እያወቅሽው ፣
ሀገር ስጠኝ አትበይኝ ፣ በእንቆቅልሽ ልትለውጭኝ
ክልልና ዘር ነው ያለኝ ፣ ውሰጅና ሀገር ስጭኝ
.......
በላይ በቀለ ወያ

@getem
@getem
@getem