ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ኖርኩ አልልም እኔ
(ቡሩክ ካሳሁን)

የባንክ አካውንቴ ሞልቶ ካልፈሰሰ
መንግስት ሊቀፍለኝ ድግስ ካልደገሰ
የግቢዬ ቅጥር ከኤርትራ ካነሰ
ሲራጩ የኖሩት ይስጡ ትንታኔ
በየትኛው አፌ ኖርኩ ልበል እኔ?

ቁርሴን አዲሳባ ምሳ ፓሪስ ለንደን
ለመዛናናት ቬጋስ አማዞን ለአደን
ካልፈነጨሁባት አለምን በውኔ
ኖርኩ አልልም እኔ

እኔና ሃሳቤን ተሳልቆ የናቀ
እንደ እንቧይ ፈርጦ ፊቴ ካልደቀቀ
ምን ጥሩ ብሰራ ላልተርፍ ከኩነኔ
ይህንን ካላየሁ ኖርኩ አልልም እኔ

በአለም ኑሮዬ ካልተቀማጠልኩኝ
ነብርን በጡጫ ነርቼ ካልጣልኩኝ
በመሞቴ ማግስት በመቃብሬ ላይ
በወርቃማ ቀለም ለሁሉም እንዲታይ
‹ኖርኩ አልልም እኔ› ብላቹ ፃፉበት
የውሸት ኖሪያለሁ የእውነት ልሙትበት፡፡

@getem
@getem
@getem
+ጎበዝ ባንድእንጩህ+

ሳቅና ዳንሳችን ልብስና ቋንቋችን
ከጋራ ሜዳችን ለጉድ ቢለቀቅም
ከማንነት በቀር አግባብቶን አያውቅም

ይልቁንስ ወገን
ቀን ይወጣል ሲባል ቀን እየጨለመ
ያትጠገብ ጌታ መብት ለጠየቀው ሞት እየሸለመ
ቤተሰብ አርጎብን ስርቆና ዘረፋ
እንደ ስኳር ሁሉ አቁሞ ሲያድለን ሞትን በወረፋ

ዝምብለን እያየን
አለን መስሎን እንጅ ሁላችን አልቀናል
ጎበዝ ባንድ እንጬህ ቋንቋ ቢለያየን ለቅሶ ያግባባናል፡፡

///ሀብታሙ ያለው///

@getem
@getem
@gebriel_19
♡ ስሞት አትቅበረኝ ♡♡♡

በሂወት እያለሁ እንባዬን ካልጠረግህ ፣
በእኔ እንባ ማንባት ካላዘነ ልብህ ፣
ሰታመም ዝም ካልህ ፣
እራቤ ካልገባህ ፣
ጭንቀቴም ብሶቴም ከመሰለህ ተራ ፣
ድፍርሱ ሂወቴ በፍቅርህ ካልጠራ ፣
ደብዛዛዉ ሂወቴ በፍቅርህ ካልበራ ፣
ተልካሻዉ ኑሮዬን
ካላሰናዳከዉ ፣
የተደላደለ ቦታ ካላሲያዝከዉ ፣
ማየት የተሳነዉ
ፍቅሬን ካልመራሀዉ ፣
እዉነት እልሃለሁ ዉዴ...
ስሞት አትቅበረኝ ፣
እንባም አታንባልኝ ፣
ፀፀትም አትግባ
ይልቁንስ ፍቅሬ...
እንደ ሻማ ቀልጦ ፍቅሬ ሳያልቅብህ ፣
እጂጉን አምሮ ልቤ ሳይቆርጥብህ ፣
ስታመም አስታመኝ ፣
ሰከፋ አፅናናኝ ፣
ስወድቅ ደግፈኝ ፣
የጭንቀቴን ብሶት
የዉስጤን ተረዳኝ ፣
ድፍርሱን ሂወቴን
በፍቅርህ አጥራልኝ ፣
ደብዛዛዉ ሂወቴን
በፍቅርህ አብራልኝ ፣
ተልካሻዉ ኑሮዬ
ፈጥነህ አሰናዳዉ ፣
የተደላደለ ቦታዉን አሲዘዉ ፣
ማየት የተሳነዉ
ልቤን ይዘሀ ምራዉ ፣
ደስታና ፍቅርን ከልብ አስተምረኝ ፣
ሁል ጊዜ ሳቅልኝ ፣
ይሄ ካልሆነ ግን
ስሞት አትቅበረኝ ::
ምንጭ፦ ወንጌላዊት እሙ
=======================
ለ "ስሞት አትቅበረኝ" ግጥም ምላሽ
ከአያልቅበት ሰለሞን
እሙ በህይወት እስካለሽ እንባሽን አብሼ
ስታለቅሺ ሳይሽ ተንሰቅስቄ አልቅሼ
ስትዝኚ ዕያየሁ እጥፍ ካላዘንኩኝ
ምኑን ሰው ተባልኩኝ
ሢያምሽ ካላመመኝ
እራብሽ ካልራበኝ
ምኑን አፈቀርኩሽ ምኑን ወዳጅ ሆንኩኝ
ጭንቀትሽ ብሶትሽ ከመሰለኝ ተራ
ድፍርሱ ህይወትሽ በፍቅሬ ካልጠራ
ተልካሻው ኑሮሽን ካላሰናዳሁት
የተደላደለ ቦታ ካላሲያዝኩት
ምናል ባልተዋወቅን እላለሁኝ ዕኔ
ለፍቅርሽ መከታ ስላለመሆኔ
ይልቅስ አታስቢ ፍቅሬ
ቃል ልግባልሽ ዛሬ
ስታለቅሺ አልቅሼ ስታዝኝም አዝናለው
ባስለቀሰሽ ጉዳይ ዳኛም እሆናለው
እፋረደዋለው።
ፍቅርሽን ቀንበቀን በፍቅሬ አድሳለው
ምስቅልቅል ህይወትሽን ዘውትር አድሳለው
እታመንሻለው
አይንሽ አያለቅስም
ልብሽ አይቆዝምም
ፈገግታሽ አይፈዝም
የፊትሽም ፀዳል ከቶ አይደብዝዝም
ይኸውልሽ ፍቅሬ ቃል ልግባ ደግሜ
ፍቅርሽ ተሰራጭቷል ባካልና ደሜ
ሲያምሽ ያምመኛል ሥታዝኚም አዝናለው
ስታለቅሺ አልቅሼ ስትስቂም ስቃለው
በፊትሽ ብርሐን እኔም እደምቃለው
ነገርግን ፍቅሬ ሆይ ስሚኝ በጽሞና
ምናልባት ሚሆነውን አላውቀውምና
አድምጭ እንደገና
ምናልባት ይህ ቃሌን መጠበቅ ቢያቅተኝ
ለፍቅርሽ መከታ መሖን ቢያታክተኝ
ህይወትሽን ማቃናት ባልችል በስንፍና
ይሄ ወዳጅነት ከቶ አይሆንምና
አድምጭ እንደገና
በፍቅሬ ፍቅርሽን መፈውስ ቢሳነኝ
ሀዘንሽን ማዘን ከቶ ባይቻለኝ
ዕንባሽን አብሼ
ባንቺ ፈንታ አልቅሼ
ሀዘንሽን አዝኜ
ሥታባክኝ ባክኜ
ካልተገኝኁ እኔ
ስትሞች አላለቅስም
ለቅሶ አልቀመጥም
በሞትሽ አላዝንም
ይልቅስ አድምጭ ነግርሻለው
ስትሞቺ ሞታለው
እከተልሻለው
እዚሕ በበደልኩሽ ላይ ቤት እክስሻለው
እመኝኝ ቃሌ ነው።

ምንጭ፦ አያልቅበት ሰለሞን

@getem
@getem
@getem
ትርጉምና ንፃሬ ፩

፨፨፨

በዝናብ በዶፉ መጓዝ እወዳለሁ
እንባዬ አይታይም እሄንን እውቃለሁ
ብሎ ነበር ቻርሊ ቀልደኛው ተዋናይ
ዛሬ ላይ ግን በዝቶ አልታየሁኝም ባይ
በጭጋግ እለታት ጭስ በደበቃቸው
ሲያጨሱ እሚውሉ አሸን ሰብእ ናቸው
ትርጉም ሳይገባቸው ሳያውቁት በውሉ
መደበቅ መስሏቸው ቃሉ ማስተዋሉ
መዋኛ ገንዳ ውስጥ የሚሸኑ አሉ
ህመምን መሸፈን እንባን መሰወሩ
ፈገግ ብሎ ማለፍ መልካም እያወሩ
ውስጠት ቢቃጠልም ፊትን ማቀዝቀዙ
ለመሸከም ነበር ህመምን በወዙ
ወትሮም ያልተረዳ መች አርፎ ቁጭ ይላል
መልካምን በክፋት ተግብሮት ይኮራል

፨፨፨

ኪነ ዳን ( @Nirvana134 )

@getem
@getem
@getem
#የኔ_ሴት
#ከውሰር[ጋዜጠኛው ዶክተር]
.
በተስፋ ባህር ጉዞ፣ወደ ፊት ነጎድኩኝ፤
የኔን ሴት ፍለጋ፣መልህቄን ያዝኩና፣ወደፊት ቀዘፍኩኝ፤
ግጣሜን ስስላት፣ሀዋዬን አፈቀርኩ፣ነገን ዛሬ አስቤ፤
ያላወኳት ሚስቴን ሳላዉቃት ወደድኳት፣ማፍቀሯን ተርቤ።
ስለሷ እያሰብኩኝ፤
በተስፋው ባህር ላይ፣ፍቅሬ ተንሳፈፈ፤
ጨለማው ነግቶልኝ፣ደስታዬም ገዘፈ፤
ብእሬም አድምቆ፦
የኔ ሴት እያለ፣ብዙ ግጥም ፃፈ።
.
ሌሎች ከሴታቸው፣አሉታውን ገልጠው፤
የሚስትነት ጣእም፣የላትም ይላሉ፣ጥፍጥናዋን ሽጠው።
የታል ሚስትነቷ?የታል ሴትነቷ?ይላሉ በትዝብት፤
ሚስትነቷን አጥተው፣ሴትነቷን ሸሽተው፣ዘውትረው በግርምት።
.
የብሶት ዜማቸው፣ጎልቶ ውስጤ ቢገባ፤
መልህቄን ቀዝፌ፣የኔን ሴት አየዋት፣ሠመመን ስገባ፤
በተስፋው አለም ውስጥ ጎጆዬን ስቀልስ፣የኔ ሴት ውስጥ አለች፤
እራሷን አፅድታ፣በስራ ተጠምዳ፣ሽር ጉድ እያለች፤
ሠላምታዬን ሳቀርብ፣ምላሹን መልሳ ግንባሬን ሳመችኝ፤
እንኳን ደህና መጣህ፣አረፍ በል ፍቅሬ፣ፍቅሯን ለገሠችኝ፤
የሚስትነት ለዛን፣የሴትነት ጣእሙን፣ግቱን አሳየችኝ፤
.
ጠባብ ቤቴ ያኔ አማረ፤
ሳቋ ጎልቶ ጭንቀት ቀረ፤
መዉደቅ መክሰር ተሰበረ፤
ፍቅር ነግሶ ጎልቶ ኖረ፤
መንገሳችን ተበሰረ፤
ልቦናችን በፍቅራችን፣አካላችን ተሳሠረ።
በሷ ብርታት ጠነከርኩኝ፣ፀባይ ገዛው በፍቅር ላቅኩኝ፤
በስግደቴ በረታሁኝ፣በንግስቴ ንጉስ ሆንኩኝ።
እሷ ማለት እኮ፦
የሷ መኖር የሚያኖረኝ፤
እሷ ማለት በቃ እኔ ነኝ፤
ብለው እንዳዜሙት፣ግነትን ቀላቅለው፤
በሷነት መንፈስ ውስጥ፣የኔ መንፈስ አለው፤
ገላዋ የኔው ነው፣ለሌላው ሽፍን ነው፤
የኔ ደስታ ማለት፣ስለሷ መኖር ነው።
የኔ ሴት ለእኔ፦
አይኗ እያነባ ልቧ እያዘነ፤
ቃሏ ከእውነት ውጭ፣ለሀሠት የቦዘነ፤
"ህይወቴ ባዶ ናት አንድ ቀን ያለርሡ፤"
ብላ ምትፀልይ ናት፣ቆማ ከመጅሊሡ፤
.
ፍቅሯ ያስነባኛል፣ምክሯ ይሠራኛል፤
የእሷነት ተግሳፅ፣እኔን ያኖረኛል፤
ያኔ ኮራሁ በማግባቴ፤
ውሀ አጣጬን በማግኘቴ፤
ደመቀልኝ እኔነቴ፤
አስከበረኝ ባልነቴ፤
በሀሳቤ አለች ለኔ ሚስቴ።

[KEWSER]

@getem
@getem
@Alkewsism
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ትንቢት
(ቡሩክ ካሳሁን)

ነገ
ፀሀይ በምስራቅ ትወጣለች ነፋሳትም ይነፍሳሉ
ትንቢቱ አማናዊ ነውና ምዕመናን አሜን በሉ
አሜን እንደማለት ቁጭ ብላቹ ምታፈጡ
ከአሜን ይቀራልና ዣንጥላ ይዛቹ ውጡ
ከአሜን ሚቀር ትንቢት ነው ወይ? ወይ ምርቃት? የምትሉ
አተካራውን ትታቹ እደግመዋለው አሜን በሉ!
ከነገወዲያ ነገ ትላንተ ይሆናል
ትንቢት መናገር ባላቆምም ትንቢቴ ግን ይፈፀማል
ብዙዎች ትንቢቴን አጣጥለው ይስታሉ
ነገር ግን
ከነገ ወዲያ ላይ ቆመው ነገን ትላንት ይላሉ
ለትንቢቴም ይታመናሉ
ደግም በምዕራብ ፀሀይ ትጠልቃለች
ከእርሷ መሄድ ለጥቆ ይከተላል ጨለማም
ነገ የደረሰ ምስክሬ ነውቆጥረው በትንቢት አልታማም
በጠቆረውም ሰማይ 1001 ከዋክብት ይታያሉ
ቁጥሩን ለሚጠራጠሩ ቆጥረው ማረጋገጥ ይችላሉ
በረከት በበረከት ትሆናላቹ እንደታየኝ ሌሊት ሳልም
አትጠራጠሩ እንኳን ህልሜ የምቃዠው ጠብ አትልም
በረከቱ እንዲሞላቹ በአዲስ ፀጋ እንድትሰምጡ
በኪሳቹ ያለውን ያለስስት ለኔ ስጡ፡፡


@getem
@getem
@burukassahunC
======​ለሟቹ ወዳጄ======

ይሄው ትላንትና
ያመንክበት ሚስትህ ባንተም የተመካች
ሙት አመትህ ሳይደርስ ፈጥና ሌላ ተካች።
የመስክህ አበቦች አንተን ባጡ ግዜ ጠውልገው ረገፉ
የልብህ ወዳጆችህ
የሙት ደጃፍህን እያዩት አለፉ።
ግን ዛሬም ታምኖ፣
በናፍቆትህ ታሞ፣ በቁምህ የሞተው
የቀድሞ ፍቅርህን፣ መውደድህን ባይተው
ያ ታማኙ ውሻህ ሰው መልመድ አቃተው።


@getem
@getem
@paappii

#Ezana mesfin
ክፍት የስራ ቦታ
(ቡሩክ ካሳሁን)

ድርጅታችን
ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀ
ስለሚሰራው ስራ ከ ሀ እስከ ፐ ያወቀ
ከጠቅላይ ሚኒስተሩ ሜዳልያ
ከከንቲባው ጠቦት ዋልያ
ያገኘ
የኮብል ስቶን ንጣፍ ለሰፊው ህዝብ ያበረከተ
20 አመቱ ሆኖ የ22 አመት ልምድ ያካበተ
ከተቻለ ስለ ደም-ወዝ ማያነሳ
ካልሆነ ግን ያለንን ሰጥተነው እጅ የሚነሳ
ከተገኘ ውድ አመልካች
እነዚህን አሟልተህ ከኛ ብትቀርብም
ቆንጆ ሴት ከመጣች ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡


@getem
@getem
@burukassahunC
ወንድ እና ጡት
--------------------
"ኦ!አዳም!" "ኦ!አዳም!"
ጥሪ መጣ ከአርያም!
"አቤት ባይ ግን የለም!
በጡቶቿ መሀል አንገቱን ወሽቆ፣
በለሱን ይገምጣል አዳም ተደብቆ።
ከዚያኔ ጀምሮ . . .
በጡት መሀል ልክፍት፣
አዳም ይባክናል ከህይወት እስከ ሞት።
ልጅ ሆኖ እየጠባ፣
ይደበቅበታል ጎርምሶ ሲያገባ።
==============

በላ ልበልሀ!
-----------------
በላ ልበልሀ፣
በሀገርህ ዠማ ስር
ሙግት ልግጠምሀ!

ከቢራው ግሳት ነጥሎ፣
ቁንጣኑ ይቅርብኝ ብሎ።
ኢትዮጵያን ብሎ የዋለ፣
ሀገሬን ብሎ የማለ፣
እስቲ ይቆጠር ስንት አለ?
============

የድሌ ቀን
-------------
ባልነዘረ ክራር
ባልተነፋ እምቢልታ፣
ባልተመታ ታምቡር
ባልጮኸ ጡሩንባ፣
አካሌ ሲደንስ
እስክስታ ሲመታ።
በሌለ ሙዚቃ
ብለው ለሚስቁ፣
የድል ቀን ሲመጣ፣
"ሹ.ክ.ሹ.ክ.ታ" እንኳ
ቅኝት መሆኑን ባወቁ።
===========
የ"10" ሣንቲም እውነት
በወንድወሠን ካሣ
፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨


@getem
@getem
@SABT48
ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ

@getem
@getem
#ትዝታ,,,,

ደሞ መጣ ክረምት በጋውን አባሮ፤
ያለፈ ህይወቴን ትዝታን ከምሮ፡፡
በሚወርደው የዝናብ ዶፍ መሀል፤
የበፊት ወዳጄ ፍቅሬ ይታየኛል ፤
ብርድ ባወረዛው መስኮቴ ፊት ቆሜ አሻግሬ አያለው፤
ከዝናቡ መሀል እኔና እሱን አየው፡
ወገቤን በ'ጆቹ ጠበቅ አርጎ አቅፎኝ፡
ደሞ ፈገግ አልኩኝ ሁኔታው አስገርሞኝ፡
ብዬም ተመኘሁኝ የጥንቷን ባረገኝ፡፡

አሁንም ናልኝ ፍቅሬ ፤
ና'ማ ተከተለኝ በዝናብ እንበስብስ፤
ለዘመን የሚተርፍ ትዝታን እንቀልስ፤
ህይወትን እናድስ፤
ልብሳችን ይበስብስ፤
ፀጉራችን ይበስብስ፤
ጫማችን ይበስብስ፤
በተፈጥሮ ፀጋ አካላችን ይራስ፡፡

ና'ማ ተከተለኝ በ ዶፉ እንሩጥ፤
በቃ ያስወድቀን ያ ልስልስ ያፈር ድጥ፡፡
እጆቼን ያዛቸው አጥብቀህ በጆችህ፤
በ አንደድ ትቆራኝ ህይወቴ ከ'ይወትህ፡፡

ና'ማ ተከተለኝ እንደ ልጅ እንሁን፡
ጎርፍ ውስጥም እንግባ ጭቃውም ያዳልጠን፤
ሁሉንም እረስተን በፍቅር እንስከር፤
የኔና አንተን ብቻ ሌ,,ላ አለም እንፍጠር፡፡

//ማህሌት መሰረት //

@getem
@getem
በዛ በበጋ በዛ በክረምት

በዛበበጋ በዛበክረምት
ወዳጄ ጠፍቶብኝ ፍለጋ
እውነት ሸሽታኝ ሆናብኝ አንተጋ
ካደግንበት ቀዬ፣ካደግንበት መንደር
ከሀደ ደኑ አድባር፣ከ አባቢያ ሀገር

ከዚያ ወብ ስፍራችን
አባጊዲ እግር ስር
አ፣ባ፣ጫ፣ዳ ስንቆጥር
ተኮ፣ ለማ እያልን ስንቀንስ ስንደምር
ካደግንበት ቀዬ፣ ካሳደገን መንደር
ከአዴ ኪሮስ አድባር፣ከ አያ ፈጠነ ሀገር

እስክስ ያልንበቱ ለአንባሻ ሽልማት
አዴ ከመይ ብለን እንጎቻ ለመብላት
ጨፍቅን አጅበን እልፍ ከብት መንዳት
እሳትዳር ቁጭብለን የስንዝሮን ተረት
መስማት
ትዝ ይልሀል? ትዝይልሀል አይደል ወንድምዬ
የዘመን ጓዴ እኩያዬ

ትዝ ይልሀል አይደል በዛ በበጋ በዛ በክረምት
በልጅነት ስንጫወት
ትዝ ይልሀል ወይ በብይ ስንደባደብ
በሴት ስንተራረብ
በ አሮጊት ፈስ
ስንቧቀስ

ትዝ ይልሀል አይደል ዘይቱን ስንለቅም
ካባ ወርደን ድፋርስ ውሀ ስንዋኝም
ደግሞ ለልደታ አድባር እንዳያኮርፋ
ከሰው ማሳ ፌስታል ብና በህብረት ስንዘርፍ
የእማማ እጅጋየሁን ቦርዴ ስንመጥ
የእትዬ ፀሀይን አነባበሮ ስንገምጥ
ጸግሞ ለጉዞአችን የጅሬንን አቀበት ለመውጣት
የንጉሱን ቤተመንግስት ተሳልሞ ለመምጣት
ተራራ ላይሆነን የጀሚላን ሀገር አጋሮን ለማየት
ቁም አገዳ የዘረፍነው
እልፍ ቃሪያ የነቀልነው
በዛ በበጋ በክረምት
በልጅነት በህብረት ስንጫወት
ከዚያ ካደግንበት ቀዬ፣ካደግንበት መንደር
ከአያ ጨፍቅ ግዛት፣ከሼህ ጀበል ሀገር

ትዝይልህ እንደሆን
ሴት ተናጥቀናል
ከ ጌኑ ጎመን ሰርቀናል
ከሼኪ ፓስቲ ቤት መልስ አጭበርብረናል
ጉርምስና ደርሶብን
አፍላ እድሜ ወጥሮን
ከየም ሰፈር፣ዳውሮ በር
ከአጂፕ፣ሰቃበር
ጫት ፍለጋ ስንዞር
አትረሳውም አይደል ወንድምዬ
አውቃለው መቼም አትረሳውም
ኦሾን ራምፓን አንብበን
ኪቶ ወንዝ ላይ ዮጋ መስራት ሲያምረን
ደግሞ ሙግት ስለ ጃንሆይ ተከራክረን
ስለ ቴድሮስ አብረን አዠነን
ስለ ጂብራን ደም እንባ አልቅሰን
ፐ-በዓሉ ግርማ ኦሮማይ የመፅሀፍ ቁንጮ እያልን
የአቤ አልወለድም እጅጉን ደስ ሲለን
ስለ ጉዱ ካሳ በጣሙን ሲገርመን

ምን አለፍህ
ምን አለፍህ ወንድም አለም የኔ ያንተ
የልጅነት፣የአፍላ ታሪክ እኮ ተወስቶ አያልቅም
መጨረሻው ባያምርልን
ካደግንበት ከኖርንበት ቀዬ
መጥቶ አዲስ ፈሊጥ አዲስ ዘዬ
፦እትብታችን
፦ መንፈሳችን
፦ የልጅነት ትዝታችን ካለበት መንደር
ሰፋሪ ናቹ ተብለን ስንባረር
አውቃለው! አውቃለው ወንድም አለም
ከፍቶሀል፥ከፍቶኛል
የሀደ ጃፈር ፍትፋት ናፍቆሀል ናፍቆኛል
የፋጤ ወፍራም ብና አምሮሀል አምሮኛል

የእቴትዬ ቁጣ ናፋቆሀል አውቃለው
የአዴ ኪሮስ ሽሮም ታይቶሀል አውቃለው
አቤት!አቤት ግን ጊዜ እንዴት ክፉ ነው
ወንድማማችን በዘር የበተነው
ጊዜ እንዴት ክፉ ነው?
ቋንቋ አለመቻል ልጅነት እንጂ
እውነት ግን ወንድምዬ ንቀት ነው
ዝም አትበል ንገረኝ እውነት እንደዛ ነው
የኔስ ነገር እውነት እንዳሉህ ነው
አንቺ ሸዋበር ሆይ የጅማ መርካቶ
አንቺ አራዳ ሆይ ካስፈለገም ቦሳ ኪቶ
ሁሉም ይጠየቁ
እውነት እኛን ካላወቁ
እስቲ ይጠየቁ መፈናቀላችንን ከናፈቁ
ይጨየቁ፣ ጠይቁ

ከናሆም አየለ
ለአብሮ አደጎቼ በሙሉ

@getem
@getem
@gebriel_19
🚪ልዩ የኪነ ጥበብ ምሽት

ያልታመመ አይምሮን እንዴት ማከም ይቻላል?

በ አትዮጵያ ብሄራዊ ቲያትር
ሰኞ ግንቦት 5 / 2011
11:00 ጀምሮ

አዘጋጅ ሰምና ወርቅ ሚዲያ
@tebeb_mereja @getem
@tebeb_mereja @wegoch
የሰካራሙ ሴራ*
(ቡሩክ ካሳሁን)
ዛሬ
‹‹እድል ከኔ ጋር ነች ኢላማዬ መታ
ለዚ ድንቅ ስኬት እጠጣለሁ ማታ››
ነገ
‹‹አለም ከፈችብኝ ፊቷ በኔ ዞረ
ከማጧ ይወጣል በደንብ የሰከረ
አልኮልኮ ውሀ ነው ጨጓራው ላረረ››
ብሎ እንዳልነበረ
ከንግዲ ምጠጣው በሁለት አጋጣሚ በማለት በየነ
ብለን ሳንጨርስ ‹ይሄ ሰው ሰከነ›
አጋጣሚው ለካ ልደቱ ከሆነ ልደቱ ካልሆነ!
.
ስኬቱ ቢለይም ውድቀቱ ቢለይም
ውጤቱ አንድ ነው የሞላ መለኪያ እያነሱ እልም!
እሱኮ ፅኑ ነው ከጊዜ ለውጥጋ አይቀያየርም፡፡
.
ደግሞ ለሰካራም ሰበብ መቼ ያጣል
ይሄ ግጥም ራሱ ያስጠጣል ያስጠጣል!!

*ሴራ በዚህ አገባብ ተንኮል የሚለውን አቻ ፍቺ ይዞ የሚገኝ ሳይሆን ይልቁንም በልብ-ወለድ፣ በፊልም ድርሰትና በመሳሰሉት አላባ ሆኖ ምናገኘውን ‹ሴራ› ማለትም ምክንያትንና ውጤትን በአንድ ላይ በመያዝ የታሪኩን ቅጥጥል የሚፈጥርልን እንደ ማለት ነው፡፡

@getem
@getem
@burukassahunC
👍1
*ምን አለ ? *
እንካ ሠላምቲያ በምንቲያ ሳትለኝ ቃልህን ሣልወርሰው
መልሴን ተቀምቼ በለምን ጥያቄ እንዴት ልመልሰው
.........................
እንኪ ያለኝ ሁሉ የልብ አውቃ መስሎኝ በምንቲያ የምለው ፣
ለካስ ከኔ ነጥቆ ጥሙ እንዲቆርጥለት መጥለቂያው አርጎኝ ነው

....................
አለማወቅ ደጉ መሬት እያስላሰ ነግሰሻል ይለኛል
አላዋቂ እኔ ሺ የማስከትለው መንጋ ያሰኘኛል
....................
ያለማወቅ ህመም ስቃዮን ማን አይቶት
ፈራጅ በበዛበት ቀጪው ባልተለየ በታረዘ ችሎት
......................
ፈራጅ በበዛበት ...
ልክነት ልክ አቷል
ጓራዴው ተቀምጦ ሠገባው ይቆርጣል
እውነት ነው ልክ አቷል
እንዴት ከድህነት ስቃይ ይመረጣል ?
................
ዘወርዋራ አለም እያገላበጠው
መዛኝ ልክ ቢያጣ
እንዴት ፍቅር እያለ ይመለካል ቁጣ ?
..................
እንኩ ሠላምቲያ በምንቲያ አትበሉኝ
አላውቅም ያመኛል
መዳኛዬን ጥሩት ድህነቴን ፈልጉት እሱ ይሻለኛል
............... .....
መዳኛዬን ጥሩት ፈልጉት ያድነኝ
ከራሴ ልታረቅ ሠው መሆን ያክብረኝ
....................
በምን ላለኝ ሁሉ ...
እንኪ ላለኝ ሁሉ በምንታዬን ልቸር
ምን አለ እያልኩኝ የልቤን ልናገር

.............//..............

በሔለን ፋንታሁን

@getem
@getem
@lula_al_greeko
👍1
ተረት ተረት
ድሮ ድሮ
ገዢና ተገዢ
አውራጅ እና ወራጅ
ፈራጅ እና አድማጭ
ሽቅብ እና ቁል ቁል
የሚተያዪባት
ጣሪያ ካስማ የሌላት
ዓለም እንዳበደች
ሌጣዋን ነበረች።
እሺ......
(እሺ ማለት ጥሩ)
ከዚያማ ሲኖሩ
ሲኖሩ..... ሲኖሩ ...
ከለታት ባንድ ዕለት
አላዛር ከበላይ
ባለጠጋው ከታች
እንደተቀመጡ
ባንዲት ጠብታ ውሀ
ተው ስጠኝ አልሰጥም
ክርክር ገጠሙ
(ይሄኔ ፈጣሪ እጅጉን አዘነ
ተከፍቶም አልቀረ
መፍትሄ ወጠነ።
እሺ......
(እሺ ማለት ጥሩ
ከዚያማ
የበላይ የሆነው
በታችኛው ኑሮ
አይቶ እንዳይሳለቅ
የበታች የሆነው
በላይኛው ድሎት
ቀንቶ እንዳይሳቀቅ
እግዜር እጁን ጠልቆ
ከውቅያኖስ ትቢያ
ምድርን ጋረዳት
በሰማይ ወስከምቢያ።
እሺ......
(እሺ ማለት ጥሩ)
ከዚያማ ሲኖሩ
ሲኖሩ..... ሲኖሩ ....
የላዩን ባናቅም
ከታች ግን ባሉ
ትንንሽ እግዜሮች
እንደ አሸን ፈሉ ፈልተውም አልቀሩ
ትንንሽ ሰማያት
ለራሳቸው ሰሩ
እሺ......
(እሺ ማለት ጥሩ
ከዚያማ ሲኖሩ
ሲኖሩ..... ሲኖሩ .....
ገዢና ተገዢ
አውራጅ እና ወራጅ
ፈራጅ እና አድማጭ እንዳይተያዩ
መብራት ያጠፋሉ
አንዳይገናኙ
ስብሰባ ይገባሉ
እንዳይሰማሙ
ቢሮ ይቆልፋሉ።

ዳኒ.B

@getem
@getem
@gebriel_19
///ማስመሰል///

ያ ሁሉ መታከክ መሸጎጥ ከእቅፋ
የእጆቹ መዘርጋት ፣ሮጦ ማቀፉ
የልቡን ንክሻ ሰውሮ በሸሩ
ስሞ ሲሰናበት ባስመሳይ ከንፈሩ
መግባቢያ ነበረ ይሄ ሁሉ ሴራ
ከ 30 ዲናር ወዳጆቹ ጋራ
የጌታ መከራ የስቃይ መንገዱ
ጥርጊያውን ካገኘ በይሁዳ ጓዱ
በማስመሰል ጅራፍ ጌታውን ለጎዳ
ይነስበት እንዴ ከሰቀሉት መሀል መመደብ ይሁዳ??

ዘንድሮ ዘንድሮ የይሁዳ አንጡር
ተንሰራፍቶ ከትሟል በሁላችን ሰፈር
ሙልጭልታ አንደበት አዳልጤ ሽለላ የፈገግታ ጉጠት የክፍት አተላ
በውስጡ የሞላ ስንቱ አለ ሞልጫፍ
የሳመን ሲመስለን ልክ እንደ ይሁዳ አቅፎ የሚደፍ

በዝህኛው ዘመን ቢመጣ ለሳንሱር
ይሁዳ እራሱ
ከኛ የሚማረው ብዙ ተንኮል ነበር


ግጥም።ምህረት ሻውል(Mሬ)

@getem
@getem
@getem
" ንገሪኝ "
( በአምባዬ ጌታነህ )

ሀገሬ እናቴ እምዬ የምልሽ፣
ስምሽን አስር ጊዜ ጠርቼ ማልጠግብሽ፣
እንደው ለሰላምሽ
ከቶ እንደምን አለሽ!
እኔ እንዳለሁ አለሁ
ስግነት ገምዶኝ
ከገዳይሽ ጋራ ምግብ እየበላሁ።
ደግሞ ከሟች ድንኳን ለእዝን ተቀምጬ፣
በገዳይ ስግነት በሞተው ወንድሜ ቀብር ተረግጬ፣
በዘር ነህ እሳቤ በከፋፍለህ ሴራ፣
ግማሼ ሟች ሆኖ ግማሽ ገዳይ ጋራ
ሳልሞት ተከፍየ እንደ አባት ሰባራ በሄድኩት አፍሬ፣
ከገዳይ ጋ ስስቅ በሟቹ ሳለቅስ እኖራለሁ ሳልኖር በቁም ተቀብሬ።
እንደዛች ሴት ህይወት
"የገደለው ባልሽ፣
የሞተው ወንድምሽ፣
ሀዘንሽ ቅጥ አጣ፣
ከቤትሽ አልወጣ"
እንደተባለላት
እኔም ጉዴ ሁሉ ጓድየ ጋ ሆኖ
መኖር እያስጠላኝ፣
ሞት እየናፈቀኝ፣
እንዳለሁ አለሁኝ።

:
እታተይ ሀገሬ፣
አንቺስ እንደምን ነሽ
ኑሮ እንዴት ይዞሻል፣
ትንሳኤሽ ርቆ ህዝቤን አፋጅቶታል።
ተስፋሽን ሚለኩስ የድል ችቦ ይዞ፣ አንድ ሰው ታጥቷል፣
የጎጥ ነፃ አውጭ እንጅ የአገር ነፃ አውጭ ጠፍቷል።
ንገሪኝ እማየ መቼ ነው 'ሚነጋው፣
ከጥላቻ ወተን በፍቅር ምንኖረው
ንገሪኝ እማየ
እየተራመደ በጥበብ መንገድሽ
ይሄንን የሚያደርግ ፦
ሞተው ከኖሩት ውጪ ሌላ ማን ልጅ አለሽ፣
ንግሪኝ እስኪ ቆይ
መቼ ነው አንድቀን?፣
ምንድን ነው ይነጋል?
በጎጥ ተጨራርሰን፣
ቀየሽ ባዶ ሲሆን?
ን.....ገ.....ሪ.....ኝ!


@getem
@getem
@amba8
Jeremiah:
ዉድ ቤተሰቦች እንደምን ቆያችሁ?

የፈጠረን አምላክ ከሰጠን እጅግ ብዙ መልካም ነገሮች መካከል የምንተነፍሰዉ አየር እጅግ የላቀ ዋጋ ያለው ይመስለኛል፣
ይሄን አየር በነፃነት እየተነፈሱ መኖር ደሞ እንዴት መታደል ነው!

የዚህን ጥቅም ለመረዳት ለ20 ሰከንድ መተንፈስ በማንችልበት ሁኔታ ውስጥ መሆን ብቻ በቂ ነው፡፡ እኛ ለሰከንዶች የሚከብደንን ነገር ሰዎች እየኖሩት ቢሆንስ??

ለዚህም ነው እህታችን ስመኝሽን መተዋወቅ ያስፈለገን፣ ስመኝሽ ለሰዓታት እንኳን ተፈጥሮ የቸረንን አየር በነፃነት እንድትተነፍስ
ሣንባዋ አልፈቀደላትም
ሁለቱም ሣንባዋቻ ከጥቅም ውጪ
በመሆናቸው ምክንያት በየጊዜዉ በሚሞላ የታመቀ ኦክስጅን
(oxygen bottle) እየተነፈሰች ዘወትር ከ አልጋዋ
ሣትርቅ ለመኖር ተገድዳለች፡፡
በዚህ ሁኔታ ውስጥ በመሆኗ መስራት አትችልም ፣መማር አትችልም ፣ የ 8 አመት ሴት ልጇን እንደ ማንኛውም እናት ምግብ
ልትቋጥርላት ቀርቶ ወደ ት/ቤት እንኳን
መሸኘት ተስኗታል፡፡
"እንደው ምን እንረዳሽ ዘንድ ትፈልጊያለሽ? "ብለን ስንጠይቃት
"የምትችሉትን ብቻ አድርጉልኝ በተለይ በተለይ ግን የራበኝ ሰው ነው ሰው ያስፈልገኛልና እባካችሁ ከጎንሽ ነኝ በሉኝ
ከልጄም አትራቁብኝ" ነበር ያለችው
እናም በመጪው እሁድ ስመኝሽ ቤቷ ቡና እንደምታፈላ እና ሰዉ ሁሉ እነዲጋበዝላት ትፈልጋለች እናም ለ ስመኝሽን እኔም ከጎንሽ ነኝ ማለት የፈለገ ሁሉ እሁድ ትጠብቀናለችና ሄደን የምንችለውን ሁሉ እነደርግ ዘንድ የመልካም በጎ ፈቃደኛ ቤተሰብ ጥሪ ነው፡፡
ዋጋ ያላት ነፍስ ለሌሎች የኖረችዋ ነች፡፡

የምንገናኘው፡ መገናኛ ሸዋ ሱፐር ማርኬት
ሰዓት፡ 2፡30

ለበለጠ መረጃ -0938753747
0912888649
Telegram a- @heny10 or @Ermiasgech

@getem
@wegoch