ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አንበሳ ያሆ በል ተነስ
🍺🍻🥂🥂🍻🍺
🦁🦁🦁🦁🦁🦁

መጥቷል አሉ ቢራ መንፈስን የሚያድስ
አቅልን አሳጥቶ ቤት እሚያስደረምስ
የልባሞች ቢራ የልባሞች መጠጥ
ቶሎ በል ተጎንጨው ቺርስ ብለህ ምጠጥ
ልባም ትሆናለህ ባለ ብሩህ ተስፋ
ስካር አያቅህም ጨልጠው በይፋ
ተዉን አቦ እንጨብስ እንጨፍር እንጠጣ
ቢራን ተፀያፊ ትውልድ እስኪመጣ
ችርስ...

ኪነ ዳን
🥂🍺🍻🥂

@getem
@getem
@getem
👍1
አ- በ- ው
-------------------------
(ከናሆም አየለ)
ተረትን ከምሳሌ እየደባለቁት
እያንዳንዷን ቅፅበት እያንዳንዷን ሁነት
በአንዲት ሀረግ አስረው
ትንሿን ገጠመኝ ትልቁን መከራ
በቃል አቅለውት ሲያደርጉት ተራ
ደግሞ አክብደውት ሲካብ እንደጋራ
ይሉሀል አበው
ስር ስርህ እያሉ ተረብ ነው ዘዬ'ቸው
------------------
ትላንት
ስትሰጪኝ- ስገፋ
ስትፈልጊኝ-ስሸሽ
ስትለሚብኝ-ስከፋብሽ
አንድያ ልብሽን ወንድ ያላወቃትን
ብቸኛ ፋቅርን ላንተ ብቻ ያልሻትን
ስንቅ ሳጣጥላት
ስገፋ ሳርቃት
አበው አይተው ድንገት
በእጅ የያዙት ወርቅ ብለው ያሉኝ እለት
የምን ወርቅ አመጡ
ይልቅስ ያድምጡ
ዘመድ ከዘመዱ
አህያም ካመዱ
እንዲኖር ግድ ነው
ለኔ አትገባኝም ብጤዋን ትፈልግ
እኔ ከሷ ልሆን? እኮ እንዴት ሲደረግ
ይህ ነበር መልሴ
ኩራት ያሳበጣት ተላላዋን ነብሴን አደብ አስገዝቼ
ቦታሽን እኔ ውስጥ ስፈልግ ቆይቼ
ብመለስ አንቺ ጋር
ሆነሽ ከእከሌ ጋር
ያገኘውሽ እለት
አበው እደለመዱት
ተረት ከምሳሌን እየደባለቁት
ላለፈ ክረምት ብለውኝ አረፉት፡፡

@getem
@getem
@gebriel_19
እምነት?
(ቡሩክ ካሳሁን)

አሀዱ አሀዱ
ከህጎቹ ቀደምት ከወግ ከልማዱ
ላልገደፈ ፃድቅ ላላለፈ ወጣት
ምንድነው ትርጉሙ ሲኦል ቅጣት ሀጥያት?
ሲዘልል ለኖረስ ሲጠጣ ሲዘሙት
ህጎቹን ለጣሰ በርትቶ እስኪሞት
ምን ግድ ይሰጠዋል ገነት ብትኖር ብትቀር
አለች ብሎ ማመን ምን ጠብ ሊያረግለት ከመጎምጀት በቀር?
ከዚህ በመነሳት አንዳንዶች ዋለሉ
‹እምነት እውነት ሳይሆን
ከራስ መታረቂያ ድልድይ ነው› እያሉ፡፡

@getem
@getem
@burukassahunC
:: # ሀ_ገ_ሬ
ምድርሽ ተጥለቅልቆ በቢራ ፋብሪካ
ምትንገዳገጂው ጨብሰሽ ነው ለካ
# Giday Kindaya
@getem
@getem
@getem
“ውድቀት በአንዴ እንደ ዱብ እዳ የሚወርድ መዓት አይደለም፤ ሰው በጀንበር አይወድቅም። ውድቀት ትናንሽ ስህተቶች በቀን በቀን ሲደጋገሙ ማለት ሲሆን ስኬት ደግሞ ትናንሽ ቁም ነገሮች በእየለቱ ሲከወኑ ማለት ነው።”
Join us @kindeal
🦋🦋🦋😇❄️❄️❄️
ጨጓራ ና ጉበት እየበሉ አባቶች፣
ስንት ዘመን ኖሩ ፣
ሌላውን አክብረው እየተከበሩ፣
የእኔ ዘመን ኗሪ ይሄ ግልብ ደግሞ ምላስ እየበላ፣
ሰላም ከእሱ ርቆ ሰውን እያጣላ ፣
ይኖራል በኩራት ህሊናውን ሽጦ፣
ገንዘብን ከእናት ልጅ ከስጋ አስበልጦ።

አምባዬ ጌታነህ

@getem
@amba8
@amba88
የኔታ ፍቄ ይባላል ቀደም ብሎ በግጥሞቹ ነበር ምናውቀው አሁን ደሞ ይቺን #ነጠላ_ዜማ ጀባ ብሎናል።።

Ft.Ben_X_Jordan_&_Bek_Ge-ez
🎧ያቻት
________
➡️RELEASED:2019
➡️GENERE:Reagetone Edm
➡️TYPE:#Single
➡️FORMATS:mp4 & mp3
➡️CHANNEL: @getem
_________
ሀያል ፍቅር

(ቡሩክ ካሳሁን)

ጥንቸሉ በኤሊው ኤሊው በጥንቸሉ
ከገደል በሰፋው ፍቅር ወድቀው ሳሉ
አንዱ ለአንደኛው እራሱን ለወጠ
ጥንቸሉ ሲያዘግም ኤሊው እየሮጠ!

@getem
@getem
@burukassahunC
ግራ ጎኔ ውሀ አጣጬ የኔ ተስፋ፣
ትተኛለች ወደ ማታ ልጅ ይመስል ቢራ ታቅፋ።
እሷ አምበሲት፣
ብሩህ ተስፋ እንዲታያት፣
ባንኮኒውን ተደግፋ
ሰርክ ቢራ ትጠጣለች፣
ነገን ልታይ በጠጣችው
እኔን ባሏን ለነገ አጣች።
አምባዬ ጌታነህ
@amba8 ለሃሳብ አስተያየት
@amba88 my telegram channel

@getem
@getem
የ "መ" ህጎች ተረት


ተረት ተረት......(የላም በረት)

ከዕለታት ባንዱ ቀን፣
ከህግጋት መሀል በ"መ"ሚጀምሩ፥
አንድ ላይ ሚጠሩ፣
ሶስቱ የ"መ"ህጎች፣
በሚባል ቤታቸው ይኖሩ ነበሩ።

መታቀብ፣መወ'ሰን፣መጠቀም፥
የበሽታን ጠጠር፣
ከምስር ለመልቀም፥
ሲኖሩ ሲኖሩ
ሲኖሩ......ሲኖሩ........
ለሚጠ'ቀሟቸው፣
በፈጠሯቸው አፍ፣ሰርክ ሲነገሩ፥
በነጋሪዎች ገላ፣
በሰሚው ጭን እሳት፣
አመድ ሆነው ቀሩ።

ትውልድ ሲገለገል፣በመቃብር ቤቱ፥
እንዲህ ተነበበ፣
በ'መታቀብ'ገዳይ፣
የ'መታቀብ' ሞቱ።

"መታቀብ"

"መታቀብ ተብዬው፣
የቅድመ-ጋብቻ፣ወሲብን ያግዳል፥
ህጉ እውን ከሆነ፣
ሰው ከማሕጸን ሲወጣ፣
ከመራቢያው ጋራ ለምን ይወለዳል?"

በሚል ፍልስፍና፥
መታቀብ ተሰዋች፣
በጭኖች ፍም-እሳት፣
ቃጠሎ ታፍና።



ትውልድ ሲገለገል፣በመቃብር ቤቱ፥
እንዲህ ተነበበ፣
በ"መወ'ሰን" ገዳይ፣
የ"መወሰ'ን" ሞቱ።

"መወ'ሰን"

"መወ'ስን ተብዬው፣
ካንድ በላይ አጋር፣
እንዳይኖር ያግባባል፥

ህጉ እውን ከሆነ፣

ከቅዱሱ ቃሉ ላይ፣
"ላለው ይጨመራል"
ለምን ይነበባል?"

ባላ'ቸው አንድ ላይ፣
ሌላን ለመጨመር፣ቃል እያጣቀሱ፥
በ"ቅዱስ ቃል" ቀሉት፣
ባንዲት ስንኝ ወጣ፣
የ"መወ'ሰን" ነፍሱ።


"መጠቀም"

የመጠቀም ህጉ ፣
"ኮንዶም"ን መጠቀም ፣
የሚለውን ያትታል፥

ግና ምን ያደርጋል

"ያገኙትን ዕድል
ባግባቡ መጠቀም"
በሚለው ተረቷል።
የ"መጠቀም" ህጉም-
ባንዳንዶች ሲነሳ፣
በሌሎች ይሞታል።

(ጭብጥ ሀሳብ)

የህግጋት መርቀቅ፣
ህጉን ያልወደደን እንደምን ይገዛል፥
እንደምን ይነካል፥
ህጉን ባልወደደው፣
በተገዢው ልኬት፣
ስፌቱ ተስፍቶ፣በህግጋት ይተካ'ል።



ስንታየሁ አዲሱ ሳንታ
(@San2w)
@Ezihbetsanaddis
ሚያዚያ 29/2011
ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ

@getem
@getem
@gebriel_19
እማ እውነት ነው ግዛት ቢኖረኝ ሳቅሽን ብሄራዊ መዝሙር አረገው ነበር
ክብር ለ እናቶች

መልካም የናቶች ቀን
@DEREAMANDESE
👍1
እናትዬ
🔸

ምሣሣላት አለች አይቼ ማልጠግባት
አኑርልኝ እያልኩ ዘውትር ማነባላት
ከዕድሜ ግማሹን ተችሎ ብሰጣት
ቢያንስባት እንጂ እሷ አይበዛባት
ደስታዋን እያየሁ ደስታን እንዳገኝበት
ጌታ ሆይ አኑራት...
በመኖሯ ስላለ ..የኔ ሕይወት

እናቴ የኔ እናት.....
የሚገባሽ ነገር ምን ይሆን እላለሁ?
ላረግሽልኝ ሁሉ ልመልስ እሻለሁ
ከ9ወር ጀምሬ ማብቂያውን አጣለው
ውለታሽ ተቆጥሮ ከቃላት በላይ ነው
ፍቅርሽ እንዳይወዳደር ወደር እንኳ የለው

እና እናትዬ .....እስኪ ምን ላርግልሽ?
እኔ ፈልጌ አጣሁ.. ላንቺ ሚመጥንሽ፣
ወድሻለሁ ማለት መሰለኝ ሚያንስብሽ፣
መውደዴን በምን ..ልግለፅልሽ?
እናትዬ.....እስኪ ምን ላርግልሽ?

ውብ ቃላቶች ብደረድር...፣
አይችሉም ሊገልፁ ለሆንሽልኝ ነገር፣
እናቴ ምን ልናገር...፣
አጣሁ ቃል ፈልጌ ስላንቺ ልዘረዝር፣
ግን
ወድሻለሁ ማለት ከገለፀ ፍቅር፣
ወድሻለሁ ብዬ በቃል ብቻ አልቅር፣
የሚገባሽን ሁሉ ላሳይሽ በተግባር።
እናትዬ ..እስኪ ምን ላርግልሽ?
የሚመጥን ካለ.. ለውለታሽ ምላሽ

**ብሩክ ፍፁም
"መልካም የእናቶች ቀን "

@getem
@getem
@buraaye
👍1
በነፍስና ስጋ
(በኤደን)

እኔ ያላንቺ ምንም ነኝ ያልኩትኝ
ባዶነቴ ታውቆኝ አንቺ የሞላሺኝ
ጥሩና መጥፎውን ደግና ክፉን

እንዳውቅልሽ ብለሽ
እያወራሽ ሳይሆን ተግብረሽ ያሳየሽ
አንቺ ማለት ለኔ ምርጧ እ-ናቴ ነሽ
........:... .....::::::::::
ሠው እንዴት ሞትን ሞቶ ያሳየኛል
ምንም ሳይለቀስ ነፍስሽ ሳትወጣ
ጥቁር ሳይለበስ
ትንፋስሽም ሳይቆም
በህይወት እያለሽ
እየሄደ እግርሽ
እኔን ለማኖር ነው
።።።።።።።።።።።።።።።።
በጠቆረው አለም እሳት በበዛበት
በየቦታው እሾህ ጉድጓድ በሞላበት
እንቅፋት ባለበት
ብዙ ግዜ ሞተሽ ፈጣሪ እያነሳሽ
አይዞሽ ባይ ሳይኖርሽ
ከመጠን ሳይቆጥሩሽ
ረግጠው አልፈውሽ
የህይወት ሞት ሞተሽ
ለኔ ለተራዋ ልብ ላጣች ልጅሽ
በሞትሽ እያኖርሽ
።።።።።።።።።።።።።።።
አንቺ ማለት እ-ማ
ብርቄ ድንቄ ልቤ አይኔ
ሁሉ ነገሬ ነሽ
ከሌለሽ የሌለዉ
ሲደክምሽ የምሞት
በሞተው ህይወትሽ
እየተረማመድኩ
ወደራሴ ስኬት
ወደፊት እየሄድኩ

በነፍስ ብትለይኝ
ቁልቁል ተምዘግዝጌ
አጥንቴ ማይገኝ
።።።።።።።።።።።።።።።።
እኔ ማለት ያንቺ ስሪት ነኝ
የሞትሽም ሟች ነኝ
በሞትሽ ውስጥ ህይወት ያለኝ

@getem
@getem
@gebriel_19
እናት
(ቡሩክ ካሳሁን)

እማ
ከመውደዶች ህንፃ ከፍቅሮች ከተማ
የተገነባሽው የማትፈርሽ ሀገር
የማትበታተኝ እፁብ ድንቅ ነገር
የቴውድሮስ ውጥን አስቀድሞ የገባሽ
አንቺ አንድ ሆነሽ ብዙውን ያግባባሽ
.
በአለም ኑሪ ከፍ ብለሽ እንደ ማማ…
የሰላም የተስፋ የርህራሄ አርማ
በውስጥሽ ለሚኖር የአናብስት ግርማ
ምድርን አንቀጥቅጦ ሰማትን ፈልጦ
ለሚገዛ ንጉስ ድንበርን አቋርጦ
ዙፋን እና መንበር ቀድመሽ የምትሆኚ
ለልጅሽ ፍስሀን ደስታን ምትመኚ
.
እናት
በአለም ኑሪ ከፍ ብለሽ እንደ ማማ
ዘእንበለ ድካም ወፃማ
ካንቺ ልግባባ እንጂ ካለም አልስማማ
አንቺን ከሚወስዱ ህይወቴን ልቀማ
እንዳሻቸው ሁሉ ከቤቴ ያስወጡኝ
ያለኝን ሀብት ንብረት ሁሉንም ይንጠቁኝ ሁሉንም ያሳጡኝ
ካንቺ አይነጥሉኝ በዚህ ሁሉ ግና
እንዳቺ የሚሆን ከቶ የለምና፡፡
05/09/2007 ዓ.ም

@getem
@getem
@burukassahunC
ቅመሱኝ
————
የብቻዬ ነገር ፣ በሌለባት አለም
ሚስትህን ተኛናት..
.........…......ቢሉኝም አይደንቅም
እንደ ንብ ካ’በባ ፣ ጫፋጩን ቀፍፎ
ምላሱን ለዋጀ ፣ ከማር አጠንፍፎ
ዝክር ለለመነ…
እንደ ጠበል ጠዲቅ ፣ ይሰጠዋል ድፎ
ሳይላስ በምላስ ፥ ለአይን'ኳ ሚጥም
ዳቦ እስካለ ድረስ ፥ .......ያጌጠ በቅመም
ለጉድ እየፈላ...
ቅመሱኝ ቅመሱኝ፥የሚል ወጥ አይጠፋም
.
( ሚኪ endale )
@getem
@getem
@MMIKU
አቤቱ ህዝብህን አድን

መጣሁኝ ብለክ እንደሄድክ
ይመጣል ብለን በተስፋ
ደጃፉ ገርበብ እንዳለ
በራፉን በቅጥ ሳንዘጋ
ምፃትህ ቢዘገይ ጊዜ
ተስፋችን እየሰለለ
ስንቱ አሳች ወደ ውስጥ ገባ
ስንቱስ ነው የኮበለለ።
አቤቱ ህዝብህን አድን
ከክፉም አንተ ጠብቀው
መምጫክን ወይ ሹክ በለው
ወይ ና ና በሩን ቀርቅረው ።
* * * * * * *
በስሜ ሺ ይነሳሉ
የምትል ቃልህ ቀን ነስታ
እነሆኝ እልፎች አምታቱን
ሰብለ አዳም ግራ ተጋባ።
ለስምህ ታርጋ ለጥፈው
አርገውክ ምርጫ ቅስቀሳ
ለምስልህ ዋጋ ተምነው
ሆንክብን ነፃ ጨረታ።
አቤቱ እርስትህን ባርክ ....
በምርጫው ወይ ተሸንፈን
ወይ አጥተን ሳንገዛህ ብንቀር
ብይንህ ሚዛኑን ስቶ
በፍርድህ ከምንማረር
እዚህ ነኝ የሚል ምልክት
እባክህ ከደጅህ አኑር።
* * * * * * *
ስንፀድቅ ቤታችን ጋብዘን
ስናፅ ከሰማይ ሰቅለን
ስንዘፍን ሶስትዜ አማትበን
ስንገድል እሱ ያቃል ብለን
ስንሰርቅ የግዜር ስጦታ
ስንዘሙት በግዜር ሰላምታ
አንተኑ ባንተው አፍርሰን
ሌላ ግዜር እኛው አብጅተን
ስትመጣ መልክህ ባይለየን
ሗላ ላይ እንዳታዝንብን።
አቤቱ ህዝብህን አድን.....
.... ከክፉም አንተው ጠብቀን
ፅድቅና ኩነኔ መሀል
ያኖርከው ቀጭኑ መስመር ከድፍረት ከእምነት ማጣት
ደብዝዞ ከመደናበር
እንዳሻን እየሰረዝን
እንዳሻን ከምናሰምረው
አቤቱ ፈጣሪያችን ሆይ
ቅፅሩን በግንብ አድርገው።
* * *
አቤቱ ወዴት ቆመሀል
ዝምታህ ከአውራ መብረቅ
ግርማው እጅግ ያስፈራል።
* * *
ዳኒ.B

@getem
@getem
@gebriel_19
"እንቆቅልሽ እማ"

======
እንቆቅልሽ እማ
"ማን ያውቅልህ ልጄ!"
እንቆቅልሽ ስላት "ማን ያውቅልህ" ብላ አይኖቼን የምታይ
በጉየዋ አሙቃ ቀን-አድራጊ ሰናይ
በአይኖቿ አድክማ በጥርሶቿ ገላ
ጥያቄን ልትመልስ እዝነ ህልናዬን አድማሱን ከልላ
እንግዲህ መልሺ
ጸጉሬን እየዳሰስሽ እንባዬን አብሺ
=====
ያለም ጥግጋቱን ቧጭረሽ-መርምረሽ
የእውቀት ስራስሩን ፈርቅቀሽ-ሰራስረሽ
ከጠፋሽ ቅያሱ
ሀገሩን ተይና ዘላለም
ኑሪልኝ እራስሽ ነሽና-የጥያቄው መልሱ

Mezin worku

@getem
@getem
@gwbriel_19
👍1
#የታሰረ ልብ#

በመዳፍህ ጥበብ፥በማዳንህ መክሊት
በመዉደድህ ድርሳን፥በፈገግታህ ዳዊት
ገላየን አሽረህ፥ በለኮስከዉ እሳት
ከዳዊት ጠንክረህ፥ከሰለሞን ልቀህ
ከተራራ ገዝፈህ፥ከሃሳብ ረቀህ
የልቤን ከረጢት፥እንደ ክርታስ ለብሰህ
በስጋ በደሜ፥እንደስኳር ቀልጠህ
ፍቅርን ከወለላዉ፥ከመረቁ ጨልፈህ
ለነገ ሳትሰስት፥ለዛሬ ችረኸኝ
ምነዉ ፥በጥዋት ጠፋህ፥ከጉም ጋር አሰረኸኝ
እንዳልሄድ፥እንዳልቀር፥እንዳልተኛ አርገኸኝ።

ልብ የሌለዉ ደረት፥ታቦት አልባ መቅደስ
የደረቀ ሎሚ፥ ያልተቋጨ ቀሚስ
የነቃ ብርሌ፥ ክር የሌለዉ ፍኑስ
ክንፍ የሌላት ገዴ፥ወላዋይ አረከኝ
በትዝታህ ገመድ፥የኋሊት አስረኸኝ።

ብጠራህ አትሰማኝ፥ብሮጥ አልደርስብህ
ብጠቅስህ አታይ፥ብሸሽህ አልርቅህ
በቆምኩበት ሮጨ፥ባይኔ ስከተልህ
ድንገት ብትሰወር፥ተራራዉ ጋር'ዶህ
ደርበዉ ኩታህን ፥በሩቅ ይጥራኝ ወዝህ
ካይኔ እንኳ ብትጠፋ፥እሽትቼ እንድሸኝህ።

በተኛንበት ሜዳ፥ በመስኩ ላይ፥ ልንከራተት
የቁም ቅዠቴን ልዋዥ፥ሞቴን በሞትህ ላትት
ሳቅህ፥ፋኑስ ይሁነኝ፥ዳናህን ልጥባ በሌሊት
ምስልህን፥አሽዋዉ ላይ፥እወንዙ ዳር ልሳልህ
ልግባ፥ ከፍቅርህ ሙዳይ፥አቤት ልበል በስምህ።

በለስላሳ ጣትህ፥አቅፈህ ባጎረስከኝ
በትዝታህ ሸማ፥ ፈትለህ ባለበስከኝ
ዉሉን ባፍህ ነክሰህ፥ከጉም ጋር አስረኸኝ
ከትናንት አቅርበህ፥ከዛሬ አርቀኸኝ
እንዳልወጣ ፥እንዳልወርድ፥አየር ላይ ሰቀልከኝ።

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1