እግዚአብሔርን የሚያምንና የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ በዚህ አንፀባራቂና የደስታ በዓል ደስ ይበለው፡፡ ብልህ አገልጋይ ቢኖር፥ እርሱ ወደ ጌታው ሐሴት ገብቶ ዕልል ይበል፡፡
በጾም የደከመ ቢኖር፥ አሁን ደመወዙን ይቀበል፡፡ በመጀመሪያው ሰዓት ወደ አምላኩ የቀረበ ቢኖር፥ ዛሬ ሽልማቱን ይውሰድ፡፡
በሦስተኛው ሰዓት የመጣ ቢኖር፥ እርሱ በዓሉን በምስጋና ያክብር፡፡ በስድስተኛው ሰዓት የደረሰ ቢኖር፥ አይጎድልበትምና አይጠራጠር፡፡ እስከ ዘጠነኛ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ሳይጠራጠር ይቅረብ፡፡ እስከ ዐሥራ አንደኛዋ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ስለ መዘግየቱ አይደንግጥ፡፡ ጌታ ቸር ነውና፤ በመጨረሻ የመጣውንም እንደ መጀመሪያው አድርጐ ይቀበሏልና፡፡ በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ለመጣው ከመጀመሪያው ሰዓት አንሥቶ ሲደክም ከነበረው ጋራ እኩል ይሰጧልና፡፡
መጨረሻ ለመጣው ጌታ ምሕረቱን ይለግሰዋል፤ መጀመሪያ ለመጣውም ያስብለታል፡፡ ለአንደኛው ይሰጠዋል፤ ለሌላኛውም ጸጋውን ያድለዋል፡፡ ለአንደኛው መልካም ምግባሩን ይቀበልለታል፡፡ ለሌላኛውም መልካም ፍቃዱን ይቀበልለታል፡፡ ለአንዱ ምግባሩን ያከብርለታል፤ ለሌላኛውም በቅን ልቡና የሚያደርገውን ጥረት ያደንቅለታል፡፡ ስለዚህ ኹላችሁም ወደ ጌታችሁ ደስታ ግቡ፡፡
ፊተኞች ኋለኞችም ሆይ! እኩል ደመወዛችሁን ተቀበሉ፡፡ ባለጸጐች ድኾችም ሆይ! በአንድነት ዘምሩ፡፡ እናንተ ብርቱዎች ደካሞችም ሆይ! በዓሉን አክብሩት፡፡ እናንተ የጾማችሁ መጾም ያልቻላችሁም ሆይ! ዛሬ ላይ ደስ ይበላችሁ፡፡
መሠዊያው ሙሉ ነውና ኹሉም በማዕዱ ደስ ይበለው፡፡ ፍሪዳው የሰባ ነውና አንድ ሰው ስንኳ እንደ ተራበ እንዳይሔድ፡፡ ኹላችንም የእምነት በዓሉን እንካፈል፤ ከቸርነቱና ከፍቅሩ ሀብትም እንቋደስ፡፡
ማንም ስለ ድኽነቱ አይዘን፥ ኵላዊቷ መንግሥት ተገልጣለችና፡፡ ማንም በኃጢአቱ አያንባ፥ ከመቃብሩ የይቅርታ ብርሃን ተንቦግቧልና፡፡ ማንም ሞትን አይፍራ፥ የመድኃኒታችን ሞት ከዚህ ነጻ አውጥቶናልና፡፡ ለእርስዋ በመታዘዝም ጌታ አጥፍቷታልና፡፡
በሞቱ ሞትን ገደለው፡፡ ወደ ሲዖል በመውረድ ሲዖልን በዘበዘው፡፡
ኢሳይያስም አሰምቶ እንደ ተናገረ ሲዖል ከጌታችን ጋር ፊት ለፊት ተገናኘች፤ መረራትም! ከንቱ አድርጓታልና መረራት! ሸንግሏታልና መረራት! ሽሯታልና መረራት!
ነፍሳትን ይዛ እንዳታስቀር አስሯታልና መረራት!
[መቃብር የዕሩቅ ብእሲ] ሥጋ አገኘሁ ብላ ዋጠችው፤ ስትውጠው ግን እግዚአብሔር ኾኖ አገኘችው - መረራትም!
ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል፥ መቃብርም ሆይ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ?
ክርስቶስ ተነሣ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ!
ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቸዋልና፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@getem
@wegoch
በጾም የደከመ ቢኖር፥ አሁን ደመወዙን ይቀበል፡፡ በመጀመሪያው ሰዓት ወደ አምላኩ የቀረበ ቢኖር፥ ዛሬ ሽልማቱን ይውሰድ፡፡
በሦስተኛው ሰዓት የመጣ ቢኖር፥ እርሱ በዓሉን በምስጋና ያክብር፡፡ በስድስተኛው ሰዓት የደረሰ ቢኖር፥ አይጎድልበትምና አይጠራጠር፡፡ እስከ ዘጠነኛ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ሳይጠራጠር ይቅረብ፡፡ እስከ ዐሥራ አንደኛዋ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ስለ መዘግየቱ አይደንግጥ፡፡ ጌታ ቸር ነውና፤ በመጨረሻ የመጣውንም እንደ መጀመሪያው አድርጐ ይቀበሏልና፡፡ በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ለመጣው ከመጀመሪያው ሰዓት አንሥቶ ሲደክም ከነበረው ጋራ እኩል ይሰጧልና፡፡
መጨረሻ ለመጣው ጌታ ምሕረቱን ይለግሰዋል፤ መጀመሪያ ለመጣውም ያስብለታል፡፡ ለአንደኛው ይሰጠዋል፤ ለሌላኛውም ጸጋውን ያድለዋል፡፡ ለአንደኛው መልካም ምግባሩን ይቀበልለታል፡፡ ለሌላኛውም መልካም ፍቃዱን ይቀበልለታል፡፡ ለአንዱ ምግባሩን ያከብርለታል፤ ለሌላኛውም በቅን ልቡና የሚያደርገውን ጥረት ያደንቅለታል፡፡ ስለዚህ ኹላችሁም ወደ ጌታችሁ ደስታ ግቡ፡፡
ፊተኞች ኋለኞችም ሆይ! እኩል ደመወዛችሁን ተቀበሉ፡፡ ባለጸጐች ድኾችም ሆይ! በአንድነት ዘምሩ፡፡ እናንተ ብርቱዎች ደካሞችም ሆይ! በዓሉን አክብሩት፡፡ እናንተ የጾማችሁ መጾም ያልቻላችሁም ሆይ! ዛሬ ላይ ደስ ይበላችሁ፡፡
መሠዊያው ሙሉ ነውና ኹሉም በማዕዱ ደስ ይበለው፡፡ ፍሪዳው የሰባ ነውና አንድ ሰው ስንኳ እንደ ተራበ እንዳይሔድ፡፡ ኹላችንም የእምነት በዓሉን እንካፈል፤ ከቸርነቱና ከፍቅሩ ሀብትም እንቋደስ፡፡
ማንም ስለ ድኽነቱ አይዘን፥ ኵላዊቷ መንግሥት ተገልጣለችና፡፡ ማንም በኃጢአቱ አያንባ፥ ከመቃብሩ የይቅርታ ብርሃን ተንቦግቧልና፡፡ ማንም ሞትን አይፍራ፥ የመድኃኒታችን ሞት ከዚህ ነጻ አውጥቶናልና፡፡ ለእርስዋ በመታዘዝም ጌታ አጥፍቷታልና፡፡
በሞቱ ሞትን ገደለው፡፡ ወደ ሲዖል በመውረድ ሲዖልን በዘበዘው፡፡
ኢሳይያስም አሰምቶ እንደ ተናገረ ሲዖል ከጌታችን ጋር ፊት ለፊት ተገናኘች፤ መረራትም! ከንቱ አድርጓታልና መረራት! ሸንግሏታልና መረራት! ሽሯታልና መረራት!
ነፍሳትን ይዛ እንዳታስቀር አስሯታልና መረራት!
[መቃብር የዕሩቅ ብእሲ] ሥጋ አገኘሁ ብላ ዋጠችው፤ ስትውጠው ግን እግዚአብሔር ኾኖ አገኘችው - መረራትም!
ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል፥ መቃብርም ሆይ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ?
ክርስቶስ ተነሣ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ!
ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቸዋልና፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@getem
@wegoch
በጭድ ላይ ጭነት
"""""""''''፠""""""""፠""""""""
ተከምሮ ቁልል ጭድ ታይቶ ለእሳት
ተቃጥሎ ከቀረ አለፉት አመታት
*
ያ ሁሉ ተንዶ... ጭድ 'ና ጭነቱ
ሞልቶ አያቅ "ክምር" ቢለኝ ባለቤቱ
*
እኔም አልኩ ታዲያ~
ከስር ከስሩ መዘህ ፣ ከላይ ተመንምኖ
ጭድ እ'የት ያቅና መክበድ ተመዝኖ?
.
@Johny_Debx
@getem
@getem
@getem
"""""""''''፠""""""""፠""""""""
ተከምሮ ቁልል ጭድ ታይቶ ለእሳት
ተቃጥሎ ከቀረ አለፉት አመታት
*
ያ ሁሉ ተንዶ... ጭድ 'ና ጭነቱ
ሞልቶ አያቅ "ክምር" ቢለኝ ባለቤቱ
*
እኔም አልኩ ታዲያ~
ከስር ከስሩ መዘህ ፣ ከላይ ተመንምኖ
ጭድ እ'የት ያቅና መክበድ ተመዝኖ?
.
@Johny_Debx
@getem
@getem
@getem
///ለሰከንድ አልኖርም///
አንድ ጊዜ በቀኝ አንድ ጊዜ በግራ
የያዝኩትን ሳሊዝ ያልያዝኩትን ልይዝ መከራ ስበላ
ጠዋቴም አለፈ መሸታው ላይ ደረስኩ
የምይዘው ጠፍቶኝ እንዲሁ እንደባዘንኩ
በዘላለም መሀል ቢጠልቅ እድሜዬ
የሚወስደውን እጅ ሳሰላው ቁጭ ብዬ
የሰከንዶች ሽርፍራፊ ደቂቃ ማይሞላ
መሆኑ ቢገባኝ ደርሶ ትርጉም የለሽ ምንም የማይረባ
የአለምን ጋጋታ ላልሰማ ቸል ብዬ
ፍለጋዬን ሁሉ ወደ ዃላ ጥዬ
ጤዛውን እድሜዬን ለእርሱ ሰዋውለት
ሰከንድን ለመኖር
ዘላለም እንዳልሞት
ግጥም-ምህረት ሻውል(Mሬ)
@Getem
@getem
@gebriel_19
አንድ ጊዜ በቀኝ አንድ ጊዜ በግራ
የያዝኩትን ሳሊዝ ያልያዝኩትን ልይዝ መከራ ስበላ
ጠዋቴም አለፈ መሸታው ላይ ደረስኩ
የምይዘው ጠፍቶኝ እንዲሁ እንደባዘንኩ
በዘላለም መሀል ቢጠልቅ እድሜዬ
የሚወስደውን እጅ ሳሰላው ቁጭ ብዬ
የሰከንዶች ሽርፍራፊ ደቂቃ ማይሞላ
መሆኑ ቢገባኝ ደርሶ ትርጉም የለሽ ምንም የማይረባ
የአለምን ጋጋታ ላልሰማ ቸል ብዬ
ፍለጋዬን ሁሉ ወደ ዃላ ጥዬ
ጤዛውን እድሜዬን ለእርሱ ሰዋውለት
ሰከንድን ለመኖር
ዘላለም እንዳልሞት
ግጥም-ምህረት ሻውል(Mሬ)
@Getem
@getem
@gebriel_19
# ጠይቅ !!??
¿
እውነት ማለት ውሸት
ፍቅር ማለት ተረት ፡
ፍትህ በወረቀት ፡
አለሁ ሲሉ መሞት ፡
በሆነባት መሬት ።
ቆሞ እንደ መቀመጥ ፡
ኑሮ ሲርመጠመጥ ፡
እየሄድክ የቆምከው ፡
ጠርጥር ያገሬ ሰው ፡
ሰውነት የት ሄደ ፡
ጤና የት ለመደ ።
አለሁኝ ለማለት ፡
ተኝቶ መነሳት ፡
ላይሆንህ መስካሪ ፡
ጠይቅ አንተ ኗሪ !!!
~~~~~ ~~~
መዳፌን አደማሁ በስለት ወግቼ ፡
ፍቅሬን ከተብኩልህ በፍቅር ጣቶቼ ፡
ትለኛለች # ውዴ ፡
ይታመናል እንዴ !!?
ዳቦ ለሚሻ ሆድ ለደረቀ አንጀቱ ፡
ባንቺ የፍቅር ስንኝ ይሞላል ወይ ቤቱ!!
ያንቺ የፍቅር ግጥም ፡
የራብ ቤት አይመታም ፡
ብየ እንዳልደመድም ፡
በደሌን አንፅቶ ስሜን ያስቀየረ ፡
በፍቅሩ ነው'ንጂ ዳቦው መች ነበረ ።
****
ክብሩን የቀደደ ፡
እርቃን የወለደ ፡
ሰውነት የት ሔደ !!!!!
?
ጠይቅ! ያገሬ ሰው !!!! ....
መብትህን መናድ ፡
ወረቀት ከመቅደድ ፡
አንሶ ሲታያቸው ፡
መረገጥም ሞት ነው ፡
ፈርተህ አትለፈው !!!
!!!!!!?????
****
✍
ዮናስ ፈንታው
@getem
@getem
@gebriel_19
¿
እውነት ማለት ውሸት
ፍቅር ማለት ተረት ፡
ፍትህ በወረቀት ፡
አለሁ ሲሉ መሞት ፡
በሆነባት መሬት ።
ቆሞ እንደ መቀመጥ ፡
ኑሮ ሲርመጠመጥ ፡
እየሄድክ የቆምከው ፡
ጠርጥር ያገሬ ሰው ፡
ሰውነት የት ሄደ ፡
ጤና የት ለመደ ።
አለሁኝ ለማለት ፡
ተኝቶ መነሳት ፡
ላይሆንህ መስካሪ ፡
ጠይቅ አንተ ኗሪ !!!
~~~~~ ~~~
መዳፌን አደማሁ በስለት ወግቼ ፡
ፍቅሬን ከተብኩልህ በፍቅር ጣቶቼ ፡
ትለኛለች # ውዴ ፡
ይታመናል እንዴ !!?
ዳቦ ለሚሻ ሆድ ለደረቀ አንጀቱ ፡
ባንቺ የፍቅር ስንኝ ይሞላል ወይ ቤቱ!!
ያንቺ የፍቅር ግጥም ፡
የራብ ቤት አይመታም ፡
ብየ እንዳልደመድም ፡
በደሌን አንፅቶ ስሜን ያስቀየረ ፡
በፍቅሩ ነው'ንጂ ዳቦው መች ነበረ ።
****
ክብሩን የቀደደ ፡
እርቃን የወለደ ፡
ሰውነት የት ሔደ !!!!!
?
ጠይቅ! ያገሬ ሰው !!!! ....
መብትህን መናድ ፡
ወረቀት ከመቅደድ ፡
አንሶ ሲታያቸው ፡
መረገጥም ሞት ነው ፡
ፈርተህ አትለፈው !!!
!!!!!!?????
****
✍
ዮናስ ፈንታው
@getem
@getem
@gebriel_19
*ቋንቋ ነው *
ገና ከጥንስሱ፣
ሳለ በእሳቤ
መሰረት ሻያሻ፣እንጨት ሳያስፈልጥ፣
ጭቃ ሳያስቦካ ;ማደርያ አበጅቶ
ስጋውን ሲሰፋ፣አጥንቱን ሰክቶ
እርዳታ ሳይፈልግ፣ሳይንሳዊ ጥበብ
ማደሪያውን ብቻ፣ከሔዋን ተውሶ
መሬቷን ፈቅዳለት፣በደስታ አስረክባው
ጥበብ ሲዘራበት፣አምና ተቀብላው
የተፈጥሮን ስቃይ፣ፈቅዳ ተሰቃይታ
የጥበብን ውጤት፣ላሳየች ከስታ
ስጋን ከስጋዋ፣መንጭቀው ለይተው፣
ስቃይን አምክነው
ምድር ላስገኘችው፣
ቀድሞ ለተሰጠው፣ዕድሉ አበድረው
ቤቱን አመስግነው፣መሬቱን ንቀውት
መወለድ ቋንቋ ነው፣ብለው አቀለሉት።
ፀሃፈ ብሩህ
@getem
@getem
@Birukam
ገና ከጥንስሱ፣
ሳለ በእሳቤ
መሰረት ሻያሻ፣እንጨት ሳያስፈልጥ፣
ጭቃ ሳያስቦካ ;ማደርያ አበጅቶ
ስጋውን ሲሰፋ፣አጥንቱን ሰክቶ
እርዳታ ሳይፈልግ፣ሳይንሳዊ ጥበብ
ማደሪያውን ብቻ፣ከሔዋን ተውሶ
መሬቷን ፈቅዳለት፣በደስታ አስረክባው
ጥበብ ሲዘራበት፣አምና ተቀብላው
የተፈጥሮን ስቃይ፣ፈቅዳ ተሰቃይታ
የጥበብን ውጤት፣ላሳየች ከስታ
ስጋን ከስጋዋ፣መንጭቀው ለይተው፣
ስቃይን አምክነው
ምድር ላስገኘችው፣
ቀድሞ ለተሰጠው፣ዕድሉ አበድረው
ቤቱን አመስግነው፣መሬቱን ንቀውት
መወለድ ቋንቋ ነው፣ብለው አቀለሉት።
ፀሃፈ ብሩህ
@getem
@getem
@Birukam
👍1
~ ~ _ _ እንዴት ብዬ ልይሽ ?_ _ ~ ~
(ያለችዉ ባህር ማዶ)
.
# ምንተስኖት_ዋቆ
.
ስሚኝ የኔ እመቤት ፣
የሳሎኔ ዉበት ፣
የህይወቴ ድምቀት ፤
.
ባካል ላላገኝሽ በረሀዉ አይሏል ፣
ከየብሱ ለጥቆ ባህሩ ተኝቷል ፣
ባህሩ ሲታለፍ ፡ አድማስ ተዘርግቷል ፡፡
.
እንዴት ብዬ ልኑር ፡ አይንሽን ሳላየዉ ፣
በሀሳብ ሸራ ላይ ፡ ገላሽን እያየዉ ፡፡
እንዴት ልቋቋመዉ ፡ የናፍቆትሽን በትር ፣
በምን ልሻገረዉ ፡ የለየንን ድንበር ? ::
.
መቼም እጅ አልሰጥም ፣
መቼም ተስፋ አልቆርጥም ፣
አይገድልም ህመም ነዉ
.. .. _ _ _ .. .. የናፍቆት ዉሀ ጥም ::
.
ተስፋ መቀመር ነዉ፡ ተራርቆ ፍቅር ፣
ፈንድቶ የማይለይ፡ በልብ ዉስጥ 'ሚቀር፡፡
ታዲያ እንዴት ልይሽ ?
ድንበሩን አልፌ ፣
ባህሩን ቀዝፌ ፣
ከሀሳብ እንድድን ፡ ገላሽን አቅፌ ፡፡
( ከንፈርሽን ስሜ ::)
.
.
.
# ተፈጠመ
@getem
@getem
@gebriel_19
(ያለችዉ ባህር ማዶ)
.
# ምንተስኖት_ዋቆ
.
ስሚኝ የኔ እመቤት ፣
የሳሎኔ ዉበት ፣
የህይወቴ ድምቀት ፤
.
ባካል ላላገኝሽ በረሀዉ አይሏል ፣
ከየብሱ ለጥቆ ባህሩ ተኝቷል ፣
ባህሩ ሲታለፍ ፡ አድማስ ተዘርግቷል ፡፡
.
እንዴት ብዬ ልኑር ፡ አይንሽን ሳላየዉ ፣
በሀሳብ ሸራ ላይ ፡ ገላሽን እያየዉ ፡፡
እንዴት ልቋቋመዉ ፡ የናፍቆትሽን በትር ፣
በምን ልሻገረዉ ፡ የለየንን ድንበር ? ::
.
መቼም እጅ አልሰጥም ፣
መቼም ተስፋ አልቆርጥም ፣
አይገድልም ህመም ነዉ
.. .. _ _ _ .. .. የናፍቆት ዉሀ ጥም ::
.
ተስፋ መቀመር ነዉ፡ ተራርቆ ፍቅር ፣
ፈንድቶ የማይለይ፡ በልብ ዉስጥ 'ሚቀር፡፡
ታዲያ እንዴት ልይሽ ?
ድንበሩን አልፌ ፣
ባህሩን ቀዝፌ ፣
ከሀሳብ እንድድን ፡ ገላሽን አቅፌ ፡፡
( ከንፈርሽን ስሜ ::)
.
.
.
# ተፈጠመ
@getem
@getem
@gebriel_19
****እኔና አንቺ****
(በረከት በላይነህ)
በጥምር ነፍሳችን ፣ አረፍ ስንልበት ጨለማው ወገገ፤
ፈጣሪ ተገርሞ ለደስታ ፍቺ አዲስ ቃል ፈለገ።
እኔና አንቺን እኮ!
አበቦቹ ያጅቡናል፣
ፍራፍሬው ይከበናል፤
ሕይወት ጉንጯ ሲንቆረቆር ይሰማናል።
ወፎቹ!
እኔና አንቺን አይተው ተቃቅፈው በረሩ፤
ከጨረቃ ታርቀው በምሽት በረሩ።
ኮከቦቹ!
" ጨረቃ ወለደች! " እየተባባሉ፤
ከእኛ ተጠግተው ብርሀን ተሞሉ።
በቀቀኖች እንኳን!
ከፃድቃን ቃል ውጭ መድገም የማይችሉ፤
ከእኛ ሳቅ በሁዋላ " ድምፅ ሰማን! " አሉ።
‘ ባክሽ እንዳይገርምሽ!
በእኛ ሲከፋፈት ~ የምድር የሰማይ በር፣
እንዲህ ቀልቡን ሲሰጥ ~ የአዕዋፍ የአራዊተ ዘር ፣
ሁሉን ይሸምታል ~ ፍቅር ሲዘረዘር።
@getem
@getem
@gebriel_19
(በረከት በላይነህ)
በጥምር ነፍሳችን ፣ አረፍ ስንልበት ጨለማው ወገገ፤
ፈጣሪ ተገርሞ ለደስታ ፍቺ አዲስ ቃል ፈለገ።
እኔና አንቺን እኮ!
አበቦቹ ያጅቡናል፣
ፍራፍሬው ይከበናል፤
ሕይወት ጉንጯ ሲንቆረቆር ይሰማናል።
ወፎቹ!
እኔና አንቺን አይተው ተቃቅፈው በረሩ፤
ከጨረቃ ታርቀው በምሽት በረሩ።
ኮከቦቹ!
" ጨረቃ ወለደች! " እየተባባሉ፤
ከእኛ ተጠግተው ብርሀን ተሞሉ።
በቀቀኖች እንኳን!
ከፃድቃን ቃል ውጭ መድገም የማይችሉ፤
ከእኛ ሳቅ በሁዋላ " ድምፅ ሰማን! " አሉ።
‘ ባክሽ እንዳይገርምሽ!
በእኛ ሲከፋፈት ~ የምድር የሰማይ በር፣
እንዲህ ቀልቡን ሲሰጥ ~ የአዕዋፍ የአራዊተ ዘር ፣
ሁሉን ይሸምታል ~ ፍቅር ሲዘረዘር።
@getem
@getem
@gebriel_19
እግር ባይኖርህ መሄጃ፣
ወዳሻህ ቦታ መንጎጃ፣
እንደልብ ባትችል መራመድ፣
የሱን ዉሳኔ ግን ውደድ ።
እይታ ነስቶህ ጨልሞ፣
አለምን ባታይ ፈፅሞ፣
እንዳሳነሰህ ቆጥረኋው፣
ፀጋዉን እንዳትክድ ከስረኋው።
ህመም ፀንቶብህ ክፉኛ፣
ብትሆን ያልጋ ቁራኛ፣
ጨክኖብኛል ብለህ፣
እንዳትሄድ ከሱ ርቀህ።
ሰውን በምድር ሲፈጥር፣
ለሰበብ ነውና ሊሞክር፣
በትዕግስት ላይ ሳትፀና ፣
አትችልም ማለፍ ፈተና።
አካል ቢጎልህ ሰውነት፣
ቢርቅህ ፍፁም ጤንነት፣
በልብህ ተስፋ እስካለ ፣
ብስራት ያዘለ ቀን አለ።
አመስግን በግልፅ በስውር፣
የሱ ነውና ተአምር፣
ተንትነህ ጠልቀህ ካየኸው፣
ያለህ ይበልጣል ካጣኸው።
(Hiku)
@getem
@getem
@getem
ወዳሻህ ቦታ መንጎጃ፣
እንደልብ ባትችል መራመድ፣
የሱን ዉሳኔ ግን ውደድ ።
እይታ ነስቶህ ጨልሞ፣
አለምን ባታይ ፈፅሞ፣
እንዳሳነሰህ ቆጥረኋው፣
ፀጋዉን እንዳትክድ ከስረኋው።
ህመም ፀንቶብህ ክፉኛ፣
ብትሆን ያልጋ ቁራኛ፣
ጨክኖብኛል ብለህ፣
እንዳትሄድ ከሱ ርቀህ።
ሰውን በምድር ሲፈጥር፣
ለሰበብ ነውና ሊሞክር፣
በትዕግስት ላይ ሳትፀና ፣
አትችልም ማለፍ ፈተና።
አካል ቢጎልህ ሰውነት፣
ቢርቅህ ፍፁም ጤንነት፣
በልብህ ተስፋ እስካለ ፣
ብስራት ያዘለ ቀን አለ።
አመስግን በግልፅ በስውር፣
የሱ ነውና ተአምር፣
ተንትነህ ጠልቀህ ካየኸው፣
ያለህ ይበልጣል ካጣኸው።
(Hiku)
@getem
@getem
@getem
Forwarded from Melkam74 Digital Magazine
Melkam74 ቅፅ ፩ ቁጥር 5.pdf
3.2 MB
📠 መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 5
💰 ፓኬጅ ከገዙ በ 0.70 ብር ብቻ 💰
💰 ፓኬጅ ከገዙ በ 0.70 ብር ብቻ 💰
= ጀግና ያረገኞል=
የወደድሽ ሰምን.......
ፋቅርሽ ሰባኪ ነው ሺህ መናኝ ያስጎዛል
የመነኑት ሁሉ ገድልሽን ይከትባል
ምእመን በሙሉ መናኝ እየሆኑ
ዉዳሴዉ ላንች ነው አቋቋም ሲቆሙ
ዉዳሴው ላንች ነው ቅዳሴ ሲገቡ
እኔም የወደድኩሽ ሰምን....ጀግና ያረገኛል
የምድር ክብነት ውጥቅጡ ጠፍቶኝ
ባንችነት ጥልቀት ውስጥ ተውጨ ቀረሁኝ
አንችነት የጠማው ድርሳኔ በሙሉ
ብራናየ ሳይቀር ብእሬም ተለክፎ ገድልሽን ከተብ
የወደድኩሽ ሰምን..ጀግና ያረገኛል
አንችን የሚነካ ያገፈግፈኛል
የወደድኩሽ ሰምን አያርግብኝ እና.....
ዉዴ ሰይጣን ብቶኝ ጌታም ቢዘምትብሽ
ምእመን ሳይቀሩ በፀበል በፀሎት በውህደት ቢያባሩሽ
የመላክታ ጦር በፈጣሪ ትዛዝ በመብረቅ ቢያሮጡሽ
እንዲህ ያደርገኛል የባቢሉን ዘር ዳግም ነካክቸ
አጣንን በሙሉ በብርጌድ ሰብስቤ ጦር አሰማርቸ
የባቢሎን ዘር ምሽግ አስገብቸ
ለጎልያድ ሹመት ጀነራልን ሹሜ
ለፈርኦን ሳይቀር ሹመትን ሰጥቸ
ጦሬን እሰብቃለው
በጌታ ዘምታለው
የወደድኩሽ ሰምን ...ጀግና ያረገኛል
ኢህአዲግም ባቅሙ ስንት ሰዉ ሲቀጥፍ
የስንት የወንድ ብልት አስልቦ ሲያጠፍ
በማእከላዊ ወህኔ ሄዋን እርቃን ቁማ
እልፍ ሴት ሲደፈር እልፈ ሴት ሲደማ
ህዝቡም በቃኝ ብሎ ለአመፅ ሲወጣ
ስንቱ በምት ብትር በድላ ተቀጣ
ገና ከጥስሱ ይህን ሁሉ ዓመት ህዝቡን ከሚቀጣ
ምናለ አንችየ የወደድኩሽ ሰምን አንችኑ በነካ
ኢህአዲግ የሚባል ድራሹ በጠፋ
እናም የወደድኩሽ ሰምን...ጀግና ያረገኛል
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
✍ገጣሚ ቢኒ እጠየ
19/07/2011
@getem
@getem
የወደድሽ ሰምን.......
ፋቅርሽ ሰባኪ ነው ሺህ መናኝ ያስጎዛል
የመነኑት ሁሉ ገድልሽን ይከትባል
ምእመን በሙሉ መናኝ እየሆኑ
ዉዳሴዉ ላንች ነው አቋቋም ሲቆሙ
ዉዳሴው ላንች ነው ቅዳሴ ሲገቡ
እኔም የወደድኩሽ ሰምን....ጀግና ያረገኛል
የምድር ክብነት ውጥቅጡ ጠፍቶኝ
ባንችነት ጥልቀት ውስጥ ተውጨ ቀረሁኝ
አንችነት የጠማው ድርሳኔ በሙሉ
ብራናየ ሳይቀር ብእሬም ተለክፎ ገድልሽን ከተብ
የወደድኩሽ ሰምን..ጀግና ያረገኛል
አንችን የሚነካ ያገፈግፈኛል
የወደድኩሽ ሰምን አያርግብኝ እና.....
ዉዴ ሰይጣን ብቶኝ ጌታም ቢዘምትብሽ
ምእመን ሳይቀሩ በፀበል በፀሎት በውህደት ቢያባሩሽ
የመላክታ ጦር በፈጣሪ ትዛዝ በመብረቅ ቢያሮጡሽ
እንዲህ ያደርገኛል የባቢሉን ዘር ዳግም ነካክቸ
አጣንን በሙሉ በብርጌድ ሰብስቤ ጦር አሰማርቸ
የባቢሎን ዘር ምሽግ አስገብቸ
ለጎልያድ ሹመት ጀነራልን ሹሜ
ለፈርኦን ሳይቀር ሹመትን ሰጥቸ
ጦሬን እሰብቃለው
በጌታ ዘምታለው
የወደድኩሽ ሰምን ...ጀግና ያረገኛል
ኢህአዲግም ባቅሙ ስንት ሰዉ ሲቀጥፍ
የስንት የወንድ ብልት አስልቦ ሲያጠፍ
በማእከላዊ ወህኔ ሄዋን እርቃን ቁማ
እልፍ ሴት ሲደፈር እልፈ ሴት ሲደማ
ህዝቡም በቃኝ ብሎ ለአመፅ ሲወጣ
ስንቱ በምት ብትር በድላ ተቀጣ
ገና ከጥስሱ ይህን ሁሉ ዓመት ህዝቡን ከሚቀጣ
ምናለ አንችየ የወደድኩሽ ሰምን አንችኑ በነካ
ኢህአዲግ የሚባል ድራሹ በጠፋ
እናም የወደድኩሽ ሰምን...ጀግና ያረገኛል
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
✍ገጣሚ ቢኒ እጠየ
19/07/2011
@getem
@getem
◍ አ ል ረ ሳ ሁ ት ም ◍
(© ቸርነት ኃይሉ)
-
እዝጌር ሥራው ብዙ
ሊያጠናኝ ፈልጎ ወይስ ምናውቄ
ተመንጋው ነጥሎኝ ተጭንጫ ወድቄ
ባለቀስኩ ጊዜ ትጮህ በነበረ
ማነው ለጠሎቴ ክንዱን የገበረ
ማነው ታንቺ ቀድሞ ደርሶ የነበረ?
-
ይሄ ሁለት እግር...
ሰው የሚባል ፍጡር፣ ዐለሙን የሞላ
መለገስን ያልሻ ተምራቁ ሌላ
የከንፈሩ መምጠጥ ሙዚኣዬ ሆኖ
ትቆጥር እንዳልዋልኩ ስንት የምራቅ ቦኖ
እንደ ክርስቶስ ፊት፣ የደሙ ወለላ
እንባዬን ያበሰ ማነው ታንቺ ሌላ?
-
አልረሳም አልረሳም...
የኔ ቬሮኒካ፣ የኔ ባለ በፍታ
እራፊ ጨርቅሽን አሽትቻለሁ ላፍታ
ያ ነጭ አንገትልብስሽ ዐይኖቼን ያበሰ
ለነበዘ ፊቴ
ባ'ዳም ልጆች ዐይን፥ ግርፊያ ለኮሰሰ
ተምን ብታሰሪው እንዲያ ለሰለሰ?
-
ሀገር ሙሉ ቢላ፤ ሰማይ ሙሉ ህንጣ
ሺ የመብል ዐይነት፣ እንጢቅ የሚጠጣ
በሞላበት ህዋ፣ በሞላበት ቀየ
ጉምዣው ቲያታግለኝ
ባለቀስኩ ጊዜ ዐይኔ በጨቀየ
ታንቺ የቀደመ ተ'ዝጌር የዘገየ
ማነው እንደንስር ተሩቅ ቁስሌን ያየ?
-
ሰማይ በሮቢላ፣ የብሱ በመሂና
በታንኳ ተሞልተው አባይና ጣና
እኔ የዝጌር ቁጫጭ፣ ያምሳ'ግር ጓደኛ
ስጓዝ ውየ'ማድር የጊዜ ምርኮኛ
አንሸራቶኝ ትወድቅ ወደ ጥልቁ ስ'ላክ
ማን ቀድሞሽ አወጣኝ፣ ማን የሚሉት መላክ?
-
ፈፋ ብቻ ቲሆን ሀገሩ ጠቅላላ
ተጭኖችሽ ወዲያ ~ እንጠላጠልበት ~ የት አገኘሁ ባላ?
ክረምት አልፏል ብዬ
ያስጠለለችኝን ጎጆሽን አልዘልፍም
በ'ግሬ ቆምሁ ብዬ
የተሸከመኝን እግርሽን አልጠልፍም
ምንስ ጊዜ ቢሄድ፣ ምንስ ቀኖች ቢያልፉ
ምንስ ክፉ እጣዎች
እንደ በጋ ቅጠል ተፊቴ ቢረግፉ
እኔ ማን ነኝና፥ ማን ብባል ነውሳ
ተኒያ ዘንዶ ቀኖች
ያመለጥኩበትን ጉያሽን ምረሳ!?
@getem
@getem
@gebriel_19
(© ቸርነት ኃይሉ)
-
እዝጌር ሥራው ብዙ
ሊያጠናኝ ፈልጎ ወይስ ምናውቄ
ተመንጋው ነጥሎኝ ተጭንጫ ወድቄ
ባለቀስኩ ጊዜ ትጮህ በነበረ
ማነው ለጠሎቴ ክንዱን የገበረ
ማነው ታንቺ ቀድሞ ደርሶ የነበረ?
-
ይሄ ሁለት እግር...
ሰው የሚባል ፍጡር፣ ዐለሙን የሞላ
መለገስን ያልሻ ተምራቁ ሌላ
የከንፈሩ መምጠጥ ሙዚኣዬ ሆኖ
ትቆጥር እንዳልዋልኩ ስንት የምራቅ ቦኖ
እንደ ክርስቶስ ፊት፣ የደሙ ወለላ
እንባዬን ያበሰ ማነው ታንቺ ሌላ?
-
አልረሳም አልረሳም...
የኔ ቬሮኒካ፣ የኔ ባለ በፍታ
እራፊ ጨርቅሽን አሽትቻለሁ ላፍታ
ያ ነጭ አንገትልብስሽ ዐይኖቼን ያበሰ
ለነበዘ ፊቴ
ባ'ዳም ልጆች ዐይን፥ ግርፊያ ለኮሰሰ
ተምን ብታሰሪው እንዲያ ለሰለሰ?
-
ሀገር ሙሉ ቢላ፤ ሰማይ ሙሉ ህንጣ
ሺ የመብል ዐይነት፣ እንጢቅ የሚጠጣ
በሞላበት ህዋ፣ በሞላበት ቀየ
ጉምዣው ቲያታግለኝ
ባለቀስኩ ጊዜ ዐይኔ በጨቀየ
ታንቺ የቀደመ ተ'ዝጌር የዘገየ
ማነው እንደንስር ተሩቅ ቁስሌን ያየ?
-
ሰማይ በሮቢላ፣ የብሱ በመሂና
በታንኳ ተሞልተው አባይና ጣና
እኔ የዝጌር ቁጫጭ፣ ያምሳ'ግር ጓደኛ
ስጓዝ ውየ'ማድር የጊዜ ምርኮኛ
አንሸራቶኝ ትወድቅ ወደ ጥልቁ ስ'ላክ
ማን ቀድሞሽ አወጣኝ፣ ማን የሚሉት መላክ?
-
ፈፋ ብቻ ቲሆን ሀገሩ ጠቅላላ
ተጭኖችሽ ወዲያ ~ እንጠላጠልበት ~ የት አገኘሁ ባላ?
ክረምት አልፏል ብዬ
ያስጠለለችኝን ጎጆሽን አልዘልፍም
በ'ግሬ ቆምሁ ብዬ
የተሸከመኝን እግርሽን አልጠልፍም
ምንስ ጊዜ ቢሄድ፣ ምንስ ቀኖች ቢያልፉ
ምንስ ክፉ እጣዎች
እንደ በጋ ቅጠል ተፊቴ ቢረግፉ
እኔ ማን ነኝና፥ ማን ብባል ነውሳ
ተኒያ ዘንዶ ቀኖች
ያመለጥኩበትን ጉያሽን ምረሳ!?
@getem
@getem
@gebriel_19