"አንድ ግጥም አንድ ወግ" በልዑል ሀይሌ እና አዱኛ አስራት
አይጠራጠሩ ይወዱታል!!
https://m.youtube.com/watch?v=uQeOUPsKI2k&itct=CBgQpDAYACITCJ343--S2uECFdHywQodEskBPlIk4Yqg4YqV4Yu1IOGMjeGMpeGInSDhiqDhipXhi7Ug4YuI4YyN&hl=en&gl=US&client=mv-google
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
አይጠራጠሩ ይወዱታል!!
https://m.youtube.com/watch?v=uQeOUPsKI2k&itct=CBgQpDAYACITCJ343--S2uECFdHywQodEskBPlIk4Yqg4YqV4Yu1IOGMjeGMpeGInSDhiqDhipXhi7Ug4YuI4YyN&hl=en&gl=US&client=mv-google
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
ሂወትና ፎቶ
_
በዚህ ታዳጊ ልጅ ለ‘ይን በሚያሳሳ
ውብ ፈገግታው ሲረጭ አቅልን በሚያስረሳ
ታየችኝ ሂወቴ ሻሿን ተከናንባ
በተነሳው ፎቶ ከካሜራው ጀርባ
በልጁ በስተቀኝ አያለሁ ግድግዳ
አናጣቢ እንዳላይ የነብሴን መከዳ
ተላብሶ ቲሸርቱን ሸሚዙን ደርቦ
ታየኝ ማንነቴ በኩራት ተከቦ
በሱ ቤት መስሎታል እጁን ኪሱ ከቶ
ካፈር ወዳፈር ቤት መሆኑን ዘንገቶ
ከ‘ርሱ በላይ ጀግና ከቶ ኬት ተገኝቶ
ወይ በደንብ አልሳቀ ወይ አላለቀሰ
ወይ ሰላም አልሰጠኝ ወይም አልቦከሰ
ትምህረት ይሉት ነገር ተጥሎብኝ እዳ
እመረቅ ስል ሺቼ አያለሁኝ ፍዳ
ከጀርባው ባየኋት የጮራ ፈገግታ
እንስት አልማለሁ ጥላዋን ዘርግታ
ድንገት ቀን ሞልቶልኝ ዘወር ያልኩኝ ጊዜ
ስናጥጥ አያለሁ ሆናልኝ ምርኩዜ
ደጅ በተከማቸው በነጠላው ጫማ
አያለሁ ሞገሴን በላጤነት ደክማ
ሳር ድንጋይ ሰብስቦ ካላጠናከረ
በቻውን እንጨቱ ቤት መቼ ፈጠረ
ፀጉሩን ባልነቀሰው ካናቱ ላይ ዘልቃ
ተወርውራ መልዕክት አያሰማች ሲቃ
እንዲህ ትለኛለች,,,,,,,
አንተም ልክ እንደዚህ የንባብ ዉሃ አጥተህ
እንዳታድግ ነብስህ ታሳጥራታለህ
ምንም እንኳ ብታድግ ውስብስብ ብላ
ስላመሳቀልካት አያያትም ሌላ
እነም,,,,,,,
ይሄ ፎቶ ፎቶ ብቻ አይደለም
ከመልኩ ባሻገር ይታያል ሂወትም።
በሀሰን ኢድሪስ(የዘይነብ ልጅ)
@getem
@getem
@getem
_
በዚህ ታዳጊ ልጅ ለ‘ይን በሚያሳሳ
ውብ ፈገግታው ሲረጭ አቅልን በሚያስረሳ
ታየችኝ ሂወቴ ሻሿን ተከናንባ
በተነሳው ፎቶ ከካሜራው ጀርባ
በልጁ በስተቀኝ አያለሁ ግድግዳ
አናጣቢ እንዳላይ የነብሴን መከዳ
ተላብሶ ቲሸርቱን ሸሚዙን ደርቦ
ታየኝ ማንነቴ በኩራት ተከቦ
በሱ ቤት መስሎታል እጁን ኪሱ ከቶ
ካፈር ወዳፈር ቤት መሆኑን ዘንገቶ
ከ‘ርሱ በላይ ጀግና ከቶ ኬት ተገኝቶ
ወይ በደንብ አልሳቀ ወይ አላለቀሰ
ወይ ሰላም አልሰጠኝ ወይም አልቦከሰ
ትምህረት ይሉት ነገር ተጥሎብኝ እዳ
እመረቅ ስል ሺቼ አያለሁኝ ፍዳ
ከጀርባው ባየኋት የጮራ ፈገግታ
እንስት አልማለሁ ጥላዋን ዘርግታ
ድንገት ቀን ሞልቶልኝ ዘወር ያልኩኝ ጊዜ
ስናጥጥ አያለሁ ሆናልኝ ምርኩዜ
ደጅ በተከማቸው በነጠላው ጫማ
አያለሁ ሞገሴን በላጤነት ደክማ
ሳር ድንጋይ ሰብስቦ ካላጠናከረ
በቻውን እንጨቱ ቤት መቼ ፈጠረ
ፀጉሩን ባልነቀሰው ካናቱ ላይ ዘልቃ
ተወርውራ መልዕክት አያሰማች ሲቃ
እንዲህ ትለኛለች,,,,,,,
አንተም ልክ እንደዚህ የንባብ ዉሃ አጥተህ
እንዳታድግ ነብስህ ታሳጥራታለህ
ምንም እንኳ ብታድግ ውስብስብ ብላ
ስላመሳቀልካት አያያትም ሌላ
እነም,,,,,,,
ይሄ ፎቶ ፎቶ ብቻ አይደለም
ከመልኩ ባሻገር ይታያል ሂወትም።
በሀሰን ኢድሪስ(የዘይነብ ልጅ)
@getem
@getem
@getem
🏳️ “ጥቁሩ ብርሀን” 🏴
(በ👨🏾 መፅሀፈ)
የሰው ማንነቱ የውስጡ ትርታ፣
ደብቆት የሚኖር እማይገለጥ ላፍታ፤
በስጋው ከልሎት በምሽጉ መንደር፣
ብርሀንን ለብሶ በጭለማ ሚኖር::
መልካምነት ወስዶ ተቀብሎ አደራ፣
መታመኑን ሲያውቀ በደል የሚዘራ፤ እንዴት ያለች ውስጠት ሌሎች የማያውቀት፣
በግልፅነት ባህር ድብቀት ሚዘራባት፤
በመውደድ አንደበት ፍቅርን ሲሸነግል፣
ጦርነትን ገዝቶ ሰላም የሚደልል፤
አስቀድሞ ገሎ ላንተ ሟች ነኝ ይላል፣
ለሰጠከው መውደድ በቀል ያበቅላል፤
አይቻልም እንጂ ቢቻልስ ብችለው፣
የያንዳዱን ሰው ውስጣቸውን ባውቀው፣
እኔስ እርቅ ነበር ሰው ካልሆነው ሰው::
@getem
@getem
@getem
(በ👨🏾 መፅሀፈ)
የሰው ማንነቱ የውስጡ ትርታ፣
ደብቆት የሚኖር እማይገለጥ ላፍታ፤
በስጋው ከልሎት በምሽጉ መንደር፣
ብርሀንን ለብሶ በጭለማ ሚኖር::
መልካምነት ወስዶ ተቀብሎ አደራ፣
መታመኑን ሲያውቀ በደል የሚዘራ፤ እንዴት ያለች ውስጠት ሌሎች የማያውቀት፣
በግልፅነት ባህር ድብቀት ሚዘራባት፤
በመውደድ አንደበት ፍቅርን ሲሸነግል፣
ጦርነትን ገዝቶ ሰላም የሚደልል፤
አስቀድሞ ገሎ ላንተ ሟች ነኝ ይላል፣
ለሰጠከው መውደድ በቀል ያበቅላል፤
አይቻልም እንጂ ቢቻልስ ብችለው፣
የያንዳዱን ሰው ውስጣቸውን ባውቀው፣
እኔስ እርቅ ነበር ሰው ካልሆነው ሰው::
@getem
@getem
@getem
👍1
ትርጉም !
(በረከት በላይነህ)
..
"አስቀያሚ፣
አሰጠሊታ ፣
መልከ ጥፉ፤
እንደ ደሀ ቀዬ መስቦችህ የረገፉ!
የማትባል እዚህ ግባ ፣
የሰው ፍራሽ ፣ ማማር አልባ!
ፊተ መአት ፣ ያመድ ክምር!
የጭራቅ ሳቅ ያይጥ ፞ ድምር
ባትታይም የማታምር! !!"
እረ ! ሌላም፣ ሌላም፣
ትልሀለች ብለው የነገሩኝ ለታ ፤
አቤት ሀሴት ፣ አቤት ደስታ!
ለምን ብትይ?
መልኬ ከሸለመሽ የማይሽር ጥላቻ ፤
ደስታ አሰከረኝ 'ስላየሺኝ' ብቻ
@getem
@getem
@poemempire
(በረከት በላይነህ)
..
"አስቀያሚ፣
አሰጠሊታ ፣
መልከ ጥፉ፤
እንደ ደሀ ቀዬ መስቦችህ የረገፉ!
የማትባል እዚህ ግባ ፣
የሰው ፍራሽ ፣ ማማር አልባ!
ፊተ መአት ፣ ያመድ ክምር!
የጭራቅ ሳቅ ያይጥ ፞ ድምር
ባትታይም የማታምር! !!"
እረ ! ሌላም፣ ሌላም፣
ትልሀለች ብለው የነገሩኝ ለታ ፤
አቤት ሀሴት ፣ አቤት ደስታ!
ለምን ብትይ?
መልኬ ከሸለመሽ የማይሽር ጥላቻ ፤
ደስታ አሰከረኝ 'ስላየሺኝ' ብቻ
@getem
@getem
@poemempire
ከ፦አምባ፦ጔሮ
#ፀሀፈ_ብሩህ
በተለቀመ ጥጥ፣
በሸማኔ ድውር
የሰው እራቁቱ፣
ገላ እንደሚከለል
እኩይ ስብእና፣
የታጨቀ በነውር
የበግ ለምድ ለብሶ፣
ተሰው እንደሚኖር
ማየት ማመን ብለህ፣
አይንህን አትመን
እዪዪን አታብዛ፣
ፊትህ ለሚከወን
ባየኽው አትኮንን፣
አይንህን አስዳኝተህ
የውስጥህን ግለት፣
ማየቱ ተስኖህ
ከእሳቤህ በላይ፣
የሰው ልጅ አናት ላይ
ላንተ ተሰውሮ ፣
ለግዜሩ ከሚታይ
አምባጔሮ አለ፣
ከ–እንባ–እጔሮው ውስጥ
ሰላም የሚነሳ፣
ሰውሮ የከተመ
የማንነቶች ነውጥ።
@getem
@getem
@Birukam
#ፀሀፈ_ብሩህ
በተለቀመ ጥጥ፣
በሸማኔ ድውር
የሰው እራቁቱ፣
ገላ እንደሚከለል
እኩይ ስብእና፣
የታጨቀ በነውር
የበግ ለምድ ለብሶ፣
ተሰው እንደሚኖር
ማየት ማመን ብለህ፣
አይንህን አትመን
እዪዪን አታብዛ፣
ፊትህ ለሚከወን
ባየኽው አትኮንን፣
አይንህን አስዳኝተህ
የውስጥህን ግለት፣
ማየቱ ተስኖህ
ከእሳቤህ በላይ፣
የሰው ልጅ አናት ላይ
ላንተ ተሰውሮ ፣
ለግዜሩ ከሚታይ
አምባጔሮ አለ፣
ከ–እንባ–እጔሮው ውስጥ
ሰላም የሚነሳ፣
ሰውሮ የከተመ
የማንነቶች ነውጥ።
@getem
@getem
@Birukam
" ዝናብና መብራት "
( በአምባዬ ጌታነህ )
እየውልሽ ውዴ...
በዚህ በእኛ ሰፈር
የዝናብ ጓጓታ፣
የመብረቅ ብልጭታ፣
የተሰማ እንደሆን
መብራቱ ይጠፋል፣
እኔ አንቺን ላወራ ስልኬን ያነሳሁ ለት
ባትሪዬ ይዘጋል ።
ውዴ
የእኔና አንቺ ፍቅር
የበዜና ሰብለን ለምኔ ሚያስብለው፣
አለምን ሚያስቀናው፣
ከታይታኒክ በልጦ ሁሌ የሚወራው፣
አንቺ ስትደውይ እኔ ከፍራሼ ስልኬን ቻርጅ እንዳረኩ ሳወራሽ ብቻ ነው።
ታዲያ ይሄን አውቆ ያ ድንጋይ መብራት ሀይል፣ ከፈመ ፍቅራችን፣
መብራት እያጠፋ ውሀ ቸለሰብን።
እናም የኔ ቆንጆ.....
የዝናቡን መምጣት ሰበብ እያረገ፣
በፍቅራችን ጎጆ ጠብ እየመረገ፣
ሆም ብሎ እየገባ የሚፈተፍተው በእኔና አንቺ መሀል፣
የፍቅራችን መቀስ ከመብራት ሀይል ውጪ ሌላ ማንም አይደል።
እናም ከዚህ ኋላ አንቺ ወደ እኔ ስልክ ደውልሽ ከዘጋ፣
ብልሽ ተረጅልኝ መብራት የለም እሱ ጋ።
ወይም
መብራት ሀይል የሚሉት
በእኔ አንቺ መንገድ ስላለ እንቅፋት፣
ልታወሪኝ ካሰብሽ...
መብራቱን ቸክ አርጊ ከመደወልሽ ፊት።
@getem
@getem
@getem
( በአምባዬ ጌታነህ )
እየውልሽ ውዴ...
በዚህ በእኛ ሰፈር
የዝናብ ጓጓታ፣
የመብረቅ ብልጭታ፣
የተሰማ እንደሆን
መብራቱ ይጠፋል፣
እኔ አንቺን ላወራ ስልኬን ያነሳሁ ለት
ባትሪዬ ይዘጋል ።
ውዴ
የእኔና አንቺ ፍቅር
የበዜና ሰብለን ለምኔ ሚያስብለው፣
አለምን ሚያስቀናው፣
ከታይታኒክ በልጦ ሁሌ የሚወራው፣
አንቺ ስትደውይ እኔ ከፍራሼ ስልኬን ቻርጅ እንዳረኩ ሳወራሽ ብቻ ነው።
ታዲያ ይሄን አውቆ ያ ድንጋይ መብራት ሀይል፣ ከፈመ ፍቅራችን፣
መብራት እያጠፋ ውሀ ቸለሰብን።
እናም የኔ ቆንጆ.....
የዝናቡን መምጣት ሰበብ እያረገ፣
በፍቅራችን ጎጆ ጠብ እየመረገ፣
ሆም ብሎ እየገባ የሚፈተፍተው በእኔና አንቺ መሀል፣
የፍቅራችን መቀስ ከመብራት ሀይል ውጪ ሌላ ማንም አይደል።
እናም ከዚህ ኋላ አንቺ ወደ እኔ ስልክ ደውልሽ ከዘጋ፣
ብልሽ ተረጅልኝ መብራት የለም እሱ ጋ።
ወይም
መብራት ሀይል የሚሉት
በእኔ አንቺ መንገድ ስላለ እንቅፋት፣
ልታወሪኝ ካሰብሽ...
መብራቱን ቸክ አርጊ ከመደወልሽ ፊት።
@getem
@getem
@getem
/// በእውቀቱ ስዩም//
አነጋገሬ የሰለጠነ
አረማመዴ የተመጠነ
ስደሰት ፊቴ :የግዚሀር ባውዛ
ስስም ከንፈሬ : ያበባ ጤዛ!!
ካለት ያወጋሁ
ከንብ የተጋሁ
እንደ ዘንገና : ውሃ የረጋሁ
ከጎህ ቀድሜ : ባይንሽ የነጋሁ::
ባስብ በመላ-ብናገር እውነት
ባቅፍሽ ክንዶቼ -የሃር መቀነት::
ጣትሽ ደባብሶኝ : ጥፍርሽ ቢበጣኝ
ዘቢብ ነው እንጂ :መች ደም ሊወጣኝ::
ለምድር ቢቀርብ- ቁመቴ ቢያጥር
በጎልያድ ግንባር- የማነጣጥር
ልቤ በጣቱ -ሰማይ ሚነካ
ከነራስ ደጀን- ከንጦጦ የካ
ቁመት በኩራት- የሚለካካ
ብትደገፊኝ -የላባ ፍራሽ
ብትመገቢኝ- የመና ቁራሽ::
እንኳን በጃኖ: እንኳን በሱፉ
እንደ ቁጥቋጦው : ልክ እንደዛፉ
ቅጠል ለብሼ :የምሽቀረቀር
የተለጋ ልብ: ቀልቤ ማስቀር
ያንቺው በረኛ
ያንቺው ቁንን ነኝ :ያንቺው ጉረኛ::
@getem
@getem
@gebriel_19
አነጋገሬ የሰለጠነ
አረማመዴ የተመጠነ
ስደሰት ፊቴ :የግዚሀር ባውዛ
ስስም ከንፈሬ : ያበባ ጤዛ!!
ካለት ያወጋሁ
ከንብ የተጋሁ
እንደ ዘንገና : ውሃ የረጋሁ
ከጎህ ቀድሜ : ባይንሽ የነጋሁ::
ባስብ በመላ-ብናገር እውነት
ባቅፍሽ ክንዶቼ -የሃር መቀነት::
ጣትሽ ደባብሶኝ : ጥፍርሽ ቢበጣኝ
ዘቢብ ነው እንጂ :መች ደም ሊወጣኝ::
ለምድር ቢቀርብ- ቁመቴ ቢያጥር
በጎልያድ ግንባር- የማነጣጥር
ልቤ በጣቱ -ሰማይ ሚነካ
ከነራስ ደጀን- ከንጦጦ የካ
ቁመት በኩራት- የሚለካካ
ብትደገፊኝ -የላባ ፍራሽ
ብትመገቢኝ- የመና ቁራሽ::
እንኳን በጃኖ: እንኳን በሱፉ
እንደ ቁጥቋጦው : ልክ እንደዛፉ
ቅጠል ለብሼ :የምሽቀረቀር
የተለጋ ልብ: ቀልቤ ማስቀር
ያንቺው በረኛ
ያንቺው ቁንን ነኝ :ያንቺው ጉረኛ::
@getem
@getem
@gebriel_19
አስር አረንጓዴ ጠርሙሶች
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ለሒሳብ ትምህርት...
መሰረት የጣሉ ፣ ተሰባሪ ቁሶች
የተዜመላቸው...
አስር አረንጓዴ ፣ መማሪያ ጠርሙሶች
ከትምህርት ቤቱ...
ካንዱ ግድግዳ ላይ ፣ እኩል ተደርድረው
መቀነስ ስንማር...
በተራ በተራ ፣ ያልቃሉ ተሰብረው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
"አስር አረንጓዴ ጠርሙሶች ፣ በግድድግዳ ላይ
ድንገት አንዱ መድቆ ቢሰበር ፣ ዘጠኝ ይቀራል
ዘጠኝ አረንጓዴ ጠርሙሶች ፣ በግድግዳ ላይ
ድንገት አንዱ ወድቆ ቢሰበር ፣ ስምንት ይቀራል.."
እንዲህ እንዲህ እያለ ፣ መምህሩ ያስተምራል
ለማስተማሪያ ስልት...
አስር አረንጓዴ ፣ ጠርሙስ ይሰበራል፡፡
በየ መማሪያው ቤት...
እንደ አስር ጠርሙስ ፣ ሆነው ሚቆጠሩ
በተማሪዎች ፊት ፣ ወድቀው ሚሰበሩ
ከቁጥር የበዙ...
ጠርሙሶች አውቃለሁ!
ካ'ስር ላይ ቀንሰው ፣ ዜሮ ላይ የቀሩ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በየ መማሪያው ቤት....
ከቁጥር የበዛ ፣ የጠርሙስ ስባሪ
መስበር ማይሰለቸው ፣ ሒሳብ አስተማሪ
ለሚሰበር ጠርሙስ...
መዘመር የሚወድ ፣ ያልገባው ተማሪ
በሞላባት ሀገር
ጠርሙሱ ህይወቴ ፣ ካ'ሳብ ከቶኝ ነበር፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሒሳቤን ከሀሳብ ፣ እየቀላቀልሁኝ
ሀሳቤን ከሒሳብ ፣ እያደባለቅሁኝ
ካ'ሳቤ ስነቃ ፣ መንገድ ላይ ነበርሁኝ
ሴተኛ አዳሪዎች...
ቆመው ይታዩኛል ፣ እኔ እየተማርሁኝ፡፡
እነዚህ አዳሪዎች...
አስር አረንጓዴ ፣ ጠርሙስ ይመስላሉ
አንዱ ወንድ ይመጣል...
አንዷን ይሰብራታል ፣ ዘጠኝ ይቀራሉ
አንዱ ወንድ ይመጣል...
አንዷን ይሰብራታል ፣ ስምንት ይቀራሉ
እንዲህ እንዲህ እያሉ...
ከማያቁት ገላ ፣ ወድቀው 'ሚሰበሩ
ካ'ስር ላይ ቀንሰው ፣ ዜሮ ላይ 'ሚቀሩ
እኔን ለማስተማር ፣ የሚሰበር ህይወት
ሰው ነው ጠርሙስ ማለት!!!
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እናም እኛ ሰዎች...
ነገ ተረኞች ነን ፣ ወድቀን ምንሰበር
ካ.ስር ላይ ቀንሰን ፣ ዜሮ ላይ የምንቀር፡፡
ዜሮነት ህይወት ላይ...
እልፍ ህይወት ቢባዛ ፣ እልፍ ቢጨመርም
ምላሹ ዜሮ ነው!!!
በመቀነስ ስሌት ፣ ለውጥ አይፈጠርም
ምክንያቱ ደሞ...
ዜሮ አይባዛም ፣ ዜሮ አይካፈልም፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ለውጥ ላለመፍጠር ...
የሚቀነስ ህይወት ፣ የሚሰበር አካል
ያልገባው ተማሪ ፣ ሲዘምር ይረካል፡፡
"አስር አረንጓዴ ጠርሙሶች ፣ በግድግዳ ላይ
ድንገት አንዱ ወድቆ ቢሰበር ፣ ዘጠኝ ይቀራል
ዘጠኝ አረንጓዴ ጠርሙሶች ፣ በግድግዳ ላይ
ድንገት አንዱ ወድቆ ቢሰበር ፣ ስምንት ይቀራል..."
እንዲህ እንዲህ እያለ ፣ መምህሩ ያስተምራል
ለማስተማሪያ ስልት...
አስር አረንጓዴ ፣ ጠርሙስ ይሰበራል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በየ መማሪያው ቤት...
ከቁጥር የበዛ ፣ የጠርሙስ ስባሪ
መስበር ማይሰለቸው ፣ ሒሳብ አስተማሪ
ለሚሰበር ጠርሙስ...
መዘመር የሚወድ ፣ ያልገባው ተማሪ
...........................እንዲገባው ሲባል...
ጠርሙስ ህይወት ሁሉ ፣
"ከሒሳብ ስሌት ውስጥ...
የመቀነስ ስሌት ፣ ሊቀነስ ይገባል"
እያለ ያስባል!!!
@getem
@getem
@gebriel_19
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ለሒሳብ ትምህርት...
መሰረት የጣሉ ፣ ተሰባሪ ቁሶች
የተዜመላቸው...
አስር አረንጓዴ ፣ መማሪያ ጠርሙሶች
ከትምህርት ቤቱ...
ካንዱ ግድግዳ ላይ ፣ እኩል ተደርድረው
መቀነስ ስንማር...
በተራ በተራ ፣ ያልቃሉ ተሰብረው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
"አስር አረንጓዴ ጠርሙሶች ፣ በግድድግዳ ላይ
ድንገት አንዱ መድቆ ቢሰበር ፣ ዘጠኝ ይቀራል
ዘጠኝ አረንጓዴ ጠርሙሶች ፣ በግድግዳ ላይ
ድንገት አንዱ ወድቆ ቢሰበር ፣ ስምንት ይቀራል.."
እንዲህ እንዲህ እያለ ፣ መምህሩ ያስተምራል
ለማስተማሪያ ስልት...
አስር አረንጓዴ ፣ ጠርሙስ ይሰበራል፡፡
በየ መማሪያው ቤት...
እንደ አስር ጠርሙስ ፣ ሆነው ሚቆጠሩ
በተማሪዎች ፊት ፣ ወድቀው ሚሰበሩ
ከቁጥር የበዙ...
ጠርሙሶች አውቃለሁ!
ካ'ስር ላይ ቀንሰው ፣ ዜሮ ላይ የቀሩ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በየ መማሪያው ቤት....
ከቁጥር የበዛ ፣ የጠርሙስ ስባሪ
መስበር ማይሰለቸው ፣ ሒሳብ አስተማሪ
ለሚሰበር ጠርሙስ...
መዘመር የሚወድ ፣ ያልገባው ተማሪ
በሞላባት ሀገር
ጠርሙሱ ህይወቴ ፣ ካ'ሳብ ከቶኝ ነበር፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሒሳቤን ከሀሳብ ፣ እየቀላቀልሁኝ
ሀሳቤን ከሒሳብ ፣ እያደባለቅሁኝ
ካ'ሳቤ ስነቃ ፣ መንገድ ላይ ነበርሁኝ
ሴተኛ አዳሪዎች...
ቆመው ይታዩኛል ፣ እኔ እየተማርሁኝ፡፡
እነዚህ አዳሪዎች...
አስር አረንጓዴ ፣ ጠርሙስ ይመስላሉ
አንዱ ወንድ ይመጣል...
አንዷን ይሰብራታል ፣ ዘጠኝ ይቀራሉ
አንዱ ወንድ ይመጣል...
አንዷን ይሰብራታል ፣ ስምንት ይቀራሉ
እንዲህ እንዲህ እያሉ...
ከማያቁት ገላ ፣ ወድቀው 'ሚሰበሩ
ካ'ስር ላይ ቀንሰው ፣ ዜሮ ላይ 'ሚቀሩ
እኔን ለማስተማር ፣ የሚሰበር ህይወት
ሰው ነው ጠርሙስ ማለት!!!
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እናም እኛ ሰዎች...
ነገ ተረኞች ነን ፣ ወድቀን ምንሰበር
ካ.ስር ላይ ቀንሰን ፣ ዜሮ ላይ የምንቀር፡፡
ዜሮነት ህይወት ላይ...
እልፍ ህይወት ቢባዛ ፣ እልፍ ቢጨመርም
ምላሹ ዜሮ ነው!!!
በመቀነስ ስሌት ፣ ለውጥ አይፈጠርም
ምክንያቱ ደሞ...
ዜሮ አይባዛም ፣ ዜሮ አይካፈልም፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ለውጥ ላለመፍጠር ...
የሚቀነስ ህይወት ፣ የሚሰበር አካል
ያልገባው ተማሪ ፣ ሲዘምር ይረካል፡፡
"አስር አረንጓዴ ጠርሙሶች ፣ በግድግዳ ላይ
ድንገት አንዱ ወድቆ ቢሰበር ፣ ዘጠኝ ይቀራል
ዘጠኝ አረንጓዴ ጠርሙሶች ፣ በግድግዳ ላይ
ድንገት አንዱ ወድቆ ቢሰበር ፣ ስምንት ይቀራል..."
እንዲህ እንዲህ እያለ ፣ መምህሩ ያስተምራል
ለማስተማሪያ ስልት...
አስር አረንጓዴ ፣ ጠርሙስ ይሰበራል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በየ መማሪያው ቤት...
ከቁጥር የበዛ ፣ የጠርሙስ ስባሪ
መስበር ማይሰለቸው ፣ ሒሳብ አስተማሪ
ለሚሰበር ጠርሙስ...
መዘመር የሚወድ ፣ ያልገባው ተማሪ
...........................እንዲገባው ሲባል...
ጠርሙስ ህይወት ሁሉ ፣
"ከሒሳብ ስሌት ውስጥ...
የመቀነስ ስሌት ፣ ሊቀነስ ይገባል"
እያለ ያስባል!!!
@getem
@getem
@gebriel_19
የፍቅር ሚዛን
ማነው ያቀለለው ፍቅርን እንደዋዛ
ማረፊያ ሲሆነን ለልባችን ታዛ
እንቧይ አልነበረም የፍቅራችን ካቡ
መፅናት የተሳነው ሚናድ በቀላሉ
እንዲህ አልነበረም የኔና ያንቺ ወጉ
ፍቅራችንም ሀያል የመዋደድ ጥጉ
የይስሙላ ያይደል ወረትም ያልቃኘው
ራስ ወዳድነት ቀርቦ ያልጎበኘው
እልፍ ቀኖች አሉ እኛን የሚወቅሱ
በግርምታ አፍዘው ትዝታን 'ሚጠቅሱ
እልፍ ቀኖች አሉ ያለፉ 'ሚመስሉ
ከልባችን መዝገብ ሊፋቁ 'ማይችሉ
ከ'ኔጋ ከ'ንቺ ጋር ዛሬም ድረስ ያሉ
ትላንት
አትለያየን ብሎ ሲማልድ የኖረ
ዛሬ
ጥዋቱን ተነስቶ አለያየን ብሎ ግብር ከገበረ
ለፍቅር አፀፋ ጥላቻ ካኖረ
ውህደት አፍርሶ ብቻውን ካበረ
አያሳቡ አሳቦ በሰበብ ተስቦ
ሸኙኝ ልሂድ ካለ
ታዲያ ምን ታከተ???
አያስቀሩት ነገር ልብም ከሸፈተ
ብቻ.......
በፍቅር ሚዛን ላይ ፍቅር ያመዝናል
እንከን አልባ ሆኖ ሚዛኑን ይደፋል
ጥላቻ ግን ሲሆን ፍቅርን ያጎድላል
ስህተትን ያጎላል
እናም....
ፍፅምና አይደለም የኔ መመዘኛ
ሚዛኔ ፍቅር ነው አይደል የጥላቻ
መኖርን ብትመርጪም ከ'ራስሽ ጋር ብቻ
እኔስ 'ወድሻለው ያለአቻ ለብቻ!!
ጌትነት አብይ 9/6/11
@getem
@getem
@gebriel_19
ማነው ያቀለለው ፍቅርን እንደዋዛ
ማረፊያ ሲሆነን ለልባችን ታዛ
እንቧይ አልነበረም የፍቅራችን ካቡ
መፅናት የተሳነው ሚናድ በቀላሉ
እንዲህ አልነበረም የኔና ያንቺ ወጉ
ፍቅራችንም ሀያል የመዋደድ ጥጉ
የይስሙላ ያይደል ወረትም ያልቃኘው
ራስ ወዳድነት ቀርቦ ያልጎበኘው
እልፍ ቀኖች አሉ እኛን የሚወቅሱ
በግርምታ አፍዘው ትዝታን 'ሚጠቅሱ
እልፍ ቀኖች አሉ ያለፉ 'ሚመስሉ
ከልባችን መዝገብ ሊፋቁ 'ማይችሉ
ከ'ኔጋ ከ'ንቺ ጋር ዛሬም ድረስ ያሉ
ትላንት
አትለያየን ብሎ ሲማልድ የኖረ
ዛሬ
ጥዋቱን ተነስቶ አለያየን ብሎ ግብር ከገበረ
ለፍቅር አፀፋ ጥላቻ ካኖረ
ውህደት አፍርሶ ብቻውን ካበረ
አያሳቡ አሳቦ በሰበብ ተስቦ
ሸኙኝ ልሂድ ካለ
ታዲያ ምን ታከተ???
አያስቀሩት ነገር ልብም ከሸፈተ
ብቻ.......
በፍቅር ሚዛን ላይ ፍቅር ያመዝናል
እንከን አልባ ሆኖ ሚዛኑን ይደፋል
ጥላቻ ግን ሲሆን ፍቅርን ያጎድላል
ስህተትን ያጎላል
እናም....
ፍፅምና አይደለም የኔ መመዘኛ
ሚዛኔ ፍቅር ነው አይደል የጥላቻ
መኖርን ብትመርጪም ከ'ራስሽ ጋር ብቻ
እኔስ 'ወድሻለው ያለአቻ ለብቻ!!
ጌትነት አብይ 9/6/11
@getem
@getem
@gebriel_19
እኔው ነኝ አህያዋ
'""""""""""""""""""
ለትልቅ ክብር ታጭቼ
የዋልኩ ከክብር ቦታ
ጌታዬን ተሸክሜ
በዘንባባ በሰው ሆታ
በአጀባ .........በእልልታ!!!
ጌታዬን በላዬ አኑሬ
ዘንባባውን እየረገጥኩ እንዳልተባለ እልል እልል
እኔው ነኝ አህያዋ...
በማግስቱ በመጫኛ የሸከሙኝ ኩንታል እህል
(እኔው ነኝ አህያዋ)
ተሸክሜ የተመታሁ እየተባልኩኝ ገጣባ
አለዳዬ የምሸከም ዘላለሙን የማነባ
የተቆጠርኩ ከማልረባ
(እኔው ነኝ ...አህያዋ)
በገዛ እጄ ከከፍታው
አለመጠን ያልኩኝ ወረድ
ክብር ያላት እኔነቴን
ያስቆጠርኳት እንደ ገረድ
ዘላለሙን የምዋረድ
ዘላለሙን የምዋትት
እኔው ነኝ አህያዋ
አያ ሞኚት.....አያ ጅልዋ
አመድ አፋሽ ተቀጪዋ
ተመቺዋ.....ተገፊዋ
ችሎ ማደር....ታጋሽ ልብዋ
እኔው ነኝ አህያዋ
✍አብርሃም
(😔😔😔)
@getem
@getem
@gebriel_19
'""""""""""""""""""
ለትልቅ ክብር ታጭቼ
የዋልኩ ከክብር ቦታ
ጌታዬን ተሸክሜ
በዘንባባ በሰው ሆታ
በአጀባ .........በእልልታ!!!
ጌታዬን በላዬ አኑሬ
ዘንባባውን እየረገጥኩ እንዳልተባለ እልል እልል
እኔው ነኝ አህያዋ...
በማግስቱ በመጫኛ የሸከሙኝ ኩንታል እህል
(እኔው ነኝ አህያዋ)
ተሸክሜ የተመታሁ እየተባልኩኝ ገጣባ
አለዳዬ የምሸከም ዘላለሙን የማነባ
የተቆጠርኩ ከማልረባ
(እኔው ነኝ ...አህያዋ)
በገዛ እጄ ከከፍታው
አለመጠን ያልኩኝ ወረድ
ክብር ያላት እኔነቴን
ያስቆጠርኳት እንደ ገረድ
ዘላለሙን የምዋረድ
ዘላለሙን የምዋትት
እኔው ነኝ አህያዋ
አያ ሞኚት.....አያ ጅልዋ
አመድ አፋሽ ተቀጪዋ
ተመቺዋ.....ተገፊዋ
ችሎ ማደር....ታጋሽ ልብዋ
እኔው ነኝ አህያዋ
✍አብርሃም
(😔😔😔)
@getem
@getem
@gebriel_19
የባረቀ ፍቅር
(ረድኤት አሰፋ)
.
ሴባስቶፖል ልቤ~በሚያሳብድ ፍቅር ~የተቀጠቀጠ
ከሚስጥር ጋራዬ~ለልብሽ ሊተኮስ~እንዳልተቀመጠ
.
.
ንፍገትሽ ቢደፍነው~ከንፈሬ ታጠፈ
ባጣመምሽው አፌ.~ጥያቄው ከሸፈ
ላንቺ የታለመው~የፍቅሬ ኢላማ~ለራሴው ተረፈ
.
.
.
ራሴን ወደድኩት .... !
ራሴን ገደልኩት .... !
.
"እኔ" "ያለኔ" "አልኖር " በተባለ ጥይት !
.
.
የከበበኝ ስምሽ~ከሃሜት በስተቀር.~እዉነቱን አፈነ
በ'የርሱ' ናት ተስፋ.~የፈላጊዮቼ~ጥያቄ መከነ
.
.
ካንድ ሽጉጥና~ከሶስት ጥይት በቀር~አልተረፈም በጄ
መድፌም ወደኔው ነው~ላንቺ አልወድረውም~ራሴን ወድጄ !
.
.
አንድ ሽጉጥና~ሶስት ጥይት ብቻ
"ብትኖርስ" የምለው~የለኝም ፍራቻ
.
የሶስት ጥይት ቋንቋ
"እኔ " "ያላንቺ " " አልኖርም" እሞታለሁ በቃ
.
ሊያዉም በኛ ዘመን~ሞት ዋጋው ተወዶ~እየተናፈቀ
ሳልሰስት ልሠጥሽ~የቀዳሁት ፅዋ~በንቀትሽ ታጥፎ~ካፌ ተጣበቀ
የተኮስኩት ፍቅሬ~ለራሴው ባረቀ
.
.
ራሴን ወደድኩት
ራሴን ገደልኩት
.
.
.
ሞት በናፈቀ ፊት~ቆመሻል ከፊቴ
ሽጉጤ አንድ ነው~ሶስት ናት ጥይቴ
.
.
.
ከመድፌ ትናጋ~የተኮስኩት ጥይት~ተራራ ላይ ባክኗል
ግን ልቤ ደግ ነው.~ለራሱ ካኖረው~ሶስት ፍሬ ጥይት~ሶስቱን ላንቺ
አጭቷል
.
.
የመድፌ ኢላማ~በንፍገትሽ ዞሮ~ከሽፎ ቢመለስም
ለሳሳች ተስፋዬ~መክደኛ ያልኩትን~ሶስት ጥይት አልሻም
ይኸው አንቺ ሙቺ~ "እኔ" "ያላንቺ" "አልኖርም "
"ድም" ~ "ድም " ~ "ድም"
.
@getem
@getem
@gebriel_19
(ረድኤት አሰፋ)
.
ሴባስቶፖል ልቤ~በሚያሳብድ ፍቅር ~የተቀጠቀጠ
ከሚስጥር ጋራዬ~ለልብሽ ሊተኮስ~እንዳልተቀመጠ
.
.
ንፍገትሽ ቢደፍነው~ከንፈሬ ታጠፈ
ባጣመምሽው አፌ.~ጥያቄው ከሸፈ
ላንቺ የታለመው~የፍቅሬ ኢላማ~ለራሴው ተረፈ
.
.
.
ራሴን ወደድኩት .... !
ራሴን ገደልኩት .... !
.
"እኔ" "ያለኔ" "አልኖር " በተባለ ጥይት !
.
.
የከበበኝ ስምሽ~ከሃሜት በስተቀር.~እዉነቱን አፈነ
በ'የርሱ' ናት ተስፋ.~የፈላጊዮቼ~ጥያቄ መከነ
.
.
ካንድ ሽጉጥና~ከሶስት ጥይት በቀር~አልተረፈም በጄ
መድፌም ወደኔው ነው~ላንቺ አልወድረውም~ራሴን ወድጄ !
.
.
አንድ ሽጉጥና~ሶስት ጥይት ብቻ
"ብትኖርስ" የምለው~የለኝም ፍራቻ
.
የሶስት ጥይት ቋንቋ
"እኔ " "ያላንቺ " " አልኖርም" እሞታለሁ በቃ
.
ሊያዉም በኛ ዘመን~ሞት ዋጋው ተወዶ~እየተናፈቀ
ሳልሰስት ልሠጥሽ~የቀዳሁት ፅዋ~በንቀትሽ ታጥፎ~ካፌ ተጣበቀ
የተኮስኩት ፍቅሬ~ለራሴው ባረቀ
.
.
ራሴን ወደድኩት
ራሴን ገደልኩት
.
.
.
ሞት በናፈቀ ፊት~ቆመሻል ከፊቴ
ሽጉጤ አንድ ነው~ሶስት ናት ጥይቴ
.
.
.
ከመድፌ ትናጋ~የተኮስኩት ጥይት~ተራራ ላይ ባክኗል
ግን ልቤ ደግ ነው.~ለራሱ ካኖረው~ሶስት ፍሬ ጥይት~ሶስቱን ላንቺ
አጭቷል
.
.
የመድፌ ኢላማ~በንፍገትሽ ዞሮ~ከሽፎ ቢመለስም
ለሳሳች ተስፋዬ~መክደኛ ያልኩትን~ሶስት ጥይት አልሻም
ይኸው አንቺ ሙቺ~ "እኔ" "ያላንቺ" "አልኖርም "
"ድም" ~ "ድም " ~ "ድም"
.
@getem
@getem
@gebriel_19
ፍቅር ፈራን
"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን መቀራረብ ፈራን
እንዳልተዛመድን እንዳልተዋለድን
ፈርተን መዋደድን ጉርብትናን ናድን
እኛነትን ትተን እኔነትን ለመድን
"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን ጥላቻን ሰራን ብቸኝነት ጠራን
በጋራ ቤታችን አጥር ድንበር ሰራን
"ናቅን"
በልዩነት ደምቀን ያልኖርን ያህል አንድም ቀን
እልህ ተናነቅን
"ናቅን"
መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን
ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን
አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን
"ጠላን"
መወያየት ጠላን መነጋገር ጠላን
መደማመጥ ጠፍቶ መነቋቆር በዝቶ
መናናቅ በርክቶ
መመካከርን ስንረሳ መከባበርን ስንረሳ
እጃችን በወንድማችን ላይ ዱላ አነሳ
የቃየል ምቀኝነት በልባችን ላይ ነግሳ
"ራቅን"
የተስፋ ሻማችን ተለኩሶ
ወጋገኑ መታየት ሲጀምር አድማሱን ጥሶ
እኛ ግን ራቅን ብሩህ ነገን ራቅን
ዛሬን ተጣበቅን ትላንትን ናፈቅን
©ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን
@getem
@getem
@gebriel_19
"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን መቀራረብ ፈራን
እንዳልተዛመድን እንዳልተዋለድን
ፈርተን መዋደድን ጉርብትናን ናድን
እኛነትን ትተን እኔነትን ለመድን
"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን ጥላቻን ሰራን ብቸኝነት ጠራን
በጋራ ቤታችን አጥር ድንበር ሰራን
"ናቅን"
በልዩነት ደምቀን ያልኖርን ያህል አንድም ቀን
እልህ ተናነቅን
"ናቅን"
መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን
ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን
አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን
"ጠላን"
መወያየት ጠላን መነጋገር ጠላን
መደማመጥ ጠፍቶ መነቋቆር በዝቶ
መናናቅ በርክቶ
መመካከርን ስንረሳ መከባበርን ስንረሳ
እጃችን በወንድማችን ላይ ዱላ አነሳ
የቃየል ምቀኝነት በልባችን ላይ ነግሳ
"ራቅን"
የተስፋ ሻማችን ተለኩሶ
ወጋገኑ መታየት ሲጀምር አድማሱን ጥሶ
እኛ ግን ራቅን ብሩህ ነገን ራቅን
ዛሬን ተጣበቅን ትላንትን ናፈቅን
©ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን
@getem
@getem
@gebriel_19