#አቤልና ቃዔል#
የነተበ ኮዳ፥ቀረ'ሽ እፍኝ ዉሃ
ይዞ እንደመሸፈት፥የጋሻ ቀርቀሃ
እንደማሳደድ ጥላን
እንደማጥመድ ነፋስን
እንደዚያ ነዉ፥ከራስ ጋር መፋለም
ጣይና ወዳቂ የለም፤
እንዉረድ ያለዉ ቀን
ቃዔል መንተያዉን
እግዜር መዉረጃዉ ላይ፥አሽዋ ቢከምር
ቴዎድሮስ በሽዋ ላይ፥ባልዘመተ ነበር፤
አቤል ሲገፈተር፥ከጊዮን አናት ስር
ያኔ ደሙን ጠጥታ፥እናት የኩሽ ምድር
ይሄዉ ዛሬም ድረስ፥መች ምጧ ቀለለ
በስንዴዋ ማሳ ፥እንክርዳድ በቀለ
አገር ሙሉ አቤል
አገር ሙሉ ቃዔል
አንዱ ባንዱ ሲያሴር
አንዱ ባንዱ ሲያብል
ለነተበዉ ኮዳ፥ ለእንክርዳዱ ሙልሙል።
#መታሰቢያነቱ በአሁኑ ሰዓት በሃገራች ለሚታኮሱት የልጅ አበባዎች
#መሪጌታ
@lula_al_greeko
@getem
@getem
የነተበ ኮዳ፥ቀረ'ሽ እፍኝ ዉሃ
ይዞ እንደመሸፈት፥የጋሻ ቀርቀሃ
እንደማሳደድ ጥላን
እንደማጥመድ ነፋስን
እንደዚያ ነዉ፥ከራስ ጋር መፋለም
ጣይና ወዳቂ የለም፤
እንዉረድ ያለዉ ቀን
ቃዔል መንተያዉን
እግዜር መዉረጃዉ ላይ፥አሽዋ ቢከምር
ቴዎድሮስ በሽዋ ላይ፥ባልዘመተ ነበር፤
አቤል ሲገፈተር፥ከጊዮን አናት ስር
ያኔ ደሙን ጠጥታ፥እናት የኩሽ ምድር
ይሄዉ ዛሬም ድረስ፥መች ምጧ ቀለለ
በስንዴዋ ማሳ ፥እንክርዳድ በቀለ
አገር ሙሉ አቤል
አገር ሙሉ ቃዔል
አንዱ ባንዱ ሲያሴር
አንዱ ባንዱ ሲያብል
ለነተበዉ ኮዳ፥ ለእንክርዳዱ ሙልሙል።
#መታሰቢያነቱ በአሁኑ ሰዓት በሃገራች ለሚታኮሱት የልጅ አበባዎች
#መሪጌታ
@lula_al_greeko
@getem
@getem
#ኪርያላይሶ#
ታጥፎ፥ እንደ ድግ፥ወገቧን ዞሮ
እንደ ተረኛ ቄስ፥ሳይዘ'ጋ ያይኑ ጭራሮ
ሙሉ ሌሊት ከድሟት፥በፅናፅል በክበሮ
ተፈስሒ ዘምሮ
ለክብሯ፥ አጎንብሶ
ኪዳን፥ በስሟ አድርሶ
አልተሰረዬም ንስሃዉ፥ተመልሶ ኪርያላይሶ።
የጉም ፈትል ፈትሎ፥ቀጭን ክንዱ
አልቅሶ ወደ መሬት፥የሆዱን ይዞ በሆዱ...
ሆኖ ብኩን ፥እፉዬ ገላ
የዕብድ አሞራ፥ተከታይ፥ሲላ...
እንደ ሰንበሌጥ ጣሪያ፥የልብ ቋቱ አፍሶ
በቃኝ ብሎ፥ወይ ላይችለዉ፥ ጨርሶ
ነጋ መሸ ፥እሷን ብቻ ኪርያላይሶ።
#መሪጌታ
@getem
@getem
@gebriel_19
ታጥፎ፥ እንደ ድግ፥ወገቧን ዞሮ
እንደ ተረኛ ቄስ፥ሳይዘ'ጋ ያይኑ ጭራሮ
ሙሉ ሌሊት ከድሟት፥በፅናፅል በክበሮ
ተፈስሒ ዘምሮ
ለክብሯ፥ አጎንብሶ
ኪዳን፥ በስሟ አድርሶ
አልተሰረዬም ንስሃዉ፥ተመልሶ ኪርያላይሶ።
የጉም ፈትል ፈትሎ፥ቀጭን ክንዱ
አልቅሶ ወደ መሬት፥የሆዱን ይዞ በሆዱ...
ሆኖ ብኩን ፥እፉዬ ገላ
የዕብድ አሞራ፥ተከታይ፥ሲላ...
እንደ ሰንበሌጥ ጣሪያ፥የልብ ቋቱ አፍሶ
በቃኝ ብሎ፥ወይ ላይችለዉ፥ ጨርሶ
ነጋ መሸ ፥እሷን ብቻ ኪርያላይሶ።
#መሪጌታ
@getem
@getem
@gebriel_19