ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
(ለአባቴ)
ደህና ነኝ፡፡
መንታላ ገላዬን ችጋር ቢደቁሰው
ፍቅር ስጠቀለል ክፋትን ብጎርሰው
ህልሜ ቢጨናገፍ መንገዴ ቢያደክመኝ
እንዳለኸኝ ሳስብ ተስፋ አለኝ ደና ነኝ፡፡

ማግኘትና ማጣት ቢፈራረቁብኝ
ዋዛ ሆኜ ብታይ ቁምነገር ቢያጡብኝ
ፈርሷል ብለው ሲያልፉ ሰባብረውት ውስጤን
አንተ የኔ ጋሻ ነገዬን በማጤን
በርታ 'እንጂ ስትለኝ
ተዛ እለት ጀምሮ ተስፋ አለኝ ደህና ነኝ፡፡
---
ምን አፍራሽ ቢበዛ ከየጎዳናው ጫፍ
ያዘን እንጉርጉሮ በአካላቴ ቢያልፍ
ብጎብጥ ባቀረቅር 'መላም የለህ' ብሰኝ
አባቴ ፊቴ ቁም
ስትኖረኝ ተስፋ አለኝ፡፡ ስትኖረኝ ደህና ነኝ፡፡

#ELU @Username_under_construction

@GETEM
@GETEM