ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#የእንቢታሽ ሱሰኛ!

።።።።።።።።።።
አንቺን በማሰብ ውስጥ መደሰት ለምጄ

ፍቅርሽ ሱስ ሆኖብኝ ... ማንነቴን ክጄ

ባንቺ መወድስ ስም ክታብ አሰርቼ

ስምሽን በቦርሳ ጀርባዬ ላይ አንግቼ

እንደ አሞራ ዙሬሽ በላይ አንዣብቤ

ስትሄጅ ተራምጄ ... ስትቆሚ ቆሜ 

ባንቺ ስፍር ልኬት.. .በጠርዝ ተመድሜ

ከእድሜ ከጊዜዬ ዓመታት ቆንጥሬ

ከእንቢታሽ ጋራ በእልህ ሰክሬ

ስንኞችን ጭሬ.. .

አንቺን በመጀንጀንጀን ልማድ ተጠፍሬ

በሚጣፍጥ ህመም ...

ብቻዬን በአርምሞ ሳብሰለስል ኖሬ

ከሀሳቤ ማግስት ... በስንኜ ድርድር 

ቃላት ድል ነስተውሽ በሀይላቸው በትር

እወድሀለሁ ብለሽ የነገርሽኝ ለታ 

ፍቅርሽ ጥሎኝ ጠፋ ትዝታሽ ተረታ።

@getem
@getem
@getem

#ሚካኤል አስጨናቂ
🤩1
#የእንቢታሽ ሱሰኛ!
(ሚካኤል አስጨናቂ)

አንቺን በማሰብ ውስጥ መደሰት ለምጄ
ፍቅርሽ ሱስ ሆኖብኝ ... ማንነቴን ክጄ
ባንቺ መወድስ ስም ክታብ አሰርቼ
ስምሽን አንግቼ …

እንደ አሞራ ዙሬሽአንዣብቤ በላይ
አንቺን ሳይሽ ፣ ‘ዋይ ፣ ዋይ …’

አጃኢብ ነው መቼም!

ስትሄጅ ተራመድሁ... ስትቆሚ ቆሜ 
ባንቺ ስፍር ልኬት.. .በጠርዝ ተመድሜ
ከዕድሜ ከዘመኔዓመታት ቆንጥሬ
ከእንቢታሽ ጋራበእልህ ሰክሬ
ስንኞችን ጭሬ.. .
አንቺን በመጀንጀንጀንልማድ ተጠፍሬ
በሚጣፍጥ ህመም ...
ብቻዬን በአርምሞስብሰለስል ኖሬ

ከሀሳቤ ማግስት ... በስንኜ ድርድር 
ቃላት ድል ነስተውሽበኃይላቸው በትር
እኔም በተራዬ ፣ መፈቀር ስጀምር
“ፍቅርህን ተቀበልሁ” ያልሽኝ ጊዜለታ 
ፍቅርሽ ጥሎኝ ጠፋትዝታሽ ተረታ።

(እንቢ በይኝ ዳግም
እልህን ላጣጥም ። )

@getem
@getem
@getem
👍4217😁7🔥3😱3🤩1