.........🥀
እኔማ ፡ እንደሰው
ከተራሮች ፡ ራስጌ ፡ ላይ
በጨረቃ ፡ የሚጠበቅ ፤ ኮከብ ፡ ሳላይ
ዘመን ፡ ሄደ።
ቀና ፡ ሳልል ፤
ሌት ፡ ተካደ
… ጎህ ፡ ቀደደ።
ወዮ!! ወዮ!!
እኔማ ፡ እንደሰው ፤
በኮረዳ ፡ ፍቅር
ልቤ ፡ ሳይፈነዳ
መኮራመት ፡ በላኝ
በቁዘማ ፡ ጓዳ።
ወዮ!! ወዮ!!
ዘመን ፡ አልፎ ፤
ሃጥእ ፡ ወድቆ
ጻድቅ ፡ ተርፎ
ዲበኩሉ ፤ ምድርን ፡ ቀስፎ
ከሄደበት ፤ ባዶ ፡ ቦታ
ካንቺ ፡ ጋራ… ለብቻችን
ሳንተፋፈር ፤ ሳንፋራ
ምን ፡ ሳንሰራ።
ወዮ!! ወዮ!!
ባደባባይ ፤ ፅልመት ፡ ገሎ
ብርሃን ፡ በልቶ ፡ ለማደር
እንቅልፍን ፤ በፍቅር ፡ እሽሩሩ
በመውደድ ፡ ኬሻ ፡ ለመቅበር።
የሠራነው ፡ እንዳይሰፈር (ማለት ፡ እንዳይቆጥር)
ጊዜን ፡ በምናምን ፡ አሳብደን
እስከፈለገን ፤ ለ…
መ…
ተ…
ል…
ተ…
ል…
እኔና ፡ አንቺ ፡ ሳንታደል።
ዘመን ፡ ሄደ…
ቀና ፡ ሳንል…
ሌት ፡ ተካደ
ጎኅ ፡ ቀደደ።
ወዮ!! ወዮ!!
Migbar Siraj
@getem
@getem
እኔማ ፡ እንደሰው
ከተራሮች ፡ ራስጌ ፡ ላይ
በጨረቃ ፡ የሚጠበቅ ፤ ኮከብ ፡ ሳላይ
ዘመን ፡ ሄደ።
ቀና ፡ ሳልል ፤
ሌት ፡ ተካደ
… ጎህ ፡ ቀደደ።
ወዮ!! ወዮ!!
እኔማ ፡ እንደሰው ፤
በኮረዳ ፡ ፍቅር
ልቤ ፡ ሳይፈነዳ
መኮራመት ፡ በላኝ
በቁዘማ ፡ ጓዳ።
ወዮ!! ወዮ!!
ዘመን ፡ አልፎ ፤
ሃጥእ ፡ ወድቆ
ጻድቅ ፡ ተርፎ
ዲበኩሉ ፤ ምድርን ፡ ቀስፎ
ከሄደበት ፤ ባዶ ፡ ቦታ
ካንቺ ፡ ጋራ… ለብቻችን
ሳንተፋፈር ፤ ሳንፋራ
ምን ፡ ሳንሰራ።
ወዮ!! ወዮ!!
ባደባባይ ፤ ፅልመት ፡ ገሎ
ብርሃን ፡ በልቶ ፡ ለማደር
እንቅልፍን ፤ በፍቅር ፡ እሽሩሩ
በመውደድ ፡ ኬሻ ፡ ለመቅበር።
የሠራነው ፡ እንዳይሰፈር (ማለት ፡ እንዳይቆጥር)
ጊዜን ፡ በምናምን ፡ አሳብደን
እስከፈለገን ፤ ለ…
መ…
ተ…
ል…
ተ…
ል…
እኔና ፡ አንቺ ፡ ሳንታደል።
ዘመን ፡ ሄደ…
ቀና ፡ ሳንል…
ሌት ፡ ተካደ
ጎኅ ፡ ቀደደ።
ወዮ!! ወዮ!!
Migbar Siraj
@getem
@getem
👍34❤16👎3🤩2
አይዳሰስ ውጥን ስሜት
አይታወቅ የአፍ ቃሏ
ከውጭ ነው የለት ሃሳብ
እኔው ጋር ነው ስጋ አካሏ
አላውቀውም ምላስ ስሯን
አታጨውተኝ ያንጀት ሆዷን
እንዴት አይሆን ከኔ ሌላ
ከተሻለ መዋደዷን
አላሰርኩት ህሊናዋን
በመደርደር የፍቅር ቃል
ለጋ ልቧን ለማሸፈት
ጠብደል ኪሱ ለካ ይበቃል
እንዴት ልወቅ በፈገግታ
በጉንጯ ስር ባለው ስርጉድ
ጥርሷ እንደሆን ደባቂ ነው
አይናገርም የሆዷን ጉድ
ትቻት ስኖር ከንደገና
ይናፍቃል ጥጥ ገላዋ
ቆረጠልኝ ባልኩኝ ማግስት
ይገለኛል መሃላዋ።
"እንዴት እንደምወድህ እኮ.....ዮኒዬ ሙት"
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
አይታወቅ የአፍ ቃሏ
ከውጭ ነው የለት ሃሳብ
እኔው ጋር ነው ስጋ አካሏ
አላውቀውም ምላስ ስሯን
አታጨውተኝ ያንጀት ሆዷን
እንዴት አይሆን ከኔ ሌላ
ከተሻለ መዋደዷን
አላሰርኩት ህሊናዋን
በመደርደር የፍቅር ቃል
ለጋ ልቧን ለማሸፈት
ጠብደል ኪሱ ለካ ይበቃል
እንዴት ልወቅ በፈገግታ
በጉንጯ ስር ባለው ስርጉድ
ጥርሷ እንደሆን ደባቂ ነው
አይናገርም የሆዷን ጉድ
ትቻት ስኖር ከንደገና
ይናፍቃል ጥጥ ገላዋ
ቆረጠልኝ ባልኩኝ ማግስት
ይገለኛል መሃላዋ።
"እንዴት እንደምወድህ እኮ.....ዮኒዬ ሙት"
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
👍38❤7
ድሮም ለተፈጥሮ ስስ ነበረ ጎኔ
ወትሮም ውብ ነገር ሲያይ ይድን ነበር ዐይኔ።
ከፀሐይ ሲያበራ
አእዋፍ ባየበት
ትርጉም የነቀሰ ንቦች ጣም ሲሠሩ
ወንዞቹ ባሉበት
መርምሮ የሳመ ማማርን ከስሩ
ከቅጠሎች መዳፍ
ከውቅያኖስ ቀለም
ከተራሮች ደጃፍ
ውበት ሲስለመለም
ሲያደንቅ የነበረ ከፊት ተሰልፎ
ይሄ የኔ ብሌን
እንዴት ይታወራል በሰው በኩል አልፎ?
ከዚህ ሁሉ መንጋ ከሚርመሰመሰው
ስንቱ ተራማጅ ነው ውበት የለበሰው?
ይታይ ያሉት ሁሉ ከዛ እዚህ ይላጋል
ውበት በተፈጥሮው መርጋት ይፈልጋል።
አለፈች ይሉኛል
አለፈ ይሉኛል ሎጋና ጠንበለል
መርጋት ባየ ዐይኔ የቱን ውብ ነው ልበል!
By Yadel Tizazu
@getem
@getem
@paappii
ወትሮም ውብ ነገር ሲያይ ይድን ነበር ዐይኔ።
ከፀሐይ ሲያበራ
አእዋፍ ባየበት
ትርጉም የነቀሰ ንቦች ጣም ሲሠሩ
ወንዞቹ ባሉበት
መርምሮ የሳመ ማማርን ከስሩ
ከቅጠሎች መዳፍ
ከውቅያኖስ ቀለም
ከተራሮች ደጃፍ
ውበት ሲስለመለም
ሲያደንቅ የነበረ ከፊት ተሰልፎ
ይሄ የኔ ብሌን
እንዴት ይታወራል በሰው በኩል አልፎ?
ከዚህ ሁሉ መንጋ ከሚርመሰመሰው
ስንቱ ተራማጅ ነው ውበት የለበሰው?
ይታይ ያሉት ሁሉ ከዛ እዚህ ይላጋል
ውበት በተፈጥሮው መርጋት ይፈልጋል።
አለፈች ይሉኛል
አለፈ ይሉኛል ሎጋና ጠንበለል
መርጋት ባየ ዐይኔ የቱን ውብ ነው ልበል!
By Yadel Tizazu
@getem
@getem
@paappii
👍32❤27🔥2
አንቺ ?
አንቺ እንቁጣጣሽ
ምናባሽ ልትሰሪ መጣሽ?
አሁንም ግፍ አይበቃሽም
ዘንድሮም ለምለም ትያለሽ
ካቀፍሽው ቅጠል ባለፈ
የለመለመ ምን አለሽ?
ካቻምናም አምናም መተሻል
አቅፈንሽ አጥነን ደግሰን
አመትሽ ውበቱ ላይቆይ
እያደር ሊያተራምሰን
አንቺ ?
አንቺ እንቁጣጣሽ
ምናባሽ ልትሰሪ መጣሽ?
አምና ተስፋ አስደረግሺኝ
ደክሜ ቤቴን ሰራሁኝ
አልቅሼ ልገባበት ስል
ይፈርሳል ሁሉ ሰማሁኝ
አሁንም ተስፋ አልቆረጥኩም
ቃልሽን ስመላልሰው
አመትህ ተባርኳል ብለሽ
የላክሺኝ እንደ ሞኝ ሰው
ስታገል ከማይሽር ህይወት
መቀመቅ ነፍሴን ሲውጣት
ወደፊት ፈቀቅ እያልኩኝ
ሞት ልቤን እንዳይለውጣት
"አበባ አየሆሽ" አትበዪኝ
አበባ አልቸገረኝም
ዘፈንሽ አንገሽግሾኛል
ጨዋታሽ አይሰማኝም
በያመት ደምቀሽ ስትመጪ
ህፃን ልጅ ለምትመስዪው
ግጥሙን በምነግርሽ ቃል
ስትዘፍኚ አስተካክዪው
"የሀገሬ ልጆች ውጡ በተራ
ቅስም ሰብሬ ሰው እስክሰራ
እንኳን ሰውና የለኝም እድል
ሁሌ መጣለው አመት ላጎድል
አመት አጉድዬ ስገባ ቤቴ
ደስታ ይሰማታል የእንጀራ እናቴ"
አደዪ
የሞት ጉዳዪ
"ኡኡ" በዪ
እንደዚህ ብለሽ ዝፈኚ
ግጥሙን አስተካክለሽው
በቃ አንቺም እንዳገሬ ሰው
ጊዜን ነው የተማመንሽው?
"ሆ ብለሽ መጣሽ
ሆ ብለሽ
ሆ ብለሽ መጣሽ
ሆ ብለሽ"
ሆሆሆሆ!
አታፍሪም ደግሞ
ልክ እንደ ንፁህ እንዳልበደለ
ተስፋሽ ምስኪኑን እየገደለ
ከዘመን ዘመን ማትለወጪ
ጉድ ያዘለ አመት አቅፈሽ ምትሰጪ
ሆ ብለሽ መጣሽ?
ሆ ብለሽ ውጪ!
ለተድላ ሳይሆን
ለሞት ዋዜማ ፡ እያስጨፈርሺኝ
በመጣሽ ቁጥር
ሆ የምልልሽ ፡ ሞኝ አደረግሺኝ?
አሁን ንገሪኝ
ስለ አመትሽ
ይብስብኛል ወይስ ድናለው?
ዘፈኑን ተዪ ፡ ያንቺን ስሞታ ለምጄዋለው
ባለእንጀሮችሽ በተራ ገቡ
አዝማች አባትሽ ሌላ አገቡ
እንጨቱን ሰብረሽ ቤት እስክትሰሪ
ለእንጀራ እናትሽ ሳትናገሪ
እድጅ አድረሻል ኮከብ ስትቆጥሪ
እኔ ምስኪኑ
ምን ያገባኛል ስላንቺ ኮከብ
ምን ያገባኛል የእንቅልፍሽ ማጠር
የኔ ችግር ነው ወሰን የሌለው
የኔ ስቃይ ነው የማይቆጠር
እህት አበባ ፡ እህት አበባ
እህት አበባ ስትልሽ ከርማ፤
ጥላሽ ብትሄድም በሀምሌ ጭለማ
እኔ ላይ "አዬዬ".. አትበዪብኝ፡
ለኔ አመቱ ነው የጨለመብኝ።
ተይ ባለጊዜ..
ተይ እንቁጣጣሽ..
ሀገር ጉድ አቅፈሽ ፥
ሁሌ እየመጣሽ፦
እንኩ አትበዪን፡
ሀዘን ቁስላችን ፡ ድኖ ሳይገግም፤
ካምናው የሚብስ
ሌላ አዲስ አመት ..አንፈልግም!
by @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
አንቺ እንቁጣጣሽ
ምናባሽ ልትሰሪ መጣሽ?
አሁንም ግፍ አይበቃሽም
ዘንድሮም ለምለም ትያለሽ
ካቀፍሽው ቅጠል ባለፈ
የለመለመ ምን አለሽ?
ካቻምናም አምናም መተሻል
አቅፈንሽ አጥነን ደግሰን
አመትሽ ውበቱ ላይቆይ
እያደር ሊያተራምሰን
አንቺ ?
አንቺ እንቁጣጣሽ
ምናባሽ ልትሰሪ መጣሽ?
አምና ተስፋ አስደረግሺኝ
ደክሜ ቤቴን ሰራሁኝ
አልቅሼ ልገባበት ስል
ይፈርሳል ሁሉ ሰማሁኝ
አሁንም ተስፋ አልቆረጥኩም
ቃልሽን ስመላልሰው
አመትህ ተባርኳል ብለሽ
የላክሺኝ እንደ ሞኝ ሰው
ስታገል ከማይሽር ህይወት
መቀመቅ ነፍሴን ሲውጣት
ወደፊት ፈቀቅ እያልኩኝ
ሞት ልቤን እንዳይለውጣት
"አበባ አየሆሽ" አትበዪኝ
አበባ አልቸገረኝም
ዘፈንሽ አንገሽግሾኛል
ጨዋታሽ አይሰማኝም
በያመት ደምቀሽ ስትመጪ
ህፃን ልጅ ለምትመስዪው
ግጥሙን በምነግርሽ ቃል
ስትዘፍኚ አስተካክዪው
"የሀገሬ ልጆች ውጡ በተራ
ቅስም ሰብሬ ሰው እስክሰራ
እንኳን ሰውና የለኝም እድል
ሁሌ መጣለው አመት ላጎድል
አመት አጉድዬ ስገባ ቤቴ
ደስታ ይሰማታል የእንጀራ እናቴ"
አደዪ
የሞት ጉዳዪ
"ኡኡ" በዪ
እንደዚህ ብለሽ ዝፈኚ
ግጥሙን አስተካክለሽው
በቃ አንቺም እንዳገሬ ሰው
ጊዜን ነው የተማመንሽው?
"ሆ ብለሽ መጣሽ
ሆ ብለሽ
ሆ ብለሽ መጣሽ
ሆ ብለሽ"
ሆሆሆሆ!
አታፍሪም ደግሞ
ልክ እንደ ንፁህ እንዳልበደለ
ተስፋሽ ምስኪኑን እየገደለ
ከዘመን ዘመን ማትለወጪ
ጉድ ያዘለ አመት አቅፈሽ ምትሰጪ
ሆ ብለሽ መጣሽ?
ሆ ብለሽ ውጪ!
ለተድላ ሳይሆን
ለሞት ዋዜማ ፡ እያስጨፈርሺኝ
በመጣሽ ቁጥር
ሆ የምልልሽ ፡ ሞኝ አደረግሺኝ?
አሁን ንገሪኝ
ስለ አመትሽ
ይብስብኛል ወይስ ድናለው?
ዘፈኑን ተዪ ፡ ያንቺን ስሞታ ለምጄዋለው
ባለእንጀሮችሽ በተራ ገቡ
አዝማች አባትሽ ሌላ አገቡ
እንጨቱን ሰብረሽ ቤት እስክትሰሪ
ለእንጀራ እናትሽ ሳትናገሪ
እድጅ አድረሻል ኮከብ ስትቆጥሪ
እኔ ምስኪኑ
ምን ያገባኛል ስላንቺ ኮከብ
ምን ያገባኛል የእንቅልፍሽ ማጠር
የኔ ችግር ነው ወሰን የሌለው
የኔ ስቃይ ነው የማይቆጠር
እህት አበባ ፡ እህት አበባ
እህት አበባ ስትልሽ ከርማ፤
ጥላሽ ብትሄድም በሀምሌ ጭለማ
እኔ ላይ "አዬዬ".. አትበዪብኝ፡
ለኔ አመቱ ነው የጨለመብኝ።
ተይ ባለጊዜ..
ተይ እንቁጣጣሽ..
ሀገር ጉድ አቅፈሽ ፥
ሁሌ እየመጣሽ፦
እንኩ አትበዪን፡
ሀዘን ቁስላችን ፡ ድኖ ሳይገግም፤
ካምናው የሚብስ
ሌላ አዲስ አመት ..አንፈልግም!
by @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
👍76❤30🔥9😢9🤩2😁1
❀❀|ሰርክ አሮጌ|❀❀
•
ይገርማል!
ተለያይተን እንኳን
(ተራርቀን እንኳን)
ነፍሴ ሳትቀየር
ሳትለውጥ መልኳን፡፡
ላ
አምሮበት ይሄዳል፣
በቡና ጭስና...
ተፈጥሮ ብብት ስር
(በሚነሳው ሽቶ)
አየር ይታወዳል፣
አሮጌው እኔ ስር
"አዲስ ዐመት" ይሉት
ዘመን ይወለዳል፡፡
❀
ምናልባት ምናልባት
ዘመኑ ሲታደስ ይታደሳል ዓለም፣
በ
ከ
(ሲሻሽ በየ
እኔማ.....
አምናም እንዲህ ነበርኩ!
❀
@Bekalushumye
መልካም አዲስ ዐመት
@getem
@getem
@paappii
•
ይገርማል!
ተለያይተን እንኳን
(ተራርቀን እንኳን)
ነፍሴ ሳትቀየር
ሳትለውጥ መልኳን፡፡
ላ
ንቺ ያለኝ ፍቅር- አንዳችም ሳይቀንስ
(ከልቤ ሳይወጣ)
ዘመን ተለወጠ አዲስ ዐመት መጣ፡፡
❀
ተመልከች....
ኩልል ያለ ውሃ...በተራራው ግርጌ
(ባ
በቦች መካከል )አምሮበት ይሄዳል፣
በቡና ጭስና...
ተፈጥሮ ብብት ስር
(በሚነሳው ሽቶ)
አየር ይታወዳል፣
አሮጌው እኔ ስር
"አዲስ ዐመት" ይሉት
ዘመን ይወለዳል፡፡
❀
ምናልባት ምናልባት
ዘመኑ ሲታደስ ይታደሳል ዓለም፣
በ
ኔ በኩል ግና አዲስ ነገር የለም፡፡
❀
አምናም እንዲህ ነበርኩ....
አደይ አባባ ሳይ ትናፍቂኝ ነበር
ልጆች ሲጫወቱ አስታውስሽ ነበር
(ወይም ወይም ደግሞ...)
"ባክሽ ተመለሺ እናልቅስ ተቃቅፈን፣
ተንቀጠቀጥኩልሽ በትዝታሽ ቆፈን፡፡"
(የሚለውን ዘፈን...)
እራሴ ገጥሜ
(እራሴ ደርሼ)
አዜመው ነበረ፣
ልቤ ባለበት ነው -ጊዜ እየበረረ፡፡
❀
አምናም እንዲህ ነበርኩ
(ታች አምናም እንደዛው፣)
አላለቀም ነበር
የፍቅርሽ ጥፍጥና - የመውደድሽ ለዛው፡፡
እንዲህ ነበርኩ አምናም፣
(ዛሬም ትናትናም)
ነገም ወደፊትም ፣
ላ
ንቺ ያለኝ ፍቅር ከ
ግሮቼ ስር ወድቆ - አይንኮታኮትም፡፡
(አዎ...!)
አንዴ ስታቆሚው - አንዴ ስታሮጭው፣
አንዴ ስትወስጅው - አንዴ ስታመጭው፣
አንዴ ስታነሽው - አንዴ ስትረግጭው፣
(እርም ብለሽ ቆርጠሽ)
ልቤን ለዘላለም - እረፍት ላትሰጭው፣
አንቺ ነሽ በያ
መት(ሲሻሽ በየ
ለቱ)
ምትለዋወጭው፡፡እኔማ.....
አምናም እንዲህ ነበርኩ!
❀
@Bekalushumye
መልካም አዲስ ዐመት
@getem
@getem
@paappii
❤47👍23🔥3😱3🎉2
አዲስ አመት
.
.
ያ...ጠቢብ ሰለሞን..........
ያማረ ቀለበት ከእጅሽ ያጠለቀዉ፤
ምን ያክል ዉበትሽ ልቡን ቢገዛዉ ነው?
ከአደይቷ ይልቅ ደምቀሽ ብትታይዉ፤
ሽንፈት የማያዉቀዉ ፍቅርሽ አሸነፈው።
ትዋቢበት ዘንዳ ዉብ እንቁን ለጣትሽ፤
ችግር ሲያገኝሽ ማለፊያ ለጣጣሽ፤
አንድም ለልብሽ ነዉ ማሰሪያ ለቃልሽ፤
ለቅድስቷ ምድር አንድም ለሀገርሽ።
የካም እድል ፈንታ እንቁ ዕጣ ለወጣች፤
ጸሎቷን ለማድረስእጇን ለዘረጋች፤
ህመምሽ ለሆነች ፈዋሽሽም እሷዉ፤
ለቅድስቷ ምድር አንድም ለሀገርሽ ነው።
የእምነትሽን ጥግ የቀሚስሽ ልኩን፤
በመጠበብ አየ ሰው ሰው መሽተትሽን።
ኢትዮጵያ የሚል ስም ገና ሳትነግሪዉ፤
ባንቺነሽ ክታብ ተቀልሞ ቢያየዉ፤
ሐበሻ ይሆን ዘንድ ዘሩን ቀላቀለዉ።
ዛሬም ለሀገሬ........
መከራ እንደ ሀምሌ ፀንቶ ላጨገጋት፤
ዉሽንፍር መባርቅት አብሮ ለሚንጣት፤
ቀለበትሽን አዉሻትና........
መከራዋ ያብቃ ነጭ ልብስ ትልበስ፤
ተስፋዋ ይለምልም በፍቅር ትታደስ፤
እንባዋ ታብሶ ብርሃን ይታያት፤
በዚ በአዲስ አመት ደግ ቀን ይዉጣላት።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
በኤደን ታደሰ እንደፃፈ
@ediwub
@getem
@getem
.
.
ያ...ጠቢብ ሰለሞን..........
ያማረ ቀለበት ከእጅሽ ያጠለቀዉ፤
ምን ያክል ዉበትሽ ልቡን ቢገዛዉ ነው?
ከአደይቷ ይልቅ ደምቀሽ ብትታይዉ፤
ሽንፈት የማያዉቀዉ ፍቅርሽ አሸነፈው።
ትዋቢበት ዘንዳ ዉብ እንቁን ለጣትሽ፤
ችግር ሲያገኝሽ ማለፊያ ለጣጣሽ፤
አንድም ለልብሽ ነዉ ማሰሪያ ለቃልሽ፤
ለቅድስቷ ምድር አንድም ለሀገርሽ።
የካም እድል ፈንታ እንቁ ዕጣ ለወጣች፤
ጸሎቷን ለማድረስእጇን ለዘረጋች፤
ህመምሽ ለሆነች ፈዋሽሽም እሷዉ፤
ለቅድስቷ ምድር አንድም ለሀገርሽ ነው።
የእምነትሽን ጥግ የቀሚስሽ ልኩን፤
በመጠበብ አየ ሰው ሰው መሽተትሽን።
ኢትዮጵያ የሚል ስም ገና ሳትነግሪዉ፤
ባንቺነሽ ክታብ ተቀልሞ ቢያየዉ፤
ሐበሻ ይሆን ዘንድ ዘሩን ቀላቀለዉ።
ዛሬም ለሀገሬ........
መከራ እንደ ሀምሌ ፀንቶ ላጨገጋት፤
ዉሽንፍር መባርቅት አብሮ ለሚንጣት፤
ቀለበትሽን አዉሻትና........
መከራዋ ያብቃ ነጭ ልብስ ትልበስ፤
ተስፋዋ ይለምልም በፍቅር ትታደስ፤
እንባዋ ታብሶ ብርሃን ይታያት፤
በዚ በአዲስ አመት ደግ ቀን ይዉጣላት።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
በኤደን ታደሰ እንደፃፈ
@ediwub
@getem
@getem
👍31❤15🔥2😢2😱1
ተመኘሁኝ
--------------------
ከበሮ እየመታሽ
ስትይ አበባዮሽ፣
ከደጃፌ ቆመሽ
ድንገት ልቤን ሰረቅሽ።
ከበሮ የልቤ ምት
ጭብጨባው ለሽንፈት፣
ልቤን የመስረቅሽ
እጀባ አስመስሎት።
ከብረው ይቆዩ ሲባል
እንዳያልቅ ስፀልይ፣
ገንዘብ ሰጥቻችሁ
ከኔ እንዳትለይ።
ቶሎ ብትጨርሱ
ዜማው ደግሞ ቢያልቅ፣
የማደርገው ነገር
ግራ ገብቶኝ ባላቅ።
እያየሁሽ ወደኪሴ
እጄን ሰደድኩ፣
ዝርዝር ብዬ
ወደቤቴ እየዘለኩ።
አለኝ ብለሽ
ከቦርሳሽ ውስጥ ስታወጪ፣
ተመኘሁኝ
የዛሬ አመት እንድትመጪ።
ድገሙት አይባል ነገር
ሆኖብኝ ነው!!
@abela_black
@getem
@getem
@getem
--------------------
ከበሮ እየመታሽ
ስትይ አበባዮሽ፣
ከደጃፌ ቆመሽ
ድንገት ልቤን ሰረቅሽ።
ከበሮ የልቤ ምት
ጭብጨባው ለሽንፈት፣
ልቤን የመስረቅሽ
እጀባ አስመስሎት።
ከብረው ይቆዩ ሲባል
እንዳያልቅ ስፀልይ፣
ገንዘብ ሰጥቻችሁ
ከኔ እንዳትለይ።
ቶሎ ብትጨርሱ
ዜማው ደግሞ ቢያልቅ፣
የማደርገው ነገር
ግራ ገብቶኝ ባላቅ።
እያየሁሽ ወደኪሴ
እጄን ሰደድኩ፣
ዝርዝር ብዬ
ወደቤቴ እየዘለኩ።
አለኝ ብለሽ
ከቦርሳሽ ውስጥ ስታወጪ፣
ተመኘሁኝ
የዛሬ አመት እንድትመጪ።
ድገሙት አይባል ነገር
ሆኖብኝ ነው!!
@abela_black
@getem
@getem
@getem
👍39😁15❤5🤩4🔥1
🌻 2017 🌻
ሰዓታት አለፉ 🌻 ቀናት ወራት ወልደው 🌻
🌻አመት ተቆጠረ
አሮጌው ተተካ🌻 እነሆ ዛሬ ላይ 🌻
🌻 አዲስ ተጀመረ
እንኳን አደረሰን🌻 እንኳን ለዚህ አበቃን🌻
🌻መልካም አዲስ አመት
የሰላም የደስታ🌻 የተድላ የፍቅር
🌻 ያርገው የበረከት
🌻🌻መስከረም -1-2017ዓ.ም🌻🌻
✍ በግጥም እናውጋ( @BegitimEnawga )
🌻@getem🌻
🌻@getem🌻
🌻@getem🌻
ሰዓታት አለፉ 🌻 ቀናት ወራት ወልደው 🌻
🌻አመት ተቆጠረ
አሮጌው ተተካ🌻 እነሆ ዛሬ ላይ 🌻
🌻 አዲስ ተጀመረ
እንኳን አደረሰን🌻 እንኳን ለዚህ አበቃን🌻
🌻መልካም አዲስ አመት
የሰላም የደስታ🌻 የተድላ የፍቅር
🌻 ያርገው የበረከት
🌻🌻መስከረም -1-2017ዓ.ም🌻🌻
✍ በግጥም እናውጋ( @BegitimEnawga )
🌻@getem🌻
🌻@getem🌻
🌻@getem🌻
👍37❤14🔥1
አንተ ነህ መስከረም
(በሠዓሊ እና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ)
ማለቂያ በሌለው ደማቅ ሰማያዊ፣
ከሩቅ ያለው ጋራ ተነክሮ ሐምራዊ፡፡
በዚያ ላይ ደመናው እንደ ጥጥ ተነድፎ፣
እየተራራቀ ሲያንጃብብ ተቃቅፎ፡፡
አንተ ነህ መስከረም፣
የሐምሌን ጨለማ የነሐሴን ዝናም፣
የሻርከው አንተ ነህ፣
በብርሃን ውበትህ፡፡
በክረምቱ ወራት ሰማዩን ያስጌጠው፣
የማርያም መቀነት በቀለም ያበደው፡፡
ጤዛው አርሶታል መሬቱ ላይ ለቆ፣
በቀይና ብጫ መስኩ ተለቅልቆ፡፡
ወንዝና ጅረቱ ድንጋይና አፈሩ፣
ሀገሩ ውብ ሆኗል ሜዳው ሸንተረሩ፡፡
ዕንቁጣጣሽ አንተ ስጦታህ የበዛ፣
ለሰው መታሰቢያ ውበት የምትገዛ፡፡
በሽቱ መዓዛህ ለውጠው ዓመቱን፣
ይታደስ ያረጀው ፍጥረት ሌላ ይሁን፡፡
ከምረው ዘመኑን ካበው ባመት ባመት፣
በወሩ ደረጃ ፍጥረት ይጓዝበት፡፡
ፍየሎች ይዝለሉ ቅጠል ይበጥሱ፣
ከተሰደዱበት ወፎች ይመለሱ፡፡
ይልቀሙት አህሉን፣ ይስሩ ቤታቸውን፣
ይስፈሩበት ዛፉን፣
የደስደስ ያሰሙ ንቦች ይራኮቱ፣
ይንጠራሩ አበቦች ይንቁ ይከፈቱ፡፡
አንበሳና ግልገል በመስኩ ይፈንጩ፣
ከብቶች ሣሩን ይንጩ፡፡
ሕፃናት ይሩጡ ይሳቁ ይንጫጩ፣
ዛፎች ይተንፍሱ፣ የነፋሱ ጠረን፣
ይሰራጭ በቦታው ያውደው አገሩን፡፡
ዓደይ አበባ ነህ የመስቀል ደመራ፣
ጠረንህ አልባብ ነው አየርህ የጠራ፡፡
ያገር ልብስ አንተ ነህ ነጭ እንደበረዶ፣
ሰው የሚያጌጥብህ ጥበብህን ወስዶ፡፡
ቡቃያ ነህ እሸት ጓሚያ የበሰለ፣
አረንጓዴ ልብስህ በጌጥ የተሳለ፡፡
ጥቁር አረንጓዴ፣ ብጫማ አረንጓዴ፣
ቀለም ! ቀለም ! ቀለም !
የሚያስተካክልህ የሚያስንቅህ የለም፡፡
ኀዘን የምታርቅ የገነት ምሳሌ፡፡
ይታደል ወለላህ ጠጁ በብርሌ
ይስከር በደስታ ሕዝቡ ይሳሳቅ፣
ድምፁ እየተማታ ሙዚቃው ይፍለቅ፡፡
ዕንቁጣጣሽ ብለን እንስጥህ ሰላምታ፣
ይጭብጨብ ለዝናህ፣
ይጭብጨብ ለስራህ
ይጭብጨብ ለመልክህ
አንተ ነህ መስከረም፡፡
ዘመን የምታድስ አስጊጠህ በቀለም፡፡
@getem
@getem
@paappii
(በሠዓሊ እና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ)
ማለቂያ በሌለው ደማቅ ሰማያዊ፣
ከሩቅ ያለው ጋራ ተነክሮ ሐምራዊ፡፡
በዚያ ላይ ደመናው እንደ ጥጥ ተነድፎ፣
እየተራራቀ ሲያንጃብብ ተቃቅፎ፡፡
አንተ ነህ መስከረም፣
የሐምሌን ጨለማ የነሐሴን ዝናም፣
የሻርከው አንተ ነህ፣
በብርሃን ውበትህ፡፡
በክረምቱ ወራት ሰማዩን ያስጌጠው፣
የማርያም መቀነት በቀለም ያበደው፡፡
ጤዛው አርሶታል መሬቱ ላይ ለቆ፣
በቀይና ብጫ መስኩ ተለቅልቆ፡፡
ወንዝና ጅረቱ ድንጋይና አፈሩ፣
ሀገሩ ውብ ሆኗል ሜዳው ሸንተረሩ፡፡
ዕንቁጣጣሽ አንተ ስጦታህ የበዛ፣
ለሰው መታሰቢያ ውበት የምትገዛ፡፡
በሽቱ መዓዛህ ለውጠው ዓመቱን፣
ይታደስ ያረጀው ፍጥረት ሌላ ይሁን፡፡
ከምረው ዘመኑን ካበው ባመት ባመት፣
በወሩ ደረጃ ፍጥረት ይጓዝበት፡፡
ፍየሎች ይዝለሉ ቅጠል ይበጥሱ፣
ከተሰደዱበት ወፎች ይመለሱ፡፡
ይልቀሙት አህሉን፣ ይስሩ ቤታቸውን፣
ይስፈሩበት ዛፉን፣
የደስደስ ያሰሙ ንቦች ይራኮቱ፣
ይንጠራሩ አበቦች ይንቁ ይከፈቱ፡፡
አንበሳና ግልገል በመስኩ ይፈንጩ፣
ከብቶች ሣሩን ይንጩ፡፡
ሕፃናት ይሩጡ ይሳቁ ይንጫጩ፣
ዛፎች ይተንፍሱ፣ የነፋሱ ጠረን፣
ይሰራጭ በቦታው ያውደው አገሩን፡፡
ዓደይ አበባ ነህ የመስቀል ደመራ፣
ጠረንህ አልባብ ነው አየርህ የጠራ፡፡
ያገር ልብስ አንተ ነህ ነጭ እንደበረዶ፣
ሰው የሚያጌጥብህ ጥበብህን ወስዶ፡፡
ቡቃያ ነህ እሸት ጓሚያ የበሰለ፣
አረንጓዴ ልብስህ በጌጥ የተሳለ፡፡
ጥቁር አረንጓዴ፣ ብጫማ አረንጓዴ፣
ቀለም ! ቀለም ! ቀለም !
የሚያስተካክልህ የሚያስንቅህ የለም፡፡
ኀዘን የምታርቅ የገነት ምሳሌ፡፡
ይታደል ወለላህ ጠጁ በብርሌ
ይስከር በደስታ ሕዝቡ ይሳሳቅ፣
ድምፁ እየተማታ ሙዚቃው ይፍለቅ፡፡
ዕንቁጣጣሽ ብለን እንስጥህ ሰላምታ፣
ይጭብጨብ ለዝናህ፣
ይጭብጨብ ለስራህ
ይጭብጨብ ለመልክህ
አንተ ነህ መስከረም፡፡
ዘመን የምታድስ አስጊጠህ በቀለም፡፡
@getem
@getem
@paappii
❤32👍26🔥3🤩1
..
ለገላዋ እራፊ ፡ ብጣሽ አልገዛሁም፤
እረዥም ታሪኳን ፡ ቁጭ ብዬ አልሰማሁም
ምኞት ፍላጎቷን ፡ ለይቼ አላወኩም
የእግሯን ወለምታ ፡ አሽቼ አላዳንኩም፤
አሞሌ ጭንቀቷን ፡ በሳቅ አላሟሟው፤
ያመቃትን ስቃይ ፡ ጠጋ ብዬ አልሰማው
፡
ከድርብርብ ውጥረት
አስሮ ከደበቃት፤
ሽሮ ለመላቀቅ ፡ ቀልዴ ለሚበቃት
ማድያት ሽፍታ ፡
ሲያጨላልም መልኳን፤
ተራራ ሆኖብኝ ፥
"ምነው?" ማለት እንኳን
ፈገግታ እድሜዋን ፡ ጊዜ ሲከረክም፤
የትም እንደማትሄድ ፡ የኔን ብቻ ሳክም
ለእንስፍስፍ አንጀቷ ፡ ላይሆን መቀነቻ
ወኔዬም ፣ ጀብዱዬም ፡
"ወዳታለው" ብቻ።
ይቅርታ.. እማ።
@mikiyas_feyisa
@getem
@getem
ለገላዋ እራፊ ፡ ብጣሽ አልገዛሁም፤
እረዥም ታሪኳን ፡ ቁጭ ብዬ አልሰማሁም
ምኞት ፍላጎቷን ፡ ለይቼ አላወኩም
የእግሯን ወለምታ ፡ አሽቼ አላዳንኩም፤
አሞሌ ጭንቀቷን ፡ በሳቅ አላሟሟው፤
ያመቃትን ስቃይ ፡ ጠጋ ብዬ አልሰማው
፡
ከድርብርብ ውጥረት
አስሮ ከደበቃት፤
ሽሮ ለመላቀቅ ፡ ቀልዴ ለሚበቃት
ማድያት ሽፍታ ፡
ሲያጨላልም መልኳን፤
ተራራ ሆኖብኝ ፥
"ምነው?" ማለት እንኳን
ፈገግታ እድሜዋን ፡ ጊዜ ሲከረክም፤
የትም እንደማትሄድ ፡ የኔን ብቻ ሳክም
ለእንስፍስፍ አንጀቷ ፡ ላይሆን መቀነቻ
ወኔዬም ፣ ጀብዱዬም ፡
"ወዳታለው" ብቻ።
ይቅርታ.. እማ።
@mikiyas_feyisa
@getem
@getem
❤59👍37😢8🔥2😁1😱1
...ልመንህ ወይ
ላፈቅርህ ነዉ አተወኝም
ልመንህ ወይ አትከዳኝም
ገብሬልን ማርያምን በልና ማልልኝ
በልብህ ዙፋን ላይ ቃልኪዳን ግባልኝ
አልተውሽም ብለህ በላ በላኮ ማልልኝ
አምኜህ ልቀመጥ ቀልቤ ይረፍልኝ
ደግመህ እንደማተወኝ ልቤ ይወቅልኝ
በላ በላ በላኮ ማልልኝ
By
@Hanipia
@getem
@getem
@Hanipiagetem
ላፈቅርህ ነዉ አተወኝም
ልመንህ ወይ አትከዳኝም
ገብሬልን ማርያምን በልና ማልልኝ
በልብህ ዙፋን ላይ ቃልኪዳን ግባልኝ
አልተውሽም ብለህ በላ በላኮ ማልልኝ
አምኜህ ልቀመጥ ቀልቤ ይረፍልኝ
ደግመህ እንደማተወኝ ልቤ ይወቅልኝ
በላ በላ በላኮ ማልልኝ
By
@Hanipia
@getem
@getem
@Hanipiagetem
👍52😢11❤10🎉2
በሰዉ ዘንድ መገፋት፤
ደግ ፊት መነሳት፤
እስከ ጥግ አዉቃለሁ.....
ክፉ ደግ ያሳለፍን፤
ጎረቤቶቼ እንኳን፤
ያለፍኩ እንደሆነ ድንገት በበራቸዉ፤
እንደዚህ ይሉኛል ቃል እያጠራቸዉ፤
ምኑን ቢያቀምሷት፤
በምን ቢመርዟት፤
አልባሷን ቀዳዳ ጎዳና የወጣች፤
ከሰዉ ተነጥላ ብቻዋን ያወራች፤
እርሷ እኮ እንዲህ ነች እያሉ፤
ምኑንም ሳያዉቁ ፍርድ ይበይናሉ፤
ፍፁም ሰላምና ጤንነትን ሽቼ፤
ራሴን አገኘሁ ከገዳም ሰንብቼ፤
እናም አካላቴ እዉነት ናፍቀኸኛል፤
በክንድህ መሸሸግ እቅፍህ ያሻኛል፤
ትዝ ይልሃል አይደል......
የኔ ልብ ካንተ ያንተም ልብ ከኔ፤
በፍፁም ተጋምዶ በፍቅራችን ቅኔ፤
ለሰርጋችን ድምቀት እቅድ ስናወጣ፤
ነጠላ አጣፍተን ተሳልመን ስንመጣ፤
ትዝ ይልሃል አይደል......
ለዚህ ያደረሰኝ ቤተሰብ ጓዳዬ፤
ስንት የደከምኩበት ፍቅርና አላማዬ፤
ትናንት በጉያዬ በእጄ የነበረ፤
ተስፋ ያደረኩት መና ሆኖ ቀረ።
ማነዉ ተጠያቂ ልቤ ለመድማቱ
እዉነተኛ ደስታ ከእኔ ለመጥፋቱ
ማነዉ ተጠያቂ?????
......................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
ደግ ፊት መነሳት፤
እስከ ጥግ አዉቃለሁ.....
ክፉ ደግ ያሳለፍን፤
ጎረቤቶቼ እንኳን፤
ያለፍኩ እንደሆነ ድንገት በበራቸዉ፤
እንደዚህ ይሉኛል ቃል እያጠራቸዉ፤
ምኑን ቢያቀምሷት፤
በምን ቢመርዟት፤
አልባሷን ቀዳዳ ጎዳና የወጣች፤
ከሰዉ ተነጥላ ብቻዋን ያወራች፤
እርሷ እኮ እንዲህ ነች እያሉ፤
ምኑንም ሳያዉቁ ፍርድ ይበይናሉ፤
ፍፁም ሰላምና ጤንነትን ሽቼ፤
ራሴን አገኘሁ ከገዳም ሰንብቼ፤
እናም አካላቴ እዉነት ናፍቀኸኛል፤
በክንድህ መሸሸግ እቅፍህ ያሻኛል፤
ትዝ ይልሃል አይደል......
የኔ ልብ ካንተ ያንተም ልብ ከኔ፤
በፍፁም ተጋምዶ በፍቅራችን ቅኔ፤
ለሰርጋችን ድምቀት እቅድ ስናወጣ፤
ነጠላ አጣፍተን ተሳልመን ስንመጣ፤
ትዝ ይልሃል አይደል......
ለዚህ ያደረሰኝ ቤተሰብ ጓዳዬ፤
ስንት የደከምኩበት ፍቅርና አላማዬ፤
ትናንት በጉያዬ በእጄ የነበረ፤
ተስፋ ያደረኩት መና ሆኖ ቀረ።
ማነዉ ተጠያቂ ልቤ ለመድማቱ
እዉነተኛ ደስታ ከእኔ ለመጥፋቱ
ማነዉ ተጠያቂ?????
......................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
😢23👍20❤5🤩1