ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
መልካም ልደት

የእናትነት በጎ ክብር ምስጢረኛ አለኝታዬ

የሕይወቴ ታላቅ ቀመር
                       መልካም ልደት እናትዬ


እናቴ?  ………የኔ ፀጋ
በልቤ ውስጥ ያለሽ ዋጋ

ዐይኔን በዐይኔ የማይብሽ
ጓደኛዬ አለችምላት
                ጎዶሎየን ምሞላብሽ
የጉዞዬ ድጋፍ ምርኩዝ አንችኮ ነሽ።

እማ
  የኔ ስጦታ     የአ ም' ላ' ክ በረከቴ
ኑሮ ይድላሽ ክፉሽን አያሳየኝ በሕይወቴ

ልመርቅሽ??

ቀሪው ዘመን
               ጤና ይሁን የተሟላ
እድሜሽን ያድርግልኝ ማቱሳላ

የአምላክ እናት ትጠብቅሽ 
      ከፊት ቀድማ ከኋላሽም ተከትላ።

መልካም ልደት እናቴ

በይክቤ

@getem
@getem
@getem
57👍35🤩2🔥1
====+====
ለደግነቷ ምላሽ
   ሳትጠብቅ፤
የልቧን ፍቅር
ካይኗ ሳትደብቅ፤
:
የአንጀቷን ሲቃ
ዜማ ለምቀኝ ፤
ያሳለፍኩትን
ሳትጠይቀኝ።

ፍርሃቴን አስራ
ድሌን ስትፈታ፤
አንዴም ሳትቆጥረው
  እንደ ውለታ ።
:
እያሳመምኳት
እያዳነቺኝ፥
እየገፋኋት
እያቀፈቺኝ፤
እሷን የሚመስል ላላገኝ የትም፤
የሚገባትን ፡ አልሰጠዋትም!


© @mikiyas_feyisa

@getem
@getem
@paappii
41👍22😢4🔥3
( የምትመስለው .. )
================

የኔ ልዕልት ...
ጸዳል ክብሯ ከሴት መሐል አቻ የሌለው
በማለዳ ደምቃ የፈካች
ውብ ጸሐይ ነው የምትመስለው

ብዬሽ ነበር ያኔ ድሮ ልጅ እያለው

ግና ዛሬ አደግሁና
ሁሉን በጥልቅ ሳስተውለው
ይቅር በይኝ ማሪኝ ውዴ አጥፍቻለው

ለካ ጸሐይ ራሷ ናት
ቁር'ጥ አንቺን የምትመስለው !

By #KiyorNad

@getem
@getem
@getem
57👍21🔥12😁3😢3
ያንተ ምርጫ
እጇ አለንጋ
ቁመተ ሎጋ
አመለ ሸጋ።

አንተ ፋንጋ

ያንተ ምኞት

ተረከዘ ሎሚ
ሂል ተጫሚ
ፀጉረ ዞማ
አይነ ቡናማ
የቀይ ዳማ
ጉንጨ ሮማን
ቅርፇ ያማን

ያንተ ኪንኪ
ቁመተ ኮርኪ
ጥፍረ መጥምጥ
ቦርጭህ ዝርጥጥ
አፋንጫህ ድፍጥጥ

ለምን ብሎ ይከፋሀል
እኔ አንተን በመዉደዴ
የድስት ግጣሜ ማለት አንተ አይደለሀኝ እንዴ?🤔


ትዝታ ወልዴ
(@Tizita21)

@getem
@getem
😁128👍32🤩118👎5😱1
ዛሬ፣ ደስ! የሚል ቀን ነው። ሐዘን በወረረን ግዜ፣ እንደ ተወርዋሪ ኮከብ፣ ደስታ ብቅ ሲል ያስደስታል። ከሳምንታት በፊት፣ ለመቶ ገጣሚያን መድብል ለማዘጋጀት ጥሪ ቀርቦ ነበር፤ እነሆ፣ እኔም በዚህ ጥሪ ተሳታፊ ሆኜ፣ በዛሬው እለት ከመጀመሪያዎቹ ቅፅ-1(ክንፋም ከዋክብት መድብል )ማለትም ከ50 ገጣሚያን አንዱ መሆኔን መልዕክት ደርሶኛል። እናም እጅግ ደስ ብሎኛል!

ልክ ይልማ ገ/አብ የመጀመሪያ የዘፈኑ ግጥም ከሳንሱር አድራጊዎቹ አልፏል፤ ሲባል የተሰማው ደስታ ሲገልፀው:-
' በየመንገዱ በምሄድበት ግዜ ከደስታዬ ብዛት የተጣላሁትን ሰው ባገኝ የማናግር ይመስለኛል' ብሎ ነበር። እኔም፣ ያቺ ስሜት ተሰማችኝ።

በመጨረሻም ፣ የግጥም መድብሉን የመግዛት ፍላጎት ያላቹ ወዳጆቼ
#inbox 👇
@Samuelalemu5 አናግሩኝ።
አመሰግናለሁ🙏


@Samuelalemuu


@getem
@getem
👍27🤩267🎉6
ሰላም ወዳጆቼ
ሚካኤል አስጨናቂ ነኝ። ከዚህ ቀደም ተቤራ እና ሸግዬ ሸጊቱ የተሰኙ ሁለት ስራዎቼን ወደ እናንተ አቅርቢያለሁ። አሁን ደግሞ የጸሐይ እግሮች የተሰኘ 3ኛ ስራዬን ይዤ መጥቻለሁ።

የፊታችን አርብ ጷጉሜ 1 /2016
አራት ኪሎ ኢኽላስ ህንጻ ዋልያ መጸሐፍት ላይ
ከ10:30 ጀምሮ አስመርቃለሁ

በእለቱ ብዙ አንጋፋ የጥበብ ባለሞያዎች እናንተን አክብረው ይገኛሉ።

ሁላችሁንም ጋብዣለሁ!!
አመሰግናለሁ !
👍45🔥8
[ድፍን ድርሰት]

🌍
____
¹
ትልሙንና ህልሙን —···
(በመቼት በሴራ) እያጠላለፈው ፤
ወጉን ትረካውን (በቀናቶች ክፍል)
(በገፁ በአንቀፁ) እየሸራረፈው ፤
ዓለምን በቃሉ....
(በፈጠራው ቀለም) ነክሮ የነደፈው
ደራሲው ፈጣሪ (ስለሁለታችን)
ስለ እኔ ስላንቺ — ምን ይሆን የፃፈው?
²
አፈር ከሞላበት (አመድ ከለበሰው)
(ከመጣው ከሄደው) ከተመላለሰው
ከአምና ከዘንድሮ (ከዛሬ ከድሮ)
የተከመረውን (ጥራዝ እያወጡ )
(ሕይወትን ዘርግተው) ቢገልጡ ቢገልጡ ፤
የእግዜር ድፍን ድርሰት አይገኝም ጭብጡ ።
³
(“አትመጪም ወይ?” ስልሽ...)
—··· “እመጣለሁ” ብትይ ፤
(ለመንገድ የሚሆን....)
—··· ስንቅ ብታስከትይ ፤
ልብሽ ቢሰናዳ —·· እግርሽ ቢበረታ፤
(የጎዳናው ቀያሽ የመንገዱ ጌታ....)
ደራሲው ፈጣሪ — ·· የመቼት የቦታ ፤
ምን እንደሚበጥስ
ምን እንደሚቀጥል...
ማንን እያነሳ
ማንን እንደ ሚጥል....
አውቄው አላውቅም ገምቼው ቀድሜ
የታል ስለ ነገ ፍፁም ድምዳሜ?
ስንት ነው በምድር የተሰጠኝ ዕድሜ?

(ማን ይሄን አወቀ? አሁንስ ማን ያውቃል‽)
“እመነኝ” ብትይኝ አፍሽ ቢያወጣ ቃል ፤
(ጠዋት "ለምለም" ያልነው
ባመሻሽ ይደርቃል)
ስውር ደራሲያችን የላይኛው አካል
ነባሩን ቀይሮ አዲስ ይተርካል ።
ይለየን ይሆናል...
(ያርቀን ይሆናል) በጊዜ – በቦታ ፤
ከቃል የበለጠ — ጌታ ነው “ሁኔታ” ።
(ይሆኑታል እንጂ...)
ይኖሩታል እንጂ ....
“ይግባኝ” አይባልም — እንዲህ ያለ ፍርጃ
አንቺን አምንሻለሁ — እግዜሩን ግን እንጃ ።
___
🌍
By @Bekalushumye

@getem
@getem
@getem
👍506🔥2😢1
ከገጣሚዉ ጀርባ በዔደን ታደሰ
<unknown>
........ከገጣሚዉ ጀርባ🥀🥀
ፀሐፊ እና አቅራቢ ዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
5👍3
ጋዜጠኛው መርዝን
እንዲህ ሲል ጠየቃት
"ቅፅል ስምሽ ማነው?"
ፈገግ አለችና...
"ጥሩ ጥያቄ ነው"
ካለችው በኋላ...
ያልጨረሰችው ሳቅ...
ከላይ እያፈናት...
መለሰች...
.
.
.
"ቅናት"

ዘማርቆስ

@getem
@getem
@getem
46👍23🔥6🤩6
አይን የአፍንጫን ህመም
በእንባው ተቀኘለት
በተመታ ቁጥር
እያዘነበለት
አፍንጫም የአይን እንባ
አንሶበት ለቁስሉ
ይደማ ጀመረ
በሳር በቅጠሉ
ይህን ያዩ ጣቶች
ደፈኑት ጨምድደው
አየር እንዳያገኝ
መንገዱን ገድግደው
ምስኪን አፍንጫ...
ከአይን ተኳረፈ
መድማት ላያድነው
ወትሮም ከሌላ እንባ
የራስ ደም ውድ ነው

ዘማርቆስ

@getem
@getem
@getem
34👍19👎3
ሁላቹም እንዳትቀሩ🙏🏽🙏🏽

@getem
@getem
@getem
35👍21👎1
Forwarded from Sami Alemu
ጧሪ ያጣ አሜን
(ሳሙኤል አለሙ)

ለቁርሱ---ለምሳው---ለእራቱ
አፋችን ባይነቅዝም
"ካ'መት ዓመት ያድረሰን"
ሲባል ጭጭ!
ሲባል ዝም!
"እ'ዲሁ እንዳለን አይለየን"
ሲባል ጭጭ!
ሲባል ዝም!
ዕድሜያችን አጠረ ፥ ዝምታው ሲረዝም።

ሳሙኤል አለሙ
@Samuelalemuu


@Getem
@Getem
34👍14😢10
"የሩቅ ፍቅር"
ወደኔ ቢመጣ ናፍቆት ክንፍ አውጥቶ

ከሰመመን አልፎ ግኡዝ አካል ገዝቶ

ድንገት በሀሳቤ
የእቅፍሽ ሙቀት ስስ ከንፈርሽ ቢያምረኝ

አንች ያለሽ በሩቁ ምንድን ነው የሚበጀኝ?

እሽ ቆይ
መምጣቱንስ ልምጣ
             አጠገብሽ ልገኝ
ልውጣ ከሰመመን ናፍቆቱ ይራቀኝ

እኔ የፈራሁት
የከንፈርሽ ማማር እንዴት ነው የሚያደርገኝ?

By Yikbe

@getem
@getem
@getem
59👍32😁8🎉5👎3😱3😢1
ስለ ሽያጭ ያስተማረኝ
አትርፍ ያለኝ
ነግድ ያለኝ
ብርቱ መምህሬ
በቃሉ ነቅቼ
ለገንዘብ በርሬ
ሰበሰብኩኝ ንብረት
አተረፍኩኝ ነዋይ
እሱ ግን ዛሬም ላይ
ስለ ንግድ …
ስለ ትርፍ …
እየተናገረ
በደሞዙ ማነስ
እየተማረረ…
እዛው ትምህርት ቤት
ድሀ ሆኖ ቀረ ።

(ሚካኤል አ)

@getem
@getem
@getem
49😢31👍25😁11
ብንላመድ ተቀራርበን ብናወራ እጅግ በጣም፤
ብንስማም እንደአንድ ወግ ጨዋታን ብናበዛም፤
ቢያስደስተኝ ካንቺ መዋል ሳቅ ጨዋታሽ ቢገዛኝም።
ብትጠጊኝ ከቆምሽበት አንድ እርምጃ ወደ'ኔ፤
ብትማትሪም ከልቤ ላይ የፍቅርን ቃል ሆነሽ ጎኔ።
ብለምድሽም እንደራሴ ብትወጅኝም አንቺ በጣም፤
እኔ መቼ ታድዬልሽ ለማጣጣም የፍቅርን ጣ'ም።
እኔ መቼ ልረ'ዳልሽ መች ሊገባው የልቤን በር፤
ፍራት አስሮ እየናጠኝ መች ልከትም ከፍቅር መንደር።
መች ልደርስ ከደጃፉ የት አውቄ ልቀበልሽ?፤
በየት ጎዳና ባንቺ ስሜት እንዴት ሄጄ ልከተልሽ?።
ላልጨርሰው ጀማምሬ ከምጎዳሽ በአጉል ተስፋ፤
ልቤ ደርሶ ከልብሽ ላይ በፍቅር ክር ላይሰፋ።
የተዘጋው የልቤ በር አይከፈት እኔ አውቃለሁ፤
ፍቅር ነው አትበይኝ እኔ ፍቅር እፈራለሁ።

ጦቢያ
...............................
@getem
@getem
@getem
48👍31😢19👎2🔥2
———————- ደረሰ ——————

ሰሞኑን በአዲስ ዓመት ዋዜማ ከምንጠብቃቸው የጥበብ ድግሶች አንዱ የሆነው ብዙ አንጋፋ እና ወጣት የጥበብ ሰዎች የተሳተፉበት የደራሲ እና ኢንጅነር ሚካእኤል አስጨናቂ መፅሀፍ ምርቃት ነገ ዕለተ አርብ አራት ኪሎ ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ በሚገኘው ኢ ክላስ ህንፃ ዋልያ መፅሀፍት አዳራሽ ሞቅ ደመቅ ባለ ፕሮግራሞቹ ታጅቦ ደምቆ የሚውል ይሆናል ።

👉🏿 ይሄ ከ 10 ሰዓት ተኩል አንስቶ የሚቀርበው የአዕጋረ ፀሀይ መፅሀፍ ምረቃ

> ግጥምን በጃዝ ፣
> ሙዚቃ ፣
> ስዕል እና የመፅሀፏ ዳሰሳዎች የሚስተናገዱበት መድረክ ይሆናል ።

👉🏿 መሶብ ባንዶች በዓሉን ያደምቁታል ።
በሀገራችን ወግ እና ባህል መሰረት ቡናው ፣ ፋንዲሻው ፏ ብሎ የአዲስ ዓመት መምጣትን የሚያበስር ነገሪት ይጎስማል።

የቻሌንጅ አሸናፊዎች ደጎስ ያለ ሽልማታቸውን ይቀበላሉ። ጥበባዊ ለዛ ያለው ድባብ ይኖራል ።

👉🏿 መግቢያው ፍቅር እና መውጫው ክብር የሆነበት የማይቀርበት ድግስ እነሆ ለእናንተ ተብላችኋል ቤተሰቦች።

@getem
@getem
@getem
👍20🎉154🔥3👎1
ዝና
የዛፍ እንቅልፍ
ያልተደላደለ
ነቅተው ካልወረዱ
ወርዶ መንቃት አለ።

By Rediet Aseffa

@getem
@getem
@getem
50👍22😁7🔥3
"ትንሽ ቦታ"

ስሜታዊ ሆኖ ለተናገረን ፣ ሊረዳን ፈልጎ ለሳተ ፣ ኑሮ አስክሮት ለገፋን ፣ ንዴት ገፍቶት ላጠፋ ፣ ግዜ አጣሁ ብሎ ላልጎበኘን ፣ ስናሸንፍ ላላጨበጨበ፣ ስንወድቅ ላላነሳን ፣ ስናስብለት ላልተረዳን ፣ ማደጋችንን ላላየ ፦

"ትንሽ ቦታ ለይቅርታ" አኑረናል

አማረልን ብለን ላሳዘንን ፣ አጉል ተስፋ ለሰጠነው ፣ ውድቀት ላይ ለሳቅነው ፣ ብልግናን ላጎላናው ፣ ድድብናን ላነፈስነው ፣ ማድረግ ችለን ላላደረግነው ፣ ችለን ለተጣመምነው ።

ለራሳችን ይቅርታ አደርገናል...

ቺርስ ለአዲስ ዘመን
ቺርስ ለተስፋችን
ቺርስ🙏.


By Adhanom Mitiku

@getem
@getem
@paappii
41👍27🔥1