እውነት! እውነት! እውነት!
እኛ እነሱን እንሁን
እነሱ እኛን አይሁኑ
አይኖሯትም እንደ ግዜው
አይኖሯትም እንደ አሁኑ።
እውነት! እውነት! እውነት!
#ፍትህ_ለፌቨን
ሳሙኤል አለሙ
@Samuelalemuu
@getem
@getem
እኛ እነሱን እንሁን
እነሱ እኛን አይሁኑ
አይኖሯትም እንደ ግዜው
አይኖሯትም እንደ አሁኑ።
እውነት! እውነት! እውነት!
#ፍትህ_ለፌቨን
ሳሙኤል አለሙ
@Samuelalemuu
@getem
@getem
😢89❤35👍15😱6🔥2
ፈጣሪ አምላኬ ~ ይቅር በለኝ ዛሬ
ህግህን ሳፈርሰው
አትፍረድ ብትልም ~ እኔ ግን አልቻልኩም
ፈርዳለው በዚህ ሰው።
የክፋትን ጥጉን ~ የመቆሸሽ ጥጉን
ገደቦች ላለፈ
ያንዲት ምስኪን ህፃን ~ ክብሯን በግፍ ገፎ
ነፍሷን ለቀጠፈ
የእጁን እንዲያገኝ ~ ስቃይ እና ሞቱን
ለሱ መመኘቴ
የጨቅላዋን ህመም ~ ማሰብ ቢያቅተኝ ነው
ባይችል ነው አንጀቴ
፧
፧
፧
የቆሰለ ውስጧን ~ የእናቲቱን እምባ
ሚያብሰው ሲጠፋ
ፍትህ እየተዛባ ~ ተበዳይ ሲበደል
ውስጣችን ቢከፋ
አቤቱ ፈጣሪ ~ አነባን ወዳንተ
አነባን ወደላይ
ፍርድህን አሳየን ~ ክፉዎች ቀጥተህ
በምድርና በሰማይ።
፧
፧
#ፍትህ_ያለእድሜዋ_በግፍ_ለተነጠቀች_ነፍስ
#ፍትህ_ለሔቨን
✍@BegitimEnawga
@getem
@getem
@getem
ህግህን ሳፈርሰው
አትፍረድ ብትልም ~ እኔ ግን አልቻልኩም
ፈርዳለው በዚህ ሰው።
የክፋትን ጥጉን ~ የመቆሸሽ ጥጉን
ገደቦች ላለፈ
ያንዲት ምስኪን ህፃን ~ ክብሯን በግፍ ገፎ
ነፍሷን ለቀጠፈ
የእጁን እንዲያገኝ ~ ስቃይ እና ሞቱን
ለሱ መመኘቴ
የጨቅላዋን ህመም ~ ማሰብ ቢያቅተኝ ነው
ባይችል ነው አንጀቴ
፧
፧
፧
የቆሰለ ውስጧን ~ የእናቲቱን እምባ
ሚያብሰው ሲጠፋ
ፍትህ እየተዛባ ~ ተበዳይ ሲበደል
ውስጣችን ቢከፋ
አቤቱ ፈጣሪ ~ አነባን ወዳንተ
አነባን ወደላይ
ፍርድህን አሳየን ~ ክፉዎች ቀጥተህ
በምድርና በሰማይ።
፧
፧
#ፍትህ_ያለእድሜዋ_በግፍ_ለተነጠቀች_ነፍስ
#ፍትህ_ለሔቨን
✍@BegitimEnawga
@getem
@getem
@getem
😢136👍42❤35
ዝም ስትል
ቅዱስ መንፈስ አላት የሚያረብ በላይዋ
በፍቅር አጋድሞ ልብን የሚያሰዋ
ዙሪያዋ ተከቦ በቀይ ሴቶች ሰፈር
ጠይሞ ይፈካል የርሷ አፈጣጠር ።
አይገርምም ?
አልቦ እንኳ የላትም
ለከንፈሯም ቀለም
ፍዝ ውበት ገደለኝ
እና እንደምን ልክረም ?
ነጠላዋን መሆን
ፈለግሁኝ መለበስ ፣ ከበላይዋ መጣል
አንጥፎ መተኛት ፣ ከናፍሯ መኃል ።
ያን ጊዜ ተመኝሁ
ባ’ላይ ቀያይ ሴቶች
በአርቴፊሻል ምስለት የደመቁ እንስቶች
እንጀራን በሹካ እንቁረስ የሚሉ
ቀበጥባጣ ልቆች።
ያን ጊዜ ሰለቸኝ
አፋቸው ሲከፈት
እንደዚህ ነው ማለት
ጠላሁት ዓለሙን ...
ውስኪ ዳንኪራውን
አልጥም አለኝ ጥበብ
ዜማና ሙዚቃ
የትኛው ጠቢብ ነው
ከርሷ አርምሞ ልቆ እኔን የሚያነቃ ?
ይኸው እድሜ ለሷ
ስኖር በዘመኔ
ከቀኔ ሰርቄ...
ለብዕር ወድቄ
እንዳላሉኝ መጥኔ
አልጥም አለኝ ቅኔ
ታከተኝ ፣ ሰለቸኝ
ስንኝ እና ግጥም
ዝምታዋ ታትሞ
ካላገኝሁ በ’ቀር …
መጥሀፍ አላነብም !
(ሚካኤል አ)
@getem
@getem
@getem
ቅዱስ መንፈስ አላት የሚያረብ በላይዋ
በፍቅር አጋድሞ ልብን የሚያሰዋ
ዙሪያዋ ተከቦ በቀይ ሴቶች ሰፈር
ጠይሞ ይፈካል የርሷ አፈጣጠር ።
አይገርምም ?
አልቦ እንኳ የላትም
ለከንፈሯም ቀለም
ፍዝ ውበት ገደለኝ
እና እንደምን ልክረም ?
ነጠላዋን መሆን
ፈለግሁኝ መለበስ ፣ ከበላይዋ መጣል
አንጥፎ መተኛት ፣ ከናፍሯ መኃል ።
ያን ጊዜ ተመኝሁ
ባ’ላይ ቀያይ ሴቶች
በአርቴፊሻል ምስለት የደመቁ እንስቶች
እንጀራን በሹካ እንቁረስ የሚሉ
ቀበጥባጣ ልቆች።
ያን ጊዜ ሰለቸኝ
አፋቸው ሲከፈት
እንደዚህ ነው ማለት
ጠላሁት ዓለሙን ...
ውስኪ ዳንኪራውን
አልጥም አለኝ ጥበብ
ዜማና ሙዚቃ
የትኛው ጠቢብ ነው
ከርሷ አርምሞ ልቆ እኔን የሚያነቃ ?
ይኸው እድሜ ለሷ
ስኖር በዘመኔ
ከቀኔ ሰርቄ...
ለብዕር ወድቄ
እንዳላሉኝ መጥኔ
አልጥም አለኝ ቅኔ
ታከተኝ ፣ ሰለቸኝ
ስንኝ እና ግጥም
ዝምታዋ ታትሞ
ካላገኝሁ በ’ቀር …
መጥሀፍ አላነብም !
(ሚካኤል አ)
@getem
@getem
@getem
👍32❤8🔥1
Forwarded from Mik@
ክፋትን ያለየች ነፍሷ
የአለም ግፍ የተደበቃት
ፈንድቃ ያቀፈችው ሰው
ከምድር ሲጨፈልቃት
..
እንዳትሸሽ በሩ ተዘግቷል
የአቅሟን እየታገለች:
የማን ስም ጠርታ ትታደግ?
እኗቷ ጥላት ሄዳለች።
፡
እንዳትጮህ አሸዋ ጎርሷል
ልጅ አፏ የሳቀችበት፥
እንዳትሮጥ ተከምሮባት
ተሳቃ ከቆመችበት፤
ያለአቅም ስቃይ ተግታ
እምባዋ ከአይኗ ሲረግፍ፥
ታላቋን ከማመን ውጪ
ዘመኗን ባልሰራችው ግፍ፤
ስትዳክር አላየቻትም
ለማቀፍ ምትሳሳ እናቷ፥
ብታይ ግን ሰው ትሆን ነበር?
ደም ሲወርድ ፡ ከሰውነቷ? ።
..
ለእርሷ ነው አሳር ምትበላው
ከሰው እጅ አልጠበቀችም፤
ኩርፊያዋ ፣ ሳቋ አልበቃት፡
ምላሷን አልጠገበችም።
..
ቀን ያልፋል ብላ ስትኖር፡
ሰርክ አዲስ የሚያሳቅቃት፥
ወጥመዱን ችላው ስትገፋ
ክፉ አለም ልጅም ነጠቃት።
ህፃን ነች እቅፍ ማትሞላ
እንደ አራስ ፊቷ ያባባል፤
እንኳንስ የጭንቋ ሲቃ
እምባዋ ከልብ ይገባል፤
አትችልም ቁጣ መቋቋም፡
ፍቅር ነው የተማረችው፥
ተራራ ሚገፋን ጉልበት ፡
በምን ሀይል ተቋቋመችው?።
© @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
የአለም ግፍ የተደበቃት
ፈንድቃ ያቀፈችው ሰው
ከምድር ሲጨፈልቃት
..
እንዳትሸሽ በሩ ተዘግቷል
የአቅሟን እየታገለች:
የማን ስም ጠርታ ትታደግ?
እኗቷ ጥላት ሄዳለች።
፡
እንዳትጮህ አሸዋ ጎርሷል
ልጅ አፏ የሳቀችበት፥
እንዳትሮጥ ተከምሮባት
ተሳቃ ከቆመችበት፤
ያለአቅም ስቃይ ተግታ
እምባዋ ከአይኗ ሲረግፍ፥
ታላቋን ከማመን ውጪ
ዘመኗን ባልሰራችው ግፍ፤
ስትዳክር አላየቻትም
ለማቀፍ ምትሳሳ እናቷ፥
ብታይ ግን ሰው ትሆን ነበር?
ደም ሲወርድ ፡ ከሰውነቷ? ።
..
ለእርሷ ነው አሳር ምትበላው
ከሰው እጅ አልጠበቀችም፤
ኩርፊያዋ ፣ ሳቋ አልበቃት፡
ምላሷን አልጠገበችም።
..
ቀን ያልፋል ብላ ስትኖር፡
ሰርክ አዲስ የሚያሳቅቃት፥
ወጥመዱን ችላው ስትገፋ
ክፉ አለም ልጅም ነጠቃት።
ህፃን ነች እቅፍ ማትሞላ
እንደ አራስ ፊቷ ያባባል፤
እንኳንስ የጭንቋ ሲቃ
እምባዋ ከልብ ይገባል፤
አትችልም ቁጣ መቋቋም፡
ፍቅር ነው የተማረችው፥
ተራራ ሚገፋን ጉልበት ፡
በምን ሀይል ተቋቋመችው?።
© @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
😢137👍31❤8🔥3🤩2
[እንኳን አደረሳችሁ]
ነይልኝ!
ይጠየቅ ታቦር
ይመስክር ተራራው፣
እግዜር በመለኮት
እንዴት እንዳበራው፣
ይመስክር ኤልያስ
ይናገር ለአለሙ፣
ማመን ያነሳቸው
ያልሰሙ እንዲሰሙ።
ሆያ ሆዬ ይባል
ይዘመር መዝሙሩ፣
ከበሮው ይመታ
ይሟሟቅ አድባሩ፣
እውነት እንዳዘለ
የአምላክ መገለጡ፣
ለእርሱ ምስጋና
አፎች ቃል አወጡ።
ከተራራው መሀል
ብርሀኑ በርቷል፣
የመለኮት ምስጢር
ለአለም ተዘርቷል።
ያንን የሰማ 'ለት
አለማዊ ልቤ፣
አንቺን ያስብለኛል
ይርቀኛል ቀልቤ፣
ሆያ ሆዬ ብየ
መምጣት እመኛለሁ፣
ልብሽ እንደ ሙልሙል
ቢሰጠኝ እላለሁ፣
ስትናፍቂኝ ነው
እኔ ምን አውቃለሁ።
ከልማዱ ቢርቅ
ምን ለጆሮ ባይጥም፣
ያንቺው ሆያ ሆዬ
ይሄው የኔ ግጥም።
ሆያ ሆዬ ሆ
ሆያ ሆዬ ሆ
አይንሽን ማየት ሆ
ናፍቆ ያደረ ፣ ሆ
ባታውቂለትም ሆ
ልቤ ነበረ ፣ ሆ
ባህር እንዳጣ ሆ
ባይተዋር አሳ፣ ሆ
አንቺን በማሰስ ሆ
ወድቆ ሚነሳ፣ ሆ
የፍቅርሽ ናፋቂ፣
እኔው ነኝ እወቂ።
የምመኘው ፍቅር፣
ይምጣልን ተይ አይቅር።
የወፍ አፋ የወፍ አፋ፣
ልቤ ባንቺ ጥሎኝ ጠፋ፣
የወፍ ደግ የወፍ ደግ፣
ነይ ፍቅራችን ይደግ።
ላቀረብኩ ቅኔ
ለፍቅርሽ መወድስ፣
ሰላሜን አግኝቼ
ራሴን እንዳድስ፣
በሙልሙሉ ፋንታ
ልብሽ ይታደለኝ።
አንቺም አይተሽዋል
በገጠምኩት ግጥም
መፅደቅ እንደለለኝ።
ለአምላክ ጀምሬ
ላንቺ ስጨርሰው
እግዜሩስ ምን ይለኝ?
ይቴ ( @gtmwustie
@gitimtm )
@getem
@getem
@gitimtm
ነይልኝ!
ይጠየቅ ታቦር
ይመስክር ተራራው፣
እግዜር በመለኮት
እንዴት እንዳበራው፣
ይመስክር ኤልያስ
ይናገር ለአለሙ፣
ማመን ያነሳቸው
ያልሰሙ እንዲሰሙ።
ሆያ ሆዬ ይባል
ይዘመር መዝሙሩ፣
ከበሮው ይመታ
ይሟሟቅ አድባሩ፣
እውነት እንዳዘለ
የአምላክ መገለጡ፣
ለእርሱ ምስጋና
አፎች ቃል አወጡ።
ከተራራው መሀል
ብርሀኑ በርቷል፣
የመለኮት ምስጢር
ለአለም ተዘርቷል።
ያንን የሰማ 'ለት
አለማዊ ልቤ፣
አንቺን ያስብለኛል
ይርቀኛል ቀልቤ፣
ሆያ ሆዬ ብየ
መምጣት እመኛለሁ፣
ልብሽ እንደ ሙልሙል
ቢሰጠኝ እላለሁ፣
ስትናፍቂኝ ነው
እኔ ምን አውቃለሁ።
ከልማዱ ቢርቅ
ምን ለጆሮ ባይጥም፣
ያንቺው ሆያ ሆዬ
ይሄው የኔ ግጥም።
ሆያ ሆዬ ሆ
ሆያ ሆዬ ሆ
አይንሽን ማየት ሆ
ናፍቆ ያደረ ፣ ሆ
ባታውቂለትም ሆ
ልቤ ነበረ ፣ ሆ
ባህር እንዳጣ ሆ
ባይተዋር አሳ፣ ሆ
አንቺን በማሰስ ሆ
ወድቆ ሚነሳ፣ ሆ
የፍቅርሽ ናፋቂ፣
እኔው ነኝ እወቂ።
የምመኘው ፍቅር፣
ይምጣልን ተይ አይቅር።
የወፍ አፋ የወፍ አፋ፣
ልቤ ባንቺ ጥሎኝ ጠፋ፣
የወፍ ደግ የወፍ ደግ፣
ነይ ፍቅራችን ይደግ።
ላቀረብኩ ቅኔ
ለፍቅርሽ መወድስ፣
ሰላሜን አግኝቼ
ራሴን እንዳድስ፣
በሙልሙሉ ፋንታ
ልብሽ ይታደለኝ።
አንቺም አይተሽዋል
በገጠምኩት ግጥም
መፅደቅ እንደለለኝ።
ለአምላክ ጀምሬ
ላንቺ ስጨርሰው
እግዜሩስ ምን ይለኝ?
ይቴ ( @gtmwustie
@gitimtm )
@getem
@getem
@gitimtm
👍55❤9🔥1
ደብረ ታቦር
.
.
ብርሃነ መለኮት ከተገለፀበት፤
መልኩ ተለዉጦ ፀዳል በሆነበት፤
አብም ስለ ልጁ እርሱን ስሙት ብሎ ከመሰከረበት፤
የጌታ አምላክነት የሥላሴ ምስጢር ከተሰበከበት፤
ልብን ከሚመስጥ ከዚህ ድንቅ ስፍራ፤
መንፈስ ከሚያድስ ከታቦር ተራራ፤
በዚህ መኖር ለእኛ .......
እጅጉን መልካም ነዉ ከጌታችን ጋራ።
✨እንኳን አደረሳችሁ✨
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
.
.
ብርሃነ መለኮት ከተገለፀበት፤
መልኩ ተለዉጦ ፀዳል በሆነበት፤
አብም ስለ ልጁ እርሱን ስሙት ብሎ ከመሰከረበት፤
የጌታ አምላክነት የሥላሴ ምስጢር ከተሰበከበት፤
ልብን ከሚመስጥ ከዚህ ድንቅ ስፍራ፤
መንፈስ ከሚያድስ ከታቦር ተራራ፤
በዚህ መኖር ለእኛ .......
እጅጉን መልካም ነዉ ከጌታችን ጋራ።
✨እንኳን አደረሳችሁ✨
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
👍48❤24🎉1
የእረኛው መልዕክት
(ሚካኤል አ)
አይዋዬ…
ሲመሽ አልኩህ እኮ
ጠሀይ ስትጨልም
ቀንህ ስትቆዝም
ተዋበችህ ስታሸልብ
በየትም ወርቅ ስትተካ
ሊቀ መኳስ ዩሀንስህ
በደረቱ ክፍተት ጦር ገብቶ ሲሰካ ፤
ከእጅህ የጎረሰ ጣትህን ሲነክስ
ያንተ አዝማሪ በደጅ
ካ’ዲህን ሲያወድስ
ቁንዳላህ ይቆማል
ወግ ስሪቱን አጥቶ
ኮናኝ ይተርባል
መገርጣትህን አይቶ ።
አየህ አይዋዬ !
ሲመሽ …
ፀሐይ ስትጨልም
ቀንህ ስትቆዝም
ልጓምህ ሲሰንፍ
ፈረስህ ሲለግም
ቃልህ ከአፍህ ፈልቆ
የትም ዘንድ አይደርስም ።
.
ብርሀንህ ሲያልፍ
የደጅህ አበባ
ቅጠሉን ሲያረግፍ
ለመልካም ያረከው
ይቆጠራል ከግፍ ።
.
ያኔ ትበግናለህ
ሲጠፋ መረግድ
ከኮርቻ ጫንቃ
ገብርዬህ ሲወርድ
ሲሆን ማጨናጎል
የካህን መሐራ …
ከመቅደስ እንደ እጣን
ሲምዘገዘግ ካራ …
ራዕይህ ስትመክን
ቅምጭናህ ተሰብራ …
ያኔ ትበግናለህ
በብዙ ህመም ስቃይ
ከዛ በመንደርህ ሁሉም ይላል
ዋይ ……… ዋይ
ሀዘን አይሰማህም
እንባም አያርምህም
ሁሉ ጥልህ ይሆናል ምድር ያበቀለው
ፍጥረት ተቃርኖህ ነው …
ክንድህ ተሰብስቧል
ቂምህ አመርቅዟል
ያኔ የምታጎርስ
ጠኔ ላንገላታው…
መክፈልትን አይደለም
ጥይት ሆኗል ተራው።
እንዲያ ነው አይዋ !
መቅደላ ላይ ቆመህ
ዙሪያህ ሲሆን ገደል
ዓላማህ በልጅህ ተጋርዶ ሲከለል
አትሸሽም ከእንግሊዝ
ከናፒየር ምርኮ
ወኔህ ኮርቶ ያልፋል
በሽጉጥህ ሾልኮ ።
ቡም !
አየህ እንደዚህ ነው …
የጎበዝ ስንብት
የጀግና ሰው ጉዞ
ኩራት ክብሩን ይዞ
ታዝቦ ሀገሩን
ሲሰቅል ነብዩን
እየተራገመ
እየተዋቀሰ
ይብላኝ ለአንተ ብሎ
እንባን ለፈጣሪው
በፀሎት ጠቅልሎ
ከ’ሶ አባትህን
ከ’ሶ አያትህን
ዛሬ አወረሱህ
የበደል ዋጋህን።
እንዲያ ነው አይዋ !
በገደል በዱሩ
በምድር ባ’ፈሩ
በንዋይ በዝና
በሴት ገላ ቃና
ሳቅህን አትፈልገው
ትናንት ረግሞሀል
ካሳን በመቅደላ
ብቻውን ስተወው!!
@getem
@getem
@getem
(ሚካኤል አ)
አይዋዬ…
ሲመሽ አልኩህ እኮ
ጠሀይ ስትጨልም
ቀንህ ስትቆዝም
ተዋበችህ ስታሸልብ
በየትም ወርቅ ስትተካ
ሊቀ መኳስ ዩሀንስህ
በደረቱ ክፍተት ጦር ገብቶ ሲሰካ ፤
ከእጅህ የጎረሰ ጣትህን ሲነክስ
ያንተ አዝማሪ በደጅ
ካ’ዲህን ሲያወድስ
ቁንዳላህ ይቆማል
ወግ ስሪቱን አጥቶ
ኮናኝ ይተርባል
መገርጣትህን አይቶ ።
አየህ አይዋዬ !
ሲመሽ …
ፀሐይ ስትጨልም
ቀንህ ስትቆዝም
ልጓምህ ሲሰንፍ
ፈረስህ ሲለግም
ቃልህ ከአፍህ ፈልቆ
የትም ዘንድ አይደርስም ።
.
ብርሀንህ ሲያልፍ
የደጅህ አበባ
ቅጠሉን ሲያረግፍ
ለመልካም ያረከው
ይቆጠራል ከግፍ ።
.
ያኔ ትበግናለህ
ሲጠፋ መረግድ
ከኮርቻ ጫንቃ
ገብርዬህ ሲወርድ
ሲሆን ማጨናጎል
የካህን መሐራ …
ከመቅደስ እንደ እጣን
ሲምዘገዘግ ካራ …
ራዕይህ ስትመክን
ቅምጭናህ ተሰብራ …
ያኔ ትበግናለህ
በብዙ ህመም ስቃይ
ከዛ በመንደርህ ሁሉም ይላል
ዋይ ……… ዋይ
ሀዘን አይሰማህም
እንባም አያርምህም
ሁሉ ጥልህ ይሆናል ምድር ያበቀለው
ፍጥረት ተቃርኖህ ነው …
ክንድህ ተሰብስቧል
ቂምህ አመርቅዟል
ያኔ የምታጎርስ
ጠኔ ላንገላታው…
መክፈልትን አይደለም
ጥይት ሆኗል ተራው።
እንዲያ ነው አይዋ !
መቅደላ ላይ ቆመህ
ዙሪያህ ሲሆን ገደል
ዓላማህ በልጅህ ተጋርዶ ሲከለል
አትሸሽም ከእንግሊዝ
ከናፒየር ምርኮ
ወኔህ ኮርቶ ያልፋል
በሽጉጥህ ሾልኮ ።
ቡም !
አየህ እንደዚህ ነው …
የጎበዝ ስንብት
የጀግና ሰው ጉዞ
ኩራት ክብሩን ይዞ
ታዝቦ ሀገሩን
ሲሰቅል ነብዩን
እየተራገመ
እየተዋቀሰ
ይብላኝ ለአንተ ብሎ
እንባን ለፈጣሪው
በፀሎት ጠቅልሎ
ከ’ሶ አባትህን
ከ’ሶ አያትህን
ዛሬ አወረሱህ
የበደል ዋጋህን።
እንዲያ ነው አይዋ !
በገደል በዱሩ
በምድር ባ’ፈሩ
በንዋይ በዝና
በሴት ገላ ቃና
ሳቅህን አትፈልገው
ትናንት ረግሞሀል
ካሳን በመቅደላ
ብቻውን ስተወው!!
@getem
@getem
@getem
👍21❤18
አንዲት ህፃን ማለት
ንፁህ ናት ከፍጥረት
አታውቀውም ግሳንግሱን
የዚህ ዓለም ደባ
ሸር እና ተንኮሉን።
ንፁህ ናት የነጻች
እንደ አደይ የፈካች
ያልዘለቃት … ይሄ ምድር
የትም ብትቦርቅ ፣ የትም ዘንድ ብታድር
ልቧ መልካሙን ነው ፣ ላንተ የሚዘምር ።
እናስ ወንድማለም …
እንደምን አስቻለህ እጅህን ለማንሳት
መልካሟን ለማጥፋት
እንደምን ታዘዘህ አሸዋ ለመዝገን
ተፈጥረህ በክብር ፣ ከሰው ልጆች ወገን ?
እንደምን አስቻለህ ፍርድን ለማጣፋት
ሸንጎን ለማስረሳት?
አልገባህም እንጂ !
ዕውነቷን ብታውቃት…
ታስረህም ታስረሃል
ነጻም ሆነህ እንደዛው
እጅህ ሲነሳ ነው …
ስምህ ከ’ግዜር መዝገብ ፣ የጠፋብህ ደብዛው ።
(ሚካኤል አ )
@getem
@getem
@getem
ንፁህ ናት ከፍጥረት
አታውቀውም ግሳንግሱን
የዚህ ዓለም ደባ
ሸር እና ተንኮሉን።
ንፁህ ናት የነጻች
እንደ አደይ የፈካች
ያልዘለቃት … ይሄ ምድር
የትም ብትቦርቅ ፣ የትም ዘንድ ብታድር
ልቧ መልካሙን ነው ፣ ላንተ የሚዘምር ።
እናስ ወንድማለም …
እንደምን አስቻለህ እጅህን ለማንሳት
መልካሟን ለማጥፋት
እንደምን ታዘዘህ አሸዋ ለመዝገን
ተፈጥረህ በክብር ፣ ከሰው ልጆች ወገን ?
እንደምን አስቻለህ ፍርድን ለማጣፋት
ሸንጎን ለማስረሳት?
አልገባህም እንጂ !
ዕውነቷን ብታውቃት…
ታስረህም ታስረሃል
ነጻም ሆነህ እንደዛው
እጅህ ሲነሳ ነው …
ስምህ ከ’ግዜር መዝገብ ፣ የጠፋብህ ደብዛው ።
(ሚካኤል አ )
@getem
@getem
@getem
😢52👍24❤3
መምሰል
°°°°°°°°
ከደጇ ቁሚያለሁ
በረከት ለማግኘት ከ'ናቴ ፍልሰታ፣
ማረጓን ያመነ
ይኸው ያሰማል መዝሙርና እልልታ።
"ማርያም አረገች አረገች"
ቀና ብዬ አየሁ የሰማዩን ከፈን፣
ለጠርጣራው ልብሽ ማሳረፊያ 'ሚሆን፥
ከሰጠችሽ ብዬ እንደ ቶማስ ሰበን።
አየሽ ሞኝነቴን
ከፍቅሬ የተነሳ ላንቺ ምህረት ስሻ፣
ከስንት ዘመን በፊት
ያረገች እናቴን
እንዳ'ዲስ ሳሳርግ በምናቤ ዋሻ።
ግን መጥተሽ ይሆን?
ህጻናት በክብር
ስጋ እና ደሙን ቀምሰው ሲመለሱ፣
ቆርበሽ ከሆን ብዬ
እስክትወጭ አያለሁ ከቤተ መቅደሱ።
አየሽ የዋህነቴን
በሴት ግዳጅ ታስረሽ
መግባት እንደማትችይ እያወ'ኩ ጠንቅቄ፣
ትኖሪያለሽ ብዬ
በከንቱ ሳማትር በፍቅርሽ ታንቄ።
ግን መጥተሽ ይሆን?
እልፍ ሆኖ ሳለ
እምነት የተቀባ ነጠላ ያጣፋ፣
ቅጽሩን ሙሉ ብቃኝ
አንችን የሚመስል አንድ ውብ ሴት ጠፋ።
ተመልከች እብደቴን
ተስፋዬ ተሟጦ
ለስግደት ስደፋ ከ'ናቴ ስዕል ፊት፣
ወለል ብሎ ታየኝ ያንቺ መሳይ ውብ ፊት፤
ይኸው ተገፈፈ
ማጣት ያሳወረው
የዓይኔ ላይ ጉድፍ ልክ እንደ ቅርፊት።
ቁጭ እሷን!!
ቁጭ አንችን!!
ሰዓሊ ለነ ቅድስት!!
ለማን ነው የሰገድኩት?
ግን አንቺ ነሽ?
አንቺም አር'ገሻል እንደ እመቤቴ?
አበድኩ መሰለኝ
የማይሆን ጥያቄ ወጣ ካ'ንደበቴ።
#ኤልዳን
@eldan29
@getem
@getem
@getem
°°°°°°°°
ከደጇ ቁሚያለሁ
በረከት ለማግኘት ከ'ናቴ ፍልሰታ፣
ማረጓን ያመነ
ይኸው ያሰማል መዝሙርና እልልታ።
"ማርያም አረገች አረገች"
ቀና ብዬ አየሁ የሰማዩን ከፈን፣
ለጠርጣራው ልብሽ ማሳረፊያ 'ሚሆን፥
ከሰጠችሽ ብዬ እንደ ቶማስ ሰበን።
አየሽ ሞኝነቴን
ከፍቅሬ የተነሳ ላንቺ ምህረት ስሻ፣
ከስንት ዘመን በፊት
ያረገች እናቴን
እንዳ'ዲስ ሳሳርግ በምናቤ ዋሻ።
ግን መጥተሽ ይሆን?
ህጻናት በክብር
ስጋ እና ደሙን ቀምሰው ሲመለሱ፣
ቆርበሽ ከሆን ብዬ
እስክትወጭ አያለሁ ከቤተ መቅደሱ።
አየሽ የዋህነቴን
በሴት ግዳጅ ታስረሽ
መግባት እንደማትችይ እያወ'ኩ ጠንቅቄ፣
ትኖሪያለሽ ብዬ
በከንቱ ሳማትር በፍቅርሽ ታንቄ።
ግን መጥተሽ ይሆን?
እልፍ ሆኖ ሳለ
እምነት የተቀባ ነጠላ ያጣፋ፣
ቅጽሩን ሙሉ ብቃኝ
አንችን የሚመስል አንድ ውብ ሴት ጠፋ።
ተመልከች እብደቴን
ተስፋዬ ተሟጦ
ለስግደት ስደፋ ከ'ናቴ ስዕል ፊት፣
ወለል ብሎ ታየኝ ያንቺ መሳይ ውብ ፊት፤
ይኸው ተገፈፈ
ማጣት ያሳወረው
የዓይኔ ላይ ጉድፍ ልክ እንደ ቅርፊት።
ቁጭ እሷን!!
ቁጭ አንችን!!
ሰዓሊ ለነ ቅድስት!!
ለማን ነው የሰገድኩት?
ግን አንቺ ነሽ?
አንቺም አር'ገሻል እንደ እመቤቴ?
አበድኩ መሰለኝ
የማይሆን ጥያቄ ወጣ ካ'ንደበቴ።
#ኤልዳን
@eldan29
@getem
@getem
@getem
❤35👍31👎14🤩10
..
ጭንቀቴ የታል?
የት ገባ?
አንተ ነህ አይደል፡
አባባ?
:
:
ሳልተነትነው፡
መአቴን ፤
እንዴት ሰማኸው፡
ፀሎቴን?።
@mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
ጭንቀቴ የታል?
የት ገባ?
አንተ ነህ አይደል፡
አባባ?
:
:
ሳልተነትነው፡
መአቴን ፤
እንዴት ሰማኸው፡
ፀሎቴን?።
@mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
❤81👍29🤩4
"ልጠብቅህ!?"
''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
በነሃሴ ታምር ሱባዔ ፍልሰታ፤
ከህፃን እስከ አዛውንት በጾመበት ለአፍታ።
በወርሃ ነሃሴ በቀን 16 በዕለተ ሐሙስ፤
በዚህ የቀን ቅዱስ፥
ካህናቱ ሁሉ፤
ምዕመን በሙሉ፤
ማርያም አረገች ወደገነት ሲሉ።
ለድንግል ዕርገቷ ሲያሰሙ ውዳሴ ሲያሰሙ እልልታ፤
በ16 ፍልሰታ(በ16 ለ'ታ)
ዝማሬ ውረባ ሲያቀርቡ ካህናቱ፤
ሽብሻቦ ጭብጨባ ሲያሰሙ ህፃናቱ፥ሲያሰሙ አዛውንቱ።
እኔ ግን ከአምባው ጥግ ከአፀዱ ስር ቆሜ፤
ከምድር ውዳሴ እስከ አርያም ድረስ በምናብ ታድሜ።
ከዝንት ዘመን በፊት ያረገች እናቴን እያየሁ በሃሳቤ፤
ሳሳርግ ብቻዬን ስታ'ርግ በግርማ ስስል በምናቤ።
ቅድም ሊቁ ቆመው ከፊት አትሮኖስ ላይ፤
ለቶማስ ሰበኗን ሰጠችው ከሠማይ፤
ትንሳዔዋን እንዲያውጅ ማረ'ጓን እንዲያይ።
ብለው ያስተማሩት ትውስ ሲል ለአፋታ ድንገት ከአምሮዬ፤
እኔም ወደ ሠማይ፥
ከጉልላቱ ላይ፥
ልብ ዓይኔን ተክዬ።
በትንሳዔሽ ብስራት ከትንሳዔሽ እኩል፤
አምጭልኝ ስላት የልቤን ፍቅር ኩል።
ከአንተው ከፍቅሬ ጋር ከመንገዴ ሲሳይ፤
ከምናብ ወጥቼ ዓይኖችህን እንዳይ፤
ፍቅርን እንድለቅመው ከልብህ ቃርሚያ ላይ።
ለሸፈተው ልቤ እንድትሆን ማረፊያ፤
ስለምናት አየህ ስማጸናት አየህ ከዳመናው ጣሪያ።
አርጊልኝ ከጎኔ፥
አሳይኝ በዓይኔ፥
ብዬ ስማጸናት አየህልኝ አይደል አየህ ሞኝነቴን፤
እውን አርጊው ስላት፥የምናብ ቅልቤን፤
አየህልኝ አይደል የፍቅር ህመሜን፤
አስፈቺ ያጣውን፥የታሰረው ልቤን፤
አየህልኝ አይደል የመውደዴን ልኩን፤
የማፍቀሬን መልኩን።
አየህ ሞኝነቴን አየህ የዋህነቴን አየህልኝ አይደል፤
ላ'ንት የከበደኝን ለምታውቀው ማርያም የመውደዴን መጠን ለመንገር ስታገል፤
አየህልኝ አይደል!?
ወደዋለሁና አቅርቢልኝ ስላት፤
በእንባ ስጠይቃት በእንባ ስማጸናት።
አየህልኝ አይደል!? የልቤን ውስጥ ስቃይ፤
ጉም ባፈነው ሠማይ፥
ከጉልላቱ ላይ፥
አንተን እንደሚናገሩት ስጠብቅ ከሠማይ፤
የመንገዴን ሲሳይ።
እንድታቀብለኝ አንተን ሰበን አርጋ፤
ድንግልን ስማጸን ልቤ እንዲረጋጋ።
ከአንቺ የተሰጠ ፍቅር ነው እያልኩኝ፤
ከደጀ ሠላሙ ከቅጥሩ ለመንኩኝ፤
ከአለህበት ቦታ አምጭልኝ እያልኩኝ።
ከተረዳህልኝ ከአወከው መውደዴን፤
ለተጓዡ ልብህ ማስታሻ ነገር ምትፈልግ ከሆነ ውሰድልኝ ልቤን።
ግን ፍቅሬ ዓለሜ፥ እኔ አንተን ስወድህ!
"ትመጣ ከሆነ ቆሜ ልጠብቅህ!?"
ተጻፈ፦በጦቢያ
በወርሃ ፦ነሃሴ
በቀን፦16/2016
የሆነ ሰዓት ላይ
@getem
@getem
@getem
''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
በነሃሴ ታምር ሱባዔ ፍልሰታ፤
ከህፃን እስከ አዛውንት በጾመበት ለአፍታ።
በወርሃ ነሃሴ በቀን 16 በዕለተ ሐሙስ፤
በዚህ የቀን ቅዱስ፥
ካህናቱ ሁሉ፤
ምዕመን በሙሉ፤
ማርያም አረገች ወደገነት ሲሉ።
ለድንግል ዕርገቷ ሲያሰሙ ውዳሴ ሲያሰሙ እልልታ፤
በ16 ፍልሰታ(በ16 ለ'ታ)
ዝማሬ ውረባ ሲያቀርቡ ካህናቱ፤
ሽብሻቦ ጭብጨባ ሲያሰሙ ህፃናቱ፥ሲያሰሙ አዛውንቱ።
እኔ ግን ከአምባው ጥግ ከአፀዱ ስር ቆሜ፤
ከምድር ውዳሴ እስከ አርያም ድረስ በምናብ ታድሜ።
ከዝንት ዘመን በፊት ያረገች እናቴን እያየሁ በሃሳቤ፤
ሳሳርግ ብቻዬን ስታ'ርግ በግርማ ስስል በምናቤ።
ቅድም ሊቁ ቆመው ከፊት አትሮኖስ ላይ፤
ለቶማስ ሰበኗን ሰጠችው ከሠማይ፤
ትንሳዔዋን እንዲያውጅ ማረ'ጓን እንዲያይ።
ብለው ያስተማሩት ትውስ ሲል ለአፋታ ድንገት ከአምሮዬ፤
እኔም ወደ ሠማይ፥
ከጉልላቱ ላይ፥
ልብ ዓይኔን ተክዬ።
በትንሳዔሽ ብስራት ከትንሳዔሽ እኩል፤
አምጭልኝ ስላት የልቤን ፍቅር ኩል።
ከአንተው ከፍቅሬ ጋር ከመንገዴ ሲሳይ፤
ከምናብ ወጥቼ ዓይኖችህን እንዳይ፤
ፍቅርን እንድለቅመው ከልብህ ቃርሚያ ላይ።
ለሸፈተው ልቤ እንድትሆን ማረፊያ፤
ስለምናት አየህ ስማጸናት አየህ ከዳመናው ጣሪያ።
አርጊልኝ ከጎኔ፥
አሳይኝ በዓይኔ፥
ብዬ ስማጸናት አየህልኝ አይደል አየህ ሞኝነቴን፤
እውን አርጊው ስላት፥የምናብ ቅልቤን፤
አየህልኝ አይደል የፍቅር ህመሜን፤
አስፈቺ ያጣውን፥የታሰረው ልቤን፤
አየህልኝ አይደል የመውደዴን ልኩን፤
የማፍቀሬን መልኩን።
አየህ ሞኝነቴን አየህ የዋህነቴን አየህልኝ አይደል፤
ላ'ንት የከበደኝን ለምታውቀው ማርያም የመውደዴን መጠን ለመንገር ስታገል፤
አየህልኝ አይደል!?
ወደዋለሁና አቅርቢልኝ ስላት፤
በእንባ ስጠይቃት በእንባ ስማጸናት።
አየህልኝ አይደል!? የልቤን ውስጥ ስቃይ፤
ጉም ባፈነው ሠማይ፥
ከጉልላቱ ላይ፥
አንተን እንደሚናገሩት ስጠብቅ ከሠማይ፤
የመንገዴን ሲሳይ።
እንድታቀብለኝ አንተን ሰበን አርጋ፤
ድንግልን ስማጸን ልቤ እንዲረጋጋ።
ከአንቺ የተሰጠ ፍቅር ነው እያልኩኝ፤
ከደጀ ሠላሙ ከቅጥሩ ለመንኩኝ፤
ከአለህበት ቦታ አምጭልኝ እያልኩኝ።
ከተረዳህልኝ ከአወከው መውደዴን፤
ለተጓዡ ልብህ ማስታሻ ነገር ምትፈልግ ከሆነ ውሰድልኝ ልቤን።
ግን ፍቅሬ ዓለሜ፥ እኔ አንተን ስወድህ!
"ትመጣ ከሆነ ቆሜ ልጠብቅህ!?"
ተጻፈ፦በጦቢያ
በወርሃ ፦ነሃሴ
በቀን፦16/2016
የሆነ ሰዓት ላይ
@getem
@getem
@getem
👍58❤27🤩4🔥1
.
.
.
ና አትበዪኝ ~ ምን ሰራለው?
አበሳሽን ፡ አቀላለው?
ና አትበዪኝ ~ ምን ልጠቅምሽ?
ስቃይሽን ፡ እንድደግምሽ?
ና አትበዪኝ ~ አልፈልግም!
ልሰባብርሽ ፡ ደግም ዳግም?
By @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
.
.
ና አትበዪኝ ~ ምን ሰራለው?
አበሳሽን ፡ አቀላለው?
ና አትበዪኝ ~ ምን ልጠቅምሽ?
ስቃይሽን ፡ እንድደግምሽ?
ና አትበዪኝ ~ አልፈልግም!
ልሰባብርሽ ፡ ደግም ዳግም?
By @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
❤43👍18😁6😢2🔥1
ወደ አምና መኮብለል
(✍️©እስራኤል )
አልጨበጥ ካለ ፥ ዛሬ እንደ ነፋስ
ከጠፋ 'ለኝ ያልነው፥ የተማመነው ዋስ
ግድ ይላል አንዳንዴ...
የዛሬን ወናነት የአሁንን ባዶነት፥
በትዝታ መካስ።
ሸርተት ወደ ትናንት ፥ ወረድ ወደ አምና
------- ------- ------ ----- ----- ------
ከአንቺሆዬም ከአምባሰል ፥ ትዝታ ማዘፈን
በትውስት ጥልማሞት ፥ የዛሬን አፍ ማፈን
ይጣፍጣል ህመም ፥ ይጥማል መከዳት
ትዝታ ሲጫነው ፥ ቢያምም ያምራል ጉዳት
ናፈቅሽኝ እንዳምናው ፥ እንደትናትና
ከድሮ ልዘሙት ፥ ይቅርብኝ ብህትውና
- - - - - - - - - - - - በትዝታሽ እሳት
የቀሰቀሽው ነብስ ፥ የጫርሽው ትኩሳት
ድሮም አንቺን ማቀፍ ፥ ዛሬም አንቺን ማውሳት
ከትናንትና እኩል ፥ አሁንም መሳሳት
ሳስቶ ባዝቶ ማለቅ ፥ ባክኖ ባክኖ መክሳት ።
@AdamuReta
@getem
@getem
@getem
(✍️©እስራኤል )
አልጨበጥ ካለ ፥ ዛሬ እንደ ነፋስ
ከጠፋ 'ለኝ ያልነው፥ የተማመነው ዋስ
ግድ ይላል አንዳንዴ...
የዛሬን ወናነት የአሁንን ባዶነት፥
በትዝታ መካስ።
ሸርተት ወደ ትናንት ፥ ወረድ ወደ አምና
------- ------- ------ ----- ----- ------
ከአንቺሆዬም ከአምባሰል ፥ ትዝታ ማዘፈን
በትውስት ጥልማሞት ፥ የዛሬን አፍ ማፈን
ይጣፍጣል ህመም ፥ ይጥማል መከዳት
ትዝታ ሲጫነው ፥ ቢያምም ያምራል ጉዳት
ናፈቅሽኝ እንዳምናው ፥ እንደትናትና
ከድሮ ልዘሙት ፥ ይቅርብኝ ብህትውና
- - - - - - - - - - - - በትዝታሽ እሳት
የቀሰቀሽው ነብስ ፥ የጫርሽው ትኩሳት
ድሮም አንቺን ማቀፍ ፥ ዛሬም አንቺን ማውሳት
ከትናንትና እኩል ፥ አሁንም መሳሳት
ሳስቶ ባዝቶ ማለቅ ፥ ባክኖ ባክኖ መክሳት ።
@AdamuReta
@getem
@getem
@getem
👍46😢7🔥5🎉4