ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አምና ያንቺ ሱሰኛ ነበርኩ  ሱሰኛሽ ያዉም በደስታ

መሽቶ መንጋቱን ማላምን ካለአይኖችሽ እይታ

ከራስ ፀጉሬ እስከ እግር ጣቴ ካላንቺ ድምፅ የማይፈታ

ሌት ተቀን ምኖር አብሬሽ ማልጠፋ ከጎንሽ ለአፍታ

ቃልሽን ሕጌ አድረጌው አኑሬሽ ከአማልክት ቦታ

ዘላለም ባገለግልሽ ለቅፅበት ማላመነታ

ነበርኩኝ ታማኝ አገልጋይ

ካላንቺ ሌሎች አምላኮች ማላይ

ምድር ሸሽታ ብትሄድ ቢገለባበጥ ሰማይ

አሁን ግን ምስጋና ላንቺ ዋልሽልኝ ታላቅ ዉለታ

አሳየሽኝ ሱስ እንደሚያረክስ እንደሚያወጣ ከሰዎች ተርታ

                   ዘረ-ሠናይ
           @Prince_Zeresenay

@getem
@getem
@getem
👍5312👎2
🙄አልታይሽም ወይ👀

አቃለው እንዳልሆንኩ በምድር ምነፍስ
የንፋስ ሽውታ

መኖረ ሚታወቅ ቅጠል ሳንቀሳቅስ
ወይ ደግሞ በሽታ

ታዲያ እንዴት ሆኖ በዋልሽበት ውዬ
ሳንዣብብ በዙሪያሽ

እስከዛሬ ድረስ አይኖችሽ ያላዩኝ
ገብቼ ከእይታሽ።

አልታይሽም ወይ????

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
19👍19
#የማይነቃ_ውሸት


እንደተወዛዋዥ ግንባር
በየምሶሶው የለጠፍሽው
"አለ" የምትል አድባር
ሰርክ መዳንን ብቻ አስለምደሽው
ሰርክ መኖርን ብቻ አስለምደሽው
ይረሳዋል እንደሚሞት ካልነገርሽው

ሳሙኤል አለሙ
@Samuelalemuu

@Getem
@Getem
31👍17🤩2
✍️ድንቄም ገጣሚ✍️

       ሳያዘጋጅ ብእር

       ሃሳብ ሳይደረድር

ስላሰኘው ብቻ ለመግጠም ሲሞክር

        አልሳካ ቢለው

በሰከነ መንፈስ ደግሞ ሳያስበው

የማይመስል ስንኝ ፅፎ እያሰፈረ

ካለበቂ እውቀት ለመግጠም እየጣረ

ቤት መታለው በሚል ቤት ማፍረስ ጀመረ::
:
:
:
ከሰማ ንገሩት
ቤት አታፍርስ በሉት::

<><><><><><><><><><><><><><><>

📌 ወቅቱን ታሳቢ አድርጌ ነው በድጋሚ አሻሽዬ ያዘጋጀሁት።

             ✍️ @BegitimEnawga

@getem
@getem
@getem
👍75😁189😱6👎4🤩3
😔😢ድብቅ ነው😢😔

ከንፈሬ ተገልጦ ጥርሶቼን ባይሸፍን
        ቢያለብሰኝ ፈገግታ

የውስጤን መከፋት የልቤን ጠባሳ
       ሸሸገው ከእይታ።
:
እውነታው ግን
:
ከሰው ተሸሽጌ ከጎጆዬ ስሆን
        ለብቻዬ ስቀር

ብሶቴ ተነስቶ እምባዬ ይፈሳል
      ከአይኔ ሲንደረደር።

የሚፈሰኝ እምባ አካሌን እያራሰው
       መውረዱን ባይተውም
      
     
ውስጤ ሚነደውን የልቤ ውስጥ እሳት
       ሊያጠፋው አይችልም።


<><><><><><><><><><><><><><><>
           
             ✍️ @BegitimEnawga

@getem
@getem
@getem
👍688🔥2
....አትሳቅ

ጥርስህ ሺ ገዳይ ነው እልፉን ያሳቅቃል
የተኙ ያሸለቡ ልቦችን ያነቃል
በድቅድቅ ጨለማ ብርሀንን ይሰጣል
ገዳይ ነህ አለሜ ስትስቅ ያመኛል
ስለዚ አትሳቅ ጥርስህ ያስፈራኛል
ወሰን የለሽ ገደብ ተነግሮ የማያልቅ
በፈገግታህ መሀል እኔን ከምታሳቅ
አሁንም አሁንም አሁንም አትሳቅ


By
@Hanipia

@getem
@getem
@getem
👍4812🔥3😁1
/ ለምን ጠላሻለሁ/
መቼ ተለወጥኩኝ እንደዛው ነኝ እኔ
ተለዉጧል እርሱ አይደለም እንደ ያኔ፤
እያልሽ የሌለኝን ማንነት አትስጪኝ
ከመሬት አንስተሽ ከሰው አፍ አታውጪኝ፤
ደሞስ መች ሊጨክን ልቤስ ሊደነድን
በሕይወት ሳለሁኝ ከቶ ሳልሆን በድን፤
የኔ የዋነቴን የልቤንም አይተሽ
ዛሬ ምን ሲል ታየሽ ያኔ የሄድሽው ትተሽ፤
እርግጥ ሰው ባጠፋው ፀፀቱ ባይቀርም
ወደሽኝ ቢሆን ኖሮ በኔና አንቺ አይከርም፤
ታዲያ መች እንደዛ ሆኖ ያንቺ ቀረቤታ
ፌዝ አዘል ነበረ የጥርስሽ ፈገግታ፤
ያኔ ማፍቀርን ጠግቤው መፈቀር ቢርበኝ
ያንቺ ልብ በፍቅር መች አምኖ ቀረበኝ፤
አሁን ላይ ጥያቄሽ ለይቅር ከሆነ
ጥፋት እንዳጠፋሽ ልብሽ ይህን ካመነ፤
በሰው ቂም አሊዝም ይቅር ብዬሻለሁ
ዳግም ባልወድሽም ለምን ጠላሻለሁ;
#መሳይ ግርማ

@getem
@getem
@getem
👍5223🔥1😁1
▪️የዛን ቀን▪️

እግሬ አስጠልቶኛል

አንቺ ካለሽበት የዛን ቀን ወስዶኛል።

አይኔን ማይበትን ጠልቻለው ከቶ

የዛን ቀን ከሰዎች ስላየሽ ለይቶ።

ጆሮዬንም ቢሆን አልወደው እኔማ

የዛን ቀን ያንችን ድምፅ መርጦ ስለሰማ።

እውነታው ግን

እግሬና አይኖቼን አልያም ጆሮዬን
         ለመጥላት አስቤ

ካለሽበት ሄዱ አዩሽ ሰሙሽ በሚል
         ምክኒያት አሳብቤ

አጥፍተዋል ብልም እውነታውን ሳስብ  
         ሀሳቤን ሰብስቤ

ለካስ ጉድ የሰራኝ አንቺን መውደዱ ነው
         የዛን ለታ ልቤ።

እናማ

የኔ ላላረግሽ ካጠገቤ ላጣሽ

ልቤ በወደደሽ ሆንኩኝ ሌላን ወቃሽ።

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
👍5018
...........ሳቅሽ.......

ሳቅሽ  ለመተብተብ ብቻ ሚቃጣው
የሸረሪት ድር ነው  ሸማ የማይወጣው
ሳቅሽ
የተንኮል ፈገግታ  የተንኮል ወትብትብ
የዘመን ማዘሎ  ማይቆረጥ ማተብ
ሳቅሽ
የማያልቅ ፈትል  የማይጠፋ እሳት
የሳቅሽ ሚስጥር ነው እሳትን ማስነሳት
     
By kerim

@getem
@getem
@getem
45👍13😁6🔥1
ማስታወቂያ
..................
📲Iphone 15promax

💾Internal Storage:256GB
🔋battery:100%
👌Brand New

💲PRICE-149,999birr

📩 DM @paappii

📞 0922303747
😁29👍10🔥7😱2🤩1
አይ ገላ አባ ወረት

በምናብ ሸራ ላይ ፥ በሐሳቤ ሰሌዳ
በምኞቴ ጓዳ ፥ በፍትወቴ ሜዳ
ውብ ሰውነትሽን፥ አየሁ ተቀይዳ
በስጋ እሳት ላንቃ ፥ በቁም እስር ርዳ።

የአይኖችሽን ጨረር ፥ የከንፈርሽን ማር
የአንገትሽን መርዘም ፥ የእግሮችሽን ማማር
የዳሌሽን ደጀን ፥የሽንጥሽን ጅረት
በስጋዬ አሰስኩት ፥በገላ ዳበስኩት
አወይ ገላ ግፉ፥ አይ ስጋ አባ ወረት

የጉንጭሽ ላይ ስንቡክ ፥ የአንገትሽ ስር ከርቤ
ቀመስኩት ሁሉንም ፥ መች ቀረሁ ተርቤ
የቤትኾቨን ኖታ ፥ የሞዛርት ሙዚቃ
መች ይስተካከላል ፥ ከአንደበትሽ ሲቃ
አወይ ገላ ግፉ ፥ አይ ስጋ አባ ወረት
ይገኝ ይመስለዋል ፥ ለነብስ ህመም ደዌ
አንድ የስጋ መድኅን ፥ አንድ የስጋ ሽረት።

አይጥመኝ ሐር ልብ ፥ ለስላሳ የተባለ
ከሐር ጠጉርሽ በቀር ፥  ከአለንጋ ጣቶችሽ
አላውቅም በአለም ፥ ላይ የተስተካከለ።

ይፈሳል እንደ አዋሽ ፥ ሳቅሽ እንደ መልካው
እጅ እግር አጠረኝ ፥ ነብስሽን በየት ልንካው
ሁሉን ስዳስሰው ፥ ጠጉርሽን ስለብሰው
እንደ ጠበል ጠዲቅ ፥ ከንፈርሽን ስቀምሰው
ጣፋጭ እሳትሽን፥  እንደ ኩዳድ ሳርሰው
ገላን በገላ አቅም ፥ ስትጠግቢኝ ስጠግብሽ
ንገሪኝ አንችዬ ፣
ለዚህ ጥያቄዬ ፥ ምን መለሰ ልብሽ?

አወይ ገላ ግፉ፥ አይ ገላ አባ ወረት
ምኞት ሙሉ ሜዳ ፥ ምኞት ሙሉ በረት

በአፍ እንደወደድሽኝ ፥በአይን እንደዳበሽኝ
መአት ረግረግሽ ውስጥ ፥ያኔ እንዳሰጠምሽኝ
መዘንጋት የማያውቅ ፥ ፍቅሬ እሱን ለግሽኝ
ገል አፈሩ ይቅርብኝ ፥
ገል አፈሩ ይብቃኝ፣
ነብስሽና ነብሴ ሁለቱ ይጣመሩ፥
ፍቅር እንደዚያ እንዲቃኝ።

By ©እስራኤል
(@isrik)

@getem
@getem
@getem
👍3119🔥6
🔥🔥እሳትና ውሀ🌊🌊

የታፈነ ውሀ በብረት ድስት ገብቶ

በጭቆና ሲኖር ነፃነቱን አጥቶ

     ስንት ስቃይ አይቶ
      ታጋሽ ሆኖ ሳለ

አንድ ጉልበተኛ እሳት የተባለ

ብረት ድስቱን ሊያግል እየተቀጣጠለ

ነበልባል ተላብሶ ድንገት ከተፍ አለ::
:
:
ቃጠሎ ንዳዱ ውሀው ሲበዛበት

የስቃዩ ማብቂያ ጊዜው ሲረዝምበት

ትግስቱ ተሟጦ የሚገነፍል ለት

        የእሳቱ ግለት
     ምን ያክል ቢከፋ

የታፈነው ውሀ በምሬት ሲደፋ

ሀያሉም ነበልባል አብሮት ነው ሚጠፋ::


▪️ ነገሮችን በትግዕስት ማለፍ ተገቢ ነው ግን ሁሉም ነገር ገደብ አለው። ይሄ ግጥም ገደብ እንዳለው ላልተረዱ ይድረስልኝ።

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
👍5115🎉4
...ንገረኝ በሞቴ

ንገረኝ በሞቴ ምንህ ይሻለኛል
ዘንድሮን በጠና ሆድ ሆዴን በልቶኛል
ስለዚ ንገረኝ ምንህ ይሻለኛል
እህትህም መሆን ዛሬ አሰኝቶኛል
ፍቅረኛህ እንድሆን ደሞ ተሰምቶኛል
ብቻ እንዳታረገኝ ምስኪኖ እናትህን
በስስት ምታይህ የምትሞትልህን
አንተን ቀና ብለህ ያጎነበሰችን
ውስጣን እየከፋት የሳቀችልህን
ብቻ እንዳታረገኝ ምስኪኖ እናትህን

By
@Hanipia

@getem
@getem
@Hanipiagetem
32👍17👎2😱1
/ይቀጥላል ፍቅር/
ሳላገኝሽ በፊት ሳትሆኚ በቅርቤ
በገሃድም ሳይሆን ሳለሽ በአሳቤ፤
የዛኔ የሆንኩት አንቺን ላገኝ ብዬ
ሙሾ ያስወረደኝ ያስባለኝ እዬዬ፤
ያ ፍቅርሽ ብዙ ጉድ ያሳየኝ
ጊዜው ደርሶ ዛሬ ካንቺ ቢያቆራኘኝ፤
አጣጥሜ በቅጡ ሳልቀምሰው
ልኖር ካንቺ ቤቴን ሳልቀልሰው፤
በጅምሩ በፍቅራችን ንጋት
የመውደድን ፅዋ አብረን ሳንጋት፤
" ዛሬላይ"
እስክረሳው ያንቺ ወደኔ መምጣት
እስክል ድረስ ለምን አፈቀርኳት፤
አርጎኝ የነበረው ላንቺ እንድረታ
ሰከን ያላረገኝ እንዳላስብ ላፍታ፤
የከለለኝ እሱ እንዳላይ ጋርዶብኝ
ፍቅርሽ አይደለም ሆይ ያረገኝ ባንቺሞኝ፤
ግን የሚገርመው የኔ ፅኑ አቋም
ይቀጥላል ፍቅር እንዴት ባንቺ ሊቆም:
#መሳይ ግርማ

@getem
@getem
@getem
👍2414🔥1
አንቺን እንዲያስረሳኝ እግዜርን ለመንኩኝ
ፍቅርሽ እንዲተወኝ ከአላህ ተማፀንኩኝ
እጣኑን ዘቢቡን ልሰዋ ከሰሙኝ
ለዓመት ደጁ ላልቀር ድባቡን ተሳልኩኝ

ግን እያደር ሳየው ናፍቆት ሆድ ሲያስብሰኝ
እግዜር እና አላህን መጠበቅ ሲሳነኝ
የ መርሳት ጉጉቴ ሆድ ሆዴን ቢያባባኝ
በአምላኮች መንገድ ተስፋዬን ቆረጥኩኝ
የእነሱን ቻይነት ሳልጠረጥር ባምንም
የእኔን ስለማውቀው ሚሆን አይመስለኝም

እና የአምላክ ነገር አልሳካ ቢለኝ
ተዋረስኩ ከአጋንንት ትዝታሽ ቢለቀኝ
አንቺን ከረሳሁኝ እንዳሻው እንዲያደርገኝ
ስጋዬን በቀብድ ለሰይጣን አስያዝኩኝ
ይቺ ብኩን ነፍሴን ሲዖል ወረወርኩኝ
ሠይጣን በዓለም እንጂ በፍቅር መች ይፈርዳል ይህም አልሆነልኝ

ስንቱን ልጥቀስልሽ አንዱ እንኳ አልቀረኝ
ሰንደሌን ለኩሼ ጠንቋይም አልተውኩኝ
እንዲያስረሳኝ ብዬ ስንቱን ዶሮ አረድኩኝ
እልፍ አዕላፍ ኡቃቤ ባንቺ ተማፀንኩኝ
ውቅያኖስ ናፍቆትሽን ከጠብታ አርቅቀው
ዓለም ትዝታሽን ከሀገር አሳንሰው
ያንቺን መውደድ ክብደት አቅለው ቢያሳዩኝ
እኔም እውነት መስሎኝ "አሜን" ልርሳት አልጉኝ

ወራት ቢቆጠሩ ቀናቶች ቢነጉዱ ፈገግ ስል ቢያዩኝ
"ከራማችን ፈርዷል ስለትህን አስገባ ረስተሃታል" አሉኝ
የናፍቆትሽን ፀባይ የፍቅርሽን አመል እኔ መች አጣሁኝ
ይኸው ትናንትና ድምፅሽን ብሰማ ዳግም ተነሣብኝ

                   ዘረ-ሠናይ
           @Prince_Zeresenay

@getem
@getem
@paappii
53👍23🤩4🔥3
.....ስድስት እና ስድስት

ተገጣጠሙና ወርና አመታት
ስድስት የጥላቻ ስድስቱ የናፍቆት
ማልቀስ ሳይቀር ማንባት
መቁሰል ነበር መድማት
እነዛን አመታት
ዛሬ ተቀይሮ አመታት በወር ላይ
አልውልም ትላለህ አይኖችሽን ሳላይ
የልቤ ደረሰ አንተን ሰጠኝ ከላይ
ወደድከኝ አለሜ ህይወትን ሠጠኸኝ
እሠየው አበጀህ እንካን አፈቀርከኝ
ስድስቱን አመታት በስድስት ወር ካስከኝ

4/8/2016
By
@Hanipia

@getem
@Hanipiagetem
@getem
21👍16
#ለፈገግታ 😂

😍አፍቃሪው😘

ሚበላ በገንዘብ መግዛቱ ሲከብደኝ
           ኑሮ ጣራ ነክቶ

ባፌ እንደዚህ አልኩ ልቤ አንድ ነገር
          ድንገት ተመኝቶ።

'' ምናለ እንደድል

ባገኝ እንደነሱ የኔ ማቶንን ሴት
       የማፍቀሩን እድል

እሷን ካላገባው እህል ባፌ አይዞርም
     ከቶ አልበለም እንድል
።''

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
😁51👍398🤩3
ቤት ማንም ሳይኖር ብቻዬን ሳለሁኝ
ስራ ጨራርሼ ፋታ እንዳገኘሁኝ
ትንሽ መለስ ብዬ ትናንቴን ለማየት
ያለፈው ዘመኔን ጥቂት ለመጎብኘት
የትዝታን መዝገብ ጀመርኩኝ መቃኘት።

እልፍ ደስታ ንፁህ ፍቅር 
ሀሜት የለ እዛው ንግር
የጨዋታው ለዛ ጥርስ የማያስከድን
ልጅነት ይመስገን ያ መልካም ዘመን።

ደሞ እሱ አልፎ ታድጎ ተጎርምሶ
በንፁ ልቤ ላይ አለማወቅ ነግሶ
መልካም ስሜ ሆኖ ከግብሬ ወርጄ
ይሉኝታን ገድዬ ንቀትን ወልጄ
ታዘብኩት እራሴን ወደኋላ ሂጄ።

By ሳምሪ የዝኑ ልጅ

@getem
@getem
@paappii
🔥5029👍21🤩4
ናፍቀሽኛል

ጊዜ ይሮጣል አሉ

ጊዜ ይበራል አሉ

አንደዚ በማለት ሚያወራ ሰው ሁሉ

ምናለ ቢያስረዱኝ ይህንን ከቻሉ
:
:
ለኔ ጊዜው አይሮጥም

በፍፁም አይበርም

እንደው ይባስ ብሎ መቁጠሩንም ትቷል

ካንቺ ከራቅኩ ወዲህ ቀኑ አመት ሆኗል

እናም ርዝማኔው አሁንስ ከብዶኛል

የውነቴን ነው ምልሽ በጣም ናፍቀሽኛል
:
:
ሀልጊዜም ቢሆን አንቺን ነው ማስብሽ

ከራሴ በላይ ነው እኔ የምወድሽ

በደስታ ቆዪልኝ በአካል እስካገኝሽ::


፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

           ✍️ @BegitimEnawga

@getem
@getem
@getem
👍4733😁4👎2🤩2
ከርግቦች ትራስ ስር
(አሌክስ አብርሃም)

የላባን መከዳ አምነህ አትመቻች
ቂም በቀል ነው ከታች!
የመስዋዕት አንገት አግኝቶ እስኪመዘዝ
አንዳች የሚወገር አንዳች የሚወገዝ
"ከርግቦች" ትራስ ስር የዛገ ሰይፍ አለ
በፍቅር እየማለ!
ማነህ ባለሳምንት ማነህ ባለዝክር
ተሰልፏል ከሳሽ ተሰብቋል ምስክር
ብቻ እጣ ይውጣብህ ልክም ሁን ስህተት
አንተን ሞረድ አርጎ የተረሳው ሁሉ ይነቃል ከዝገት!

@getem
@getem
@paappii
31👍20🔥5