ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ወደድኩሽ .....ጅል እስክሆን
ሄድሽ ደሞ .......ያንን ሰሞን
አንቺዬ
የተነሳሽበት ማልደርስበት መንገድ
ናፍቆትሽን ይዤ ዘላለም ል'ራመድ
ከበደኝ
ቀድሞውንስ መች ቀለለኝ።

ታድያ ይሄን እየሰማሽ
እንደምን ነህ አልሺኝ
እኔማ...
አለው እንደምንም ምንም ባለመሆን
ታውቂው የለ አፍቃሪን ያፈቀረ ሰሞን
አንዲያ ነኝ....

አዎን
የናፍቆቴን መራብ ትውስታ ላይገታው
ዝምብዬ ምኳትን ህመሜን ላይረታው
መጣው ስላልሺኝ ነው አሁንም ምበረታው።
አንቺዬ
ውዬ አድሪያለው እና እስክትመጪ በፆም
ባክሽ ብቅ በዪ እስትንፋሴ እንዳትቆም።

✍️#በረከት_ሐ(@berii34)
@getem
@getem
@getem
👍4122👎5
በይ.አኩርፊ💜
#በረከት_ሐ
የፈገግታሽ አለም ቢኖረውም እውነት
መሳቅ ብቻ አይደለም የሁሉ ሰው ውበት።

አንቺዬ
ሳቅሽንም ተይው ጥርስሽም ይ'ከደን
ድንገት አኩርፊ እና ጉድ ይበል ይህ ዘመን።

#በረከት_ሐ
(
@berii34)
@getem
@getem
@getem
👍2911
በይ.አኩርፊ💜
#በረከት_ሐ
የፈገግታሽ አለም ቢኖረውም እውነት
መሳቅ ብቻ አይደለም የሁሉ ሰው ውበት።

አንቺዬ
ሳቅሽንም ተይው ጥርስሽም ይ'ከደን
ድንገት አኩርፊ እና ጉድ ይበል ይህ ዘመን።

#በረከት_ሐ
(
@berii34)
@getem
@getem
@getem
16👍16
የፍቅርን እንባ የመውደድን እንባ በሳቅሽ አነባው
ፈገግታሽን ልስል ከአፀድሽ ገባው።

አንቺ
አፀድ አለሽ ህይወት የሚዘራ
ህይወት አለሽ አፍቃሪን ሚጠራ..

አጀብ አጀብ ነው ፈገግታሽ
ፈውስ አለሽ አሉ በፍቅር ለነካሽ
... አጀብ

#በረከት_ሐ
(@berii34)

@getem
@getem
@getem
👍179🤩2
ልብህ ከታወረ ......ፅልመት ከወረሰው
እንደምን ቆጠርከው እራስህን እንደሰው?
እንደምን?
እንደማን?
ሰው መሆን ከባድ ነው መሸንገል ህሊናን ።
ይልቅ
ከጠቆረው ቤትህ ሰው መሆንን አስስ
አልያም ከቻልክበት መኖሪያህን አፍርስ
ወዳጄ
የነገሩን ሁሉ ሀቅ እርቆታል ከእውነት አይዋደድ
ዘር......... ከእህል እንጂ ........ከሰው አይዛመድ
ታድያ
ከዚህ ...እግዜሩን ከረሳ ከባከነ ዘመን
ያዩልህን ሳይሆን ያየኸውን እመን
በል ንቃ
በል አሁን ውጣ ጫጫታውን ትተህ
ብራንህን ፈልግ ሽንቁር አበጃጅተህ
በል አሁን ተነስ
ስንኩል ልብህን አቅና
ሰው መምሰል አደለም ሰው መሆን ነው ደህና
             ይቅናህ.....።

               #በረከት_ሐ
(@berii34)
@getem
@getem
@getem
👍4419
.
ናፍቆት ያለ ፍቅር
ገጣሚ ያለ ብእር ፣ እንደምን ይውላሉ
ባንዳች ነገር ታስረው እስከተፈጠሩ።

አየሽ
እንዲያ ነበርን እኛ፣ ምንም ያልጎደለን
አንዳች ነገር ቀልሞ ፣ አንድ ለይ የሳለን
አንድ ለይ ያዋለን።

ደግሞም እንደ ንፋስ ፣ ባህር ውቅያኖሱን
ተራራ እና የብሱን ፣ ነፍሰን እንዳላለፍነው
በነበር እንዲቀር ፣ እግዜር አስኪፅፈው።

እንቺዬ
እንዴት ነበርን ብልሽ
ምን ይሆን ግን መልስሽ?።

እንዳልተዋደድን ፣ እንዳልተፋቀርን
በእግዜርሽ ፣ በሞቴ እንዳልተማማልን
እንዴት ግማሽ ጣዖት
እንዴት ግማሽ ጽላት ሆንን?።
እንዴት?....

#በረከት_ሐ
(@berii34)
@getem
@getem
@getem
👍28😢3🔥2😱2😁1
ረሀብ አምጦት ፣ ማጣት የወለደው
ከሐበሻ ሰማይ ስር ፣ ለቅሶ በዛ ምነው?
ጩኸት በዛ ፣ ረሀብ እና እንባ
ክፋትም አየለ ፣ ቅናት እና ደባ።
እግዜሩም ዝም አለ
ተማፅኖን ዝም አለ ፣ ወይ አይሰጠን ፍቅር
ምስኪኑ አለቀሰ ፣ ከጥቁር ሰማይ ስር።
አስኪ ጠይቋቸው
እስኪ ጠይቋቸው ፣ የጦቢያዬን ልጆች
ዳቦ ሚለምኑ እነዛን ፣ ውብ አይኖች
እንደምን ውለዋል ፣ እንደምን አድረዋል
የዛሬን ባያውቁም ፣ ትናንት አልቅሰዋል።
ነገስ?

                               #በረከት_ሐ
                  (@berii34)
@getem
@getem
@getem
👍38😢1110👎3
"እንቆቅልሽ ፣ ምን አው...ህ/ሽ"

ሰከን ያለ ልብ ፣ በለሆሳስ ሚጓዝ
ደግሞም
ፀጥ ያለች ነብስ ፣ ወደራስ የምትፈስ
ሁካታን የጠላች ፣ ጫጫታን የቀጣች
ከዚህ ሁሉ ፍጡር ፣ ፍጥረት ላለመባል ብቻዋን የከሳች ፣ ብቻዋን የወዛች።
ሁሉን የምታክል ፣ ሁሉን የምትስል
በፊደል ምትደማ ፣ በቃል የምትቆስል
ከውብ ግጥሞች ስንኝ ፣ አንዷን የምትመስል::
ማንናት ?
ማነች ?
በራስ ክራር ስልቷ ትዝታን የቃኘች...
ማነች ?
       ካላወቃቹ እንግዲህ ሀገር ስጡኝ...

                  
#በረከት_ሐ
@getem (@berii34)
@getem
@getem
👍3112👎1🔥1
ቃሉዋን ይዤ ድንገት
ትንሽ ትንሽ እምነት ፣ ያሳየዋት ሰሞን
እቀፈኝ አለችኝ ፣ ከእቅፌ ለመሆን።
አቀፍኳት
ልክ እንደ ወዳጅ እንደ ጓደኛ
አሷ ግን
እንደመውደድ እንደ ፍቅረኛ።
እቅፍ ፣ ጥምጥም ፣ ጋደም አለች
ደግሞም ቀና ብላ ፣ አይኖቼን እያየች
             ትወደኛለህ ብትለኝ
             ቃል አጣው ጨነቀኝ
እኔ...
እኔ...ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ ምን ልበላት ?


                                      #በረከት_ሐ (@berii34)
@getem
@getem
@getem
31👍15👎4😁4
መንገድ ይወስዳል
መንገድ ይመልሳል ብለው ያሉኝ ጊዜ
ጉዞዬን ጀመርኩኝ የያዝኩትን ይዤ።
                             ሁዋላ  
ደ.ከ.መ.ኝ
መ.ረ.ረ.ኝ
አ.ቃ.ተ.ኝ...
ጫፍ የለውም መንገድ  ፣ እስከመች ልጓዘው
ምን ነበር ቀድሞውንስ ፣ ልብን ያፈዘዘው።
ልመለስ ብል እንኳ
ልመለስ ብል እንኳ ፣ እልፍ መንገዶች ታዩኝ
የትኛው ነበረ ይመልሳል ያሉኝ?

                   #በረከት_ሐ ( @berii34 )
@getem
@getem
@getem
👍5534👎4
እድሜ እያላላኝ ፡
ግዜ እየቀጣኝ
ብሸራረፍ እንኳን ፡
አረሳውም መልኳን።
እጇን ...
ትናንት ይመስላል የዳበስኩት፣
መጠበቅ አርቆኝ ያስተዋልኩት።
ደሞ..
የናፈኳት ሰሞን
አመት ቅፅበት ሲሆን
ግዜ ሚዛኑ ሲላወስ
አብራው ምታዘግም የኔ ነብስ
ትታያለች........ደጇን እንዳጠረች...።💔

                            #በረከት_ሐ ( @berii34 )
@getem
@getem
@getem
40👍36😱4🔥3👎1🎉1
ማንነቴን  ባልኩኝ
ቀለሜ ነው ባልኩኝ የእምዬን ሰንደቅ
                 ዛሬ
ለምን ያዝክ ተብዬ ለነብሴ ልሳቀቅ።

ልጠይቅ ሀገሬ ጠይቂ ለምን በይ
ላንቺ መኖራችን
ላንቺ መሞታችን ብኩንነት ነው ወይ?

ቢገባቸው እንጂ
ቢመሰላቸው እንጂ
ቃላት የማይወጣን
ታድያ ለምንድነው
ቀና ባልን ቁጥር ጥይት የማያጣን?!

ለምን በይ ሀገሬ!!!

                                          #በረከት_ሐ( @berii34 )
@getem
@getem
@getem
🔥39👍25👎1
ፍቅር ፡ ያልነካካው
ናፍቆት ፡ ያላቦካው
ንፁ ልብ እንዳለኝ
አሎዳትም እላለሁ ፡ መሄዷ እያመመኝ።

አልወዳትም !!

#በረከት_ሐ(ይሉ) @berii34

@getem
@getem
@getem
🔥2814👍13😢3
ግዜ ጓዙን ጥሎ ፡ ሲያዘግም ተገኘ
አልመሽ ላለላት ፡ ነብስ ጥፋተኛ ሆኖ ፍርድ ቤት ተዳኘ
ፈራጅ እግዜር ነበር ፡ እግዜር ፈራጅ ነበር
ከሳሽም ያቺው ነፍስ ፡ ምስክርም አላት
ሲመሽ እንደምታልፍ ፡ ማን በነገራት።

#በረከት_ሐ(ይሉ) @berii34

@getem
@getem
@getem
33👍13😢6🔥5
.      .ለሷ
ከግጥሞቼ መሀል ፡ አንዱን አበደርኳት
''ናፍቆት'' ከሚል እርስ ፡ ጨምሬ ደገምኳት
                                .  ግን እሷ
ግጥም ፡ ምን ግዷ
ስዕል ፡ ምን ግዷ
ሙዚቃ ፡ ምን ግዷ
ፀጥጥጥ ያለ ፡ ባህር ነው  
ልቦናና ነብሷ።  
                      .    እሷ

         #በረከት_ሐ(ይሉ) @berii34

@getem
@getem
@paappii
21👍9🤩3