ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ስረቅ!
ንጠቅ!
ዝረፍ!
ግረፍ!

ክፉ ሀሳብ
ነፍሴን ሊቀጭ ውስጤን ሲያምስ፣
#ስዕልሽ ፊት
ላፍታ ብቆም ጥፋት እብስ!

ተንኮል ወሮኝ
ቅጥፈት ባህር ሊዘፍቀኝ ሲል፣
#ተአምርሽን
ድንገት ባስብ ጋኔል ቅጥል!

እርጉም ሀሴት
ሊያሳፍሰኝ ከሴት ጭን ስር፣
እርኩስ ስሜት በደል ሲጭር፤
#ውዳሴሽን
ገልጬ ባይ ሰይጣን እርር!

ውድቀት ጠርቶኝ
ክፋት አንቆኝ በኃጢአት ስዋጥ፣
#ማር_ስምሽን
ልክ ስጠራ ዲያቢሎስ ላጥ!

ኃጢአት ጦሩን
ሲሰድ ሰብቆ በጥላቻ፣
#ጋሻዬ ነሽ
#ድንግል_ማርያም
ያጋንንትን መርዝ መግቻ።

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@paappii
71👍25🤩4
ህመም አንቆኝ
ደዌ አስሮኝ
ዘመናትን ካልጋ ሸንኮር ተጣብቄ
ፈውስ ስሽት በእርጉም መንገድ ተዘፍቄ
ሚያውቁኝ ሁሉ ስሄድ በእግሬ ድኜ ቢያዩ
በምን ተአምር ህመሙ ጋር ተለያዩ
ይላሉ

ጽልመት ውጦኝ
ብርሃን ናፍቆኝ
ጨለማ ስር ተሸጉጬ ስንደፈደፍ
ንጋት ርቆኝ በቁራጭ ጧፍ ድቅድቅ ልገፍ
ስውተረተር
ስፍጨረጨር
ሚያውቁኝ ሁሉ ድንገት ቢያዩ ገጼ አብርቶ
በምን አስማት ተሞልቶ ነው ሚታይ ፈክቶ
ይላሉ

ውድቀት አቅፎኝ
ቁልቁል ደፍቆኝ
የትም ጎሬ ተወትፌ እንባ ስጭር
ደስታ ሸሽቶኝ ሐዘን ስኩል በሞት ስንጥር
ሚያውቁኝ ሁሉ ዐይናቸው ቢያይ ማቄ ወልቆ
ምን ጉድ ዳብሶት ንቃት ጠራው ማጣት ፍቆ
ይላሉ

ቢገባቸው
ቅድስት ሀኪም ነፍስን ፈዋሽ
መድኃኒት ልጅ ለዓለም ለጋሽ
ድንግል ፀሐይ ጽልመት ገፊ
ብርሃን አምላክ ወልዶ አቃፊ
ማርያም ትንፋሽ ሞት ጠራጊ
ከሀሊ ጌታን ሰው አድራጊ

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
23👍17🔥4🎉1🤩1