#እኔ_እራሴን_የሆንኩኝ_ለት
፡
፡
፡
እኔ እራሴን አይደለሁም፣
እያለውኝ ግን የለሁም።
አጉል ጉራን ስቸረችር
ማልበገር ሲመስላቸው፣
በሆዴ ውስጥ ብዬ አውቃለው
ባረገልኝ እንደ አፋቸው።
ክንብንቤን ገፈው ጥለው
ማንነቴን ቢያስተውሉ፣
የኔስ ሕይወት ድብብቆሽ
ከራሴው ጋር አኩኩሉ።
፡
፡
አንደበቴም አንድ ብሎ
ዋሾነትን ከለመደ፣
ፍቅር ልቤን ስልብ አድርጎት
እሩቅ ትቶኝ ከነጎደ፣
እምጥ ሰዶ ተንሰራፍቶ
ናፍቆት ሥሩን ከዘረጋ፣
ውሸት ጉራን እየነዛው
ስንቴ መሽቶ ስንቴ ነጋ።
፡
፡
ለሰው እንጂ ማስመሰሌ
ዳሩ ለኔ ምን ፋይዳ አለው፣
ባደባባይ የሚቃጣኝ
ጀግና ኩሩ ልብ እንዳለው።
ድንቄም ኩሩ ድንቄም ጀግና፣
ለነገሩ ማን አውቆብኝ
እኔ እራሴን መች ሆንኩና።
፡
፡
እውነቱማ
ቁርሾ ዘልቆ መሀላችን
ስንራራቅ ስንለያይ፣
ካንጀት ፈልቆ የሚፈሰው
ሳቄም ሆኗል ካንገት በላይ።
እህል ውሀው አራቀኝም
ሆዴም ጠግቧል ልቤ እርቦት፣
በሞላ ሰው አንቺን ይላል
ጀሌ ጅጊ አጀብ ከቦት።
ትከሻዬ ምን ቢሰፋ
መንፈሴ ግን ተሰበረ፣
ትዝታሽም ከጫንቃዬ
እንደ ቋጥኝ ተከመረ።
ለነገሩ ምን ፋይዳ አለው፣
መች ለማለው መች ሰማለው፣
እኔ እራሴን እኮ አይደለው።
፣
፣
ወደ ራሴው ተመልሼ፣
ማስመሰሌን ከቀበርኩት
ላያዳግም መሬት ምሼ፣
እውነት እውነት፣
እኔ ራሴን የሆንኩኝ ለት፣
እሺታሽም ታክሎበት፣
ድሪቶውን ወዲያ ጥዬ
ሀቁን ላንቺው ብናገረው፣
የፍቅራችን ዳግም ውልደት
ያኔ ነበር ሚከበረው።
፡
፡
ለነገሩ ምን ሊጠቅም፣
አልናገር አልጋገር
እኔ እራሴን ሆኜ አላውቅም።
#ሄኖክ_ብርሃኑ (@yeneeyita)
@yeneeyita
@getem
@getem
@getem
፡
፡
፡
እኔ እራሴን አይደለሁም፣
እያለውኝ ግን የለሁም።
አጉል ጉራን ስቸረችር
ማልበገር ሲመስላቸው፣
በሆዴ ውስጥ ብዬ አውቃለው
ባረገልኝ እንደ አፋቸው።
ክንብንቤን ገፈው ጥለው
ማንነቴን ቢያስተውሉ፣
የኔስ ሕይወት ድብብቆሽ
ከራሴው ጋር አኩኩሉ።
፡
፡
አንደበቴም አንድ ብሎ
ዋሾነትን ከለመደ፣
ፍቅር ልቤን ስልብ አድርጎት
እሩቅ ትቶኝ ከነጎደ፣
እምጥ ሰዶ ተንሰራፍቶ
ናፍቆት ሥሩን ከዘረጋ፣
ውሸት ጉራን እየነዛው
ስንቴ መሽቶ ስንቴ ነጋ።
፡
፡
ለሰው እንጂ ማስመሰሌ
ዳሩ ለኔ ምን ፋይዳ አለው፣
ባደባባይ የሚቃጣኝ
ጀግና ኩሩ ልብ እንዳለው።
ድንቄም ኩሩ ድንቄም ጀግና፣
ለነገሩ ማን አውቆብኝ
እኔ እራሴን መች ሆንኩና።
፡
፡
እውነቱማ
ቁርሾ ዘልቆ መሀላችን
ስንራራቅ ስንለያይ፣
ካንጀት ፈልቆ የሚፈሰው
ሳቄም ሆኗል ካንገት በላይ።
እህል ውሀው አራቀኝም
ሆዴም ጠግቧል ልቤ እርቦት፣
በሞላ ሰው አንቺን ይላል
ጀሌ ጅጊ አጀብ ከቦት።
ትከሻዬ ምን ቢሰፋ
መንፈሴ ግን ተሰበረ፣
ትዝታሽም ከጫንቃዬ
እንደ ቋጥኝ ተከመረ።
ለነገሩ ምን ፋይዳ አለው፣
መች ለማለው መች ሰማለው፣
እኔ እራሴን እኮ አይደለው።
፣
፣
ወደ ራሴው ተመልሼ፣
ማስመሰሌን ከቀበርኩት
ላያዳግም መሬት ምሼ፣
እውነት እውነት፣
እኔ ራሴን የሆንኩኝ ለት፣
እሺታሽም ታክሎበት፣
ድሪቶውን ወዲያ ጥዬ
ሀቁን ላንቺው ብናገረው፣
የፍቅራችን ዳግም ውልደት
ያኔ ነበር ሚከበረው።
፡
፡
ለነገሩ ምን ሊጠቅም፣
አልናገር አልጋገር
እኔ እራሴን ሆኜ አላውቅም።
#ሄኖክ_ብርሃኑ (@yeneeyita)
@yeneeyita
@getem
@getem
@getem
👍58❤9😱8🔥1
#የታል?
፡
፡
፡
ፈጣሪ ጥበቡን ሊያሳይ ውብ አርጎ ስለፈጠራት፤
መሬት አይንካኝ እያለች ይመሻል ቀኑ እያጠራት።
ኩራት ልቧን ወድሯት ምድር አንሷት ይመስል፤
አግዝፋው የራሷን ምስል፤
በመልኳ ስትጓደደው ያዙኝ ልቀቁኝ እያለች፤
ካንጀቴ ታስቀኛለች።
፡
፡
የፈጣሪ እደ ጥበብ የውበት ዳር የታየበት፤
ፍፁም ገላ ፍፁም ውበት፤
እግዜር ሰጥቷት ተላብሳለች፤
በራሷ አይል እሷ ለሷ አንዳች ቅጥል ምን አርጋለች?
፡
፡
ዓይኗን ሰራች?
ጥርሷን ሰራች?
ወይ ከንፈሯን?
ደም ግባቷን?
ወይስ መላ ሰውነቷን?
የፈጠራት በጥበቡ ቸሯት እንጂ ውብ ቁንጅና፤
ለማማሯ ለውበቷ ተጫውታለች አንዳች ሚና?
፡
፡
ካካላቷ ለሚታየው ለሰፈረው ውብ ታንጽኦ፤
የቱኛው ነው የሷ ድርሻ ያኖረችው አስተዋጽኦ?
ምንም የለም ካለም የታል?
ባልፈጠረው ሰው ሲጎበር ጭንቅላቱን ያስገምታል።
ንገሯት!
#ሄኖክ_ብርሃኑ (@yeneeyita)
@yeneeyita
@getem
@getem
@getem
፡
፡
፡
ፈጣሪ ጥበቡን ሊያሳይ ውብ አርጎ ስለፈጠራት፤
መሬት አይንካኝ እያለች ይመሻል ቀኑ እያጠራት።
ኩራት ልቧን ወድሯት ምድር አንሷት ይመስል፤
አግዝፋው የራሷን ምስል፤
በመልኳ ስትጓደደው ያዙኝ ልቀቁኝ እያለች፤
ካንጀቴ ታስቀኛለች።
፡
፡
የፈጣሪ እደ ጥበብ የውበት ዳር የታየበት፤
ፍፁም ገላ ፍፁም ውበት፤
እግዜር ሰጥቷት ተላብሳለች፤
በራሷ አይል እሷ ለሷ አንዳች ቅጥል ምን አርጋለች?
፡
፡
ዓይኗን ሰራች?
ጥርሷን ሰራች?
ወይ ከንፈሯን?
ደም ግባቷን?
ወይስ መላ ሰውነቷን?
የፈጠራት በጥበቡ ቸሯት እንጂ ውብ ቁንጅና፤
ለማማሯ ለውበቷ ተጫውታለች አንዳች ሚና?
፡
፡
ካካላቷ ለሚታየው ለሰፈረው ውብ ታንጽኦ፤
የቱኛው ነው የሷ ድርሻ ያኖረችው አስተዋጽኦ?
ምንም የለም ካለም የታል?
ባልፈጠረው ሰው ሲጎበር ጭንቅላቱን ያስገምታል።
ንገሯት!
#ሄኖክ_ብርሃኑ (@yeneeyita)
@yeneeyita
@getem
@getem
@getem
👍32❤22🤩8🔥4😢2