ለውብ ቀን!
💚
///ህዳር ሆይ///
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
አደይ አበባዬን...
ከመስቀል ወፍ ጋራ አንድ ላይ ጠቅልዬ
መስከረምን ተውኩት
ለእንቁጣጣሽ ብዬ ለመስቀል ነው ብዬ
ጥቅምትም አበባየማር የእሸት ወዙ
ጸጋውን ተፈጥሮ የሰጠው በብዙ
ህዳር ወር ነው የኔ ህዳር ህዳር ህዳር
የወራቶች ንጉሥ
የኔ ብቻ ፅደይ የኔ ብቻ መኽር
ህዳር ህዳር ህዳር
ከሰው ተሰውረን ካድባር ቅየው ጠፍተን
እኔና እሷ ብቻ እኔና እሷ ሆነን
ዞማ ፅጉሯ መሃል አበባ ሰክቼ
እርብትብት ከንፈሯን ጉንጮቿን ነክቼ
እኔና እሷ ብቻ እኔና እሷ ሆነን
አሁን አሁን አሁን
ህዳር ህዳር ህዳር
ከለምለሙ ሜዳ ከዛፎች ጥላ ስር
ፍቅር ስናወራ ፍቅር ስንዘምር
በጀርባችን ሆነን መሬት ላይ ተኝተን
ጨፌ ተንተርሰን በጤዛ ረስርሰን
በንብ ዜማ ዘመን ቢራቢሮ ይዘን
ህዳር ህዳር ህዳር
አሻግረን እያየን ጽንፍ የለሹን ሰማይ
እጄ ከወገቧ አንገቷ ክንዴ ላይ
ዝንት አለም አንድ ሆነን መቼም ላንለያይ
ከአይኖቻችን መሃል አይኖቻችንን ስናይ
ህዳር ህዳር ህዳር
ደግሞ እንደልጅነትሽ አባሮሽ ጨዋታ
በድንገት ስትሮጥ ከሜዳ ተነስታ
ለስለስ ያለው ንፋስ
ቀሚሷን አንስቶ ሸሚዟን ከፋፍቶ
ገላ ስር መአዛ ያንገቷ ስር ሽቶ
እኔነቴን ሲያውድ ከንፋስ ተጋብቶ
ልይዛት ስነሳ ላባርራት ስሮጥ
ሳር ሃረጉ ጠልፏት መሬት ላይ ስትቀመጥ
ባየር ተንሳፍፌ ቀዝፌ ስይዛት
መያዙ ሳይበቃኝ ደግሞ አጥብቄ ሳቅፋት
ማቀፍ ሳያጠግበኝ ከንፈሯን ስስማት
ትንፋሽ እያጠራት
ሲቃው እያነቃት ደስታ እያሳበዳት
ዐይኖቿን ጨፍና አንገቴ ስር ገብታ
ያን ቀን ቀኑ ሲመሽ ያን ቀን ወደ ማታ
ብቻዋን የሆነች ጨረቃዋ ቀንታ
ህዳር ህዳር ህዳር
ፍቅር ከሆነች ጋር በፍቅር ስንሰክር
የቀኑ ሳይበቃን በለሊት ስንዞር
ማንም አያክላት ምንም የላት አቻ
ከሷ ጋር ሆኜ ከሷ ጋራ ብቻ
እግዜሩ ደስ ብሎት
አምሳለ መላእክትን እርግቦችን ልኮ
ዜማ እየወረደ ቀድሶና ባርኮ
ደግሞ ሌላ ህይወት ደግሞ ሌላ ዘመን
ደግሞ ሌላ ዓለም ደግሞ ሌላ ሆነን
ምሳሌ እንድንሆን ፍቅር እንዲፅና
ደጋግመህ ደጋግመህ ህዳር ሆይ ቶሎ ና!!!
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
(በሰለሞን ሣህለ)
#እስቲ ግጥሟ ደስ ስለምትል በድምፅ እንሞክራት
@getem
@getem
@balmbaras
💚
///ህዳር ሆይ///
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
አደይ አበባዬን...
ከመስቀል ወፍ ጋራ አንድ ላይ ጠቅልዬ
መስከረምን ተውኩት
ለእንቁጣጣሽ ብዬ ለመስቀል ነው ብዬ
ጥቅምትም አበባየማር የእሸት ወዙ
ጸጋውን ተፈጥሮ የሰጠው በብዙ
ህዳር ወር ነው የኔ ህዳር ህዳር ህዳር
የወራቶች ንጉሥ
የኔ ብቻ ፅደይ የኔ ብቻ መኽር
ህዳር ህዳር ህዳር
ከሰው ተሰውረን ካድባር ቅየው ጠፍተን
እኔና እሷ ብቻ እኔና እሷ ሆነን
ዞማ ፅጉሯ መሃል አበባ ሰክቼ
እርብትብት ከንፈሯን ጉንጮቿን ነክቼ
እኔና እሷ ብቻ እኔና እሷ ሆነን
አሁን አሁን አሁን
ህዳር ህዳር ህዳር
ከለምለሙ ሜዳ ከዛፎች ጥላ ስር
ፍቅር ስናወራ ፍቅር ስንዘምር
በጀርባችን ሆነን መሬት ላይ ተኝተን
ጨፌ ተንተርሰን በጤዛ ረስርሰን
በንብ ዜማ ዘመን ቢራቢሮ ይዘን
ህዳር ህዳር ህዳር
አሻግረን እያየን ጽንፍ የለሹን ሰማይ
እጄ ከወገቧ አንገቷ ክንዴ ላይ
ዝንት አለም አንድ ሆነን መቼም ላንለያይ
ከአይኖቻችን መሃል አይኖቻችንን ስናይ
ህዳር ህዳር ህዳር
ደግሞ እንደልጅነትሽ አባሮሽ ጨዋታ
በድንገት ስትሮጥ ከሜዳ ተነስታ
ለስለስ ያለው ንፋስ
ቀሚሷን አንስቶ ሸሚዟን ከፋፍቶ
ገላ ስር መአዛ ያንገቷ ስር ሽቶ
እኔነቴን ሲያውድ ከንፋስ ተጋብቶ
ልይዛት ስነሳ ላባርራት ስሮጥ
ሳር ሃረጉ ጠልፏት መሬት ላይ ስትቀመጥ
ባየር ተንሳፍፌ ቀዝፌ ስይዛት
መያዙ ሳይበቃኝ ደግሞ አጥብቄ ሳቅፋት
ማቀፍ ሳያጠግበኝ ከንፈሯን ስስማት
ትንፋሽ እያጠራት
ሲቃው እያነቃት ደስታ እያሳበዳት
ዐይኖቿን ጨፍና አንገቴ ስር ገብታ
ያን ቀን ቀኑ ሲመሽ ያን ቀን ወደ ማታ
ብቻዋን የሆነች ጨረቃዋ ቀንታ
ህዳር ህዳር ህዳር
ፍቅር ከሆነች ጋር በፍቅር ስንሰክር
የቀኑ ሳይበቃን በለሊት ስንዞር
ማንም አያክላት ምንም የላት አቻ
ከሷ ጋር ሆኜ ከሷ ጋራ ብቻ
እግዜሩ ደስ ብሎት
አምሳለ መላእክትን እርግቦችን ልኮ
ዜማ እየወረደ ቀድሶና ባርኮ
ደግሞ ሌላ ህይወት ደግሞ ሌላ ዘመን
ደግሞ ሌላ ዓለም ደግሞ ሌላ ሆነን
ምሳሌ እንድንሆን ፍቅር እንዲፅና
ደጋግመህ ደጋግመህ ህዳር ሆይ ቶሎ ና!!!
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
(በሰለሞን ሣህለ)
#እስቲ ግጥሟ ደስ ስለምትል በድምፅ እንሞክራት
@getem
@getem
@balmbaras
አወራሽ ይመስል
ቁርጥ ቁርጥ
ይላል ቃሌ ከስልኬ ሲሰፍር
አያድርስ ነው አቦ
ይጃጃሉትም የል ወንድ ልጅ ሲያፈቅር
ቁርጤን እንዳላውቀው እያዘላበድሽኝ
ወይ እሺ
ወይ እንቢ የሚል ቃል ሳይወጣሽ
ድንገት አሳበድሽኝ
ጨርቅ መጣል ቀረኝ
የገላዬን ሽፋን
እኔና ይህ ቀልቤ
በትግል ተላፋን
ሰው እንዴት ከግሉ
ሰው እንዴት ከውሉ
ይላፋዋል ትግል
እሺ በይኝና ለክብርሽ ላገልግል።
ህይወት አይሉት ወይ ሞት
ቃሉ ተምታቶብኝ የአገባብ ፍቺው
በይ አሳይኝ አንቺው
ከአፍሽ ላይ ቃል ይውጣ እየተሯሯጠ
እቋቋመዋለሁ ወንድ ልጅ ቆረጠ
ቆርጫለሁና በምታወጪው ቃል
እሺታን ማን ያውቃል
እንቢታን ማን ያውቃል
#እስቲ_እንተዋወቅ!
ከንደገና መለስ
ወደኋላ ቀለስ
አሁን ለጠየኩሽ አይጠፋም 1 መልስ።
እውነቴን ነው ምልሽ
የበላኝን መዳፍ ደጋግሜ ሳከው
አገኘኋት ይላል ባንቺ የታወከው
ግራዬን
ወይ
ቀኜን....አላስታውሰውም
ብቻ ያዝኩሽ ይላል ባይታወቅ አንድምታው
ባይን ብቻ ፍቅር
ቀርቤ ሳላውቅሽ እንዴት ነው ምረታው
እንደ ፈሪ ዱላ መተንኮሶ ነው ልምዱ
መጣው ይላል አይንሽ እግሮችሽ ሲሄዱ
ቻው ይለኛል ጀርባሽ ሄዶ በዛው ሊቀር
እንዲህ ነው ሚያደርገው ሰው በሰው ሲፈቀር
ኩራት ጥግብ
ጅንን
እንደ እትጌ መነን........
እስቲ እንተዋወቅ!
ሳላውቅሽ ነው እንግዲ
እንቢታን ምጠይቅ እሺታን ምለምን
ሳይተዋወቁ ይቻላል እንደምን?
መብላቴን ሳላውቀው ታጥቤ የቀረብኩት
እኔው ነኝ እንግዳሽ ወጤን የረገጥኩት
የራሴን መስመር ልክ ላንቺ ላንዷ ብዬ የተተላለፍኩት።
አልጨረስኩም!
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
ቁርጥ ቁርጥ
ይላል ቃሌ ከስልኬ ሲሰፍር
አያድርስ ነው አቦ
ይጃጃሉትም የል ወንድ ልጅ ሲያፈቅር
ቁርጤን እንዳላውቀው እያዘላበድሽኝ
ወይ እሺ
ወይ እንቢ የሚል ቃል ሳይወጣሽ
ድንገት አሳበድሽኝ
ጨርቅ መጣል ቀረኝ
የገላዬን ሽፋን
እኔና ይህ ቀልቤ
በትግል ተላፋን
ሰው እንዴት ከግሉ
ሰው እንዴት ከውሉ
ይላፋዋል ትግል
እሺ በይኝና ለክብርሽ ላገልግል።
ህይወት አይሉት ወይ ሞት
ቃሉ ተምታቶብኝ የአገባብ ፍቺው
በይ አሳይኝ አንቺው
ከአፍሽ ላይ ቃል ይውጣ እየተሯሯጠ
እቋቋመዋለሁ ወንድ ልጅ ቆረጠ
ቆርጫለሁና በምታወጪው ቃል
እሺታን ማን ያውቃል
እንቢታን ማን ያውቃል
#እስቲ_እንተዋወቅ!
ከንደገና መለስ
ወደኋላ ቀለስ
አሁን ለጠየኩሽ አይጠፋም 1 መልስ።
እውነቴን ነው ምልሽ
የበላኝን መዳፍ ደጋግሜ ሳከው
አገኘኋት ይላል ባንቺ የታወከው
ግራዬን
ወይ
ቀኜን....አላስታውሰውም
ብቻ ያዝኩሽ ይላል ባይታወቅ አንድምታው
ባይን ብቻ ፍቅር
ቀርቤ ሳላውቅሽ እንዴት ነው ምረታው
እንደ ፈሪ ዱላ መተንኮሶ ነው ልምዱ
መጣው ይላል አይንሽ እግሮችሽ ሲሄዱ
ቻው ይለኛል ጀርባሽ ሄዶ በዛው ሊቀር
እንዲህ ነው ሚያደርገው ሰው በሰው ሲፈቀር
ኩራት ጥግብ
ጅንን
እንደ እትጌ መነን........
እስቲ እንተዋወቅ!
ሳላውቅሽ ነው እንግዲ
እንቢታን ምጠይቅ እሺታን ምለምን
ሳይተዋወቁ ይቻላል እንደምን?
መብላቴን ሳላውቀው ታጥቤ የቀረብኩት
እኔው ነኝ እንግዳሽ ወጤን የረገጥኩት
የራሴን መስመር ልክ ላንቺ ላንዷ ብዬ የተተላለፍኩት።
አልጨረስኩም!
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
👍45❤15😱1