ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
--- ኤሊነት ----
-----
ያምረኛል አንዳንዴ
ማቀረቅር ለታ
አርምሞ ጽማዌ
ማስተዋል እርጋታ
ትዕግስት ያደለበው
ቻይ የድንጋይ ኩታ
የኤሊ ተፈጥሮ የኤሊ ዝግታ
ከራስ ስር መደበቅ
ከራስ ጋር ጨዋታ....

ያምረኛል አንዳንዴ
ከዘመን መዘግየት
ስከንፍ የሚጠፋኝ
መሻቴን ለማግኘት
ከአለት መሰንቆ
ነጻነት ዜማዬን ዳግም ለመቃኘት
ኤሊነት ተፈጥሮን
ከራስ ለማዋሐድ
ከራስ ለማስቀረት...

ያምረኛል አንዳንዴ
ያምረኛል አንዳንዴ
ዝግ እያሉ ኑሮ
ቀስ እያሉ ህይወት
.... ግን እየበረረ
ለሚያሳሳኝ እድሜ
ልጓም ከየት ላምጣለት ?
:
እንዲየውም የእውነታ
መዝገቡ ሲከፈት
አለማወቁ ነው የሰው ትልቅ ድክመት
እንዴት እንዲስማሙ
ንግግር ከአርምሞ
ጊዜ ከ ሰውነት..

@getem
@getem
@paappii

#Kiyorna (Dagmawi)
👍417🔥3😢1
====+========

የወደዱኝ "ጣፋጭ
ውብ የማር ዘለላ ፤"..
የጠሉኝ "ከንቱ ሬት
ከራራ መራራ"
እያሉ ሲሰፍሩኝ ሚዛን ባደላበት
የሰውነት ጎራ...

እንዲ እመልሳለሁ

እኔ በእኔነቴ...
መርሬ ጣፍጬ ቆምጥጬም አላውቅም
ውሀ ነው ፍጥረቴ
ጣዕም ቀለም ውበት
አንድም የሉበትም
:
የአብሮነትን ጽዋ
ከልቤ ተጋርተው መኖር ሲያሻቸው ግን
ሁሉም የቀመሱት በንጹህ አካሌ የጨመሩበትን !

#kiyorna

@getem
@getem
@getem
👍3913