ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ከሚላ
የት እንደምንደርስ ባይገኝም ተንባይ
ፍቅራችን ግልፅ ነው በአፅኖት ለሚያይ።
ትናንት...
  ብዙ ገጥሚያለው
  ብዙንም ፅፌያለው ስለመለያየት
ሕልሜ እየተናደ አንቺ የሔድሽ 'ለት
ምስክር ስትሰጠኝ ባብሮነት ጊዜያችን
ዛሬ ቃሏን ሽራ ብትል አንድ ያልነበርን
ጨረቃን ታዘብኳት።
ብዬ እንኳን ቢገባት
እጅ ለእጅ ተያይዘን እንደደመቅንባት
ብዙውን ባዋያት፤
ግን አንዱም አልገባት።
ቃል እንደጠፋበት ጀማሪ ገጣሚ...
እኔ አልኩኝ እንጂ
አልኩኝ ገባኝ ገባኝ
እንኳንስ ያልገባኝ
የገባኝ መች ገባኝ
ያልገባኝ ሲገባኝ
የገባኝ መች ገባኝ
እያልኩ አወራለው
የገባኝን ቅኔ ባልገባኝ ሽራለው።
ሐዘን ውስጤን ሰብሮት ተንኮታኩቶ ልቤ
ሀሳብ ሲያዋልለኝ ስነጠቅ ከቀልቤ
የሆንኩኝ መሰለኝ የረከስኩ ቆርቤ።
አንቺን በማጣቴ...
ለወራቶች በርተሽ ላ'መት ብትጠፊ
ከህልሜ ባነንኩኝ እንደመታኝ ጥፊ።
መምጣትሽን ሳስብ...
ፍቅራችን ተጥሶ በጥላቻ ማዕበል
መለየት ሲዳኘን ልባችን ለየቅል
ሆኖ እያደረ፤
መድረሻችን ታውቆ በሩቅ ታይቶ ቀረ።
ግና ይሄ ሁሉ የትናንት ታሪክ ነው።
የጥላቻ አምድ!!!!!
በልዩነት መሀል ፍቅራችን የሚነድ
ዛሬ.....ነገር ተቀይሯል
የፍቅራችን ማህተም ቅሩ ተጎንጉኗል
በመምጣትሽ ፋና ውስጤ ተጠግኗል።
መራራቅ የዳኘው ሰባራው ልባችን የተንኮታኮተው
በእውነተኛ ስሜት ፍቅርን...ማደሪያ አደረገው።
እልሽ እንደነበር...
   ታግሶ ለኖረ ጊዜ መልስ ይሰጣል
  ህመም የትም ቢገኝ ሳቅ ግን ያስከፍላል።
  እጁን ካ'ፋ ገቶ
በለሱን ያቆየ ፍሬዋን ይበላል።
እልሽ እንደነበር...
  የፃፈ በሙሉ ገጣሚ ካይደለ
  ጦር ሜዳ ያለ ሁሉ ጀግናን አይወክልም፤
  የወደደሽ ሁሉ አፍቃሪሽ አይደለም።
ግን አንተስ ብትዪኝ...
   መሔድ አንድ ስም ነው፤
   አጠገቤ ሆነሽ ትናፍቂኛለሽ...እናፍቅሻለው።
  ባፈቀርኩሽ ዘዬ ቃላት አልከሽንም
  ከሌላ አኑሬሽ በሌላ አልመዝንም።
አሁን ግን...
ከልቤ ፅላት ላይ ስያሜ ተፅፏል።
የፍቅርሽ ክያኔ ማንነቴን ገዝቷል።
በማይገልፅሽ ቃላት ሰኝቼሽ ከሚላ
ከ'ቅፌ ስለሆንሽ አልታትርም ሌላ።

#ሊዮ_ማክ
#ባሌ_ጎባ
ተፃፈ፦04/02/2013ዓ.ም

@getem
@getem
@getem
👍327🔥1🎉1
____
የእድሜ ጀንበር
#ገጣሚ_ሊዮ_ማክ
🦋🦋🦋🦋
#ባሌ_ጎባ
@getem
@getem
@getem
👍115🤩1
ኑረት
የተፈጥሮ መገብርሽ
ህላዌያዊ ጡዘትሽ
በእኩሌታዊ እውነታ
እስትንፋስን ለዘራበት
መኖሩ ቢዳኝ በሽረት
ተዘሎ ወጣ ከኑረት።
ላየው...
ለኖረው...
ወለልሽ ጉድጓድ
በደከመው ላይ የሚናድ
ተስፋ ቢስ ጭላንጭል
ላ'ፍታ ከድካም የሚያስጠልል
ቅንጣት ቢታጣ
ያርምሽ ጀመር በብሂል
"ህይወት ብርቱ ሰልፍ ናት"
የ'ፎይታ ዳስ መዳረሻ የሌለባት፤
ሲል ይሰማል በትዝብት
ሰርክ እየሮጠ ያለ እረፍት።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡።።።\\\////።።።።።።
ገጣሚ፦ሊዮ ማክ
#ባሌ_ጎባ

@getem
@getem
@getem
👍285🤩1