--- ኤሊነት ----
-----
ያምረኛል አንዳንዴ
ማቀረቅር ለታ
አርምሞ ጽማዌ
ማስተዋል እርጋታ
ትዕግስት ያደለበው
ቻይ የድንጋይ ኩታ
የኤሊ ተፈጥሮ የኤሊ ዝግታ
ከራስ ስር መደበቅ
ከራስ ጋር ጨዋታ....
ያምረኛል አንዳንዴ
ከዘመን መዘግየት
ስከንፍ የሚጠፋኝ
መሻቴን ለማግኘት
ከአለት መሰንቆ
ነጻነት ዜማዬን ዳግም ለመቃኘት
ኤሊነት ተፈጥሮን
ከራስ ለማዋሐድ
ከራስ ለማስቀረት...
ያምረኛል አንዳንዴ
ያምረኛል አንዳንዴ
ዝግ እያሉ ኑሮ
ቀስ እያሉ ህይወት
.... ግን እየበረረ
ለሚያሳሳኝ እድሜ
ልጓም ከየት ላምጣለት ?
:
እንዲየውም የእውነታ
መዝገቡ ሲከፈት
አለማወቁ ነው የሰው ትልቅ ድክመት
እንዴት እንዲስማሙ
ንግግር ከአርምሞ
ጊዜ ከ ሰውነት..
@getem
@getem
@paappii
#Kiyorna (Dagmawi)
-----
ያምረኛል አንዳንዴ
ማቀረቅር ለታ
አርምሞ ጽማዌ
ማስተዋል እርጋታ
ትዕግስት ያደለበው
ቻይ የድንጋይ ኩታ
የኤሊ ተፈጥሮ የኤሊ ዝግታ
ከራስ ስር መደበቅ
ከራስ ጋር ጨዋታ....
ያምረኛል አንዳንዴ
ከዘመን መዘግየት
ስከንፍ የሚጠፋኝ
መሻቴን ለማግኘት
ከአለት መሰንቆ
ነጻነት ዜማዬን ዳግም ለመቃኘት
ኤሊነት ተፈጥሮን
ከራስ ለማዋሐድ
ከራስ ለማስቀረት...
ያምረኛል አንዳንዴ
ያምረኛል አንዳንዴ
ዝግ እያሉ ኑሮ
ቀስ እያሉ ህይወት
.... ግን እየበረረ
ለሚያሳሳኝ እድሜ
ልጓም ከየት ላምጣለት ?
:
እንዲየውም የእውነታ
መዝገቡ ሲከፈት
አለማወቁ ነው የሰው ትልቅ ድክመት
እንዴት እንዲስማሙ
ንግግር ከአርምሞ
ጊዜ ከ ሰውነት..
@getem
@getem
@paappii
#Kiyorna (Dagmawi)
👍41❤7🔥3😢1