ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
‹‹አንድ ጥይት መቀነስ›› የኪነ
ጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

የኢፌዲሪ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን ከተስፋ ፊልም
ፕሮዳክሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና በተፈጥሮ፣ በዘመንና የሰው ልጆች
ግንኙነትና መስተጋብር ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገው ‹‹አንድ ጥይት መቀነስ››
የተሰኘ የኪነ-ጥበብ ምሽት የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 10፡30 ጀምሮ በብሄራዊ
ቴአትር ይካሄዳል፡፡
በዝግጅቱ ላይ #ደራሲና ሀያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ ሥነ-ጽሑፍና ተፈጥሮ፣
#የሙዚቃ ባለሙያ ሰርፀ ፍሬ ስብሃት ሙዚቃና ተፈጥሮ፣# ሀኪም አበበች
ሽፈራው የባህል ሕክምናና እፅዋት፣ #ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ኢስላምና
ተፈጥሮ፣ #ፕ/ር ሽብሩ ተድላ ደግሞ በእንስሳት ዙሪያ፣ #ደራሲ አለማየሁ ዋሴ
(ዶ/ር) ቤተ ክርስቲያንና ተፈጥሮ፣ #ፕ/ር ታደሰ ደሴ ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ
አለማት በእንስሳትና በእጽዋት አያያዝና ተሞክሯቸው ዙሪያ በሚል
ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን #ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም፣ #ደራሲና ጋዜጠኛ
ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ #ፕ/ር ሰብስቤ ደምሴ፣ በተመሳሳይ ርዕስ ስራዎቻቸውን
ያቀርባሉ ተብሏል፡፡
#ገጣሚ ረድኤት ተረፈና ገጣሚ #ተዋናይ ተፈሪ አለሙ ግጥሞቻቸውን የሚያነቡ
ሲሆን፣ ‹‹አንድ ጥይት መቀነስ›› የተሰኘ የ15 ደቂቃ አጭር ተውኔት
እንደሚቀርብም አዘጋጆቹ ገልጸዋል::

@getem
@balmbaras
#ገጣሚ#ፀሃፊ_ተውኔት#መምህርና #የሥነ_ፅሁፍ ተመራማሪ #ደበበ_ሰይፉ #ረቂቅ ግጥሞች መካከል ኣንዷ:
.
#ተይው_እንተወው
.
ተይው እንተወው
የዘመን ቃፊሩን
ማለፍ ኣልቻልንና
ይህ ዓለም ጥበቱ አልመጠነንና
ተይው እንተወው
ውጥኑ ግብ ይሁን
ጅማሬው ፍፃሜ
ቅፅበቷ ሙሉ እድሜሽ
ወቅቷ ዘላለሜ
ተይው እንተወው ።
.
#ደበበ_ሠይፉ

@getem
@getem
#alex_yih
1
​​፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨

(((እኔም #ገጣሚ_ነኝ)))

ስሙኝ.......
እኔም #ገጣሚ_ነኝ!
በሶሻል ሚዲያ
ስሜ ያልተጠራ
ብዙም ያልታወኩኝ....
በደሳሳ ጎጆ
ህልሜን ያጠበብኩኝ
እኔም #ገጣሚ_ነኝ!
*
*
*
ከምሁራን ተርታ
ፈፅሞ ያልተሰለፍኩ
ከእውቅ ፀሀፊያን
መሀል ያልተካተትኩ
እኔም #ደራሲ_ነኝ!
በሰላች ብእሬ
ስሜቴን የገለፅኩ
*
*
ነገር ግን......
እንደነ እንትና
እስካርፕ አልጠመጠምኩ
እንደ ሀያሲያን
ሸሚዝ በከረባት
ታጥቄ አለበስኩ
በአምስቱ ጣቶቼ
የእከሌን መፅሀፍ
ይዤ አልተሽከረከርኩ....
በሄድኩበት ሁሉ
#ደራሲ_ነኝ እኔ
እውቅ ነው ሀሳቤ
ብዬም አልተናዘዝኩ.....
*
*
.........ግናም እፅፋለሁ........
ብእር ከወረቀት
እያዋደድኳቸው
ለሰው የማይገባ
ዝብርቅርቅ ሀሳባት
እኔም አፈሳለሁ ...
በሀሳቤ አርግዤው
ለአእላፉ ቀናት
እያብሰለሰልኩት
ይዤው እከርማለሁ...
የቁርጥ ቀን መቶ
እስክገላገለው
ወረቀት ከብእር
እስከማጋጥመው
ብዙ አምጣለሁ...
ያማጥኩት ተባርኮ
በመድብል ሲወለድ
ማየትን እሻለሁ..
*
*
እና እንደሌሎቹ.....
#እኔም_ገጣሚ ነኝ!
ብዬ አልዘባርቅም...
የገጠምኩት #ግጥም
የደረስኩት ድርሰት
የከሌ ነው ታሪክ ነው
ብዬ አልናገርም...
*
*
እውነቱ ገብቷቸው
አንተ #ደራሲ_ነክ
የሰዎችን እውነት
በብእር የገለፅክ
ብለው እስኪረዱኝ
በቤቴ የምኖር
እኔም #ገጣሚ_ነኝ!

ተፃፈ በ @Mak_bale
ግንቦት 1,2012

@getem
@getem
@getem
#ገጣሚ_ሰለሞን_ሳህለ

#ያችን_ልጅ_ንገርዋት

እኔ ቃል ጨረስኩኝ ያችን ልጅ ንገርዋት
ልከ እንዳገሩ ነዉ የሚወድሽ በሉዋት
አወ እንዳገሬ ነዉ…
እንደ ምንጩ ጣእም እንደ አፈሩ ሽታ
ልጎንጭሽ የምላት…
ልዳብስሽ የምላት ጠዋትና ማታ
ለብሻት የምኖር…
እንደ ቀዩ ጃኖ እንደ ነጩ ኩታ
ጋቢዋ ነኝ እኔ…
ጠላት የተኮሰዉ ንፋስ እንዳይነካት
ሁለት ግዜ ዙሬ…
ወገቡዋ ላይ ያደርኩ የማርያም መቀነት
እንደ አገር አርጅታ…
እንደ አገር አዉግታ ደግሞ ተበሳጭታ
እድሜዉ ይሁን ንዴት ጸጉርዋን አሸብታ
አፋፉ ላይ ቁማ…ብቻዋን ቆዝማ
ድንገት ብታገኝዋት…
እኔ ቃል ጨረስኩኝ ያችን ልጅ ንገርዋት
ልክ እንዳገሩ ነዉ የሚወድሽ በልዋት
ንገሩልኝ ዘመድ ንገሩልኝ ወገን
እኔ በሱዋ ፍቅር እንዴት እንደምሆን
እንደተዋለበት ጤናዉን እንዳጣ
በጠላ አስተናግር በጥብጦ እንደጠጣ
ያስለፈልፈኛል ጩህ ጩህ ያሰኘኛል
የቀኑ ሳይበቃዉ ሌሊት ያስዞረኛል
ጎርፉን እጠጣለሁ አፈር እቅማለሁ
ጎርፉን እየጠጣሁ….ሃገሬን እላለሁ
ጨለጥኩዋት እላለሁ
አፈሩን እየቃምኩ….ሃገሬን እላለሁ
በላሁዋት እላለሁ
ጸጉሬን እነጫለሁ ልብሴን እቀዳለሁ
እንዳይሆን እንዳይሆን እንዳይሆን ሁኛለሁ
እናም ያች የኔ…
የምጠብቃት ሴት የመጣች እንደሆን
መስከረምን አልፋ…
ጥቅምትን ተሸግራ ህዳሩ ሲታጠን
ገላየ ቆሽሾ አካላቴ ዝሎ
ገጼ ተጎሳቅሎ
ድንገት አልፋኝ ብትሄድ…
ፍቅሬ ተዘንግትዋት…
ማንነቴ ጠፍትዋት…
እኔ ቃል ጨረስኩኝ ያችን ልጅ ንገርዋት
እንዳገሩ ነበር የሚወድሽ በልዋ
.
.
@getem
@getem
👍3
የአፍቃሪ ምኞት
------------------------
ሲከፍህ አልወድም እኔን ይከፋኛል
አፍቃሪህ ነኝ እና ህመምህ ያመኛል
ለአንድ ደቃቃ እንኳን ፈገግታ እንዳርቅህ
ሀዘን ካንተ ይራቅ እኔ ልዘንልህ
እንደፈለክ ቦርቅ ሁልጊዜ ተዝናና
እኔ ላንተ ደስታ መስዋዕት ነኝና
ምንም እንኳን ባትሆን ዛሬ ላይ ከጎኔ
ባለህበት ሆነህ ደስ ይበልህ ሁሌ
ይሄንን ነው ላንተ የምመኘው ፍቅሬ
.

#ገጣሚ Lidu

@getem
@getem
@getem
👍2
#የሕይወት_ድርሰት

የሕይወቴን ድርሰት አበለሻሺቼ
ከምድር ከሰማይ ከሁለቱም አጥቼ
ይሄው እኖራለሁ ዛሬም ድረስ ሞቼ።


ዛሬ ግን በእምነት ብዕሬን አንስቼ
የተበላሸውን ድርሰቴን አጥፍቼ

የጥበብ ብረሃና ከፍቴ ዘርግቼ
ሌላ እደርሳለሁ ምኞቴን ገትቼ።


#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
በ14/01/2013

@getem
@getem
@getem
👍3
#አፍቃሪ_ያሳጣሽ

ካለሽ ውበት በላይ አምረሽ ተኳኩለሽ
ከቤት ስትወጪ እንደ ፀሀይ ደመቀሽ

በምቴጂው መንገድ.....
ከአንድ አንቺ በስተቀር ሰዎች አይኑሩበት
አንቺን የማይነካም ወጥመድ ይዙርበት።

ተወለጋገጂ ስተሄጅ በመንገዱም
ማንም አይመኝሽ ለወዳጅ ዘመዱም።

ያርግሽ ነገረኛ ከሰው አትስማሚ
ለምመለከትሽ ምሰይ ታማሚ።

ብቻ......
የኔ ሰሞነኛ የዘወትር ፀሎቴ
ይህ ነው አለሜ ውዳሴ ዳዊቴ።

ምክኒያቱም አለሜ ስስቴ ሁነሻል
እልቤ ማሳ ላይ ውብ ፍቅር ዘርተሻል።



ብቻ........
በይ እስኪ እወቂ የልቤን ውስጥ እውነት
በፍቅርሽ ደክሜ እንዳጣሁኝ ገሉበት
አንቺን ለማግኘት ስል እንደገባሁ ስለት

አንቺን እያሰብኩም ከቤተ መቅደሱ
አሀዱ እንዳሉ መስቀል ይዘው ቄሱ።

ብቻ......
የዘወትር ፀሎቴ ውዳሴ ዳዊቴ
አፍቃሪ ያሳጣሽ የሚል ነው ስስቴ።

አዎ አለሜዋ የኔ ሁሉ ነገር
አፍቃሪ ያሳጣሽ ከአንድ እኔ በስተቀር።

#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
30/12/2013 #ገቺ

@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho
----Edited----
#አፍቃሪ_ያሳጣሽ

ካለሽ ውበት በላይ አምረሽ ተኳኩለሽ
ከቤት ስትወጪ እንደ ፀሀይ ደመቀሽ

በምቴጂው መንገድ.....
ከአንድ አንቺ በስተቀር ሰዎች አይኑሩበት
አንቺን የማይነካም ወጥመድ ይዙርበት።

ተወለጋገጂ ስተሄጅ በመንገዱም
ማንም አይመኝሽ ለወዳጅ ዘመዱም።

ያርግሽ ነገረኛ ከሰው አትስማሚ
ለምመለከትሽ ምሰይ ታማሚ።

ብቻ......
የኔ ሰሞነኛ የዘወትር ፀሎቴ
ይህ ነው አለሜ ውዳሴ ዳዊቴ።

ምክኒያቱም አለሜ ስስቴ ሁነሻል
እልቤ ማሳ ላይ ውብ ፍቅር ዘርተሻል።



ብቻ........
በይ እስኪ እወቂ የልቤን ውስጥ እውነት
በፍቅርሽ ደክሜ እንዳጣሁኝ ገሉበት
አንቺን ለማግኘት ስል እንደገባሁ ስለት

አንቺን እያሰብኩም ከቤተ መቅደሱ
አሀዱ እንዳሉ መስቀል ይዘው ቄሱ።

ብቻ......
የዘወትር ፀሎቴ ውዳሴ ዳዊቴ
አፍቃሪ ያሳጣሽ የሚል ነው ስስቴ።

አዎ አለሜዋ የኔ ሁሉ ነገር
አፍቃሪ ያሳጣሽ ከአንድ እኔ በስተቀር።

#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
30/12/2013 ገቺ

@getem
@getem
@getem
👍31
#አንዳንዴ ...

የሕይወት ውጥንቅጥ ባንተ ላይ ሲደፋ
እርምጃህ ተገቶ ስትቆም ያለ ተስፋ

እንኳን መኖር ቀርቶ ስቆ በፈገግታ
መስማት ያዳግታል ዝም ያለን ዝምታ።

#አይዞን

#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ

@getem
@getem
@getem
👍4
👍121👎1
____
የእድሜ ጀንበር
#ገጣሚ_ሊዮ_ማክ
🦋🦋🦋🦋
#ባሌ_ጎባ
@getem
@getem
@getem
👍115🤩1