ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#አንዳንዴ

ያሳወረህ ጠላት
ምርኩዝህን ነጥቆህ የድንገት ይሞታል።

#ደሞም_አንዳንድዜ
ከትንሽ መካከል
አብይ ሃሳብ ያለው መሪም ይከሰታል

Ezana Mesfin

@getem
@getem
#አንዳንዴ...

አንዳንዴ...
እንዲህ ያደርገኛል...
ጀንበር በወጣችበት
ቀን ይጨልምብኛል፣
ሰውን ማየት...
ጠልቼ ያነጫንጨኛል፣
ትኩሳቴ ግሎ
ሳያመኝ.......ያመኛል፣
አንዳንዴም...
እንዲህ እሆናለሁ...
አጫዋች ፍለጋ
ባ'ይኔ እቃብዛለሁ፣
በወይን ስካር ውስጥ
ሳቅ....እናፍቃለሁ፣
የኑሮ ሸክም ላቀል
ማሰብ...አቆማለሁ፣
አንዳንድ...
ጊዜ ደግሞ...
ሐሳቤ...
መጪውን አልሞ፣
ተስፋ ያሳየኛል
ከፊቴ......አቁሞ፣
ይኸው እስከዛሬ...
ባ'ንዳንድ አጋጣሚ
ሰውን.....እጠላለሁ፣
ባ'ንዳንድ አጋጣሚ
ሰው.....እናፍቃለሁ፣
ባ'ንዳንዴዎች ውዬ
አምሽቼ...አድራለሁ፣
ባ'ያሌው በብዙ...
አንዳንዴዎች ተስፋ፣
ዛሬን እኖራለሁ...
አንዳንድ ቀን ስገፋ !!!

#ሀብታሙ_ወዳጅ
@getem
@getem
@kaleab_1888
👍1
#አንዳንዴ ...

የሕይወት ውጥንቅጥ ባንተ ላይ ሲደፋ
እርምጃህ ተገቶ ስትቆም ያለ ተስፋ

እንኳን መኖር ቀርቶ ስቆ በፈገግታ
መስማት ያዳግታል ዝም ያለን ዝምታ።

#አይዞን

#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ

@getem
@getem
@getem
👍4