ግጥም ብቻ 📘
66.5K subscribers
1.54K photos
31 videos
61 files
175 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ስብዕናችን #Humanity:
🙏🙏እጅግ ከልብ እናመሰግናለን ብዙ ሰው ተሳትፏል 😁አብዛኛዎቹ ተመሳሳይ ናቸው በዚህ ምድር ፍትህ የለም ፍትህ ያለው በሰማይ ቤት የሚል ድምዳሜ ያላቸው ሰዎች በዝተውብናል.....አንዳንዶቹን ሞግተናቸዋል አሁን ከተላኩልን መርጠን (የሁላችሁንም ማቅረብ ስለማንችል) አንድ አራቱን እንያቸው.....



እኔ የምምነውን ከሆነ የምትጠይቀኝ ፍትህ የሚባል ነገር የለም። ተፈጥሮ ለፍትህ ግድ በማይሰጣቸው የራሷ ህግጋት ነው የምትንቀሳቀሰው፣እውርና አንዳንዴም ጨካኝ ናት። እንስሳም ሆን እኛ የተፈጥሮ ጉማጅ ነን፤ይህን ህግ ብናለዝበውም አይፋታንም። ከእንስሳ ፍትህ ትጠብቃለህ? አሳብ እንድንጋራ ከሆነ ግን ፍትህን (justice) በተለያየ ጊዜ የተለያየ ትርጓሜና መልክ ስንሰጣት ኖረናል። ሃይማኖተኛ ከሆንክ ትክክለኛ (justly-served) ፍትህን በሰማይ ለመጠበቅ ትገደዳለህ። ሙሴ ደግሞ አይን ያጠፋ አይኑ ይጥፋ ሲል ምድራዊ ፍትህን ማስፈኑ ነበር፤ነገር ግን አንድ ሰው በስህተት ወይም በድንገት የሰው አይን ቢያጠፋና መልሶ የእሱ እንዲጠፋ ቢደረግ ፍትህ ሊባል ነው? በስህተት ይሁን ሆን ብሎ እንዳጠፋስ ማነው የሚመሰክረው? አየህ እኩል ዋጋ ቢከፈል እንኳን ፍትሃዊ (just-act) ሊባል አይችልም። ዘመናዊው አለም ደሞ እንዳልከው ፍርድ ቤት ያቋቋመው ፍትህን ለማስፈን ነው። ነገር ግን አሁንም በማስረጃ፣መረጃ፣ምስክርና እንዲሁም በጉቦና መሰል ጉዳዮች ሳቢያ ነገሩ ግቡን አልመታም። እንደው ለነገሩ አስራ ሶስት ሰው አርዶ የገደለ ሰው እድሜ ልክ ቢታሰር ወይም ቢገደል ፍትህ ሊሆን ነው? የሟች ቤተሰቦችስ ተካሱ? ሰማይ ቤት ቢሆን አስራ ሶስት ጊዜ እየገደለ እያነሳ ያካክስ ይሆናል፤ለዛም ነው ብዙው ሰው ፍትህን ከላይ የሚጠብቀው። በነዚህ የሃይማኖትና አለማዊ ተቋማት የእንስሳን አለምን በጥቂቱ አሻሻልነው እንጂ ፍትህ በቃሉ ሙሉነት ደረጃ ለዘለአለም የሚተገበር አይደለም። ማካካሻ (compensation)፣እኩልነት (equality) ምናምን እያልክ ነው ፍትህን የምታካክሰው።




"* ፍትህ ምንድነው ?
ሰው ፍትህ እፈልጋለሁ ሲል ምን ማለቱ ነው ?

* ፍትህ የምትገኘው ከእውነት ነው ? ወይስ ከማስረጃ ?
አይታችሁ እንደሆን ዓለምላይ በጠቅላላ የፍትህ መገኛ ናቸው የሚባሉት ፍርድቤቶች እውነት ይዘህ ብትከራከር ማስረጃ ከሌለህ ፍትህ የለም ይሉሀል ? ቆይ እሺ ፍትህ እውነት ኳልሆነ ምንድን ነው ?" የሚለውን ጥያቄህን እንደ ሀሳብ የማስበውን ላጋራህ..


በመጀመርያ ፍትህ ምንድነው ለሚለው ብዙ ትርጓሜዎች እንዲሁም የተለያዩ ነገሮችን ማተት ይቻላል እንደኔ በኔው መዝገበ ቃላት ፍትህ ማለት እኩልነት ነው ብዬ አስባለሁ ይህ ማለት ግን እኩልነት ማለት ፍትህ ነው እያልኩህ አይደለም ምክንያቱም እኩልነት ሁሉንም ሰው እኩል treat ማረግ ነው ፍትህ ግን ሁሉንም ሰው እኩል ሳይሆን ፍትሀዊ በሆነ መንገድ treat ማረግ ነው ስለዚህ እንደኔ ...ፍትህ የግድ ሀቅ አይደለም እውነት እንነጋገር ከተባለ ፍትህ በዚህ አለም ፈፅሞ የለም ደሞም በአንድ በኩል አለ ብንል ራሱ ፍፅምና የለውም ከተግባር የተለየ ስም ብቻ አቅፎ የያዘ ነው ... ፍጽምና ከሌለው ደሞ አንጻራዊ ነው ማለት ነው!!..ምክንያቱም ወዳጄ ፍትህ ማለት እኮ የህሊና ፍርድ ነው ሁላችንንም የሚይዘን የሚዳኘን እራሳችን ለራሳችን ነው በአለም ባይኖርም ባንቀበለውም በህሊናችን ውስጥ ያለ ነገር ነው ልባችን እያወቀ ነው ምንክደው ህሊና ፍፁም ፍትህ ያለበት የፍርድ መድረክ ነው!..የሰው ደካማ ጎን ይሁን አይሁን ባላቅም ፍትህ የሚለው ነገር ይከብደናል..

ወደ እውነት ከመግባታችን በፊት እውነት ምንድነው ብለን ስናይ..
"እውነት እርቃኗን በባዶው መራመድ ይችላል ውሸት ግን ሁል ጊዜ አምሮና ደምቆ መልበስ ይፈልጋል" የሚባለው አነጋገር በደንብ እውነትን ይገልፃል ብዬ አስባለሁ..

ብዙ ጊዜ ሰዎች ፍትህና ትክክለኛነትን ያምታቱታል...አንድ ነገር እውነት ሳይሆን ትክክለኛ ሊባል ይችላል ይህ ነው Exeptionu conversely ግን ትክክለኛ ሳይሆን እውነት ሊባል አይችልም! reasoning ደግሞ የእውነተኝነት መፈለጊያ መሣሪያም አይደል ስለዚህ ትክክለኝነት የምንለው የሆነ ነገር የሆነበት እይታ ነው ወይም መንገድ ነው።

ሰው ፍትህ እፈልጋለሁ ሲል ምን ማለቱ ነው ላልከው

ይሄ ማለት አንድን ሰው ከአንድ ሰው የምንዳኝበት ሚዛናዊ መንገድ ማለት ሳይሆን እውነትነቱን ምናልባትም ያለ ማስረጃ አምኖ የህሊና ሚዛን እንጂ በህግ የተመረኮዘ ፍትህ አይደለም ይህ ሰው ሚጠይቀው ብዬ አምናለሁ (its ma opinion )..



በነገራችን ላይ ስለ እውነት even በፍልስፍናው አለም ሶስት ሀሳብ አለ.. ምናልባትም በነፊሮ..ሶቅራጠስ..ሱፊስቶች..ፕሎቶ..አርስቶትል..etc በምንላቸው መሠረትም
፩, እውነት አለ #ፍጹማዊም ነው
፪, እውነት አለ ግን #አንፃራዊ ነው
፫, እውነት ብሎ ነገር የለም የመሳሰሉት ሀሳቦች አሉ እንደ አጠቃላይ...

ፍትህ የሚገኘው ከማስረጃ ነው ከእውነት የሚለውን ጥያቄህን ለመመለስ ፍትህን ለሁለት ከፍዬ አየዋለሁ
1.የህግ ፍትህ
2.የህሊና ፍትህ

የህግ ፍትህ በማስረጃ ላይ የተመሠረተ እውነትን ይቀበላል

የህሊና ፍትህ ደሞ አንድና አንድ እውነት ላይ የተመረኮዘ ፍትህን ይቀበላል

...ታድያ አለም በየትኛው እየተመራች ትገኛለች ብለህ ብትጠይቀኝ ምመልስልህ የህግን ፍትህ ነው አሁን ላይ አለምን በጣቱ የያዛትና ሚያሽከረክራት..ፍርድ ቤትም በአለም ስር ነውና በመረጃ የተደገፈን እውነትን እንደሚጠቀም አንዘንጋው ነገር ግን መረጃ ከሌለን እውነታችን እውነት አይደለም በአለም መነፅር ..ሰው መሆናችን እንዳለ ሆኖ..

አሁን ለምሳሌ አንድ ሰውዬ አንዲት ሴትን አስገድዶ ቢደፍራት ና ይህቺ ሴት ደሞ ባለትዳር የነበረች ሴት ብትሆን ማለትም ድንግል ባትሆን መደፈሯን ያየ ማንም ሰው ባይኖርም በህክምናው መደፈር አለመደፈሯ ይረጋገጣል ...ያሰው ግን እሱ ስለመሆኑ ስላለመሆኑ ይህንን ድርጊት እንደፈፀመው በቂ ማስረጃ ባይገኝ እሱነቱን ሚያረጋግጥ በ ህግ ፊት ግን ይቺ ሴት እውነት አላት እውነታዋ ግን ድምፅ አልባ ጩኸት ነው... ማስረጃ ከሌላት አሱ ለመሆኑ ማረጋገጫ ...አለምም አንደልማዷ ኢፍትሀዊነቷን ትቀጥላለች በማስረጃ የተደገፈ እውነት እንጂ እውነትን ብቻ ስለማትቀበል..

ፍትህ እውነት ካልሆነ ምንድነው ላልከኝ አንድ የምልህ ነገር ቢኖር ፍትህ እውነትን ሊመስላት እንጂ ሊሆናት አይችልም ምክንያቱም እውነት አንድ ራሷን ብቻ ነው ምትመስለው ፍትህም እንደዛው ራሱን ነው ሚመስለው...አንዳንዴም እውነትና ፍትህ የምንላቸው ነገሮች ከሰው ልጅ አዕምሮ በላይ ነው ብዬ አምናለሁ...

አመሠግናለሁ



ፍትህ በእኛ አይምሮ ውስጥ ያለው እውነተኛው ሚያሸንፍበት ማስረጃውም የገዛ ህሊናችን የሆነበት ነበር.....



አሁን አሁን ግን ፍትህ ልክ ክርስቶስ እንተሰቀለባት ሰዓት ሆኗል፤ ትልቅ እውነት እያለህ ግን ሀሰተኞች በዙሪያህ ስለበዙ ምትረታበት፤በምታቃቸው ግን በማያቁህ አንተ ለመሰከርክላቸው ግን ባንተ ላይ ለመሰከሩብህ የተሞላች ለእውነት እውነት ማያቁትን ሰብስባ የተቀመጠች ነች




ፍትሕ በአእምሮሕ ውስጥ እምትሰራው ስራ ነው ማለትም አእምሮህን ማዘጋጀች ለምሳሌ በደል ደርሶብሕ መረጃ ባይኖር ካሳ ባታገኝ ነገር ግን አእምሮሕ ላይ መስራት ትችላለህ።
እኔ አንዴ እንዲህ አጋጥሞኛል አጎቴን ሰው ገደለው አይኔ እያየ ከሰስን ዳኛው
👍1
3 ምስክር አምጡ አለ በወ

ቅቱ ከኔ ውጭ ማንም አልነበርና ክሱ አልጸናም ገዳይ በነጻ ተለቀቀ አሁንም አለ። ለብዙ ጊዜ ፍትሕ ተነፍጌ ኖርኩ አሁን ግን ፍትሕ አግኝቸአለሁ እንዴት ካላችሁ እንዲህ ማሰብ ጀመርኩ፦ ገዳዩ ደደብ ነው ዳኛውም ደደብ ነው ስርአቱም ደደብ ነው የሰው ልጅ በተለይ ሀበሻ ዝግመተለውጡን ያልጨረሰ ድንዝዝ ነው። ስለዚሕም ገዳዩም ዳኛውም የስርአቱ አውጭወችም ተያይዘው ሲኦል ይገባሉ። እያልኩ አእምሮየን ማለማመድ ችያለሁ አሁን በቃ በኔ ቤት ፍትሕ አግኝቸ አለሁ።😁😁😁


በጥቂቱ እነዚህን ይመስላሉ.....እያየን የምንጨምር ይሆናል።

ሸጋ ቀን!💚 ናካይታ ለሀገራችን!💚

@getem
@Nagayta
@balmbaras
እንቢ በል !

(ሚካኤል አስጨናቂ)

የሀያላኑ ክንድ ሀይሉ ሲበረታ

በነቀዘ ስንዴ

ሽንገላ ተታለህ ሳትኖር በቸልታ

በጤፉ በስንዴው በእርዳታው ፈንታ

አንተው ዘሪ ሆነህ

አንተው አራሽ ሆነህ ድረስ ለገበታ!

እንቢ በል !

አባትህ ቴዎድሮስ ያ መይሳው ካሳ

የቋራው አንበሳ

ለመንግስቱ ግብር ለርሱ እጅ መንሻ

እህል ሲያቀርቡለት ጠይቋል ማረሻ

እንቢ በል !

ተመፅዋች አድርገው በሴራ ባሻጥር

አርቀህ ለማየት ሲሰጡህ መነጥር

ቅርብህ ተደብቋል ይሄን ብቻ ጠርጥር

እንቢ በል !

ለምለም ምድር ታቅፈህ ውስጡ አረንጓዴ

ለምን ትረዳለህ?  ልጠይቅህ ጓዴ !

ከሞኝ ደዳፍ ሞፈር ይቆረጣል ሚሉት

የአባቶችህ ተረት

አይደለም የዘበት!

ተሻገር እያሉ መርከብን ሲሰጡ

የመርከብ ስሪቱ እውቀት አመጣጡ

ከየት ነው መነሻው ብለህ ነው መጠየቅ

መድረሻ አልባ ጉዞ ለመስጠም መሆኑን

ይሄን ብቻ እወቅ! 
እንቢ በል !

በዘር ጎሳ ስሌት ሰበዝህን ሲመዙ

መሶብ ወርቅ መሆን ነው የውበትህ ወዙ

የቆምክበት ምድር የምታየው አፈር

የስጋ ፍራሽ ነው አብዲሳ ሲገበር

የደሙ ዋጋ ነው ያ ባልቻ ሲቀበር

እንቢ በል !

ተምሳሌት ሲያሳጡህ በታሪክ ፈጠራ

ሚኒልክ ገዳይ ነው ብለህ ሳታጓራ

ስር አልባ ሲያደርጉህ ቁስልህን በመጠቅጠቅ

ከፍለው ሊገዙህ ነው ይሄን ብቻ እወቅ!

እንቢ በል !

የነጭ ለምዳም ተኩላ 

መፅሀፍ አንግቶ ሲያሳልምህ መስቀል

አሜን አሜን ብለህ በእምነት አትታለል

በጎችን የሚነጥቅ የሰይጣን አለቃ

ለኢየሱስ ብሎህ ነው አንተን የሚያጠቃ

እንቢ በል !

የኢትዮጵያዊ ልህቀት የሀበሻ ጀብዱ

ባንዳ ሲወረው ነው የሚለየው ጉዱ

እሺ ለጌታህ ነው ለላይኛው አምላክ

እሱን መታመን ነው ለሱ ብቻ መላክ

ልጠብቅህ ለሚል ለአስመሳይ ቀመር

ዋርካህን አትገድስ ለጠላትህ ሞፈር !

እንቢ በል !

እሺ ማለትህ ነው ተብታቢው ሰንሰለት

እሺ ማለት ላይ ነው አዲሱ ባርነት

እንደ እንስሳ ታስረህ ለገበያ ድምቀት

ዋጋህ ሳይተመን...

ፍቅርህን አደርጀው ለነፍስህ አርነት

እንቢ በል !

አሰብንልህ ሲሉ በእነሱ ቋንቋ

ሀገር አጣህ በቃ !

ልማት አጣህ በቃ!

ለራስ ክብር ለግመህ ስትፈልግ ጠበቃ

መሪህ ጠላት ሆኗም ይሄን እወቅ በቃ! !

@getem
@getem
@getem

#Mikael aschenaki
👍1
Audio
እናት አለሜ🤱🏽 ♥️
Yohannes_Lawgaw @Sleenee ስለ እኔ ስለ ኔ ዮሀንስ ላውጋው
እናት አለሜ🤱🏽 ♥️
ስለ_እኔ
Yohannes_Lawgaw 🌿
#High_quality
@getem
@getem
@getem 🌿
👍1
🔆ፊደል ነው ጠላትሽ🔆

የእውነት: ደራሲ: የታደለ: ጠቢብ
አምላክ:ያቀመሰው:ከሰሎሞን:ዘቢብ
በምናብ: አለሙ: የሚኖር:ተራቆ
ነገር :የሚከትብ:በስሜት:ውስጥ:ጠልቆ
ከተራማጁ ሰው: ከአዳም -ዘር: ሁሉ
(ordinary person)
እጅግ:የሚለየው::ረቂቅ:አመሉ:-
የእውነት: ደራሲ : ከሆነ: ፈላስፋ
1-ሃሳቡ:ገናና: ምልከታው :የሰፋ!!!!
2-አኗኗሩ :ግሩም: :የደፋበት:ውበት
ጠባዩ :የተለየ: ጥያቄ :ያለበት::
3-የስሜቱን: ይዘት :የሚፅፍ :በብዕር
ኮከብ: ነው: ደራሲ: የህይወት: መምህር!
🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆አንቺም:ተለይተሽ:በገጣሚው :ልብ:ውስጥ:ብታገኚም:ቦታ
ቆንጆ :ተለይተሽ:በደራሲው:ልብ:ውስጥ:ቢኖርሽም:ቦታ
ሲያሻኝ:ትሻርያለሽ:ሲያሻኝ:ትተኪያለሽ:በብዕሬ:ቃታ
እናልሽ:አንዳንዴ:እጅጉን:ከራኩሽ
እናልሽ:አንዳንዴ/ትኩረት:ከነፈኩሽ
በማስታወስ:ፋንታ:ውዴ :ቸላ:ካልኩሽ
ያንቺ:ተቀናቃኝ:ሌላ:ሴት :ሳትሆን ፊደል:ነው:ጠላትሽ!!


ገጣሚ:::ዳዊት :ጥዑማይ

2/12/2013E.C

@getem
@getem
@paappii
👍2
አንድ ቀን በድንገት !
(ሚካኤል . አ )
አፈቀርኩሽ የሚል ስፅፍ አንዲት ጦማር
ነው ለካ በስካር!
ወደድኳት እያልኩኝ ለሰው ሳወራ
ደልቶሀል ይለኛል ሁሉም በየተራ
ሀገር ለጦር ከቶ ሲወጣ ዘመቻ
ዱላውን ሲያነግት ለጠላቱ መምቻ
ከወንድ ሁሉ ቀበጥ እኔ ነኝ ለብቻ!
አፍቃሪ ሰው ስሆን...
ኑሮ በአንድ ጎኑ ሲያወርድብኝ እቶን
በርበሬና ሽሮ ዋጋው እየናረ
ወድጃለሁ ማለት ቅብጠት ሆኖ ቀረ!
ደግሞ ሌላ ጦማር.. .
ደግሞ አዲስ ስካር.. .
አይንሽ ይመቸኛል ፀጉርሽ ይገርመኛል
ስስ ልቤ በለሊት አንቺን ይከጅላል
እያልሁ እየፃፍኩኝ
ፍቅሬን እያለምኩኝ
እህል አልወርድ አለኝ... ብዬ እንዴት ላክል?
እንቅልፍ እንቢ አለኝ ... ብዬ እንዴት ላክል?
በልቶ ም ለመተኛት
ማለፍ ያስፈልጋል የመከራን ክልል ።
በቃ እንደውም ተውኩት አልፅፍም ደብዳቤ
አፍራለሁ ለመውደድ...
ማፍቀሬ ቧልት ነው
ህዝቤ በቋፍ ታስሮ.. . ክምር ሆኖ ሲነድ።
ደግሞ ሌላ ጦማር
ደግሞ አዲስ ስካር
አነሳሁኝ ብዕር.. .አነሳሁ ወረቀት
ኑሮ ሲያነሳልኝ የጫንቃየን ክብደት
ይኼን እፍን አየር ሰላም ሲያረብበት
እልካለሁ ብዬ አንድ ቀን በድንገት
"ይድረስ ላንቺ" ብዬ ጀመርኩኝ ፅህፈት!

@getem
@getem
@paappii
1
" ማርያምን!" እያለ
#ቃለአብ ፀጋዬ
ኪሴ የመሉትን የሳንቲም ጥርቅም
እራብ ይድፋኝ እንጂ አንዷን አላጎልም
እል እንዳልነበርኩኝ
ግጠምልኝ ብለሽ
ብዕሬን ሳስተፋ ወረቀቴን ሰቀድ
ሳንቲሜን ጨረስኩኝ
ምን አውቅልሽ
ብለሽ?
ቃላትን ወርውሮ ቤት ስለመደብደብ
በለዛ በጥበብ
ስለመግለፅ ሀሳብ
. . . . . . . .. .. . .. . .. ... . .. . . .. . .
ሂጂ እሱን ጠይቂ . . .

ቃላት መርጦ ቆርጦ
በወግ ያገንሻል
አይ! ካልሽ አይገደውም
ቃላት አስሸብርቆ ልዕልት የሰኝሻል
"ማርያምን!" እያለ
ማመን መቀበልን ላንቺ ይተውልሻል

እኔ እንዲያ አይደለሁ . . . . .
ምትሐት ካለው ምናብ
የሚያማልል ሐሳብ
ምሉዕነት ካለው
ድንቅ ችሎታው ላይ
ጥቂት እንዲያደርስሽ
ሚካኤል ጋር ሄደሽ

ቅጥ የጣ ፍላጎት
ግዙፍ ግብዝነት
ይህ ሁሉ አመልሽን . . .
በቃላት ቆራርጦ
ብዙ ትንንሾች አድርጎ አስቀምጦ
እንደምትፈልጊው
በስንኝ ቆጣጥሮ እጅግ ያረቅሻል
"ማርያምን!" እያለ
እንኳን እምነትሽን ልብሽን ይወስዳል፡፡

እሱን ፈራሁ እንጂ: እነግረው ነበረ
ማርያም በቸረችው
መግጠምን ያውቀዋል ቃል እየቀመረ፡፡
@Kalsagi
ነሀሴ 4/2013
ለ፡ ሚካኤል አስጨናቂ
ለድንቅ ችሎታ ጥቂት ሙገሳን ለመለገስ. . . ጥሩ ለሰራም ምስጋና ይገባው ዘንድ እነሆ፡፡

@getem
👍5
የት ልሁን ንገሩኝ

ከግራ ወይስ ከቀኝ
የት ሄጄ ልገኝ
ከማን ጋር ልመደብ
በየትኛው መዝገብ
በምን አይነት ስሌት በየትኛው ቀመር
እ-ን-ዴ-ት-ስ ልሳፈር 
የቱ ጎራ ልግባ ማንንስ ልከተል
ሄጄ የቱን ልምሰል

የት ልሁን ንገሩኝ
መጥታቹ አማክሩኝ
ብቻ.............. ከውነታዉ አካፍሉኝ
ምንም አትደብቁኝ
ላይነጋ ከመሸም
ብርሀን ከሸሸም
ግዴለም ልወቀው
መጀመሪያዬ ላይ ደርሼ እንዳየዉ

የት ልሁን ንገሩኝ
ግልምቢጥ  መንገዴ መርቶኝ ከምጠፋ
መድረሻዬን ልወቅ አንዴ ላግኝ ተስፋ

ተፃፈ በ ጃሒዝ (@ja_hiz)
-2012-

@getem
@getem
👍2
Forwarded from አቶ anu😎
#ወዲያ_ሽሽ_ይለኛል!

© ሲራክ ወንድሙ @siraaq
.
ኑረት ሲረክስብኝ ፥ ሲሆን እንደ እቃ 'ቃ ፣
አዎን ያስፈራኛል ፥ የዘመን አታሞ
.................... ፥ የዘመን ድለቃ ፤
የድግግሞሽ ሰልፍ ፥ የእሽ ፡ ክርክሪት ምልዓት ፣
ሰው ሆኖ ተኝቶ ፥ ትል ሆኖ እንደመንቃት ።

ንጋት አድባር ሆኖ ፥ የሀገር ጌጥ የሀገር ዳስ ፣
ጀምበር በሰረቀ በአመሻሹ ፈለግ ፥ እንደካህን መርከስ ፤
እንደምኩራብ ከብሮ ፥ እንደ እንትን መንኳሰስ ።

አዎን ያስፈራኛል...
ወዲያ ሽሽ ይለኛል...
ወዲህ ግድም እሩጥ ፣
ወዲህ ግድም አምልጥ ፤
ወዲያ ጥግህን ያዝ ፥ ይለኛል ይለኛል ፤
የዘመኑ ቅኔ የዘመኑ መንፈስ ፥ መንን ያሰኘኛል ፤
ወዲያ ሽሽ ይለኛል ።
.............. | ። | ...............
ነሐሴ ፳፻፲፫ ዓ.ም
@getem
@Getem
@getem
👍3
በ +251984740577
ወይም @gebriel_19 ላይ ፎቶ በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ ሥዕል ማዘዝ ይችላሉ!
#ሥዕል_ብቻ የቴሌግራም ገፅ


@seiloch
@seiloch
#ጅብ እና ዘንድሮ

የድሮ ጅብ ትህትናው
ከማያውቁት ሄዶ፣<<ቁርበት አንጥፉልኝ ?>>
ነበረ ልመናው ።

የዛሬ ጅብ ድፍረቱ
ባለቤቱ እያየው ፣ ባይኑ በብረቱ
ይሰለቅጥና ፣ ላሚቱን ዘርግፎ
እበረቱ ያድራል ፣ ቁርበቷን አንጥፎ።

@getem
@getem
👍4
#አንዲት አንቺ

ባንዲት ሕይወት
ባንዲት ዓለም
አንዲት ሩህ
ለማለምለም ፤

አንዲት አንቺ - - - -
ያንዲት ምሥጢር ፣ አንዲት ፍቺ
ያንዲት ፍቺ ፣ አንዲት ፋና
ያንዲት ፋና ፣ አንዲት ዳና
አንዲት እንቺ - - - - - -
ያንዲት አንዲት - ህልውና
መጣሽ ሙሉ ፣ ጠፋሽ ኦና !

@getem
@getem
1
#ውሉድ ወወላድ*


የወለደች ኹሉ . . .
እናት አትባልም ! ግብሯ ካልተለየ ፤
የተወለደ ልጅ . . .
አይባልም ጧሪ ! ምግባሩ ካለየ ።

ዘር ስላካፈለ . . .
የአባት መሆን ክብር በከንቱ አይሰጥም !
ከልጅ ስም ቀጥሎ ስሙ አይቀመጥም !

እፍኝትን እይዋት . . .
እናት ትሞታለች ፣ ትውልድ ለማስቀጠል
አባትም ይሠዋል ፣ በፍትወት መቃጠል ።
አንበሳም ደቦሉን . . .
በጊዜው ካልቀጣ ንግስናው ይቀማል ፤
የልጅነት ሥሥት ፣
የአባትነት ድርሻ ለክብር ይወድማል ።

አዎ !
እናት ክብሯን ይዛ ፣
ልጅ ግብሩን ተላብሶ ፣
አባት በስም ነግሦ ፣
ካልተነፃፀረ ፤
የመዳን ምሳሌው ትንቢቱ ተሻረ ።

#የሞት ጥቁር ወተት
#ተስፋሁን ከበደ
@getem
@getem
@beckyalexander
👍2
ይነጋል !
አዳም መንገደኛው ተስፋውን ይባጃል
ነገን እከብራለሁ ብሎ ላብ ይዘራል።
"ነገ እረዳለሁ ሚስኪናን ደጅ ሄጄ
ነገ እነፃለሁ ... ሀጥያቴን ክጄ
ነገ እወልዳለሁ ... አንዲት ሴት አግብቼ"
ብሎ እያሰበ ... ከቀን ጋር ይበራል...ከቀን ጋር ይከንፋል !
ማታ አመሻሽ ላይ ...
ቀስቱን የወደረ አዳኝ ሙት መልዐክ አዳም ላይ ይስቃል።

....#(ሚካኤል . አ)

@getem
@getem
@getem
#የእረኛ_ማዕረግ
.
.
ከወዲያ ከጨፌ ከውድማ ከመስኩ፣
ሺህ በግ መጠበቅ ነው የእረኛ ልኩ።
ቀበሮ ቢለፋ ተኩላ ቢነፋፋ፤
ጅብ ጥላውን ቢጥል ቢያጓራ ቢጀነን፣
ለበጎቹ መንጋ፤
መልካ አዋቂ ብልህ እረኛ ነው ደጀን።

ከጥንትም ከወንዙ፤
ተኩላ ያልበጠሰው ጅብ ያላፈረሰው፣
የቀትር ቀማኛ ቀበሮ ያልዳሰው።
የተቆላለፈ የተጠላለፈ፤
ዕጣ ያስተሳሰረው የመዋደድ ሀረግ፣
ተኩላዎች ሲራቡ፤
በኩር በግ መሆን ነው የእረኛው ማረግ።

ለዘመኔ ጥበብ፤
ለዘመንህ ኩታ፤
"ቀን ያልፋል" ላሉት ቃል፤
ጥለቱ እስኪቋጭ እኔ ችዬም አልደርስ፣
እረኛም ልሁን በግ፤
መሰሪም ልሁን ደግ፤
ተኩላው ከሚበላኝ በልቼው ልቀደስ።


"ዐብይ" ( @abiye12 )

@getem
@getem
@getem
1👍1
::::ጭስ::::

እኔ ማለት ጭስ ነኝ፣ መውጫ መግቢያ የማላጣ፣
የማልሞክረው የሌለኝ፣ወደ ሰማይ እስክወጣ፤
ምን አልባት ግን ጭስ ካልሆንኩ ስጋ ሁኖ ሰውነቴ ፣ እኔ ማለት ደፋር ሴት ነኝ መፍጨርጨር ነው ሽልማቴ።
(አቢሲኒያ ፈንታው)

ቅዳሜ ነሐሴ 15 በብሔራዊ ቲያትር "ስንቅ" መጽሐፌ ይመረቃል። ተጋብዛችኃል።

@getem
@getem
👍1
አትመጪም አውቃለው
ምድር አትችልሽም የት አደርግሻለው?

@getem
@getem
@paappii

#Migbar siraj
👍2