ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ሞት ደጋሽ መዳፎች!!

( ሚካኤል አስጨናቂ )

።።።

በቀን መባቻዋ

ከእጭነት ዘላ

ስትበር ለነበረ

ለጀማሪ ትንኝ

አጨብጫቢው ሁሉ

አድናቂዋ መስሎ

ነበር የሚታያት!



ከ’ለታት ባንዱ ቀን

ከጭብጫቦው ወጥመድ

ሰተት ብላ  ገብታ……..

ሞትን እስክትቀምሳት።

።።።

አዎን!



ከለምለሙ ስፍራ

በገነት እያለች

እባብ ቀርባ መታ

የሠማይ የምድር

ንግስት አርጋት ሾማ

ወድቃ ስትሰግድላት

.

ሄዋን ለምትባል

ለዛች ምስኪን እንስት

ይሄ እጅ መንሻ

ነበር ብርቅ ሆኖባት!



በኒህ ክፉ ቃሎች

ትምክህቷ ንሮ

የአምስት ቀን ተኩል

ፍዳ ተጫነባት።

።።።

ያኛው እምነበረድ

ከደጃፍ የቆመው

የቤተ ክህነት

መግቢያ የነበረው

.

ሁሉም እየመጣ

እርሱን በመሳሙ

ሀጫነቱን ትቶ

ከሰለ በቁሙ።



የዛ ደጃፍ ድንጋይ

ዕጣ የደረሰው

ኢየሱስ ጌታውም

ለሰው ልጆች ግዞት

ታጭቶ የነበረው

ወዳጁ ይሁዳ…….

እንዴት ዋልክ? ብሎት

ጉንጮቹን ስሞ ነው።

።።።

እናም ይህን ጊዜ

ሌላው ብልሀተኛ 

ምጥን ስንኞቹን 

እንደዚህ ቋጠረ



“መሳምና መንከስ

መንከስና መሳም

ግብራቸው ቢለያይ

ዋጋቸው አንድ ነው



ተነካሽ ቆዳና

የተሳመ ደጃፍ

ሁሉም ጠቋሪ ነው።”

@getem
@getem
@paappii
#ሁለት #ሞት

ማንም ጨከነ ~ ማንም በደለ
ሰው አይደለም ወይ ~ የተገደለ
?
ግፍ የጣላት ነብስ ~ ዳግመኛ ላትቆም
ምን ይፈይዳል ~ ጣት መጠቋቆም
?
ማንም አለመ ~ ማንም ተኮሰ
ሰው አይደል ወይ ~ ደሙ የፈሰሰ
?
የንፁሀን ደም ~ ከንቱ ቢፈስም
ገዳይ መቀየር ~ ሟች አይመለስም
===||===

@getem
@getem
@getem

ከሙሉቀን ሰ•
👍1
#ሞት ደጋሽ መዳፎች!!
።።።
በቀን መባቻዋ
ከእጭነት ዘላ
ስትበር ለነበረ
ለጀማሪ ትንኝ
አጨብጫቢው ሁሉ
አድናቂዋ መስሎ
ነበር የሚታያት!

ከ’ለታት ባንዱ ቀን
ከጭብጫቦው ወጥመድ
ሰተት ብላ ገብታ……..
ሞትን እስክትቀምሳት።
።።።
አዎን!

ከለምለሙ ስፍራ
በገነት እያለች
እባብ ቀርባ መታ
የሠማይ የምድር
ንግስት አርጋት ሾማ
ወድቃ ስትሰግድላት
.
ሄዋን ለምትባል
ለዛች ምስኪን እንስት
ይሄ እጅ መንሻ
ነበር ብርቅ ሆኖባት!

በኒህ ክፉ ቃሎች
ትምክህቷ ንሮ
የአምስት ቀን ተኩል
ፍዳ ተጫነባት።
።።።
ያኛው እምነበረድ
ከደጃፍ የቆመው
የቤተ ክህነት
መግቢያ የነበረው
.
ሁሉም እየመጣ
እርሱን በመሳሙ
ሀጫነቱን ትቶ
ከሰለ በቁሙ።

የዛ ደጃፍ ድንጋይ
ዕጣ የደረሰው
ኢየሱስ ጌታውም
ለሰው ልጆች ግዞት
ታጭቶ የነበረው
ወዳጁ ይሁዳ…….
እንዴት ዋልክ? ብሎት
ጉንጮቹን ስሞ ነው።
።።።
እናም ይህን ጊዜ
ሌላው ብልሀተኛ
ምጥን ስንኞቹን
እንደዚህ ቋጠረ

“መሳምና መንከስ
መንከስና መሳም
ግብራቸው ቢለያይ
ዋጋቸው አንድ ነው

ተነካሽ ቆዳና
የተሳመ ደጃፍ
ሁሉም ጠቋሪ ነው።”
....
....(ሚካኤል አስጨናቂ)...

@getem
@getem
@paappii
👍1