ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ገለባ አይደለሁም !
አውሎ ነፋስ ደርሶ ~ የሚያርገበግበኝ
ወንጭፍም አይደለሁ
ማንም እያሾረ ~ የሚወዘውዘኝ
እኔ ደራሽ ውሀ
የመንፈስ አምሀ
እሳቱን የሀሜት ~ ምላስ የማከስም
ድኩማኗን ነፍሴን ~ በተጣፉ ቃላት
በፊደል የማክም...
ወጀቡን ነፋሱን ~ የማልፋቸው ጥዬ
አጎንብሼ 'ማልቀር ~ መንፈሴን አ..ዝዬ
ገለባ ነው ሲሉኝ ~ ፍሬ የማፈራ
ሊከስም ነው ሲሉኝ ~ ከርሞ 'ምጎመራ
የርግማን ውርጅብኝ ~ ከቶ የማልፈራ
በጭብጨባ ብዛት ~ ደንቆኝ የማልኮራ
የዝምታው ዳኛ...
በሸክላ ገላና ~ ብረት ልብ ያነፀኝ
እንደ እያሪኮ ግንብ.. .
በጩኸት የማልፈርስ የእጆቹ ስራ ነኝ።
#ሚካኤል አስጨናቂ

@getem
@getem
@getem