ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ፅና!!!!!!

ሃገሩ በሞላ፤
ድምፅህን ባይሰማው፤ ለጀማው ባትደምቅም፤
ሰው የለኝም ብለህ፤ ከጀመርከው መንገድ መሄድ እንዳትደክም፤
እስከዛሬ ድረስ፤
ከጩኸት በስተቀር፤
እውነት በሰው ብዛት፤
ፍትህ በሰው ብዛት፤ተበይኖ
አያውቅም!!!!"

((( ጃ ኖ ))💚💛❤️



@getem
@getem
@balmbaras
ህይወት እና ቅኔ
------------// ©ሲራክ //---------------

ዝምታ ቅኔ ነው
ትዝታ ህይወት ነው
ህይወት ፣ አለት ፣ ዜማ ፣ ምስል እና ቅራኔ
ጥልቅ ፣ ረቂቅ ፣ መንገድ ፣ የሀሳብ ምናኔ
ህይወት አለት ሆና ዜማ ስትቀኝ
ምስሏም ይገለፃል ቅራኔዋም በቀኝ
እንዲህ ነው ትዝታ
የህይወት ትውስታ
ቅኔ ረቂቅ ነው ጥልቅ ነው መንገዱ
ምናኔ ሀሳብ ነው ቅራኔው ጥማዱ
ስለዚህ
ትዝታም ቅኔ ነው ምስጢር የታወረ
ዝምታም ህይወት ነው ዜማው የሰመረ
.............ትዝታ
..............ህይወት
................ቅኔ
............ዜማ
የምናኔ መንገድ ሲቃረን ሲስማማ
ይህ ነው ሌላ የለም የኑረት አላማ
///////////////- #ሲራክ ////////////////
ሲራክ ነኝ
ከሚዛን ተፈሪ
ኢትዮጵያ
@siraaq

@getem
@getem
@getem
- ዋሻ

ድሮ የሰው ፍጡር እዋሻ ነበረ
ተራራ አለቱን እየቦረቦረ
አፈሩን ድንጋዩን እየሰረሰረ
ተራራን እንደጨርቅ እየተረተረ።
ዝናብ እንዳይመታው ፀሀይ እንዳይመታው
ይሰራ ነበረ ዋሻ በየቦታው።
ብርዱ እንዳይገለው ሙቀትንም ሽቶ
እሳትን ፈጠረ ድንጋይን አጋጭቶ
ነበልባል ፈጠረ አለትን አፋጭቶ።

አሁን በዚ ዘመን ዋሻ ኑሮ ቀርቶ
ሁሉም ከትንታጉ ከዋሻው ተፋቶ
ያን የትንፋግ ህይወት
የላቦቱን ሙቀት ሁሉንም ረስቶ
ያ መጠጋጋቱን
ያ መጨራመቱን
ያ መተፋፈኑን
ያ መገፋፋቱን ያንን ሁሉ ትቶ
ባለበት ሰዓት ላይ
ብዙ ዘመን አልፏል
ብዙ ህፃን ተወልዶ ብዙ አዛውንት አርፏል
ወንበር ተቀያይሯል ዙፋን ተለዋውጧል
መንበር ተዟዙሯል ስርዓት ተገላብጧል።
ከቀለበት ቅምያ ግብግቡ መሃል
ቀምቶ የተቀማው በእጅጉ ያዝናል
መቀማቱን እንጂ
እሱም መቀማቱን ፈፅሞ ይረሳል።

ከቀለበት ቅምያ ግብግቡ መሃል
ቀምቶ የተቀማው በእጅጉ ያዝናል
ሰዉ ሁሉ ሞቆት እሱን ይበርደዋል
በጠራራ ፀሃይ ብርድ ብርድ ይለዋል
ተራራ ፈልጎ ጥልቅ ዋሻ ይሰራል
አለቱን በብልሃት ይቦረቡረዋል።
ከዘመናት በፊት ሰዎች ሚያረጉትን
ድንጋይ እያጋጩ እሳት ሚፈጥሩትን
ሙቀትን ፍለጋ ድንጋዮች ያጋጫል
ያረጁ አለቶችን እርስ በርስ ያፋጫል
ያፋጫል ያጋጫል ያጋጫል ያፋጫል
ሙቀትን ፍለጋ ድንጋዮች ያጋጫል።
የዋሻው አለቶች እንዳይፈራርሱ
ወጣ ወጣ ሚሉት እንዲለሰልሱ
ቅቤ ይቀባቸዋል በእጁ በምላሱ።

ቀምቶ የተቀማው ያ ቀለበት ፀር
ድንጋይ እያጋጨ
ዘመናት ያለፈ አለት እያፋጨ
ለራሱ ሙቀት ሲል እሳትን ሲፈጥር
ምናልባት አንድ ቀን
በግዚያት መካከል በቀናቶች ክምር
ያገኘው ይሆናል እራሱን ካለት ስር
ዋሻው ተደርምሶ
አለቱ ፈራርሶ
ድንጋዩም በስብሶ
ያገኘው ይሆናል
እራሱ ተጥሎ ከፍርስራሹ ስር
ከክምሩ መሃል ከአለቱ ንብርብር።

[አቶ እገሌ]


@getem
@getem
@getem
"ህይወትም ህልም ናት
የአልጋ ላይ መኝታ
ሰው ከእንቅልፉ ይነቃል
የሞተ ለታ"
ከበደ ሚካኤል
መንቃት እንጂ ዛሬ
ሳልሞት ተቀብሬ
ለምን ልውረድ ካፈር
አስቤ ሳልሰራ
ሰርቼ ሳልከብር
ክብር ልበል እንጂ
እድሜ እንደሆን አጭር
ትላንት የነበረው
ዛሬ ሲቀነጭር
አይቻለሁ ባይኔ
__...ወይኔ

Join me
@hanahailu

@getem
@getem
"የአንድ አይነት አይነቶች"
( መልአኩ ስብሐት ባይህ)
መጋቢት 18-2011ዓ.ም
:
:
ፍቅሬ ባንቺ በኩል የኔ መልክ ይታያል
በአበባየሁሽ ቅኝት ሆያ ሆዬ ደምቋል።
በአታሞሽ ድላቄ በትረ ምቴ ልቋል
ሞቋል በቃ ትንፋሻችን ሞቋል።
የእኔነቴ አንድምታ ካንቺነትሽ ዘልቆ
በከንፈርሽ ካፊያ ውርጭ ንጥለት ደርቆ
አረም ኩርፈታችን በእቅፈታችን ደቅቆ
የዛች እመ-ምኔት ምርቃቷ ጠድቆ
የአንቺነትሽ ድርሳን እኔነቴን ሰብቆ
ሞቋል በቃ ትንፋሻችን ሞቋል
የእኔነት ሕላዌ እኛነትን ጠልቋል።

@poem_with_mela

@getem
@getem
"እነሆ ለፈጠረኝ"
(መልአኩ ስብሐት ባይህ)
*************
የልቤ ናርዶስ ጸዳል
ፍቅርህ ከፅናት ሲበቅል።
ከደጅህ ምዕራፍ ብጠጋ
ብለብስ ግርማ ወፀጋ።
በመቅደስህ ማዕጠንት ቡራኬ
ብሩህ ሲሆን ጭጋግ መልኬ።
በምጥቁ መአዛህ መረዋ
የውስጤ እርኩሰት ሲሰዋ።
አለኸኝ አልኩኝ ድጋፌ
ምስለ ፈውስህን ታቅፌ
ኃጥእ በሰናይ ቀርፌ።
ከፍትህ ሚዛን ወለል ላይ
ክህደተ ጴጥሮስ ሲሰማኝ።
ፍርሀት ልቤን አናውጦ
ስማፀን ቀኔን ቀን ውጦ።
ዘልቀህ ድንገት ከህዋሴ
ስትለግስ ምህረት ለነፍሴ።
ይቅር ባይነትህ ሲበዛ
ምናቤ ላንተ ሲገዛ።
አለኸኝ አልኩኝ ድጋፌ
ምስለ ፈውስህን ታቅፌ
ኃጥእ በሰናይ ቀርፌ።
በድኩም አካል በእንጭጬ
ገድለ ጠበልክን ሲረጬ።
ሳምራዊ ትምከት ሲሰማ
ቀና ሲል ዝንብል ጨለማ።
ኩሉህ ብርሃን አርፎብኝ
ጥኡም ምግባርህ ሰፍሮብኝ።
ከጀንበሯ ጥልቅ ስፍራ
የሲቃዬ እቶን ሲገራ።
ለሚያልፍ ዕለት
የማያልፍ እውነት ስታበራ።
አለኸኝ አልኩኝ ድጋፌ
ምስለ ፈውስህን ታቅፌ
ኃጥእ በሰናይ ቀርፌ።
ከቤትህ ስር ከታቦቱ
ከውዳሴህ በረከቱ።
በእልፍ ኣላፍ የተመን ጫፍ
አጥልተኸብኝ እፁብ አክናፍ።
ስሸጋገር ከጣረ-ሞት
ወደ ጸዳል ምሉዕ ሕይወት።
በእናትህም በእናቴ
ለምድር "ማር" ለሰማይ "ያም" በእመቤቴ።
ከስሞ ሳየው የምጤን ማት
እርሷን ባንተ ስሳለማት።
አለኸኝ አልኩኝ ድጋፌ
ምስለ ፈውስህን ታቅፌ
ኃጥእ በሰናይ ቀርፌ።
.
.
.
ተጻፈ:- ፳፻፰ ዓ.ም
@poem_with_mela


@getem
@getem
🌻 የጳጉሜ እንባ 🌻
•°•°•°•°•°•°•°•°••°•°•

ዓመት ዞሮ ሲሄድ
መስከረም ሊጠባ፤
ጳጉሜን ሆድ ሲብሳት
ሰማዩ ሲያነባ፤
ከዓመቱ ጉድፍ
ነፍሴ እንድትፀዳ፤
ዛሬ ላይ ልከፍል
የከረመ ዕዳ፤
በጳጉሜ እንባ
የ'ኔን እንባ ላብስ፤
በሰማዩ ለቅሶ
የ'ኔን ገላ ላድስ፤
በጳጉሜ እንባ እኔ እጠመቃለው፤
በሰማዩ ለቅሶ አካላቴ ሲርስ ነፍስን እዘራለው።

. . . . . . .

#ኤልቆሻዊው
{የጳጉሜ}

@getem
@getem
@gebriel_19
*ሀገር ቤት ሲታሰብ*
(ምግባር ሲራጅ)



ያነፈሰን ነፋስ
ያቃጠለን ፀሐይ
የመሸብን ፅልመት
የጋረደን ሰማይ፡፡
በኑሯችን መሃል
የሰማነው አዛን
አሜን ያልነው ኪዳን
ተጋግዘን ያዘንነው
የባልንጀራ ሃዘን፡፡

ከረመዳን ጧሚ
የቀመስነው አፍጥር
አንጀት ያስጠፈረን
የማርያም ለት ዝክር፡፡

ሰላም ለመሳጣት
ካስቀዳሽ ትከሻ
ስመን ያነሳነው
የከርቤ እንክብል
ከሩቅ የሰማነው፤ ያድባር ሽማግሌ
የሚከረክር ሳል፡፡

ጣራችን ያረፈ
የደመራ ቁራጭ
ጥቋቁር ጥላሸት
በድግግም ብዛት
ተቀብለን ያልነው
መንዙማ ማህሌት፡፡
አንድነት፤
ባንድነት፡፡
በስውር መዳፉ፤ እያጨባበጠ
ሀገር ከመናፈቅ፤ የለም ያመለጠ፡፡

#ዘንባባ ከተሰኘችው መፅሀፍ የተወሰደ

@getem
@getem
@getem
👍2
አጥቢ ሀገር
(በላይ በቀለ ወያ)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
.
.
ሰማይ እርቃን ሲሆን...
የደመናን ካባ ፣ ከላዩ አውልቆ
ፀሐይ ጭኗን ስትከፍት...
ምድር በሷ ሙቀት ፣ ቆፈኑን አላቆ
አዲስ አመት ገባ !
"ኢዮሐ አበባዬ ፣ ኢዮሐ አበባ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ልጇ ጡት እንዲጥል...
ሀገር የጡቷን ጫፍ ፣ ሬት ሳትቀባ
ለዘመናት ሳያድግ...
አሁንም ይኖራል ፣ መሥከረም ሲጠባ፡፡
ኢዮሐ አበባዬ ፣ ኢዮሐ አበባ
አዲስ አመት ገባ ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ኢዮሐ አበባዬ
መስከረም ጠባዬ
መሥከረም ሲጠባ...
ያ'ደይ አበባና ፣ የመሥቀል ወፍ ሶሪት
ታይቶ በመጥፋት ውል ፣ በመርገፍ አዙሪት
ባ'መት አንድ ጊዜ ፣ ዞረው ሲገናኙ
ነፋስ ሲያሳልፉ ፣ ሳሮች እየተኙ
በነፋስ ተገፍተው...
ሚረግፉ ቅጠሎች ፣ ይህንን ተቀኙ፡፡
"ዛፍ " የሚሏት ሀገር...
ፀሐይ ንጉስ ሾማ ፣ ከላይ ስትቃጠል
ነፋስ የገፋው ቀን...
መርገፍ ነው እድሉ ፣ "ህዝብ" የሚሉት ቅጠል፡፡
ምን ቅጠል ቢረግፍ...
ወድቆ ቢሰበሰብ ፣ ቢጣባ ካፈሩ
አበቦች ሚያፈካ ፣ ፍግ ነው መቃብሩ፡፡
።።።።፣፣።።።፣፣።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣።፣፣፣፣፣፣
ኢዮሃ አበባዬ ፣ ኢዮሃ አበባ
ሀገር የጡቷን ጫፍ ፣ ግራዋ ሳትቀባ
ዘመን ሲቀያየር...
የማያድግ ልጇ ፣ መስከረም ሲጠባ...
ከቢራቢሮ ጋር ...
ልጆች ሲጫወቱ ፣ ለመያዝ ሲለፉ
አበባ ለመሳም ፣ ንቦች ሲጣደፉ
በአሞሮች ልፊያ...
ጭራሮ አካሎች ፣ ተሰብረው ሲረግፉ
ይህንን ተቀኙ ፣ ይህንን ለፈፉ...
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
"ዛፍ በሚሏት ሀገር ፣
በቅጠሎች መርገፍ ፣
በሐዘን ተጎድቶ ፣ የሚኖር ጭራሮ
እጣው ችቦነት ነው ፣ ይማገዳል ታስሮ፡፡
በቅጠሎች መርገፍ ፣
ቁጭት አቅም ነስቶት ፣ የሚኖር ጭራሮ
እንኳንስ አሞራን...
መሸከም አይችልም ፣ አንዲት ቢራቢሮ ።
ካለበት ተለቅሞ...
"ችቦ ነህ" ተብሎ ፣ ምን ታስሮ ቢማገድ
ሀቅን ይጠቁማል ፣ ጭስ ሆኖ በመሥገድ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ምን አቅሙን ቢያጣ...
አስረው ሲማግዱት ፣ ቢያከስመው መንደዱ
ባ'ማኞች ግንባር ላይ...
የመሥቀል ቅርፅ ይዞ ፣ ይታያል አመዱ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ዛፍ የሚሏት ሀገር...
ፀሐይ ንጉስ ሾማ ፣ ከላይ ስትቃጠል
በነፋስ ሲገፋ...
መርገፍ ነው እድሉ ፣ ህዝብ የሚሉት ቅጠል
የቅጠሎች መርገፍ...
ያገባኛል ብሎ ፣ ሚወግን ጭራሮ
ካለበት ተለቅሞ...
ችቦ ነህ ተብሎ ፣ ይማገዳል ታስሮ፡፡
።።።።።።።።።።።።።፣፣፣፣፣፣።።።።።፣
እያጠባች ምትኖር...
ሀገር የጡቷን ጫፍ ፣ ጡት አስጥል ሳትቀባ
ዘመን ሲቀያየር ፣
የማያድገው ልጇ
ጡት ያልጣለ ልጇ ፣ ያው መሥከረም ጠባ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ኢዮሃ አበባያ ፣ ኢዮሃ መስከረም
የቅጠሎች መርገፍ...
ትንሳኤ ይሆናል ፣ ላበቦች መለምለም፡፡
ኢዮሃ አበባዬ ፣ መስከረም ጠባዬ
ለረገፈ ሳዝን...
አስረው ያነዱኛል ፣ ችቦ ነው ተብዬ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ምን ጭራሮ ቢነድ...
ከህይወት ቢቀነስ ፣ ሲደመር ደመራ
ከስሞ አመድ ሲሆን...
ባማኞች ግንባር ላይ ፣
የመስቀል ቅርፅ ይዞ ፣ ይታያል ሲያበራ፡፡

( በላይ በቀለ ወያ )

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

@getem
@getem
@getem
👍1
*መለየት
(በእውቀቱ ስዩም)

የለም ! የለም !
መለየት ሞት አይደለም
ሞትም መለየት አያክለው
መለየትም ሞትን አይመስለው
ትርጓሜያቸው ለየቅል ነው
አንቺም እኔም ጅረት ኾነን
ከራሳችን ምንጭ ፈልቀን
በራሳችን ፈለግ ፈስሰን
አገር ምድሩን አድርሰን
ሄደን ! ሄደን ! ሄደን ! ሄደን
ወርደን ! ወርደን ! ወርደን ! ወርደን !
ሞት በሚሉት ውቅያኖስ
አንድ ስንኾን ተዋሕደን
ተገናኘን 'ንጂ መች ጨርሰን ተለያየን
የለም ! የለም !
መራቅ መለየት አይደለም
ሰው በሰዎች ግዞት
ችግር መከራ ይዞት
አገር ቀዬውን ጥሎ
ስልቻውን በጫንቃው አዝሎ
ቅሉን ጨርቁን አንጠልጥሎ
ብቻውን ሄደ ብለው ሰፈርተኛው ተጃጅሎ
እርሱ በልቡ ሕንፃ በማይዘመው በማይፈርሰው
ከተጓዘ አኑሮ ሰው
አሁን ይኼ መለየት ነው ?
የለም የለም !
መለየት ይህ አይደለም
ትርጓሜያቸው እንቀይረው
ላ 'ንቺና ለ'ኔ ሌላ ነው
ከፊቴ ቁጭ ብለሽ
ከፊትሽ ቁጭ ብዬ
ክንድሽን ከአንገቴ ጥለሽ
ክንዴን ከአንገቴ ጥዬ
የምታወሪው ሳይገባኝ
የማወራሽ ሳይገባሽ
ለይስሙላ ጥርስሺ ሲሥቅ
ቻው ቻው ሲለኝ ቀልብሽ
ደህና ኹኚ ሲልሽ ዐይኔ
መለየት ይህ ነው ለ'ኔ፡፡

@getem
@getem
@getem
... ላንቺ 2...
የነፋስን በሬ ወጀቦ እያረሰው
የተፈጥሮን አጥር አርቴ እያፈረሰው
ቅንድብ ተቀንድቦ ኩልም እያነሰው
ወዝ በጠረረበት በዚህ የምጥ ጊዜ
ሴቶች መስታዊት ፊት ሲያበዙ ትካዜ
መታደል ነው እንጅ መባረክ አብዝቶ
እንዲህ ያል ቁመና
እንዲህ ያል ወዘና
እንዲህ ያል ደምግባት ከወዴት ተገኝቶ
የክንፍሽን ብርታት እያወቀው ሆዴ
የማትበላ ወፍ በከንቱ ማጥመዴ
ቃላት ማሰማመር ስንኝ መደርደሬ
አላስችል ቢለኝ ነው ይቅር በይኝ ፍቅሬ
ዘመን ሲለዋወጥ መስከረም ሲጠባ
ወይንም ባልጋብዝሽ ባልሰጥሽ አበባ
እንደ መስቀል ወፌ ስትመጭ ለዓመቱ
ከንፈርሽ ባይስመኝ ባይንሽ ዳብሽኝ እቱ
አውደ ዓመት ሲበሰር በወፎቹ ዜማ
እንኳን አደረሰሽ ውቢት የኔ ዓይናማ

ዶ/ር ጌታነህ ካሴ ለMeti
@getanehkassie

@getem
@getem
@getem
👍1
( በላይ በቀለ ወያ )
.
.
.
"ከብረው ይቆዩን ከብረው
በአመት ወንድ ልጅ ወልደው
ሰላሳ ጥጆች አስረው
ከብረው ይቆዩን ከብረው"
ከሚል ምርቃት ላይ ፣ ጥያቄ ነጎደ
መክበር አይችልም ወይ ፣ ሴትን የወለደ ?
"ፍቅር ያሸንፋል" ...
የሚል ጥቅሷን ይዛ ፣ በተነሳች ሀገር
አይቻላትም ወይ
ከሰላሳ በላይ ፣ እልፍ ጥጃ ማሰር?
።፣፣፣፣።።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
ሁልጊዜ ወንድ ልጅ ፣ እየተከበረ
ሁል ጊዜ ሰላሳ ፣ ጥጃ ከታሰረ
ድግግሞሽ እንጂ ፣ ይህን ምን ይሉታል
ይኸው አዲስ አመት ፣ አዲስ ነገር የታል?
።።።።
(በላይ በቀለ ወያ)

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

@getem
@getem
@getem
አንቺ


አንቺ ጥቁሯ ሴት ጠይም ነዉ ቀለምሽ
አንቺ ሳቂታ ሴት ነጭ' ናቸው ጥርሶችሽ
አንቺ ተላላ ሴት ደማቅ ነው እምነትሽ
አንቺ ገራገር ሴት አረንጓዴ ቤትሽ
አንቺ ስታለቅሺ የማይታይ እንባሽ
አንቺ ስትጮሂ የማይረብሽ ድምፅሽ
አንቺ ጠንካራ ሴት ከነ ትልቅ ህልምሽ
አንቺ ኢትዮዽያዊት በቀለም ታጅበሽ
በስሜት ተከበሽ
ለአዲሱ አመት እንኳን አደረሰሽ ::

@getem
@getem
@olan_yzo
👍1
ይነጋል
(በረከት በላይነህ)
.
.
ታድለሻል ቢሉም፣
የ13 ወር ፀሀይ፣ የ13 ወር ፀጋ
ብርሀንሽ ተሰርቆ፣
ሲጨላልም እንጂ፣ መች አየን ሲነጋ?
ተፈጥሮ ቸር ሆና፣
ሰማይዋ ባይነጥፍ፣ ምድሯ ቢለመልም
ከልጆቿ ልብ ውስጥ፣
ፍቅር ሲጎድል ነው፣ ሀገር የምትጨልም!
።።።
"አረ ነግቷል" ቢሉ ፣ የታለ የነጋው?
አዕላፋት ተቧድነው፣ በየጎጥ በመንጋው፣
ሰው ከነገ ይልቅ፣ ዛሬን እያሰጋው
የታለ የነጋው?
።።።።
ታሪኩን እንዳይፅፍ፣ ትውልድ እጁ ታስሮ፣
በትላንቱ ሾተል ፣ ዛሬው ተሸንቁሮ
ባልኖረው ተካሶ፣ ባልሰራው ተዋቅሶ
ለፀብ መዶለቻ፣ ያ'ያቱን ስም ጠቅሶ
ላለፈው ሲናከስ ፣ ለመጪው ሳይተጋ
በምን ስሌት ይሆን፣
ትዉልዷ ጨልሞ ፣ ሀገር የምትነጋ?
።።።
የህሊና መስታወት ፣ በጥበብ ሲፀዳ
ማስተዋል እንዳ'አደይ ፣ ፈክቶ ሲፈነዳ
መገፋፋት ሲቀር ፣መደጋገፍ ነግሶ
አንዱ ማገር ሲሆን፣ ሌላኛው ምሰሶ
የአብሮነትን ሸማ ፣ ትዉልዱ ሲሸምን
ያኔ ነው ሀገሬ ፣መንጋቷን የማምን።

@getem
@getem
@getem
Forwarded from አንድነት ይሻላል ፨ ፍቅር ያሸንፋል
ለአዲስ አመት ውድ የአዕምሮና የነፍስ ስጦታ!
ውብ የእናት ገበታ፣ ለየት ያለ ግብዣ!
መጽሐፍ ይሸምቱ፣ ለበጎ አድራጎት ያግዙ፣ ከጥበብ ገበታም ይቋደሱ...
"አንድ ሃገር፤ ቢየ-ቶኮ" የተሰኘው የዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ አዲስ መጽሐፍ ለሁሉም አንባቢ ቀርቧል። ደራሲው ኤቶዮጵ የተሰኘው መጽሐፉ በበርካቶች የተወደደለትና ብዙዎች ምስክርነትን የሰጡለት ሲሆን አሁን ደግሞ ከፋፋዮች በበዙበት ወሳኝ ጊዜ ያለችን እንዲህ የዋህ የሆነች አንድ እናት ነች ሲል "አንድ ሃገር" ብሎ የጥበብ ማዕዱን አቅርቧል። አዝናኝና አስተማሪ ምርጥ ምርጥ ወጎች፣ አጫጭር ግጥሞችና ምስሎችን ያካተተው ስራ ደጃችሁ ላይ ቀርቧል።
ጷግሜ 1 በደማቅ ሁኔታ በሃገር ፍቅር ቲያትር ቤት ተመርቆ ለአንባቢያን የቀረበው መጽሐፍ ዋጋው መቶ ብር ብቻ ነው፤ ከሽያጩ የሚገኘው ግማሽ ገቢም ለሙዳይ የወላጅ አልባ ህፃናት ማሳደጊያና የሴቶች መረዳጃ ድርጅት የሚሰጥ ሲሆን መጽሐፉን ገዝቶ ማንበብ የሚፈልግና በበጎ አድራጎቱም መሳተፍ የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ "አንድ ሀገር" መጽሐፍን ከታች በተዘረዘሩት አድራሻዎች ማግኘት ይችላል።
."በአዲስ አበባ" - ፒያሳ፣ 4 ኪሎ፣ ብሔራዊ ፣ ለገሃር ወዘተ ባሉ ሁሉም መጽሐፍ ቤቶችና አዟሪዎች እጅ ላይ፤
"በጎንደር" - ዣንተከል ዋርካ ፊትለፊት ሰሎሞን መጽሐፍት ቤት፤
"ሐዋሳ" - ሰሚራ መጽሐፍት መደብር ገብርኤል አካባቢና በላይ መጽሐፍት ቤት፤
"በጅማ" - ሰሎሞን መጽሐፍ ቤት መርካቶና መዳ ጋሪ መጽሐፍ ቤት ፋርሚድ፤
"ባህር ዳር" - ፓፒረስ ፊትለፊት አዳነ መጽሐፍ ቤት፤
"አዳማ" - ተስፋዬ ኦሎምፒክ 1ኛ መንገድ - ምንተስኖት መጽሐፍ ቤት፤
"ድሬዳዋ" - ዋናው አደባባይ አለፍ ብሎ የሚገኘው ኪዳኔ መፅሐፍ ቤት፤
"ደብረ-ማርቆስ" - ጨረር መጽሐፍ ቤት ቱቲ ህንፃ
ለበለጠ መረጃ 0913108312 መኮነን ብለው ይደውሉ፤
#ሃሳብዎን በነፃነት ይስጡ!

ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ከዚህ በታች የቀረቡት ቃለመጠይቆችን ከመስከረም 2011 ዓ.ም አንስቶ እስካሁን ባሉት ጊዜያት የተፈፀሙ ወይም የተከናወኑ ጉልህ አገራዊ ሁነቶች የሚመለከቱ ናቸው። ዓላማውም የቻናላችን አንባብያን የዓመቱ ምርጥ፣ ተወዳጅ፣አሳዛኝና አስደንጋጭ ክስተቶች በተመለከተ ሀሳባቹን ወይም አስተያየታቹን መሰብሰብ ነው።ምላሽ በመስጠት የተለመደውን ተሳትፏቹን እንጠብቃለን። እናመሰግናለን!🙏🙏


1 የዓመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ የክልል ፕሬዝዳንት
2 የዓመቱ ስኬታማ የመንግስት ተቋም
3 የዓመቱ አሳፋሪ የመንግስት ተቋም
4 የዓመቱ ተስፋ የሚጣልበት የዲሞክራሲ ተቋም
5 የዓመቱ አስደማሚ የመንግስት ስኬት
6 የዓመቱ ስኬታማ አገራዊ ንቅናቄ
7 የዓመቱ አስደንጋጭ ስኬት
8 የዓመቱ ተፅእኖ ፈጣሪ አክቲቪስት
9 የዓመቱ ምርጥ የፓለቲካ (የመንግስት ) መሪ
10 የዓመቱ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ጣቢያ
11 የዓመቱ ተወዳጅ የሬድዮ ጣቢያ
12 የዓመቱ ምርጥ ኢ-ልቦለድ መጽሐፍ
13 የዓመቱ ተወዳጅ የኪነ ጥበብ ምሽት
14 የዓመቱ የሰላም የፍቅር አርዓያ
15 የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ድራማ
16 የዓመቱ ነጠላ ሙዚቃ
17 የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም
18 የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ
19 የዓመቱ አሳፋሪ የፓለቲካ ውዝግብ
20 የዓመቱ ምርጥ የበጎ አድራጎት ድጋፍ


🤔 ማስታወሻ :- ስማቹን ፣ ፣ የምትኖሩበት ቦታ አብራቹ መላካቹን እንዳትረሱ 🙏🙏🙏

👇👇

@balmbaras
👍2
Kaleab FM:👇👇👇

1 ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ
2 ገቢዎች ሚነስትር
3 አዴፓ
4 ኦነግ
5 ችግኝ ተከላ
6 ብሔራዊ የኩራት ቀን
7 የዛላምበሳው ድንበር መከፈት
8 ጀዋር መሀመድ
9 በቀለ ገርባ
10 ፋና
11 97.1
14 ታከለ ኡማ
15 ዘመን
18 ኤልያስ መሰረት
19 አብን
20 የአበበች ጎበና

#ቃለአብ ከአዳማ


Ãŝĥ€ ªbű:👇👇👇

ስም አሸናፊ
አድራሻ አ.አ

1= የሱማሌ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት
2= ብሄራዊ ሎተሪ
3= ደኢህዴን
4= ምርጫ ቦርድ
5= የህዝብ ፍቅር ማግኘት
6= ችግኝ ተከላ
7= ተቃዋሚዎች በሞላ ሀገር ቤት መግባታቸው
8= ስዮም ተሾመ
9= አብይ አህመድ
10= FANA
11= Sheger
12= ትውልድ አይደናገር እኛም እንናገር (አንድአርጋቸው ፅጌ)
13= ጦቢያ (ግጥምን በጃዝ)
14= የወላይታ አባቶች
15= ሰንሰለት
16= አይ መሬት ያለ ሰው (ዲንቢ)
17= አስቴር አወቀ
18= ተመስገን ደሳለኝ no ETV
19= ኦነግ የፈጠረው ነገር በሞላ...
20= የሀይሌ ትምህርት ቤት ማስገንባት

Bin@m:
ቢኒያም ከፉለ👇👇

ከ አቦምሳ

1.ዶ/ር ደብረፂሆን
2.ገቢዎች ሚኒስተር
3.ት/ት ሚኒሲተር
4.ምርጫ ቦርድ
5.የማዕከላዊ ሙዝየም መሆን
6 ችግኝ ተከላ ሀምሌ 22
7. ያለ ቪዛ ለ አፍራካዊያን የተሰጠ ዕድል
8.ኢጄቶ የ ሲዳማው
9 ዶ/ር አብይ አህመድ
10. Arts tv
11. ኢትዮ ኤፍ .ኤም107.8
12 .የምድራችን ጃግና ዘነበ ወላ
13. ጦቢያ ግጥምን በጃዝ
14. ዶ/ር አብይ ( የኔ)
15. አለም ዘጠኝ ሲትኮም
16. ኤፍሬም አማረ " እሰይ "
17. ጎሳዬ ተስፉዬ ሲያምሽ ያመኛል
18 .L tv ቤቴልየም " ኤል ቲቪ ሾው "
19. የ ኮንዶምንየም ዕጣው ጉዳይ
20.ቤት ለመቅዶንያ የሰጡ እናት


 :👇👇👇

1 የዓመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ የክልል ፕሬዝዳንት :no one
2 የዓመቱ ስኬታማ የመንግስት ተቋም: gumruk
3 የዓመቱ አሳፋሪ የመንግስት ተቋም:tele
4 የዓመቱ ተስፋ የሚጣልበት የዲሞክራሲ ተቋም:no one
5 የዓመቱ አስደማሚ የመንግስት ስኬት:- ye media shifan
6 የዓመቱ ስኬታማ አገራዊ ንቅናቄ:- chigign tekela
7 የዓመቱ አስደንጋጭ ስኬት:- ye biheri poletica
8 የዓመቱ ተፅእኖ ፈጣሪ አክቲቪስት:- no one
9 የዓመቱ ምርጥ የፓለቲካ (የመንግስት ) መሪ:- Dr. Abiy
10 የዓመቱ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ጣቢያ:- Esat
11 የዓመቱ ተወዳጅ የሬድዮ ጣቢያ:- sheger fm
12 የዓመቱ ምርጥ ኢ-ልቦለድ መጽሐፍ:no
13 የዓመቱ ተወዳጅ የኪነ ጥበብ ምሽት:no
14 የዓመቱ የሰላም የፍቅር አርዓያ:lidetu ayalew
15 የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ድራማ:zemen
16 የዓመቱ ነጠላ ሙዚቃ:- Teddy afro: tikura
17 የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም:- Jacky gossaye - Balambaras
18 የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ:no
19 የዓመቱ አሳፋሪ የፓለቲካ ውዝግብ:- yebiher poletica
20 የዓመቱ ምርጥ የበጎ አድራጎት ድጋፍ:- Dr. Abiy legodana tedadariwochi .....

#Befikadu ; AA



Bêsüfekãd:👇👇👇

1 ye Somalia presdent
2 ethio tele com
3 ye tena tbeka minister
4 .
5.ke artria gar yetefeterew erke selam
6.ye arguade ashara niknake
7....
8 .tamagni beyene
9.D/r abiy ahmed
10.walta TV
11.Ethiopia radio
12....
13. Addis Ababa university bekrbu yazegajew ye kine tbeb mshit
14.D/r abiy Ahmed
15.Zemen drama
16.ete abay--abreham /shalaye/
17.siyamsh yamegnal -gosaye album
18.simeneh bayferis - walta TV
19,ye mefenkle mengst mukera
20.le gedio mahbereseb yetederegew dgaf

#Besufekad Tesfamariam
Ke Dessie



እናመሰግናለን🙏🙏 የሌሎቻቹን ያላቀረብነው #የላካቹልን ስላልተሟላ ነው.......እንጠብቃቹሃለን #ሀሳባቹን በነፃነት ስጡ !🙏


@balmbaras
👍3
አምላክ አስተኔ
(ምግባር ሲራጅ). ከ #ዘንባባ መፅሐፍ


በፀሎቴ መሃል
በስግደቴ መሃል
በአርምሞዬ መሃል
ምስልሽ እየመጣ
ካማልክት ቡራኬ
ሰርክ ያናጥበኛል፡፡

ለዪ! ሚና ለዪ!

አምላኬን ሳስታውስ
ከመጣ ያንቺ ምስል
ፍቅር ሲታሰበኝ
ከቃለ አብ ቀድሞ
ከሰማው ያንቺን ቃል

ለዪ! ሚና ለዪ!

ለዪ ፀሎትሽን
መልሺ ስግደቴን
በህልውናሽ ክብደት
ማደሪያ ነጥቀሽው
ፅድቄ ሲንቀዋለል
ማረፊያ እንዳታጣ
ነፍሴ እንዳትበደል፡፡

ለዪ! ሚና ለዪ!

@getem
@getem
@getem
1👍1
Èyãsû gøssäyé:👇👇👇

1 የዓመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ የክልል" ፕሬዝዳንት :musxefa Ali(Somali)
2 የዓመቱ ስኬታማ የመንግስት ተቋም: tele
3 የዓመቱ አሳፋሪ የመንግስት ተቋም:elpa
4 የዓመቱ ተስፋ የሚጣልበት የዲሞክራሲ ተቋም:no one
5 የዓመቱ አስደማሚ የመንግስት ስኬት:-hagerawi megbabat
6 የዓመቱ ስኬታማ አገራዊ ንቅናቄ:- chigign tekela
7 የዓመቱ አስደንጋጭ ስኬት:-ye bejet gudlet😂
8 የዓመቱ ተፅእኖ ፈጣሪ አክቲቪስት:- no one
9 የዓመቱ ምርጥ የፓለቲካ (የመንግስት ) መሪ:- Dr. Abiy
10 የዓመቱ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ጣቢያ:-asham
11 የዓመቱ ተወዳጅ የሬድዮ ጣቢያ:- bisrat
12 የዓመቱ ምርጥ ኢ-ልቦለድ መጽሐፍ:no
13 የዓመቱ ተወዳጅ የኪነ ጥበብ ምሽት:no
14 የዓመቱ የሰላም የፍቅር አርዓያ:Ethiopian (real ones)
15 የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ድራማ:9gnaw shih
16 የዓመቱ ነጠላ ሙዚቃ:- no
17 የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም:- no
18 የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ:ye asham TV documentary aqrabiw Girma assef
19 የዓመቱ አሳፋሪ የፓለቲካ ውዝግብ:-sayxaxamu megenxel mebalu
20 የዓመቱ ምርጥ የበጎ አድራጎት ድጋፍ:-memarya kusakus le temariwoch

#Ke eyasu gossaye
Debrezeit

Nikodimos Enyew:👇👇👇

Nikodimos Enyew Addis Ababa
1 የዓመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ የክልል ፕሬዝዳንት
-> ዶ/ር ደብረጽዮን
2 የዓመቱ ስኬታማ የመንግስት ተቋም
-> Ethio Telecom
3 የዓመቱ አሳፋሪ የመንግስት ተቋም
-> ትምህርት ሚንስትር
4 የዓመቱ ተስፋ የሚጣልበት የዲሞክራሲ ተቋም
-> መከላከያ ሚንስትር
5 የዓመቱ አስደማሚ የመንግስት ስኬት
-> የዕዳ ቅነሳ ስምምነት ከቻይና ጋር
6 የዓመቱ ስኬታማ አገራዊ ንቅናቄ
-> ሐምሌ 22
7 የዓመቱ አስደንጋጭ ስኬት
-> የክረምት በጎ ፈቃድ
8 የዓመቱ ተፅእኖ ፈጣሪ አክቲቪስት
-> ኦባንግ ሜቶ
9 የዓመቱ ምርጥ የፓለቲካ (የመንግስት ) መሪ
-> ዶ/ር አብይ
10 የዓመቱ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ጣቢያ
-> ፋና
11 የዓመቱ ተወዳጅ የሬድዮ ጣቢያ
-> ሸገር
12 የዓመቱ ምርጥ ኢ-ልቦለድ መጽሐፍ
-> ትውልድ አይደናገር እኛም እንናገር
13 የዓመቱ ተወዳጅ የኪነ ጥበብ ምሽት
-> ጦቢያ
14 የዓመቱ የሰላም የፍቅር አርዓያ
->
15 የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ድራማ
-> ውርስ
16 የዓመቱ ነጠላ ሙዚቃ
-> ገራገር
17 የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም
-> ጎሳዬ/አስቴር/ዘሩባቤል
18 የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ
-> ፀጋአብ ወልዴ (Tikvah)
19 የዓመቱ አሳፋሪ የፓለቲካ ውዝግብ
-> ሰኔ 15
20 የዓመቱ ምርጥ የበጎ አድራጎት ድጋፍ
-> ለጌዲዮ እና ጉጂ ተፈናቃዮች በታማኝ በየነ የተሰበሰበው ድጋፍ

Gedel gibu:👇👇👇

ada....ke a.a


1 የዓመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ የክልል ፕሬዝዳንት .....የሱማሊያ ክልል ፕሬዝዳንት
2 የዓመቱ ስኬታማ የመንግስት ተቋም....በጣም ባይባልም ምርጫ ቡርድ
3 የዓመቱ አሳፋሪ የመንግስት ተቋም.....ት/ት ሚኒሰቴር
4 የዓመቱ ተስፋ የሚጣልበት የዲሞክራሲ ተቋም....ምርጫ ቦርድ
5 የዓመቱ አስደማሚ የመንግስት ስኬት......ማስመሰል
6 የዓመቱ ስኬታማ አገራዊ ንቅናቄ....ችግኝ ተከላ
7 የዓመቱ አስደንጋጭ ስኬት.....የዘውግ ፓለቲካ መሰራፋት
8 የዓመቱ ተፅእኖ ፈጣሪ አክቲቪስት....?.As positively no one but negatively gawar Mohamed
9 የዓመቱ ምርጥ የፓለቲካ (የመንግስት ) መሪ no one
10 የዓመቱ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ጣቢያ.....art tv
11 የዓመቱ ተወዳጅ የሬድዮ ጣቢያ sheger fm
12 የዓመቱ ምርጥ ኢ-ልቦለድ መጽሐፍ......ትውልድ አይደናገር.....
13 የዓመቱ ተወዳጅ የኪነ ጥበብ ምሽት...
14 የዓመቱ የሰላም የፍቅር አርዓያ.....ታማኝ በየነ
15 የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ድራማ......ዘመን
16 የዓመቱ ነጠላ ሙዚቃ.....ገራገር
17 የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም.....ደጊ ደን
18 የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ.....
19 የዓመቱ አሳፋሪ የፓለቲካ ውዝግብ ኦነግ
20 የዓመቱ ምርጥ የበጎ አድራጎት ድጋፍ......

I HAVE DREAM!:👇👇👇

1.Mustafa Omar Somalia
2.may be ethiotelecom
3.timirt Minster
4.?
5.Ethiopia and Eritrea selam mewired
6.chigign tekelew hamile 22
7.?
8.ታማኝ በየነ
9.ልደቱ አያለው 👍👍👍👍👍👍
10.L TV
11.fana fm specilay "jilalo awol"
12.amalkit & tawotat (pilatos or halegiorgis mamo)
13.gonder university kenun alasatawism epherem syium ena lelochi
14.መጋቤ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ
15.9ሺ
16.?
17.astuka chewa🙏🙏🙏
18.simeneh bayiferes walta tv
19.የአዴፓ እና የህወሀት መግለጫ
20.yesefer lijoch gar hunen 2010 lay ye akimedekama bet yeseranew

#Tewodros mengesha ke wollo raya kobo


Biniyam:👇👇👇

1 የዓመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ የክልል ፕሬዝዳንት --Mustafa (somali kilil)
2 የዓመቱ ስኬታማ የመንግስት ተቋም--Gebiwoch minister
3 የዓመቱ አሳፋሪ የመንግስት ተቋም---Mebrat hayl
4 የዓመቱ ተስፋ የሚጣልበት የዲሞክራሲ ተቋም---Mircha Bord
5 የዓመቱ አስደማሚ የመንግስት ስኬት---Wuyiyitin masfafat
6 የዓመቱ ስኬታማ አገራዊ ንቅናቄ--chigign tekela
7 የዓመቱ አስደንጋጭ ስኬት--Chigign tekela
8 የዓመቱ ተፅእኖ ፈጣሪ አክቲቪስት ---Jawar
9 የዓመቱ ምርጥ የፓለቲካ (የመንግስት ) መሪ....Dr. Abiy
10 የዓመቱ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ጣቢያ---Fana B.C
11 የዓመቱ ተወዳጅ የሬድዮ ጣቢያ---Zami FM
12 የዓመቱ ምርጥ ኢ-ልቦለድ መጽሐፍ --Harrison
13 የዓመቱ ተወዳጅ የኪነ ጥበብ ምሽት---I don't know
14 የዓመቱ የሰላም የፍቅር አርዓያ ---Dr. Abiy
15 የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ድራማ--I don't know
16 የዓመቱ ነጠላ ሙዚቃ- Gerager
17 የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም - Gosaye's
18 የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ- Elias Meseret
19 የዓመቱ አሳፋሪ የፓለቲካ ውዝግብ - coup d'etat of sene 15
20 የዓመቱ ምርጥ የበጎ አድራጎት ድጋፍ - Sitota le addis abebaye

#Biniyam , ke A.A


እኔስ የ ማርያም ነኝ:👇👇👇

1.no one
2.ye fth tekuam
3.football federation
4.sebawi mebt komision
5. ye ethio ertra wedajnet
6.arenguade zemecha
7.ye metek sra megalet
8.no one
9.d.r abiy Ahmed(king)
10.fana TV
11.ethio FM
12.yemdrachn jegna zenebe wela
13.tobiya (gtmn be jazz)
14.Dr abiy Ahmed
15.9naw s
👍2