" ዛሬም ወድሻለው "
ዘምናትን ኖሬ እንደ ሌለው ሆኜ
ብቻዬን ሥወድሽ በፍቅርሽ ባክኜ
መክሳቴን አይቼ ልተውሽ ወስኜ
መክሳቴ ጀብድ ይሁን ለፍቅር ታምኜ
በነጋ በጠባ በሀሳቤ አንቺ ነሽ
ለኑሮዬ ድርሰት ታሪኬ የምልሽ
ከልቤ ላይ ፅፌሽ ሳነብሽ ሳነብሽ
እንደ ልዩ ድርሰት ስገረም በስምሽ
የደመቀው ምስልሽ ከቀለም የፈካው
ቀለም በምን አቅሙ ካንቺ የሚልካካው
ከውብ ገፅታሽ ላይ ፍቅር
ተጨምሮ
ቢያደማኝ ቢያቆስለኝ ገላዬን አጥቁሮ
ጉልበት እስኪከዳኝ ቢርቀኝ ውበቴ
ዛሬም ወድሻለው ዛሬም ነሽ ህይወቴ
ባጥንቴ እስክቀር እስከለተ ሞቴ
ገጣሚ ኢብራሂም ለጃ
@ebro43
@getem
@getem
ዘምናትን ኖሬ እንደ ሌለው ሆኜ
ብቻዬን ሥወድሽ በፍቅርሽ ባክኜ
መክሳቴን አይቼ ልተውሽ ወስኜ
መክሳቴ ጀብድ ይሁን ለፍቅር ታምኜ
በነጋ በጠባ በሀሳቤ አንቺ ነሽ
ለኑሮዬ ድርሰት ታሪኬ የምልሽ
ከልቤ ላይ ፅፌሽ ሳነብሽ ሳነብሽ
እንደ ልዩ ድርሰት ስገረም በስምሽ
የደመቀው ምስልሽ ከቀለም የፈካው
ቀለም በምን አቅሙ ካንቺ የሚልካካው
ከውብ ገፅታሽ ላይ ፍቅር
ተጨምሮ
ቢያደማኝ ቢያቆስለኝ ገላዬን አጥቁሮ
ጉልበት እስኪከዳኝ ቢርቀኝ ውበቴ
ዛሬም ወድሻለው ዛሬም ነሽ ህይወቴ
ባጥንቴ እስክቀር እስከለተ ሞቴ
ገጣሚ ኢብራሂም ለጃ
@ebro43
@getem
@getem
👍1🎉1
*ዋይታ*
✍ስንታየሁ ሙሉጌታ
በወየው ወየው ሀገር
በወይኔ ወይኔ ቀዬ
እሪታ የቀፈፈው ኑሮዬ
በጎ ነገር ይሰማ እንደሁ
ይናፍቃል ጆሮዬ፡፡
@getem
@getem
@gebriel_19
✍ስንታየሁ ሙሉጌታ
በወየው ወየው ሀገር
በወይኔ ወይኔ ቀዬ
እሪታ የቀፈፈው ኑሮዬ
በጎ ነገር ይሰማ እንደሁ
ይናፍቃል ጆሮዬ፡፡
@getem
@getem
@gebriel_19
ፍርድና እውነታ
########
ልብ ልብ ሳይል
በትዝታ ማዕበል
በሃሳብ ሲጉላላ...በፍቅር ሲዋልል
*
እግር የልብ ሎሌ
ሲሆንለት ታዛዥ
ባለመመበት ሳይሆን
እንዳመራው ተጓዥ
ሂድ እንዳለው ሄዶ
ባላሰበው ደራሽ
*
ዓይንም የልብ አሽከር
ልብ የጆሮ ጌታ
ዓይተው የማያዩ
ሰምተው የማይሰሙ የዓለምን ሁኔታ
ሰው ፊት ላይ የኖሩ እንዲያው ለእይታ
*
እሳትን ከበሪድ
የማይለይ ሆኖ እጅም የማይዳስስ
ጣፋጭ ከመራራ አላጣጥም ብሎ
ምላስም የማይቀምስ
አፍንጫም በቁሙ ምንም የማይሸተው
ሽታ አለይ ቢለው ቢምገው ቢምገው
*
...እንዲ እንዲህ ሆኖ
...በትዝታ ማዕበል
እያስፍወነጨፈ..ልብ እግር ካበጀ
ቀልቤ በሌለበት....
በድኔ በቆመው...
"ለየለት!!!" እያለ...ሰው እኔን ፈረጀ?
አብርሃም
@getem
@geteM
@gebriel_19
########
ልብ ልብ ሳይል
በትዝታ ማዕበል
በሃሳብ ሲጉላላ...በፍቅር ሲዋልል
*
እግር የልብ ሎሌ
ሲሆንለት ታዛዥ
ባለመመበት ሳይሆን
እንዳመራው ተጓዥ
ሂድ እንዳለው ሄዶ
ባላሰበው ደራሽ
*
ዓይንም የልብ አሽከር
ልብ የጆሮ ጌታ
ዓይተው የማያዩ
ሰምተው የማይሰሙ የዓለምን ሁኔታ
ሰው ፊት ላይ የኖሩ እንዲያው ለእይታ
*
እሳትን ከበሪድ
የማይለይ ሆኖ እጅም የማይዳስስ
ጣፋጭ ከመራራ አላጣጥም ብሎ
ምላስም የማይቀምስ
አፍንጫም በቁሙ ምንም የማይሸተው
ሽታ አለይ ቢለው ቢምገው ቢምገው
*
...እንዲ እንዲህ ሆኖ
...በትዝታ ማዕበል
እያስፍወነጨፈ..ልብ እግር ካበጀ
ቀልቤ በሌለበት....
በድኔ በቆመው...
"ለየለት!!!" እያለ...ሰው እኔን ፈረጀ?
አብርሃም
@getem
@geteM
@gebriel_19
👍1😢1
እኔ እወድሻለው ልክ እንደ ድርሰቴ
እንደ ሰውነቴ
ልክ እንደ አቦጊዳ ልክ እንደ ቃላቴ
ሀሳብ እንደ ሞላው እንደ ልብ ምቴ
እኔ እወድሻለው ልክ እንደ ሀረጌ
ልክ እንደ ስንኜ ልክ እንደ ማረጌ
እኔ እወድሻለው ልክ እንደ ልብወለድ
አስቦ አሰላስሎ ግጥም እንደመውለድ
እኔ እወድሻለው ቤት እንደመምታት
ሀያ መፅሀፎች ፃፍኩ እንደማለት
ደራሲ ነህ ተብሎ እንደመጠራት
እኔ እወድሻለው ለእናት እንደመግጠም
ዶ፡ር አብይ አንገት ልክ እንደመጠምጠም
እኔ እወድሻለው ልክ እንደ በውቀቱ
እንደ ታገል ግጥም እንደወረቀቱ
ልክ አንደራዕዬ ልክ እንደሎሬቱ
እያልኩኝ እያልኩኝ ምሳሌ ደርድሬ
ሀሳበ መውደዴን በፅሁፍ አስፍሬ
ላስጨነቀኝ መውደድ ላላወቅሽው ፍቅሬ
የፃፍኩት ደብዳቤ ከዚሁ አስፍሬ
ደግሜ ባነበው ደግሜ ባነበው ሆነብኝ አሰልቺ
ፍቅሬን ለማስረዳት አልቻልኩም አይበጅ
የመድረስ አምሮቴን ተናገርኩት እንጂ
✍✍Dani yop
@getem
@getem
@gebriel_19
እንደ ሰውነቴ
ልክ እንደ አቦጊዳ ልክ እንደ ቃላቴ
ሀሳብ እንደ ሞላው እንደ ልብ ምቴ
እኔ እወድሻለው ልክ እንደ ሀረጌ
ልክ እንደ ስንኜ ልክ እንደ ማረጌ
እኔ እወድሻለው ልክ እንደ ልብወለድ
አስቦ አሰላስሎ ግጥም እንደመውለድ
እኔ እወድሻለው ቤት እንደመምታት
ሀያ መፅሀፎች ፃፍኩ እንደማለት
ደራሲ ነህ ተብሎ እንደመጠራት
እኔ እወድሻለው ለእናት እንደመግጠም
ዶ፡ር አብይ አንገት ልክ እንደመጠምጠም
እኔ እወድሻለው ልክ እንደ በውቀቱ
እንደ ታገል ግጥም እንደወረቀቱ
ልክ አንደራዕዬ ልክ እንደሎሬቱ
እያልኩኝ እያልኩኝ ምሳሌ ደርድሬ
ሀሳበ መውደዴን በፅሁፍ አስፍሬ
ላስጨነቀኝ መውደድ ላላወቅሽው ፍቅሬ
የፃፍኩት ደብዳቤ ከዚሁ አስፍሬ
ደግሜ ባነበው ደግሜ ባነበው ሆነብኝ አሰልቺ
ፍቅሬን ለማስረዳት አልቻልኩም አይበጅ
የመድረስ አምሮቴን ተናገርኩት እንጂ
✍✍Dani yop
@getem
@getem
@gebriel_19
ህይወት ከጠራችኝ ከካቧ ወድቄ
እድል ሲጎትተኝ በሀሳብ ታንቄ
ባለፍንበት መሄድ መመለስ ባይኖርም
ትዝታ ሸጋ ነው ያሻግራል የትም
...የትም ...የትም...
በቃላት ልውውጥ የትም ስልህ ውዴ ..
የትም ካለህበት ይታያል መውደዴ
ከንፋስ በላቀው በከፍታው ሰማይ በጉርዱ ጎዳና
ባዝተው የቆለሉት ጥጥ መሰል ደመና
መሀሉ ሰንጥቄ ስመጣ ባየሁት
በፀጥታው ወደብ ከምድር እርቀት
ጭንቀትና ስጋት የህይወት እድምታ
ነብሴ ከስጋዬ ላትወድቅ ተጠግታ
ደስታዬ ከጭንቀት ተቀላቅለውበት
ህልም እየመሰለኝ የሰማዩ ሂደት
አገሬ ገብቼ ኪንዳን የማስርበት
ያለከልካይ ጉዞ ህግ እማይረቅበት
ያሁን ነፃነቴን እዛ ነው የጀመርኩት
ሸክላ መሰል ወለል የምድሩ ንጣፉ
ከሰማዩ በታች ከደመና በላይ
አልሜ ወስጄህ እዛው ከፍታ ለይ
ደብቄ ባኖርኩህ እያልኩ እመኛለሁ
የምድር ጭንቀቴን እዛ ስለረሳሁ
ባየ በቀመሰ ምስክርህ ሆኜ
በፍቅር ጥላ ስር ላንተ ስል ታምኜ
ባንተ ውስጥ ወልደኸኝ በውስጥህ ሳክትም
የነብሴ መኖሪያው እስትንፋሴም ቢቆም
ባንተ ውስጥ እስካለሁ
ይመቸኛል የትም..የትም
በኔ እና አንተ አለም የማይሆነው የለም
የውልህ የኔ ውብ..!
ከሰማይ ከፍታ ምድሪቱን ስረግጣት
ሲጠቁም ያየሁት አንዱን ያ ሌባ ጣት
እጣውን ሊሸልም እሷን ሲጠቁማት
እሱን አስታውሼ ቀን እዘክራለሁ
ያገሬን ነፃነት ፍቅርህ ውስጥ እያየሁ...!!!!
@getem
@getem
@paappii
ሮዚ የያቡ
እድል ሲጎትተኝ በሀሳብ ታንቄ
ባለፍንበት መሄድ መመለስ ባይኖርም
ትዝታ ሸጋ ነው ያሻግራል የትም
...የትም ...የትም...
በቃላት ልውውጥ የትም ስልህ ውዴ ..
የትም ካለህበት ይታያል መውደዴ
ከንፋስ በላቀው በከፍታው ሰማይ በጉርዱ ጎዳና
ባዝተው የቆለሉት ጥጥ መሰል ደመና
መሀሉ ሰንጥቄ ስመጣ ባየሁት
በፀጥታው ወደብ ከምድር እርቀት
ጭንቀትና ስጋት የህይወት እድምታ
ነብሴ ከስጋዬ ላትወድቅ ተጠግታ
ደስታዬ ከጭንቀት ተቀላቅለውበት
ህልም እየመሰለኝ የሰማዩ ሂደት
አገሬ ገብቼ ኪንዳን የማስርበት
ያለከልካይ ጉዞ ህግ እማይረቅበት
ያሁን ነፃነቴን እዛ ነው የጀመርኩት
ሸክላ መሰል ወለል የምድሩ ንጣፉ
ከሰማዩ በታች ከደመና በላይ
አልሜ ወስጄህ እዛው ከፍታ ለይ
ደብቄ ባኖርኩህ እያልኩ እመኛለሁ
የምድር ጭንቀቴን እዛ ስለረሳሁ
ባየ በቀመሰ ምስክርህ ሆኜ
በፍቅር ጥላ ስር ላንተ ስል ታምኜ
ባንተ ውስጥ ወልደኸኝ በውስጥህ ሳክትም
የነብሴ መኖሪያው እስትንፋሴም ቢቆም
ባንተ ውስጥ እስካለሁ
ይመቸኛል የትም..የትም
በኔ እና አንተ አለም የማይሆነው የለም
የውልህ የኔ ውብ..!
ከሰማይ ከፍታ ምድሪቱን ስረግጣት
ሲጠቁም ያየሁት አንዱን ያ ሌባ ጣት
እጣውን ሊሸልም እሷን ሲጠቁማት
እሱን አስታውሼ ቀን እዘክራለሁ
ያገሬን ነፃነት ፍቅርህ ውስጥ እያየሁ...!!!!
@getem
@getem
@paappii
ሮዚ የያቡ
“SHE IS A CAREER WOMAN NOT A DRUG TRAFFICKER!” FAMILY AND FRIENDS OF ETHIOPIAN WOMAN DETAINED IN CHINA SAY
https://telegra.ph/ANALYSIS-SHE-IS-A-CAREER-WOMAN-NOT-A-DRUG-TRAFFICKER-FAMILY-AND-FRIENDS-OF-ETHIOPIAN-WOMAN-DETAINED-IN-CHINA-SAY-03-16
https://telegra.ph/ANALYSIS-SHE-IS-A-CAREER-WOMAN-NOT-A-DRUG-TRAFFICKER-FAMILY-AND-FRIENDS-OF-ETHIOPIAN-WOMAN-DETAINED-IN-CHINA-SAY-03-16
Telegraph
ANALYSIS: “SHE IS A CAREER WOMAN NOT A DRUG TRAFFICKER!” FAMILY AND FRIENDS OF ETHIOPIAN WOMAN DETAINED IN CHINA SAY
Zecharias Zelalem
ግጥምና ፍቅር
(ደሱ ፍቅርኤል)
የኔ ፍቅር............
ግጥም ልፅፍልሽ አሰብኩ አሰብኩና አሰብኩ አሰብኩና
ቃላት አጠሩብኝ እንደአፍሪካ ፀጉር እንደ ቦትስዋና
የኔ ፍቅር.........
እንደ ኢህአፓ ጓድ አሁንም አሁንም ሰዓቴን አያለሁ
ስንኝ ሲነጥፍብኝ
ጭረት የበዛበት ቆሌ የመሰለ ስዕል እስላለሁ
(የሚገርምሽ ነገር)
ስላንቺ ማሰቤን ለጊዜው አቁሜ
እንደ ባህር ከዘራ ሃሳቤን ቆልምሜ
ስለከዱኝ ሴቶች ብዕሬን ባነሣ
የቅኔ ስካሬ ዓይኑን እያሻሼ ከ'ንቅልፉ ተነሣ
ላንቺ ለምወድሽ ፈልጌ አስፈልጌ ከቆጡ ከባጡ
(ያጣኋቸው ቃላት)
ለነገር ሲሏቸው እየተራኮቱ በምናቤ መጡ
ያፈቀረን ትቶ ለካደ ማሽቃበጥ ስሙ ምን ይባላል?
(ሳምንሽ ጉድ ሰራሽኝ
ስወድሽ ጎዳሽኝ)
ምናምን እያሉ እንደ ሴት ገጣሚ ማላዘን ያስጠላል
(ኤጭ)
የኔ ፍቅር..........
ፍቅርሽ ተዓምር ነው እንደ ባታ ጸበል ድውይ ይፈውሳል
የከንፈርሽ ቃና እንኳንስ ከዱካክ ከሙታን ያስነሳል
ታስታውሽ እንደሆን የሆነ ጊዜ ላይ
ማታውን ስመሽኝ ጧቱን ጀግና ሆንኩኝ
ኢንፎርቲዬን ትቼ
ዝናሬን ፈትቼ
ከንፈርሽን ታጥቄ ጦር ሜዳ ዘመትኩኝ
ታስታውሽ እንደሆን
ጥይት እንዳይመታኝ በፍቅርሽ ተከለልኩ
በጡቶችሽ መሃል ተደብቄ ተረፍኩ
አንችኮ መውደዴ አንቺኮ ናፍቆቴ
የጥይት ማምከኛ ያ'ስማት ክታቤ ነሽ ኩንፈል መድኃኒቴ
ግና ይኸው አሁን
ግጥም ልፅፍልሽ አሰብኩ አሰብኩና አሰብኩ አሰብኩና
ቃላት አጠሩብኝ እንደአፍሪካ ፀጉር እንደ ቦትስዋና
@getem
@getem
@paappii
(ደሱ ፍቅርኤል)
የኔ ፍቅር............
ግጥም ልፅፍልሽ አሰብኩ አሰብኩና አሰብኩ አሰብኩና
ቃላት አጠሩብኝ እንደአፍሪካ ፀጉር እንደ ቦትስዋና
የኔ ፍቅር.........
እንደ ኢህአፓ ጓድ አሁንም አሁንም ሰዓቴን አያለሁ
ስንኝ ሲነጥፍብኝ
ጭረት የበዛበት ቆሌ የመሰለ ስዕል እስላለሁ
(የሚገርምሽ ነገር)
ስላንቺ ማሰቤን ለጊዜው አቁሜ
እንደ ባህር ከዘራ ሃሳቤን ቆልምሜ
ስለከዱኝ ሴቶች ብዕሬን ባነሣ
የቅኔ ስካሬ ዓይኑን እያሻሼ ከ'ንቅልፉ ተነሣ
ላንቺ ለምወድሽ ፈልጌ አስፈልጌ ከቆጡ ከባጡ
(ያጣኋቸው ቃላት)
ለነገር ሲሏቸው እየተራኮቱ በምናቤ መጡ
ያፈቀረን ትቶ ለካደ ማሽቃበጥ ስሙ ምን ይባላል?
(ሳምንሽ ጉድ ሰራሽኝ
ስወድሽ ጎዳሽኝ)
ምናምን እያሉ እንደ ሴት ገጣሚ ማላዘን ያስጠላል
(ኤጭ)
የኔ ፍቅር..........
ፍቅርሽ ተዓምር ነው እንደ ባታ ጸበል ድውይ ይፈውሳል
የከንፈርሽ ቃና እንኳንስ ከዱካክ ከሙታን ያስነሳል
ታስታውሽ እንደሆን የሆነ ጊዜ ላይ
ማታውን ስመሽኝ ጧቱን ጀግና ሆንኩኝ
ኢንፎርቲዬን ትቼ
ዝናሬን ፈትቼ
ከንፈርሽን ታጥቄ ጦር ሜዳ ዘመትኩኝ
ታስታውሽ እንደሆን
ጥይት እንዳይመታኝ በፍቅርሽ ተከለልኩ
በጡቶችሽ መሃል ተደብቄ ተረፍኩ
አንችኮ መውደዴ አንቺኮ ናፍቆቴ
የጥይት ማምከኛ ያ'ስማት ክታቤ ነሽ ኩንፈል መድኃኒቴ
ግና ይኸው አሁን
ግጥም ልፅፍልሽ አሰብኩ አሰብኩና አሰብኩ አሰብኩና
ቃላት አጠሩብኝ እንደአፍሪካ ፀጉር እንደ ቦትስዋና
@getem
@getem
@paappii