ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
መልስ ያጣ ጥያቄ

ይደረስ ለጌታ
እደምነህ ጌታ እንደምነህ እግዜር
የምድሩ ገዢ ባለ ሰፊ መንበር
ባለ ሰፊ ምድር ባለ ሰፊ ሀገር
ውስጤን የሚያስጨንቅ ልቤ የጠየቀኝ
መልስ ያልተገኘለት አንድ ጥያቄ አለኝ
መልሱን ስላጣሁት አንተ መልስልኝ

በወንዶች አገር ላይ ወንዶችን ሳመክን
የሀገሬን ህዝቦች ሳበግን ሳተክን
ወጣት ስጨፈጭፍ ጎልማሳ ስገድል
እናት መካን ሳረግ ጥፍርን ስነቅል
ልክ ያኔ አይሁዶች አንተን እንዳረጉህ
በሰንሰለት ጅራፍ ምንትስ ሺ ግዜ እንደገሸለጡህ
በብረት በዱላ ልጆችህን ስገርፍ
ክፋይህን ስቀጥፍ
በጨረር አብስዬ ቆዳቸውን ስገፍ
የአንተን ህግ ጥሼ ስነግስ በህዝብህ
የአንተ ክፋይ ሆኜ ስጨክን በልጅህ

በባሩድ እሳት ናላውን ሳጨሰው
በጥይት አረር አካሉን ስጠብሰው
በጨለማ አኑሬ አይኑን ሳጨልመው
መኖሩን አስትቼ ሞቱን ሳስለምነው
እንደዚህ ስፈፅም እንደዚያ ሳረገው
እኔን የሚገርመኝ ያንተ ዝምታ ነው
ስለዚህ
የኔ መደምደሚያ መዝጊያ የሚሆነው
ይህን ሁሉ ሳረግ ዝም ብለህ ያየኸው
የተመለከትከው
ህሊናዬን ለኔ ስላስሰጠኸኝ ነው
ጥያቄዬ ይህ ነው
እስቲ መልስልኝ ሀቅ ነው ሀሰት ነው።

((ናብሊስ))

@getem
@getem
@gebriel_19
////-------/////

የማይነጋ ሕልም ሳልም
የማያድግ ችግኝ ሳርም
የማይድን በሽታ ሳክም
የሰው ሕይወት ስከረክም
እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም፡፡

#ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
እኔም ወድሃለው

ስትወደኝ ወደድኩህ
ከልቤም አፈቀርኩህ
አንተም አፈቀርከኝ
ከልብህ ወደድከኝ

ፍፁም ካንቺ ሌላ አይኔ
አያይም አልከኝ
በመውደድህ ገዝተህ
በፍቅርህ አሰርከኝ

ልክ እንደ ህፃን ልጅ
አይዞሽ የምትለኝ
አንተ እየበረደህ..
እኔን ያለበስከኝ

እንዴት መታደል ነው
ለወደዱት መኖር
በሃሳብ ተግባብቶ
በፍቅር መጣመር

እኔም አፈቀርኩ ከልቤ ካንጀቴ
ላላይ ካንተ ሌላ እስካለች ህወቴ

# ሄለን አወቀ #

@getem
@getem
@Beba_D1
"..............."
(ኤልያስ ታረቀኝ)

የምስራች ብሎ~መርዶ ነጋሪ
ብርሃና አቃጣይ~ነጭ ወረቀት ሰሪ
በዝንጀሮ ሸንጎ~አንበሳ ላይ መስካሪ
አልቦ ገቢር~ሙዳይ ሰባሪ
ከጀበና ስር~ማሕቶት ሰርቆ አዳሪ
በሞላበት ቀየ~በሞላበት ሀገር
"ሀገሬ" እያሉ የወል ስሜት መጋራት
በኡሪ ወንጭፍ~ በአምስት ፍሬ ጠጠር
ግዙፍ ሆነህ ሳለህ~ትብያ መዘረር
በአያት ጦስ~በምንጅላት ግብር
1+1=3 በሚመስል ሂሳባዊ ቀመር
ህግ ባላወቀ~ህግ በጣሰ ድምር
በበቀደሙ story~አሁን መቦጫጨቅ
ተሸንፎ መመፃደቅ~አሸንፎ መሳቀቅ
ህመም ነው~ታላቅ ውድቀት
ሃፍረት የበዛበት~ቅሌት የሞላበት

@getem
@getem
@lula_al_greeko
👍1
ጥፍር፣ጸጉር፣ክራንቻ


ከማሰብ በግራ
ከሰውነት ጽንፉ፣
በድንገቴ ክስተት
ሰዎች ገደብ ሲያልፉ፣
እንዳስብ አረገኝ
እንዳስተነትነው
ባንዲት የሰው ልብ ውስጥ
ከሰብዓዊነት ጎን አውሬነት እንዳለው።
ዳሩ
ሁሉን ሠሪ እግዜሩ ያውሬነትን ምስል
ከልብ ውስጥ ሳይገባ አኑሮታል ቀድሞ፣
በውጪው ገጻችን
ጥፍርን፣ጸጉርን፣ክራንቻን አትሞ።

<<<በተስፋ ብዙወርቅ>>>
@Tesfa_urji

@getem
@getem
👍1
አላፊው...
እንዳላየ አይቶ እያለፈኝ፣
አላልፍ ያለው...
ቀን ነው ... እኔን የደቆሰኝ !!!

#ሀብታሙ_ወዳጅ
@getem
@getem
🖤 🛩🖤

ጥርሴ ሲነቃነቅ
ወልቆ አሳየኝ በህልሜ፣
ግራ እየተጋባ
መከደን አቃተው አይኔ በድጋሜ፣
አንዴ በቀኝ
አንዴ በግራ
......ቢመስል መጫወቻ፣
ብርድ ልብሱን ይዞ መገላበጥ ብቻ፣
=====
የማይነጋ የለህ
ላይ ታች ቢኳትን ህልም ፈቺ አቶ፣
ዕለተ ሰንበቱ
ህልሜንም ፈታና
በተግባር አሳየኝ ወገኔን ቀምቶ።

🖤
🛬በኢትዮጵያ አየር መንገድ በደረሰው የመከስከስ አደጋ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን🛬
🖤

((ሳሙኤል አለሙ))

@getem
@getem
@getem
እሳት ያለበት ቤት
እሳት ያለበት ቤት መች ጭስ ይጠፋዋል
የወደቀም እንጨት መጥረቢያ ይበዛዋል
ሀገሬ ምስኪኗ ምጧ የረዘመ
ሀዘኗ የበዛ ቁስሏ ያልታከመ፡፡

ሕይወታቸው ላጡ ወገኖቻችን ነበሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑር😭😭

ብሌን

@getem
@getem
ግጥም ከ ማንጎ ፍሬ...

ወቅትህ ደርሱዋል ብለው
ሊያወርዱኝ ከዛፉ
መብሰሌን አይተውት ለመብል ሊያውሉኝ በጉጉት ሲላፉ

እንደ ቀደምቶቼ በወጉ አውርደው ገበያ ሊሸጡኝ ወይ እዛው ሊገምጡኝ
ና እስኪ ውረድ ብለው ሁሉም ቢለምኑኝ
በመኩራራት መንፈስ አሻፈረኝ አልኩኝ

እህህህ.........

ተስፋ አልቆረጡም ሌላ እድል ሰጡኝ
ድንጋይ አወናጭፈው ሞከሩ ሊያወርዱኝ
ዘንግተሀል ብለው የበቀልኩበትን ፍሬ ወርውረው ሊመቱኝ

ግን ምን ያደርጋል....

ወጣትነት ሆኖ በትዕቢት አብጬ ስፎክር ሳሽላላ
ሁሉም አለፈና በስብሱዋል ተብዬ
ቀረዉ ሳልበላ

በ ኑእሸም....

@getem
@getem
@Beba_D1
--ከተማሪዋ ለጉልቤው የተላከ--


ጭሱም የእናቴ ነው ከማድቤቱ ማውቀው
ቅጠሉም ባገሬ ከዛፉ ላይ ሆኖ የሚወዛወዘው
ፍየል አይደለሁኝ ቅጠል ባፌ ይዤ የማመነዠከው
ምድጃም አይደለሁ ጭሱን ከአፌ በራፍ የማንቦለቡለው
መማሬ መልፋቴ ካልቀረ መድከሜ
ፍየል መሆን ሳይሆን ሰው መሆን ነው ህልሜ።

እናምልህ ጓዴ፡ ጓዴ ጉልበተኛው አትበለኝ እንቃም
የምኖረው እድሜ እንኳንስ ለመቃም ለመኖር አትበቃም
አስታውሳለሁኝ ያኔ...
ሀገር ማለት ላንተ ምንድነው ያልኩህ ለት
"ሀገር ማለትማ 'country'ማለት ናት የምንኖርባት''
ብለህ ስትመልስ ከአይምሮዬ አይጠፋም የቋንቋክም ለዛ
አልተጠራጠርኩም ሀገርህን ሸጠህ ጫት እንደምትገዛ።

ጉልቤው በጉልበትህ ትምህርትህ ተሳክቶ
አንደማይህ አውቃለሁ ይሄ ስብዕናህ ለኀላፊነት በቅቶ
ታድያ እንደለመድከው በዙሪያህ ያሉትን በጉልበትህ ገዝተህ
ስትኖር ይታየኛል በሀብት ተትረፍርፈህ
በየዋሀን እንባ አንተ ተደስተህ
ደግሞም ይታየኛል
ድሀው ገንዘብ አቶ ሳይበላ አንባሻ
በጀርባክ ተኝተህ ስትጠባ ሺሻ
ይታየኛል አዎ በአይኔ ድቅን ይላል
የሚደበደብ ህዝብ ጩሀት ይሰማኛል
የህፃን ልጆች እንባ ከሩቅ ይታየኛል
አዛውንቱ ቆሞ አንተን ይለምናል።

ከዚ ሀሉ መሀል
ያንተ የጭካኔ ሳቅ በጆሮዬ ይመጣል
ከምትቅምበት ቤት የሚወጣው እጣን በአፍንጫዬ ያልፋል
በምናቤ እያሰብኩ እኔኑ ያመኛል
ስለዚህም ጓዴ፡ጓዴ ጉልበተኛው አትበለኝ እንቃም
የምኖረው እድሜ እንኳንስ ለመቃም ለመኖር አትበቃም
ህዝብ እያለቀሰ ካንተ ቤት አልመጣም
ወገኔ ውሀ ጠምቶት እኔ ውስኪ አልጠጣም።

ይልቅ ባንተ ኑሮ በወደፊት ምናብ እኔው ከምታመም
በተስፋ ገስግሼ ወደ ነገዋ እኔ በሀሳቤ ልትመም
ብዙ በጎ አላማ ትልቅ ህልም አንግቤ
የህዝብ ኀላፊነት አደራን ደርቤ
ልታገል መጣሁኝ ያንተ አይነቱን ጉልቤ
ሀገሬና ህዝቤን ማገልገል ተርቤ
አይደለም ጉልቤነት ኩራትና ልብሴ
ለፍትህ መሞት ነው የማንነት ውርሴ
የሀገሬን ችግር ሸክም ልቀበላት
የህዝቤን አደራ የተረከብኩ ሰአት
ልጅዋን ለማስተማር የምትጓጓ እናት
ዘመዴ መሆኗ መስፈርቷ አይሆንም
ልጅዋ እንዲማርላት
የተጎዳ ደሀ የእውነት ፈራጅ ያጣ
100ብር መያዙ አያሳስበውም ወደኔ ሲመጣ
የስራ ሀሳብ ይዘሽ ወደኔ ስትመጪ
በሀሳብሽ እንጂ በመልክሽ አይደለም ምትስተናገጂ፡፡

የሚደበደብ ህዝብ የሚያለቅስ ህፃን
እግዚኦታን ሚያሰማ የአዛውንት እርግማን
ዳግም ላይመለስ ከሀገሬ ምሎ
በኔ ጊዜ ይወጣል ከቀዬው ኮብልሎ
አንተ ግን
ለፈፀምከው ስህተት ላፈሰስከው እንባ
የፀፀት አለንጋ ቅጣት ነው ሚገባህ
እንዲህ ያለ አላማ ስላለኝ ትልቅ ህልም
እውቀትን ነው እንጂ እኔ ጫት አልቅምም
ስለዚህም ጓዴ አትበለኝ እንቃም
የምኖረው እድሜ እንኳንስ ለመቃም
ለመኖር አትበቃም።

(( ንፁህ ግርማ))

@getem
@getem
@gebriel_19
"ይድረስ ለሄዋኔ "

ኑሮ እንዴት ይዞሻል እንዴት ነሽ ሄዋኔ
ይመስገን ደህና ነኝ አታስቢ ለእኔ
..................ይልቅስ ሄዋኔ
ወጣትነት አልፎ እርጅና ሳይመጣ
ከቻልሽ ነይልኝ ፡ካልሆነ እኔ ልምጣ
ግን ልትመጪ ከሆነ ፡መንገድ
ሳትጀምሪ
ማንነቴን ሰምተሽ ፡ከቀረሽም ቅሪ
ወደ እኔ ለመምጣት ሀሳብ ስትሰንቂ
የሞላ ቪላ ቤት ፎቅ እንዳትጠብቂ
ጥሪትም የለኝም ወርሼ የማወርስሽ
ቤት ማጀቴ ፡ባዶ ጮማ እንዳላጎርስሽ
ልብሴም ድሪቶ ነው ፡ፊቴም ውበት
የለው
ልቤም የእንባ ናዳ ክህደት ፡ያቆሰለው
ግን ይህን ሁሉ አይተሽ መፀየፍ
ሳይረታሽ
ንፁህ ፍቅሬ ገዝቶሽ ፡ወደ እኔ
ከመጣሽ
እ.ጠ.ብ.ቅ.ሻ.ለ.ሁ........በደስታ
ፈንጥዤ
በሰባራው ልቤ ንፁህ ፍቅርን ይዤ፡፡

@getem
@getem
@gebriel_19
1
+++++

ካንተ ቤት...
ቋንጣ ተሰቀለ
ሻኛ ተቆረጠ፣ ወይን እየተጠጣ፣
...
ያ’ዳም ዘር ወንድምህ
ያለ ሁዳዴ ፆም በ’ራብ የ’ተቀጣ፡፡


ይገርማል
አንተ ማለትኮ...
አንተ ማለት ጠጋብ ያለልክ ሠልቃጭ፣
እሱ ማለት ደግሞ...
እሱ ማለት ሚስኪን ካንተ ቤት ቀላዋጭ፣
...
እንዲህ ነው ተፈጥሮ እግዜሩ ሲያዳላ፣
አንዱ ፆሙን ሲያድር ሌላኛው ሲበላ፡፡


...
በተራበች ነፍሱ
...........................ቀልቡ እየዋለለ፣
ድህነት ሰቅዞት
...........................ሳይበላ እየዋለ፣
ሂወት ጨክናበት
ቆዳ ምላሽ ሊያገኝ
..........በጌቶቹ ቅዬ ፍሪዳ እየጣለ፣
ለሁዳዴው ፆም ፍቺ
በግ ሲጠባ ያድራል ቢለዋ እየሳለ፣
...
እንዲህ ነው ተፈጥሮ እግዜሩ ሲያዳላ፣
አንዱ ፆሙን ሲያድር ሌላኛው ሲበላ፡፡


...
ትቀምሰው ያጣች ነፍስ ቁራሽ ንጣይ ቅምሻ፣
በጣር ሲቃ ታንቃ ስታጣ መድረሻ፣
ፍርድ አጥተን ከሰማይ የ'ግዜር እጅ መንሻ፣
ሠው የሠው አገልጋይ ሠው የመንደር ውሻ፣
ሲ ጎ መ ጅ ይኖራል - በ በ ሊ ቶ ች ጉርሻ፡፡

@getem
@getem
@gebriel_19
///ፍጥረተ ገመድ///
❖❖❖❖
ፍፁም ይገርመኛል የገመድ ተፈጥሮ
ነፃነቱን ያጣል ባላንጣውን አስሮ

(በረከት ታደሰ)

@getem
@getem
የኑረዲን ኢሳ (እኔ ምን አገባኝ) በሚለው ግጥም ላይ የተመሰረተ ግጥም ( ርዕሱ ነው)


እኔ ምን አገባኝ የምትሉት ሀረግ
እሱ ነው ሀገሬን ያረዳት እንደበግ
የሚል ግጥም ልፅፍ ብድግ አልኩኝና፤
ምን አገባኝ ብዬ ቁኝ አልኩ እንደገና።


ይህን ግጥም ሊፅፍ
ብዕሩን አንስቶ
ምን አገባኝ ብሎ የተቀመጠ ሰው፤
ምንስ አግብቶት ነው
ምን አገባኝ የሚል ግጥሙን የፀፋው።

የሚል ግጥም ልፅፍ
ብድግ አልኩኝና ፤
ምን አገባኝ ብዬ ቁጭ አልኩ እንደገና።

ስንታየሁ አዲሱ ሳንታ
(@san2w)
2011 woldia university

@getem
@getem
@gebriel_19
።።። እሺ ይበልጣል ከሺ ።።።።።።

ይሄንንም እሺ...........
ያኛውንም እሺ...........
ሁሉን ስለው እሺ........
የኔ ምለው ጠፍቶ ተካፈልኩኝ ለ ሺ
ሀ.ገ.መ

@getem
@getem
@gebriel_19
(((( ልመና ))))
እንቅፋቴ በዝቶ ህይወት ቢያስጨንቀኝ
ጠላቴ እንዲጠፋ ፈጣሪን ለመንኩኝ::
"
"
ታድያ . . . . . .
"
"
"
ፀሎቴን ጨርሼ ብገልጥ አይኖቼን
አጣዉ ጓደኞቼን::

@getem
@getem
@gebriel_19
/////ብስል እንደ ጥሬ////

ሳንተያይ ...ተሳስበን ፤
በጥቅሻ ....ተጠራርተን፤
ቃል ሳይወጣ ...ተግባብተን፤
ተለያይተን..... ተገናኝተን ፤
ተገናኝተን..... ተለያይተን ፤
ሳንግባባ .....ብንጋባ ፤
ፍቅር ገደል ገባ ።
«ጨዋታው ፈረሰ አባይ ደፈረሰ።»
ያኔ ባሳለፍነው የእቃቃ ጨዋታ፤
ዛሬም በአዋቂነት አብሮነት ተገታ ።

ደረጄ ዳኜ
@getem
@getem
@gebriel_19