ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
የትኛው ነሽ አንቺ



ፀደይ ነሽ መስከረም ?
ግማሽ መልክሽ አደይ ግማሽ መልክሽ አረም።
ግማሽ የሚቀጠፍ ግማሽ የሚነቀል ፣
የትኛውን ልመን ምንሽን ልቀበል፤
የተኛው ነሽ አንቺ ምህረት ወይስ በቀል?
ስምዖንን መስለሺኝ መስቀሌን ስትይዢ
ለአንድ ሠሞን ፍዳ፣
በየት ዞረሽ ሸጥሽኝ ለብቻ መከራ
ደግሞ እንደ ይሁዳ።


✍️©እስራኤል
   (@AdamuReta)

@getem
@getem
@getem
🔥47👍3719😁7🤩6😱4🎉1
እኔ እንደናፈቅኩሽ ታውቂያለሽ አውቃለሁ
አንቺ ሌላ ወደሻል ሌላ ተላምደሻል አዎን ሰምቻለሁ
የሰማሁት ነገር ሀሰት ይሁን ብዬ
አምላክ ለምኛለሁ
ሻማውን ለኩሼ ጧፍ እያበራሁኝ ተማፅኘዋለሁ
አንቺን ያጣሁ ዕለት ጠፍቷል የኔ ብርሃን
እንደ አምላክ ስቅለት ያውም በእኩለ ቀን
ይሄን ሁሉ መዓት እያየሽው ባይንሽ 
ነገ የተሻለ ነው ለምን ትይኛለሽ ?
የኔ ፀሐይ ትናንት ማለፉን እያየሽ
የኔ ጀንበር አንቺ መሆንሽን እያወቅሽ ?
በርግጥ ነገ እንዳለ በልቤ አምናለሁ
ቀኑ መሽቶ ይነጋል ይህንን አውቃለሁ

ግን ታውቂያለሽ አንዳንዴም

የ ጀንበር መውጣቷ ሌሊት አያነጋም
ጎህ መቅደዱ ብቻ ጨለማ አያጠፋም
በትር የያዘ ሁሉ ባህሩን አይከፍልም
ባለ ወንጭፍ ሞልቶ ጎልያድን አይጥልም
ገባኦን ካልሆነ አትቆምም ፀሐይም
አንቺ የሌለሽበት ሁሌ ጨለማ ነው ጀንበር ባትጠልቅም

                        ዘረ-ሠናይ
               @SenayArt
@getem
@getem
@getem
👍5726🔥9😢5👎2🤩2🎉1
ሀገር ስጠኝ...

ሀገር ስጠኝ እስቲ ወዳጄ
ማለት ሚያስችለኝ ''እዛ ሄጄ
ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ"

ሀገር ስጠኝ የምኮራበት
መልስ የሌላቸው እንቆቅልሾች የማይበዙበት
ግራ ሲገባኝ ምን አውቄልህ ማልባልበት

እስቲ ሀገር ስጠኝ አንድ ትልቅ
ከሰፈር ጎሳ ከብሄር ሚልቅ

ሀገርን ስጠኝ ሰላም ያለበት
ሰው ለፍቶ ሰርቶ የሚያተርፍበት
ካለሰቀቀን የሚኖርበት::

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
👍7322🔥2🤩1
ትናንትና ጠዋት
ፀሐይ የመሰለች ቆንጆ ልጅ አይቼ
በሊቀ መልዓኩ
እንዴት ምታምሪው አልኩኝ ድምፅ አውጥቼ
ትንሽ ኮራ እያለች ጥቂት ፈገግ ብላ አለችኝ "ከላይ ነው"
ባለቤቱ የፈራው "ዉስጥሽ"ስ እንዴት ነው ?

                  ዘረ-ሠናይ
@SenayArt

@getem
@getem
@paappii
🔥23👍218😁7😢2
እዉነት እንዳይመስልሽ
.
.
ዛሬ ......ምን ብትደምቂ፤
ከቆነጃጅቱ እጅጉን ብትልቂ፤

ኑሮ ተመችቶሽ ያ.... ፊትሽ ቢወዛ፤
ወደድኩሽ የሚለዉ አፍቃሪሽ ቢበዛ ፤

ሴትነትሽ ማለት... መልክ ከመሰለሽ፤
ፍፁም አትመኪ እዉነት እንዳይመስልሽ፤

አንቺን ሳያማክር........

የጠቆረዉ ፀጉርሽ.. በሽበት ይተካል፤
ጸአዳዉም መልክሽ በፍጥነት ይረግፋል፤

ሴትነትሽ ማለት መልክ ከመሰለሽ፤
ፍፁም አትመኪ እዉነት እንዳይመስልሽ።
..........................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
58👍23👎4
ጥላሞት
(shadow
)



አንድ ጥያቄ አለ
ነብሴን ሁልግዜ
የሚያብሰለስላት
ገሀድ የማይገልጠው
ማነው የኔ ጠላት?
ማነው እንቅፋቴ
ጉድባ ለመንገዴ
ሌላ አካል አለ
ወይስ ክፉ ገዴ?

ማነው ከነብሴ ጋር
ያረገኝ ባላንጣ
ህዋው ነው ጠላቴ
ወይስ ክፉ እጣ?

ጀርባዬን ለህልሜ
ማነው ያሰጠኝ ሰብ
ወይስ አቅቶኝ ነው
ተስኖኝ ነው ማሰብ?

ማነው ማነው ማነው?

በዳይ ስጋ ችሮኝ
'ሚያስረግም ዕለቴን
ሬት ሆኖ ኑሮ
'ሚያስናፍቀኝ ሞቴን

ማነው ማነው ማነው?

ስደምር ስቀንስ
ስመትር ስለካ
እኔ ፊት የቆምኩት
ራሴው ነኝ ለካ።

ይሄን ያወቅሁኝ ቀን
ይሄ የገባኝ 'ለት
ፊት የቆመው እኔን
ገለል አረግሁለት።

አሁን ጸሐይ ወጣ።


✍️©እስራኤል


@AdamuReta

@getem
@getem
@getem

Inspiration(ንሸጣ) : psychological podcast about self sense and shadow
👍3630
ልማድ ቢሆንብን ቃሉ ከአፋችን
"እንዴት ነህ?"
ስንባል ደህና ነው መልሳችን
ለሰው የማይነግሩት ቢሆን ታሪካችን
ይሸሸግ ጀምሯል በሶስት ፊደላት
ጥልቁ ህመማችን

:- "እንዴት ነህ?"
:- ደህና ነኝ!!

በኪሩቤል አሰፋ @Ebuh_bhr

@getem
@getem
@getem
👍7821🔥9
ጊዜ ደጉ 🕔

ሰው ከኔ ሲለየኝ

ያመንኩት ሲርቀኝ

መሄጃው ሲጨንቀኝ

ፍረሀት እምነቴን እየሸረሸረ

እንዴት እሆን ብዬ እሰጋ ነበረ
:
:
:
ለካ ጊዜ ደጉ ለሁሉም ይደርሳል

እምባዎች ያብሳል

ቁስል ይፈውሳል

ፈጠነም ዘገየም መከራን ያስረሳል።

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
56👍43🔥1😢1🎉1
.....
እሱ እኮ.. እያሉ ባሞገሱህ ቁጥር፤
አንተን እያነሱ ባወደሱህ ቁጥር፤

ልብህን አይሙቀዉ ፍፁም ደስ አይበልህ፤
ቀን የከፋ ለታ.........
ቁልቁል ይጥሉሃል....... እላይ የሰቀሉህ።
......................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
👍6311
▪️▪️አባቴ▪️▪️▪️

ምተማመንብህ ምኮራብህ አባዬ

ስወድቅ ምታነሳኝ የኔ መከታዬ

ለቤትህ ምሰሶ ትከሻህ ጠንካራ

ለልጆችህ ስትል ሳትደክም ምትሰራ።
:
:
ፍቅርህን ሳትሰስት ሰጥተህ ያሳደከኝ

መልካም ሰው መሆንን ለኔ ያስተማርከኝ

አባቴ ውለታህ እጅጉን ብዙ ነው

ከማመስገን በቀር ሌላ ምን እላለው።
:
:
ምፈልገው ቢኖር ታላቁ ምኞቴ

ደስታህን ማየት ነው ሳለው በህይወቴ

አባቴ አድምጠኝ ስማኝ ይሄን ስልህ

በጣም ወድሀለው እኔ ያንተ ልጅህ።

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
68👍31👎4🔥2😱1
ሲያምርብሽ ቀሚስ ጥልፉ
ሲያምርብሽ ነጭ በነጩ
ህፃናቶች ከእግርሽ ስር
ተኮላትፈው የሚንጫጩ
እረበሹሽ ከጸሎትሽ
የዳዊቱን ቦታ አጣሽ?
እንደ መልአክ ነጭ አልብሶ
ቤተመቅደስ ምን አመጣሽ?
ከመልክሽ ላይ ይታየኛል
የአብ እጁ ልዕልና
በሁዳዴ ቤቱ መጣሽ
ጌታን ልትይ ሆሳዕና?

ሆሳዕና በአርያም
ሆሳዕና በአርያም
ንጉስ አየን ከድንግል ሴት
ፀሀይ ወጣ ከአርያም

ከቅዳሴው ዜማ ሰማን
መንበር መሃል እጣን ጨሰ
ህዝበ እስራኤል
ጨርቁን ሁሉ
እመሬት ላይ አለበሰ

የምስጋናው ዜማ ጦፈ
መንፈስ ቅዱስ ህዝቡን መላ
በወንጌሉ ክብር አገኘች
የያዘችው ውርንጭላ

ህዝቡ ሞልቷል ከመቅደሱ
ወንዱም ሴቱም ለየብቻ
በነጠላ ተሸፍነሽ
ምትታዪኝ አንቺ ብቻ
ከአጠገብሽ ጎልማሳ ሴት
ሲደገፉሽ ማትከፊ
የደከማት አራስ እናት
ልጇን ይዘሽ የምታቅፊ
በነጠላ የሚያምር ገጽ
ለመንካትም የሚያሳሳ
ጸጉርሽን ሸፍነሻል
ዋናው ነገር ፊትሽሳ?

ላለማየት እጥራለው
ነጣላሽን ስታጣፊ
ወዴት ላርገው ይዤ ቆምኩኝ
የዘንባባ ዝንጣፊ

ምን ላድርገው ዘንባባውን ?
መስቀል ልስራ ለግንባርሽ
ከብልጭልጭ ከወርቅ አልማዝ
መስቀሉ ነው ሚያሳምርሽ

በቢጫዋ ዘምባባስ ግን
አይኔ አይቶ ከመረጣት
ቀለበትን ልስራ ይሆን
ለእጆችሽ ሰልካካ ጣት?

በአራቱም መአዘናት
ተነበበ ወንጌል ለአለም
ምህላችን ይቀጥላል
እስኪመጣ ለዘላለም
አንድ ሳምንት የፆም ስግደት
ህማማቱ ሊጠብቀን
ከበሮውን ሰማይ ሰቅለን
አመስግነን ለአንድ ቀን

ከመድረኩ ነጭ ለብሰው
ከበሮውን እየመቱ
ክብ ሰርተው ሲዘምሩ
እንደያኔው ህፃናቱ
ምን ተሰማሽ በድምቀቱ
አይኔ ካንቺ ተመልክቷል
ጠብታ ውሃ የምታክል
ዘለላ እንባ ከአይንሽ ወቷል
ለምን አዘንሽ በደስታ ቀን
ይታወቃል
የልቦናሽ   ንጽህና
የእግሮችሽን ጣቶች ላንፃ
ፀሎተ ሀሙስ ይድረስና?

አትፈልጊም አውቃለሁኝ
እንኳን ማጠብ እንዲያዩሽም
የኤደን ውስጥ በለስ እንጂ
የዱር ኮሽም አይደለሽም
ታዲያ ያለሙን ጣጣ ረስቶ
ልቤ ሰከን ከሚልበት
እንዲታወክ ቤተ መቅደስ
ባትመጪ ምን አለበት?

ሆሳዕና በአርያም
ሆሳዕና በአርያም
ንጉስ አየን ከድንግል ሴት
ፀሀይ ወጣ ከአርያም

የገላውን ስጋ ቆርሰው
በቀናት ውስጥ የሚገሉት
ጨርቃቸውን አገላድመው
በእልልታ ተቀበሉት
የኛ ህዝብም ደምቋል ዛሬ
መስቀል ሰርቷል ከመረጠው
ጎልጎታ ላይ እስኪሰቀል
ወዳጅ ስሞ እስኪሸጠው
የኔ ግና ተበጥሷል
የአይኔ ላይ መቀነቻ
ከዚህ ሁሉ ተነጥለሽ
ምትታዪኝ አንቺ ብቻ
ምናለበት ባገለግል
ቤተመቅደስ ሌላ አላጣሽ
እንደ መልአክ ነጭ አልብሶ
እኔ ደብር ምን አመጣሽ?

By @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
83👍33😢6🎉5🔥2😱1
ድብልቅልቅ ነው ውስጡ
ውልቅልቅ ነው ጌጡ ....
ሰባራ ነው ውበት 
ጥቁር አለው የኛ ሽበት!
ወጣት ነው የጠገበ
ነበልባል ነው የረገበ
መዳፍ ነው የማይሞላ
ፍቅር አለን የሚያባላ !
ሰላም ነው የሚረብሽ
ንፁህ ነው የሚቆሽሽ
መሬት ነው ሁሉንም ቻይ
እያኖረ ገዳይ!
ሰፊ ነው ገፀ ብዙ
ጠባብ ነው ፅንስ ሙሉ
በቂ ነው ቻይ ተራፊ
ለ'ኔ ና አንቺ ሰፊ!
ባህር ነው ሞገደኛ
ሃይቅ ነው ሰላምተኛ
አለም ነው ዥንጉርጉሩ
አንጀት ነው ለኛ ሩሩህ!
ፍቅር ነው ፍፁም ልዩ!!


   
Follow my IG & Tiktok @be_Olyon

       ✍️ Olyon
                       
           
              አስተያየት (@be_Olyon)


     @getem
                   @getem
                                  @getem
👍7023👎3😱3🔥2
ሥዕል ለወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ማበርከት የምትፈልጉ በ+251984740577 ይደውሉ።


ወይም @gebriel_19 ላይ  ፎቶ  በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ  ማዘዝ ይችላሉ!



@seiloch
@seiloch
7👍6
ሥዕል ለወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ማበርከት የምትፈልጉ በ+251984740577 ይደውሉ።


ወይም @gebriel_19 ላይ  ፎቶ  በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ  ማዘዝ ይችላሉ!



@seiloch
@seiloch
5👍5
ሙሾ አውራጅ እንባ አርጋፊ
ምሬት ዘሪ ሞት አቃፊ
ደስታ ማላቅ ሐዘንተኛ
ሁሌ አልቃሽ ብሶተኛ

ግና ዛሬ
ድቅድቅ ጥሼ እንባ ላፈስ
በመንገድ ላይ ስንከላወስ
ድንገት ቆመ
የቅጽሩን ጥግ እግሬ ታኮ
ይጸልያል ምዕመኑ ተንበርክኮ

አሰገግኩ ወደ ውስጥ
አማተርኩ አጮልቄ
ምን ልተንፍስ? ... ምን አውቄ?
ምስጋና እንደው አልለመደኩ
በዝምታ አለቀስኩ

{ለቅሶ አይደል የለት ጉርሴ?
ምሬት አይደል እስትንፋሴ?}

እመቤቴ
በእንባ መሐል አየሁ ምስልሽን
ስታጫውች ውብ ልጅሽን

በዛች ቅጽበት
ተሰለበ ሹል ብሶቴ
ተገፈፈ ጽልመት ፊቴ
ልቤ ጠጣ
ከእቅፍሽ ሀሴት ቀድቶ
እንኳን እኔ
ሐዘን ሳቅ አንቺን አይቶ

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
70👍22🤩3😁2😢2🔥1
ረዘምዘሜ
--------------

ይወድሻል ቢሉሽ

ጸሀይ ትገባለች
ቢሉሽ በስተምስራቅ፣
ውሸት ነው በያቸው፣
ከነሱ በመራቅ፡፡

ምድር ጠፍጣፋ ነች፣
ቢሉሽም መልሰው፣
ሀሰት ነው በያቸው፣
ሳትቆጥሪያቸው ከሰው፡፡

አውራ ዶሮ እንቁላል
ይጥላል በማለት አጉል ቢሞግቱሽ፣
ቅጥፈት ነው በያቸው፣
የማይሆን ቢግቱሽ፡፡

ጽጌረዳ አበባን፣
ቢሉሽ ይች አደይ ናት፤
ሀቅ አይደል በያቸው፣
ትጊና በጽናት፡፡

ይሆናልም ቢሉሽ
ሰው እያደር እሸት፣
ብለሽ አጋልጫቸው---
‹‹አቤት! አቤት ውሸት! ››

ከኤሊና ጥንቸል፣
ቢሉሽ ኤሊ ፈጣን፣
ቀላማጅ! በያቸው፣
ተሞልተሸ በሥልጣን፡፡

ይህ ሰው አስር ሺ ዐመት፣
የሚኖር ነው ቢሉሽ ያለቅንጣት እፍረት፣
ይህ እውነት አይደለም፣
በያቸው በድፍረት፡፡

በዙ ውሸት ዋሽተው፣ ግን ቢሉሽ አንችዬ፣
‹‹ፍቅሬ ይወድሻል ከነፍሱ አስበልጦ!››
አንዳች ሳታመነች ‹‹እውነት ነው!›› በያቸው፣
ድምጽሽን ከፍ አርገሽ ፣ ሰምተሸ በተመስጦ፡፡

4/30/2017

By fikre tolosa

@getem
@getem
@paappii
👍3725🔥2😁2🤩2
#ፀሃይና_ጨረቃዬ
.
.
.
በራሷ ልክ ለምታውቀኝ የኔን ናፍቆት ያቺን ድሃ፣
ላንዱ ልቤ የልቡ ራ'ብ ሆና ብትፈልቅ የፍቅር ውሃ።
ነይ ብሏታል ሰርክ ናፍቆ እዝነ ነፍሴ ተመልክቷት፣
ከሺ ልባም ከሴት መሃል ከቀይ እንቁ እሷን ሽቷት።

ትመጣለች እኔን ብላ፤
ትመጣለች ሀሳብ ጥላ፤
የምታውቀው ሩህሩህ መላዕክ በፍቅር ዘንግ እየመራት፣
መቼም እሱ ያውቅበታል፤
ከመጨከን ሳይቀላቅል ልቤ መሃል እሷን 'ሰራት ።

ከቆምኩበት ከዚያው ስፍራ፤
ባክሽ ፍጠኝ ድረሽ እያልኩ ከራሴ ጋር ሳጉረመርም፣
ከሀሳብ ባህር የወደቀን ብኩን እኔን ቆሜ ሳርም።
መጣችልኝ ያይኔ አበባ መጣችልኝ የልቤ ሰው፣
እንባና ሳግ ወንድ አንጀቴን ቁጡ ፊቴን ሳቅ ወረሰው።
( እኔ የምልሽ ? መቼ ነው ግን፤ )
( ስሜሽ ስሜሽ ስሜሽ ስሜሽ ከጥጋብ ደጅ የምደርሰው ? )
እንጃ'ባቴ !!!!!

ልብላ አላለች ወይ ልጠጣ፤
ልውረድ የለም ወይም ልወጣ፤
ናፍቆት ሆኖ የሷም ረሃብ ካለም ሁሉ የተለየ፤
ከወንዶቹ አስበልጦ ከህዝበ አዳም እኔን ያለ።
ፍቅር  አይኗን ከደነችው፤
ጠፍር አልጋ መሃሉ ላይ ግራ እጄን ተንተርሳው፣
ሙቅ ትንፋሿ እፍፍ ሲለኝ ወንድ አካሌ ነፍሴን ረሳው።

አጀብ መቼም ያየሁትን፤
ስትነካካኝ በጣቶቿ ስትዳብሰኝ በመዳፏ፣
ንጉስ መሆን የዛን'ለት "የኔ አባት" ሲለኝ አፏ።
በነፍሷ ጫፍ ምኑ ዳሬን የቱ ጋር ነው የነካችኝ፣
የተጣላሁ ከራሴ ጋር በምን ብልሃት አስማማችኝ ?

በአርምሞ በፀጥታ፤
አይኗን አየሁ ሽፋሽፍቷን፤
ተመለከትኩ የነፍሷን ሀቅ ተኝታለች አለም ረስታ፣
አንገቴ ስር ካገኘችው ስስ ህይወቷን ተጠግታ።
የዛን'ለታ........
እያለ
እያለ
እያለ "ልሂድ" አለኝ፤
እኛን ሲያዩ የፈገጉ ሰማይ ምድር ተላቀቁ፤
በመሄድ ውስጥ ተከርችመው ነገን ሊሉ ሲታረቁ።
እቅፍ ብርሃን ፈነጠቀ ከአፅናፍ አፅናፍ ተዘረጋ፣
ፀሃይና ጨረቃዬን፤
በአክናዴ እንዳቀፍኳት ሆነ አዲስ ቀን ሌቱ ነጋ።
.
.
.
"አይኗን ገልጣ አይኔን አየች ከኔ ማዶ የራሷን ሀቅ፣
ፈገግ ብላ አዋሰችኝ የሰጧትን የ'ግዜሯን ሳቅ።"
                     
            ስትችልበት !!!!!!


ዓቢይ ( @abiye12 )




@getem
@getem
@getem
👍4425🔥4🤩1
እሱና እሷ

እሱና እሷ ከአንድ ቀን እይታ፣
ወዳጅነት ፈጥረው ፍቅር ተገንብታ፣
ተፈቃቅረው ከርመው ዓመታትን ቆጥረው፣
ጎጆ ለመቀለስ በአንድ ለመጠቅለል ሽማግሌ ልከው፣
ህይወት በአዲስ መልኩ ተጀመረ ይኸው።

የአንድ ቀን እይታ ዛሬ ፍሬ አፍርቶ፣
ሙሽሪት ፀንሳ ቤተሰብ መስርቶ፣
ሁለትነት ቀርቶ በዝተው ተበራክተው፣
ዘር የሚያስቀጥል አዲስ ትውልድ ፈጥረው፣
ባል አክብሮ ሚስቱን ሚስት ለባል ተገዝታ፣
ፍቅርና መቻቻል በእነሱ ላይ ታይታ፣
ለማየት በቅተናል ፍቅራቸው አፍርታ።

በሳምሪ የዝኑ ልጅ

@getem
@getem
@getem
55👍35🔥3👎2🎉1