ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ ይህንንም #ቤተ መቅደስ #ናቡከደነጾር ተነስቶ #በ587 ዓ.ዓ #አፈረሰው {2ኛ ነገ 25፤ 8-17}። ብዙዎችንም #ንዋየ ቅዱሳትና ህዝቡን #ማርኮ ወደ #ባቢሎን ወሰዳቸው። ይሁን እንጂ እንደገና #ከ70 ዓመት ቡኋላ #ዘሩባቤል ተነስቶ #ቤተ #መቅደሱን ሰራ {ዕዝ 3፥6}። #ሄሮድስም እንደገና አስፋፍቶ ሰራው። #ዘካርያስ ሲያገለግልበት የነበረው #ቤተመቅደስ #የሄሮድስ #ቤተመቅደስ ሲሆን ንድፉ ይህን ይመስላል፦
<<የቃል ኪዳኑ ታቦት፤ በባቢሎናውያን ተዘረፈ፤ ወይስ ወደ ኢትዮጵያ መጣ፤ ወይስ ምድር ዋጠችው?>>

* "የእግዚአብሄርንም ንዋየ ቅድሳት ትልቁንም ትንሹንም ሁሉ፥ የእግዚአብሄርንም #ታቦት የንጉሡንም ቤት ዕቃ ሁሉ #ዘርፈው ወደ #ባቢሎን ወሰዱ" (ዕዝራ ካልዕ 1፥54 የ2000 ዕትም)

" እግዚአብሄርን የሚያገለግሉበት ንዋየ ቅድሳቱን ጥቃቅኑንምና ታላላቁንም ዕቃ ሁሉ፥ የእግዚአብሄር ማደሪያ #ታቦትንም ከቤተ መንግሥት ዕቃ ቤትም ያለውን ሳጥን ሁሉ #ማርከው ወደ #ባቢሎን #ወሰዱ" (ዕዝራ ካልዕ 1፥54 የ1980 ዕትም)

* የቃል ኪዳኑ ታቦት በሰለሞን የንግሥና ዘመን በቀዳማይ ምንሊክ አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል። (ክብረ ነገስት)
እንደ ክብረ ነገስት ዘገባ ታቦቱ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው በሰለሞን የንግሥና ዘመን ነው። እንደ ዕዝራ ካልዕ ደግሞ በሴድቅያስ የንግሥና ዘመን ተዘርፎ ወደ ባቢሎን ተወስዷል። የሰለሞን የንግሥና ዘመን መጨረሻ 931 ቢወሰድና በ2ቱ ሰዎች መካከል የነበረውን ዘመን ልዩነት ለማወቅ ጥረት ሲደረግ የ344 ዘመን ልዩነት መኖሩን ማወቅ ይቻላል። ማለትም በዕዝራ ካልዕ መሰረት የቃል ኪዳኑ ታቦት ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል ከተባለ ከ344 ዓመታት ቡሀላ ባቢሎናውያን ዘርፈው ወስደውታል።

* "ባሮክና ኤርምያስም ወደ ቤተ መቅደስ ገቡ፤ የሚያገለግሉበትንም ዕቃ ሁሉ ጌታ እንዳዘዛቸው ለምድር ሰጧት፤ ምድርም ያን ጊዜ ተቀብላ #ዋጠችው" (ተረፈ ኤርምያስ 8፥13 የ1980 ዕትም)

"ባሮክና ኤርምያስም ወደ ቤተ መቅደስ ገቡ፤ የሚያገለግሉበትንም ዕቃ ሁሉ ጌታ እንዳዘዛቸው ለምድር ሰጧት፤ ምድርም ያን ጊዜ ተቀብላ #ዋጠችው" (ተረፈ ባሮክ 2፥13 የ2000 ዕትም)

ዩቱ ነው ትክክል?

፦ ቴዎድሮስ ደመላሽ "80 አሀዱ በእግዚአብሄር ቃል ሲመዘን" 3ተኛ ዕትም ጥር 2010.

@gedlatnadersanat