Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
300 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሩሲያ እየተከናወነ ከሚገኘው የዓለም አቀፍ የአቶሚክ ፎረም ጎን ለጎን ከዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኢኔርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ማርያኖ ግሮሲ ጋር ተወያይተዋል።
7👍1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያዩ
++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የኃይል ማመንጫ፣ ግብርና፣ የጤና ጥበቃ ልማትና የመከላከያ ትብብርን ጨምሮ ሰፊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ለማኅበረሰብ አገልግሎት የሚውል ንፁህ ኃይል ምንጭ የጋራ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ የማልማት ስምምነቶችን ጨምሮ የጋራ ፍላጎት በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይቱ መካሄዱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመልክቷል። #PMOEthiopia
13👍5
እንኳን ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ

የመስቀል በዓል ሲታሰብ እውነት ተቀብራ እንደማትቀር እናስባለን። መስቀሉ የተቀበረበት ቦታ ተራራ ሠርቶ ነበር። የቀበሩት ሰዎች ከዚህ በኋላ እንደማይወጣ ደምድመው ነበር። አንዳንድ አማኞችም ተስፋ ቆርጠው ነበር።

ጊዜው በረዘመ ቁጥር ቀባሪዎቹ ያሸነፉ መስሏቸው ተደሰቱ። የተቀበረው መስቀልም ታሪክ የሆነ መሰለ።

ብርቱ ሰዎች፣ እውነት ፈላጊ ሰዎች፣ አቧራውን የሚገልጡ፣ ቆሻሻውን የሚያነሡ ሰዎች፣ ሲመጡ ግን መስቀሉ ከተቀበረበት ወጣ።

እውነት አይቀበርም። ጊዜው ሲደርስ አቧራውን አንሥቶ ዐሻራውን ያሳያል። ሐሰቱን እንደ ጉም አትንኖ፣ ሐቁን እንደ ዐለት አግንኖ ያሳያል።

የኢትዮጵያም እውነት እንደዚሁ ነው። የአውራ ዶሮዎች ጩኸት የፀሐይን መውጣት አያስቀረውም። የሌሊት ወፎች ክንፍ የፀሐይን ንጋት አያግደውም። በዚህም ተባለ በዚያ ፀሐይ ትወጣለች።

የኢትዮጵያ እውነት እንደ መስቀሉ ሁሉ አቧራውን ጥሶ፣ አፈሩን አፍልሶ፣ ቆሻሻውን ደርምሶ ይገለጣል። የወጓት ያዩዋታል። ከላይ ሆነው እንዳዩዋት ሁሉ፣ ከታች ሆነው ይገረሙባታል።

በመደመር ደመራ እየተመራን፣ በትጋት እየቆፈርን፣ የኢትዮጵያን ብልጽግና እናወጣዋለን። ይህ ዓመት የኢትዮጵያ ብርሃን ሲወጣ የምናይበት ይሆናል።

በድጋሚ መልካም የደመራና የመስቀል በዓል ይሁንልን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ.ም
8👍2😁1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ያደረጉት ውይይት‼️

#PMOEthiopia
👍53
#ጋዜጣ_ፕላስ- የመስቀል ደመራ አከባበር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ‼️
3
የመስቀል ደመራ በዓል በባህርዳር ከተማ መከበር ጀመረ
++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የመስቀል ደመራ በዓል በባህርዳር ከተማ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ መከበር ጀምሯል።
2