“ኢትዮጵያ ማርበርግ ቫይረስን በአጭር ጊዜ መቆጣጠሯ የጤና ስጋቶችን የመመከት ብቃት እንዳላት አሳይቷል”
- የዓለም ጤና ድርጅት
++++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስ በሽታን በአጭር ጊዜ ውስጥ መቆጣጠሯ ከባድ የጤና ስጋቶችን የመመከት ብቃት እንዳላት በተግባር ያሳየ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ሺሳካ ካሶሎ አስታወቁ።
ኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሯን በተመለከተ በተዘጋጀው የማብሰሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት ፍራንሲስ ሺሳካ ካሶሎ (ፕ/ር) እንደገለጹት፤ ሀገሪቱ የዓለም ጤና ድርጅት ባስቀመጠው መስፈርት መሠረት በሽታውን መቆጣጠሯ ተረጋግጧል።
በሽታ ድንበር እንደማያከብር የጠቀሱት ተወካዩ፤ ቫይረሱ በታወጀ በ24 ሰዓታት ውስጥ የዓለም ጤና ድርጅትና ሌሎች አጋሮች የተቀናጀ ድጋፍ ማድረጋቸውን አብራርተዋል።
ኃላፊው አክለውም ለጤና የሚደረግ ወጪ እንደ ኢንቨስትመንት መታየት እንዳለበትና ቫይረሱን በመቆጣጠር ሂደት የተገኙ ትምህርቶችን ለወደፊት ዝግጁነት መጠቀም እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ በአንድነት ቫይረሱን ድል ያደረገች ሲሆን፤ በቀጣይም ጠንካራ የጤና ሥርዓት ለመገንባት መሥራት እንዳለባት አመልክተዋል።
በሄለን ወንድምነው
#ጋዜጣ_ፕላስ #ማርበርግ_ቫይረስ #ጤና_ሚኒስቴር #የዓለም_ጤና_ድርጅት #ፍራንሲስ_ካሶሎ #ኢትዮጵያ

❤3👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ክህሎትና አዳዲስ ስራ ፈጠራዎች......
የኢትዮጵያ መንግሥት ወጣቶች የራሳቸውን የፈጠራ ስራዎች (startups) እንዲጀምሩ፣ ወደ ስራው ዓለም እንዲቀላቀሉና በዘመናዊው ኢኮኖሚ ስርዓት ውስጥ ስኬታማ እንዲሆኑ የሚያስችሏቸውን ተግባራዊ ክህሎቶች ለማስጨበጥ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና መርሃ ግብሮች ላይ ሐብት ፈሰሰ እያደረገ ይገኛል።
በሙያ፣ በቴክኖሎጂና በስራ ፈጠራ ዘርፎች ላይ ቀጥተኛ ልምድ በመስጠት፣ እነዚህ መርሃ ግብሮች አዳዲስ ፈጠራዎችን ያነቃቃሉ፤ የሥራ ዕድሎችን ይፈጥራሉ፤ እንዲሁም የኢኮኖሚ ዕድገትን በመሠረታዊነት ያፋጥናሉ።
ወጣቶችን ከገበያው ፍላጎት ጋር የተጣጣሙ ክህሎቶችን ማስታጠቅ፣ የግለሰቦችን የኑሮ ሁኔታ ከማሻሻሉም ባሻገር የተነቃቃና ለስራ ፈጣራ አመች የሆነ ኢኮኖሚ እንዲገነባ በማድረግ የልማቱ ተጠቃሚነት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች እንዲዳረስ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
#PMOEthiopia #VisionOfProsperity #የኢትዮጵያብልጽግናራእይ

❤1
በመልዕክት መላላኪያ ፕላትፎርሞች የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶችን አስመልክቶ የቀረበ የጥንቃቄ መልዕክት
+++++++++++
#ፕሬስ_መረጃ_ማጣሪያ_ በዋትሳፕ፣ በቴሌግራምና በሌሎች የመልዕክት መላላኪያ ፕላትፎርሞች የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶችና የማጭበርበር ድርጊቶች በመበራከታቸው ፕላትፎርሞቹን ሰንጠቀም ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ለፕሬስ መረጃ ማጣሪያ በላከው መግለጫ አሳስቧል።
የግል መረጃ ለመስረቅ፣ የባንክ ሂሳቦችን ለመመዝበርና የዲጂታል ደህንነትን ለማናጋት በተቀናጀ መልኩ እየሰሩ መሆኑን አስተዳደሩ በክትትልና በምርመራ ማረጋገጡን ገልጿል።
👉 https://www.facebook.com/share/p/1Mi7fs37hG/
#ኢንፎርሜሽንመረብደህንነትአስተዳደር #informationNetworkSecurityadministration

❤5👍1
በ2030 የኢትዮጵያ የመድኃኒት ገበያ 3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል
+++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | እ.ኤ.አ በ2030 የኢትዮጵያ የመድኃኒት ገበያ 3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስና ሀገሪቱ የአፍሪካ የመድኃኒት ኢንዱስትሪ ማዕከል ለመሆን እየሠራች መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፍሬህይወት አበበ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ በተደረጉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች የሀገር ውስጥ የመድኃኒት አቅርቦት በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ይገኛል።
የመድኃኒት አምራቾች እስከ አምስት ዓመት ከታክስ ነፃ የእፎይታ ጊዜ ማግኘታቸው ለዘርፉ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አብራርተዋል።
የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን የብስለት ደረጃ ሦስትን ማሳካቱ በሀገር ውስጥ የሚመረት መድኃኒት በየትኛውም ሀገር ገበያ ላይ እንዲቀርብ ዕድል እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎችን በመፍጠር ለሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ለውጭ ገበያ የሚተርፍ የመድኃኒት ምርት ለማምረት በቁርጠኝነት እየሠራች መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ አመልክተዋል።
በክብረአብ በላቸው
#ጋዜጣ_ፕላስ #ጤና_ሚኒስቴር #መድኃኒት_ኢንዱስትሪ #ኢንቨስትመንት #የምግብና_መድኃኒት_ቁጥጥር #ኢትዮጵያ

❤8
የኢትዮጵያ የስንዴ ፕሮግራም ምርታማነትን በመጨመር፣ የመስኖ ሥርዓትን በማስፋት፣ የዘር አቅርቦት ሥርዓትን በማጠናከር ብሎም በዋና ዋና አካባቢዎች አነስተኛ አርሶ አደሮችን በመደገፍ የሀገራችንን ራስን የመቻል ጉዞ ግብ ላይ የተመሠረተ ነው።
በ2018 የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሩብ ዓመታት አጠቃላይ የስንዴ ምርት 126.69 ሚሊዮን ኩንታል ደርሷል። ይኽም የመስኖ ስንዴ ምርትን ሳይጨምር ነው። አርሶ አደሮቻችንን ማድነቅና ማመስገን እፈልጋለሁ። ይኽንኑ የሥራ ጽናት ቀጥሉበት!
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
#ስንዴ #መስኖ_ልማት #የበጋመሰኖ #የበጋመሰኖስንዴ #ግብርና #አርሶአደሮች

❤1🤮1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የገጠር ትሥሥር....
መንግሥት የሐገሪቱን አርሶ አደሮችን ከአካባቢያቸውና ከክልል የገበያ ስርዓቶች ጋር ለማስተሳሰር የገጠር መንገዶችንና መሰረታዊ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ላይ ይገኛል።
ይህም በመላ ሀገሪቱ የሸቀጦችና የግብዓቶች ዝውውር እንዲሻሻል እያደረገ ነው። እነዚህ ተግባራቶች ይወስድ የነበረውን የጉዞ ስዓትና የትራንስፖርት ወጪን በመቀነስ አርሶ አደሮች ምርቶቻቸውን በብቃት እንዲሸጡ፣ ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ እንዲሁም እንደ ጤና ጥበቃ፣ ትምህርትና የግብርና ድጋፍ ያሉ አስፈላጊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ያስችሏቸዋል።
በጥቅሉ የተሻሻለ የትስስር መረብ የአካባቢ ኢኮኖሚን ከማጠናከሩ ባለፈ፤ ልማት በሁሉም የሐገሪቱ ክፍሎች እንዲዳረስ በማድረግ አካታች እድገት እንዲሰፍን አይተኬ ሚና ይጫወታል።

❤6👎1🔥1