✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.2K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
💚 @mezmurat123 💚
💛 @mezmurat123 💛
❤️ @mezmurat123 ❤️
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🔆ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ለማወቅ ትክክለኛው ቻናል🔅
👇
ለመቀላቀል ከስር ሰማያዊውን ይጫኑ
⚠️JOIN OUR⚠️
CHANNEL & GROUP

♻️ 📖 ገና እንዘምራለን
🔺የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇
👉 @mezmurat123 👈
👉 @mezmurat123 👈
👉 @mezmurat123 👈
👉 @mezmurat123 👈
👉 @mezmurat123 👈
👆👆👆👆👆👆

♻️ 📖 ደጓ እናቴ ማርያም
♦️የእመቤታችን አስራት ልጆች መሰባሰቢያ፣ መማሪያ ድንቅ ቻናል
✔️ @embtee
✔️ @embtee
✔️ @embtee
✔️ @embtee

♻️ 📖 ️የ እመብርሀን ልጆቸ
🔺ኦኦርቶዶክስ ተዋህዶ እናቴ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 https://tttttt.me/joinchat/EmxkTg3kSPqonu9_bhCMsg
https://tttttt.me/joinchat/EmxkTg3kSPqonu9_bhCMsg
https://tttttt.me/joinchat/EmxkTg3kSPqonu9_bhCMsg
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

💢እስከ አሁን እነዚህን ድንቅ ድንቅ ቻናሎች ያላዩ ወዳጆች አሏችሁ
አሁኑኑ ለአምስት ወዳጆቻችሁ ብቻ ላኩላቸው
እናመሰግናለን።
⚠️ለሌሎች እንዲደርስ📩#Share እንዳይረሳ

🔰ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር።🔰
✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️
✞ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ✞
† †እንኳን ለአብሳሪ መልአክ፣ ለነገደ አርባብ አለቃ፣ ለራማው ልዑል ቅዱስ
ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን †

ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ
ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ በክርስቲያኖች ዘንድ
ይወደዳል፡፡ ምክንያቱም ያዘኑትን ለማጽናናት የምሥራች ለመንገር
ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ይላካልና፡፡
ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል ጌታና አገልጋይ ማለት ነው፡፡
ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱሳን ሰማእታት ገድላቸውን እንዲፈጽሙ
እሳቱንና ስለቱን ተሳቀው ወደ ኋላ እንዳይመለሱ ይረዳቸዋል፡፡
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን የቅዱሳን መላእክትን ወርኃዊና ዓመታዊ
በዓላቸውን በፀሎትና በምሥጋና ታከበራለች፤ በተለይ ታህሣሥ 19 ቀን
የሚከበርበት ምክንያት ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሠለሥቱ ደቁቅን
ከዕቶነ እሳት ( ከነደደ እሳት ) ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡
በጣዖት ፍቅር እጅግ ከመጠን በላይ ልቡ ተቃጥሎ የነበረው የባቢሎን መሪ
ናቡከደነጾር ቁመቱ ስድሳ ወርዱ ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቅ ምስል አሰርቶ
መኳንንቱን ሰብስቦ ሕዝቡ በሙሉ ለጣኦት እንዲሰግድ አዋጅ አወጀ፡፡ ያ ዘመን
ለእግዚአብሔር ወዳጆች የፈተና ዘመን ነበር፡፡ አስመሳዮች ለጣኦት ሰገዱ
ተረበረቡ፡፡ እውነተኛው አማኞች ግን በእግዚአብሔር ላይ ያላቸው እምነት ንጉሥ
የወደደው ጊዜ የወለደው በሚል አስተሳሰብ አይለወጥም፡፡
በዚያ ፈታኝ ዘመን ነበር ሶስት ታማኝ የእግዚአብሔር ባለሟሎች የተገኙት፡፡ ንጉሡ
ላቆመው ጣኦት ያልሰገደ ወደ እቶን እሳት ተጥሎ እንደሚሞት ቁርጥ ውሣኔው
መሆኑን ወጣቶቹ በሚገባ ያውቁታል ግን ይህንን አልፈሩም፡፡ ንጉሥ ሆይ
አምላካችንን በመካድ አንተ ላቆምከው ጣኦት አንሰግድም አሉት፡፡ ሶስቱ
ወጣቶች የወሰዱት ይህ አቋም ለንጉሡ ታላቅ ራስ ምታትን ፈጠረ፤ ንጉሡም
አገልጋዮቹን ጠርቶ እሳቱ ሰባት እጥፍ እንዲነድ ትዕዛዝ ሰጠ እሳቱም ሰባት
እጥፍ ነደደ፡፡
ወዲያውኑ የንጉሡ አገልጋዮች አናንያን፣ አዛርያ፣ ሚሳኤልን እያንከበከቡ ወደ
እቶን እሳት ወረወሯቸው ፡፡ ሠለስቱ ደቂቅ ከየት እንደመጣ ከማይታወቅ እንግዳ
ጋር በመሆን በዕቶን እሳት ውስጥ ይንሸራሸሩ ጀመር፡፡ ይህ ተዓምራት ንጉሡንና
መኳንንቱን አስገረመ ንጉሡም በዚህ ወቅት እነሆ እኔ በእሳቱ መካከል
የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ እሳቱ ምንም አላቆሰላቸውም አራተኛውም
የአማልክትን ልጅ ይመስላል አለ፡፡
የነደደ እሳት ውስጥ ገብቶ ከመውጣት ባልተናነሰ መከራ ውስጥ ገብተው
በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ከሞተ ሥጋ ነፍስ ድነው እውነተኛ
ምሥክርነታቸውን የሚሰጡ ብዙዎች ናቸው፡፡ በመልአኩ ስም በፈለቀው ጠበል
ተጠምቀው ደዌ የራቀላቸው እጅግ በርካታ ናቸው፡፡ በየዓመቱ በቁልቢና በቅዱስ
ገብርኤል ስም በታነጹ አብያተ ክርስቲያናት የሚሰበሰበው ምዕመናን ሥዕለቱ
የሰመረለት ልመናው የተሰማለት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ ለመላእክት አለቃ
ለቅዱስ ገብርኤል የተሰጠውን ጸጋ ተረድተን የመልአኩን አማላጅነት በመጠቀም
ልናከብረው ይገባል፡፡
የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ረድኤት እና በረከት አይለየን - አሜን
#Join 👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEzwE8Rx0_ELfmMHsg
Forwarded from Dere blak
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ✞
ታህሳስ 24
† †እንኳን ለጻድቁ አባታችን ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት የልደት የመታሰቢያ
ክብረ በዓል ዋዜማ በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን ከጻድቁ አባታችን ከአቡነ
ተክለ ሃይማኖት ረድኤት በረከት ያሳድርብን አምላከ ተክለ ሃይማኖት በቸርነቱ
አይለየን አሜን !!! † †
ታህሳስ 24 በዚህች ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለሃይማኖት የተወለዱበት ቀን
ነው። የትውልድ ቦታቸው ሸዋ ጽላልሽ አወራጃ ዞረሬ ነው፤ የአባታቸው ስም ጸጋ
ዘአብ የእናታቸው ስም እግዚ ሐርያ ይባላል መካን ነበሩ ልጅ እንዲሰጣቸው ወደ
እግዚያብሔር ዘወትር ይጸልዩ ነበር፤ መጋቢት 12 ቀን እንዲህ ሆነ፤ ሞተሎሜ
የተባለ ጣኦት አምላኪ ንጉስ አገራቸውን ወረረ መንደሩንም አጠፋ ጸጋ ዘአብ
ወንዝ ውስጥ ገብቶ አመለጠ እግዚ ሐርያ ግን ተማርካ ሄደች፤ በጣም መልከ
መልካም ስለነበረች ሞቶሎሜ ሊያገባት አሰበ ታላቅ ድግስም ደገሰ አገር
ምድሩ ተሰብስቦ ሲዘፍን ሲጨፍር ሳለ ቅዱስ ሚካኤል ታላቅ መብረቅ ነጎድጓድ
አሰማ ብዙዎች ሞቱ እግዚሐርያን በክንፎ ተሸክሞ ዞረሬ ከቤተክርስቲያን ውስጥ
አስቀመጣት ከባለቤቷ ጸጋ ዘአብ ጋር ተገናኙ ተቃቅፈው ተላቀሱ፤ከሁለት ቀን
በኋላ መጋቢት 24 ቀን ተክልዬ ተጸነሱ በ 1167 ዓ/ም ተወለዱ ቀኑ አርብ ነበር፤
በተወለዱ በ3ኛ ቀናቸው እሁድ በ 3 ሰዓት “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ
ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” ብለው ስላሴን አመሰገኑ፤ ሁለተኛ ተአምር
ከዚህ በታች ያለው ስዕል ተክልዬ የአንድ ዓመት ከመንፈቅ ህጻን እያሉ ነው፤
በድፍን ሸዋ ርሃብ ተከስቶ ነበር በተለይም በዞረሬ እግዚሐርያ አዘነች አለቀሰች
ምነው እርቧት ነው ጠምቷት ነው ቢሉ የለም እርቧትስ ጠምቷትስ አይደለም
የቅዱስ ሚካኤል ዝክሩ ታጎለቢኝ ብላ እንጂ፤ ህጻኑ ተክልዬ ከእናቱ ጭን ወርዶ
እየዳኸ ወደ ጓዳ ሄደ አንስታ አቀፈችው እርሱ ግን አለቀሰ ዱቄት የተቀመጠበትን
እንቅብ እንድትሰጠው በእጁ ጠቆማት ሊጫወትበት መስሏት ሰጠችው በትንንሽ
እጆቹ እንቅቡ ላይ አማተበ ዱቄቱ ሞልቱ ፈሰሰ ዳግመኛ የቅቤ የዘይት
ማስቀመጫ ማድጋዎች ላይ በተመሳሳይ አማተበ ሞልቶ ፈሰሰ ቤቱ በበረከት
ተትረፈረፈ፤የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን አዘከረች አገሬውን ጠርታ
መገበች፤ለተቸገሩትም አብዝታ ሰጠች፤ ይህ በረከት ሁለቱም እስኪሞቱ ድረስ
አላለቀም ይላል ገድላቸው። ተክልዬ በ 99 ዓመት ከ 10 ወር ከ 10 ቀን በዚህ
ምድር ኖረው ነሐሴ 24 ቀን አርፈዋል። በደብረሊባኖስ ገዳማቸው የንፍሮ ውኃ
አይነስውር ያበራል ድውይ ይፈውሳል ገድላቸው ሊነበብ ሲወጣ አጋንንት
ተቃጠልን ይላሉ ሲገርም ምን ያህል ባለጸጎች ነን። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።
አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ለመስቀሉ ክቡር አሜን ። ይቆየን
#Join 👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEzwE8Rx0_ELfmMHsg
♻️ እግዚአብሔርን አመስግኑ ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም ነውና
መዝ፣117-29

📣ገና እንዘምራለን🔉
♥️የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት

#Join👇👇 ይቀላቀሉ
♦️ @mezmurat123
♦️ @mezmurat123
♦️ @mezmurat123

🔰 ኑ አብረን እናመስግን🔰
♦️ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት ,ጥያቄ እንዲሁም
መዝሙሮች ለመላክ
ለመዘመርም
የመዝሙር ግጥም Lyre.ለመላክ👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

Contact👇👇ይላኩልን

1⃣ @bezaale

2⃣ @maryamn123bot

3⃣ @yitaya

⛔️ታይቶ አይታለፍም ሼር ይደረጋል

ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር።
በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት ኃጢአታችንን በሦስት መልኩ
እንናዘዛለን፡፡ በመጀመሪያ ለራሳችን ፣ ከዚያም በካህናት ፊት በዝርዝር ፣
እንዲሁም በጸሎት በእግዚአብሔር ፊት ከጾምና ስግደት ጋር እንናዘዛለን፡፡
ለራሳችን መናዘዝ እንዳለብን የሚያስረዳን የጠፋው ልጅ ታሪክ ነው፡፡ የአባቱን
ንብረት ይዞ ወደ ሩቅ ሀገር የሔደው ያ የጠፋው ልጅ ወደ ልቡ ሲመለስ እንዲህ
ብሎ ነበር ፡- ‹ወደ አባቴ ቤት እሔዳለሁ … እንዲህ እለዋለሁ .. አባቴ ሆይ
በሰማይና በፊትህ በደልሁ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅህ ልባል አይገባኝም ከባሮች
አንዱ አድርገኝ› (ሉቃ. 15፡17) ከዚህ በኋላ ወደ አባቱ ተነሥቶ ሔዶ ይቅርታን
አግኝቷል፡፡ያለቦታው ለራስም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ኃጢአትን መናዘዝ ግን በቂ
አይደለም ፤ በቂ ቢሆን ኖሮ የአስቆሮቱ ይሁዳ ‹ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ
በድያለሁ› በማለቱ ይድን ነበር፡፡ (ማቴ. 27፡4)
ሁለተኛው ኑዛዜ ከታች በዝርዝር የምንመለስበት በካህናት ፊት የምንናዘዘው ኑዛዜ
ነው፡፡
ሦስተኛው ኑዛዜ ደግሞ በካህናት ፊት ከተናዘዝን ተገቢው ተግሣጽ ምክርና ቀኖና
ከተሠጠን በኋላ በእግዚአብሔር ፊት በጾምና በስግደት የምናቀርበው የንስሐ
ጸሎትና ኑዛዜ ነው፡፡ ለዚህም ምሳሌ የሚሆነን በእግዚአብሔር ነቢይ በናታን ፊት
‹እግዚአብሔርን በድያለሁ› ብሎ ኃጢአቱን ካመነ በኋላ ‹‹አቤቱ እንደቸርነትህ
መጠን ማረኝ እንደ ይቅርታህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ ፤ ከበደሌ ፈጽሞ
እጠበኝ ከኃጢአቴም አንጻኝ› በማለት ያነባው ንጉሥ ዳዊት ነው፡፡ (2ሳሙ. 12፡
13 ፤ መዝ. 50፡1)
ከሦስቱ ኑዛዜዎች በአንዳንዶች ዘንድ ጥያቄ የሚያስነሣው በካህናት ፊት
የሚደረገው ኑዛዜ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በካህናት ፊት ኃጢአትን ስለመናዘዝ ምን
ይላል?
ከቀድሞው የብሉይ ኪዳን ዘመን ብንጀምር አንድ ሰው በእግዚአብሔር ሕግ
ከተሠራው በአንዱ በደል ቢገኝበት ኃጢአቱን በካህን ፊት ኃጢአቱን እንዲናዘዝና
ካህኑ ኃጢአቱን እንዲያስተሰርይለት ታዝዞ ነበር፡፡ (ዘኁ.5፡5-6) አካን የተባለ ሰው
ኃጢአትን በሠራ ጊዜም በወቅቱ ለነበረው የእግዚአብሔር አገልጋይ ለኢያሱ
ኃጢአቱን ተናዝዞ ነበር፡፡ ኢያሱ ኃጢአቱን እንዲናዘዝ አካንን ሲጠይቀው ‹‹ልጄ
ሆይ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብርን ሥጥ ለእርሱም ተናዘዝ ፤
ያደረግከውን ንገረኝ አትሸሽገኝ›› በማለት ኃጢአትን ለካህን መናዘዝ
ለእግዚአብሔር ክብር መሥጠትና ለእርሱም መናዘዝ እንደሆነ አስረድቶናል፡፡
(ኢያ. 7፡7)
ይህንን ስንጠቅስ ታዲያ አንዳንድ ሰዎች ‹ይኼማ ብሉይ ኪዳን ነው ፤
አልፎበታል› ይላሉ፡፡ ወደዚህ ጉዳይ ሳንገባ ግን ለካህናት ኃጢአትን መናገር
የእግዚአብሔርን ክብር የሚጋፋ ከሆነ በብሉይ ኪዳንም የነበረውም አምላክ
እግዚአብሔር አይደለም ወይ ለምን ለካህናት ተናዘዙ ብሎ ፈቀደ? ብለን
መጠየቃችን የግድ ነው፡፡
በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት መጀመሪያ አዋጅ ነጋሪ የነበረው መጥምቁ ዮሐንስም
በዮርዳኖስ እያለ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ እየመጡ ‹ኃጢአታቸውን እየተናዘዙ›
ይጠመቁ ነበር፡፡ (ማቴ. 3፡6) ኑዛዜን መስማት የጌታን ክብር መገፋት ቢሆን ኖሮ
መንገድ ጠራጊው ቅዱስ ዮሐንስ በፊቴ አትናዘዙ ብሎ እንደልማዱ ያለ ፍርሃት
በገሠጻቸው ነበር፡፡
በግልጽ ደግሞ ጌታችን ለሐዋርያቱ ‹በምድር ያሰራችሁት በሰማይ የታሰረ ፤
በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሆናል› በማለት ሥልጣንን ሰጥቷቸዋል፡፡
ይህም ሐዋርያቱ የሚፈቱልን እስር ‹ማዕሰረ ኃጢአት› (የኃጢአት ማሰሪያ)
እንደሆነ በዮሐንስ ወንጌል የበለጠ ግልጽ ሆኖ ‹ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው
ይቀርላቸዋል ፤ የያዛችሁባቸውም ተይዞባቸዋል› ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (ማቴ.16:19
ዮሐ. 20:23) ሐዋርያት ሰው ራሱ በኑዛዜ ያልነገራቸውን ኃጢአት ይቅር ሊሉትም
ሆነ ሊይዙበት አይችሉም፡፡ በተሠጣቸው ጸጋ የሰውን ኃጢአት ያለ ኑዛዜ አውቀው
ይቅር ቢሉ እንኳን የሰውን ግላዊ አጥር (privacy) የሚጋፋና ‹ልትድን
ትወዳለህ› ሳይሉ ማዳን ይሆንባቸዋል፡፡ በዚህ መሰረትም ሰዎች በሐዋርያት
ስብከት ወደ ክርስትና ሲመጡ ‹ያደረጉትን እየተናዘዙ› ነበር፡፡ (ሐዋ. 19፡18)
ቅዱስ ያዕቆብም በመልእክቱ የታመመ ሰው ካህናትን ይጥራ ካለ በኋላ በዚያው
አንቀጽ ‹እርስ በእርሳችሁ ኃጢአታችሁን ተናዘዙ› በማለት እንደኛው ሥጋን
በመልበሳቸው እኛን ለሚመስሉ ስንታመም ለሚጸልዩልን ለካህናት
ኃጢአታችንንም እንድንናዘዝ አዝዞናል፡፡ (ያዕ. 5፡16-17)
ኃጢአታችንን ለካህናት መናዘዝ እንዲመክሩን እንዲገሥጹን ብቻ አይደለም ፤
‹ይቅር ያላችኋቸው ይቅር ይባልላቸዋል› በሚለው ሐዋርያዊ ሥልጣን
ስለተሾሙና ይቅርታን የማሠጠት ሥልጣን ስላላቸው ነው፡፡ ለሐዋርያት
የተሠጠው ሥልጣን ሲወርድ መምጣቱን (Apostolic succession)
ስለምናምን ነው፡፡ ለምክር አገልግሎት ብቻ ከሆነማ ቢሮ ከፍተው የሚያማክሩ
የስነ ልቡና ባለሙያዎች ሞልተዋል፡፡
የካህናት ኃጢአትን ይቅር ማስባል ከክርስቶስ ሊቀ ካህናትነት እና ይቅር ባይነት
ጋር የሚጋጭ የሚመስላቸውና በሐዲስ ኪዳን ከሊቀ ካህናት ክርስቶስ በቀር
ሌሎች ካህናትና አገልግሎታቸው አያስፈልግም የሚሉም አሉ፡፡ ለዚህ ብዙ
ሳንደክም ከጥያቄው ላይ መልስ ማውጣት እንችላለን፡፡ ሊቀ ካህናት የሚለው
ስም ብቻ ራሱ ሌሎች ካህናት መኖራቸውን ያሳያል፡፡ሊቀ ካህናት ማለት
የካህናት አለቃ ማለት ሲሆን ሌሎች ካህናት በሌሉበት የካህናት አለቃ የሚል
ስያሜ ሊኖር አይችልም፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ የካህናት አለቃ ፣ የእረኞች አለቃ
ሲሆን ቀሳውስት ደግሞ ካህናት እረኞች ይባላሉ፡፡ (ራእ. 5፡9 ፤ 1ጴጥ. 5፡4)
በኦሪት ሦስት ዓይነት ስያሜ ነበረ ፤ ሊቀ ካህናት (የአሮን ቤት የበኩር ልጅ) ፤
ካህናት (በኩር ያልሆኑ የአሮን ልጆች) ፤ ሌዋውያን (ከአሮን የማይወለዱ የሌዊ
ነገድ ልጆች) ነበሩ፡፡ ሊቀ ካህናቱ በዓመት አንዴ ወደ ቅድስቱ የሚገባውና እጁን
ዘርግቶ የእንስሳ መሥዋዕት የሚያቀርበው ነበር፡፡ ካህናት የሚባሉት ደግሞ
መሥዋዕቱን በመሠዊያው ላይ በማድረግና በዕጣን ማጠን በመሳሰለው
አገልግሎት የሚራዱት ናቸው፡፡ ሌዋውያን ደግሞ ካህናቱን ዝቅ ብለው
የሚታዘዙ አገልጋዮች ነበሩ፡፡ በሐዲስ ኪዳን እጆቹን በመስቀል ላይ ዘርግቶ ራሱን
መሥዋዕት አድርጎ ስለእኛ የሠጠ ሊቀ ካህናት መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፡፡
ይህን ‹ብሉ ጠጡ› ብሎ የሠጠንን መሥዋዕቱን (ሥጋና ደሙን) በመሠዊያው
(በታቦተ ምሥዋዑ) ላይ የሚያቀርቡና የሚያገለግሉት የዛሬዎቹ ካህናት ደግሞ
ቀሳውስት ናቸው፡፡ እንደ ቀደሙት ሌዋውያን የዛሬዎቹን ካህናት ቀሳውስትን
እየተራዱ ለተልእኮ የሚፋጠኑት ደግሞ ዲያቆናት ናቸው፡፡ ሊቀ ካህናት ክርስቶስ
ዛሬም ከካህናቱ ጋር በቤተ መቅደሱ አለ ፤ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ቅዱስ
ጳውሎስ እንዳለው የቀደሙት ‹በድንኳኒቱ የሚያገለግሉ (የኦሪት ካህናት)
ከእርሱ ሊበሉ የማይቻላቸው መሠዊያ (ታቦተ መሥዋዕ (Christian Altar))
አለን፡፡ ሊቀ ካህናት የሚለው ቃል ኦርቶዶክሳዊ ሥዕሉ ይህ ነው፡፡(ዕብ. 13፡10)
የቀረን የመጨረሻ ጥያቄ ካህናት በኑዛዜ ኃጠአትን ይቅር ማስባላቸው
ከእግዚአብሔር ይቅር ባይነት ሥልጣን ጋር የሚጋፋ አለመሆኑ ነው፡፡ ይቅር ባይ
ልዑል እግዚአብሔር ነው ፤ ካህናት የሚጸልዩልን የንስሐ ጸሎትና ፍትሐት
ዘወልድ መልእክቱም ይህ የእግዚአብሔር ይቅር ባይነት ነው፡፡ የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት ኃጢአታችንን በፊታቸው ከተናዘዝን
በኋላም ሙሉ ሥልጣን እንደተሰጣቸው "ኩኑ ፍቱሐነ (የተፈታችሁ ሁኑ) ቢሉም
ጸሎታቸውን ሲያሳርጉ ግን በት
ሕትና ‹‹ከኃጢአት ማሰርያ እግዚአብሔር ይፍታ››
ይላሉ እንጂ ‹ፈትቼሃለሁ ፤ ንጻ ብዬሃለሁ› የሚል ቃል ብቻ ከአፋቸው አይሰማም፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEzwE8Rx0_ELfmMHsg
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ✞
✞ ✞ እንኳን ለቸሩ መድኃኔዓለም ወርኃዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም
በጤና አደርሳችሁ አደረሰን ! መድሐኒዓለም ክርሰቶስ በምህረቱ በቸርነቱ
ይጎብኘን አሜን !!! ✞ ✞
ጌታችን አምላካችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ህይወታችን ነው ፣
ሰላማችንና እረፍታችን እርሱ ነው ፤ የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ የጥበባት ሁሉ
ምንጭ እርሱ ነው ፤ መጀመሪያ የሌለው አልፋ መጨረሻም የሌለው ኦሜጋ እርሱ
ነው ፤ እርሱ ሁሉን የሚወድ ነው ፤ እርሱ የአለም መድሃኒት ነው!!!!
እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት ነፍሱን
ስለ ወዳጆቹ ከማኖር ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለውም እኔ ያዘዝኋችሁን
ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም
ባረያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቀውምና ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ ከአባቴ
የሰማሁትን ሁሉ ለ እናንተ አሳውቄአችኋለሁና እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ
አልመረጣችሁኝም አብም በስሜ የምትለምኑትን እንዲሰጣችሁ ልትሄዱና ፍሬ
ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ይህንን
አዘዝኋችሁ ዮኀ . 15: 12 - 17 ✞ ✞
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEzwE8Rx0_ELfmMHsg
#መድኀኔዓለም አዳነን

መድኀኔዓለም አዳነን በማይሻር ቃሉ/2/

ደስ ይበለን/2/ እልል በሉ /2/ አዳነን በማይሻር ቃሉ /2/

እንኳን ለአባታችን ለመድኀኔዓለም ወርሃዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ከበዓሉ በረከት ያድለን

👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @Mezmurat123 👈
👉 @mezmurat123 👈
👉 @mezmurat123👈
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
የገና ዛፍ ከየት መጣ ከእፅዋት ሁሉ የጽድ ዛፍ ብቻስ
ለምን ሆነ ???
。。。。。。。。?。。。。。。。。。
የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርሰረቶስ
የልደት በዓል ሲከበር ዘውትር እያየናቸው ካሉና የበዓሉ አንድ
አካል እየሆኑ ከመጡ ነገሮች መሀከል ዋነኛው የገና ዛፍ ነው።
ይህን የገና ዛፍ አብዛኞቻችን ዝም ብለን ከማድረግ ባለፈ መቼቱ
የት እንደሆነ ምን አይነት ምስጢር እንዳለው የምናውቅ
አይመስለኝም ነገር ግን የቤተክርስቲያን ታሪክ ወደኋላ መለስ
ብለን ስናይ ምንጩ ከወዴት እንደሆነ ይነግረናል የመጀመሪያዎቹ
ክርስቲያኖችና ሐዋርያት በነበሩበት ዘመን ራሳቸውን የእውቀት
ባለቤት አድርገው የሚቆጥሩ በክርስትና ላይ የመጀመሪያውን
የምንፍቅና ትምህርት ማንሳት የጀመሩ # ግኖስቲክስ የሚባሉ
ሃሳውያን ነበሩ የስማቸው ትርጉም በግሪክ ቋንቋ ጠቢባን
አዋቂወች ማለት ነው። መሪያቸው ስምኦን መሰሪ ይባላል ይህ
ሰው በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ሐዋርያትን የመንፈስ ቅዱስን ፀጋ
በገንዘብ እንዲሸጡለት ጠይቋቸው የነበረ ደፋር ሰው ነው።
ታዲያ እነዚህ እርሱ የሚመራቸው እራሳቸውን ጥበበኞች ብለው
የሚጠሩ መናፍቃን ከፍልስፍና ሃይማኖታቸው ብዙ
አስተምህሮዎች መካከል ዋነኛው 【ሁለት አምላኮች አሉ】
ብለው የሚያምኑት ነገር ሲሆን እነዚህ አማልክት አንዱ ክፉ
አንደኛው ደግሞ ደግ ናቸው ይላሉ።መልካም የሆኑና ጥሩ ናቸው
ብለው የሚያስቧቸውን ነገሮችን ሁሉ ለምሳሌ ከሰው ወንድን፣
ከወቅት በጋን ፣ፀሀይን፣ነፍስን፣ሰማይን፣ገነትን.....ደጉ አምላክ
ፈጠራቸው ፤ክፉው አምላክ ደግሞ የላይኞቹን ተቃራኒ የሆኑትን
ክረምትን፣ሴትን፣ስጋን፣ምድርን፣ሲኦልንና በአጠቃላይ መጥፎ
ናቸው ብለው የሚያስቧቸውን ሁሉ ፈጠረ ይላሉ። በዚህም
አስተምህሯቸው መሰረት በጋን የፈጠረው ደጉ አምላክ ከባዱን
የክረምት ወቅት የዝናቡን ጊዜ የሚያሳልፈው በጽድ ዛፋ ላይ
አድሮ ነው ብለው ያምናሉ። ለዚህ ደግሞ ማስረጃ የሚያረጉት
ጽድ በክረምትም በበጋም ወቅት ያለመድረቁ ምስጢርና
ቅጠሉም የማይረግፈው ለዛ ነው ብለው ያስቀምጣሉ።ይህ
ፍልስፍናቸውን ይዘውም ክረምታቸው በሚገባበት ጊዜ የጽድ ዛፍ
ላይ የተለያዩ ጌጣጌጦችን አድርጎ በማስዋብ ለደጉ አምላካቸው
አምልኮን ያቀርባሉ።ከጊዜ በኋላ ይህ የግኖስቲኮች የአምልኮ
ሥርዓት ልማድ ሆኖ ምዕራባውያንና አውሮፓውያን የጌታን ልደት (የዘመን መለወጫቸውን) በዓል ከማክበራቸው ከሳምንት በፊት
ጀምረው የጽድ ዛፍን በማሰጌጥ መብራቶችን በማንጠልጠል
ከበፊቱ በበለጠ ሥርዓቱን ይፈፅሙታል። የገና ዛፍ እና
ከእፅዋትም ጽድ የመሆኑ ነገር ታሪካዊ አመጣጡ ይህን
ይመስላል።

ወደ ሀገራችን ስንመጣ ደግሞ በእውቀት ማነስ ምክንያት በፊት
ዛፍ እየተቆረጠ አሁን ተመስሎ በተሰራው የፕላስቲክ ዛፍ
ኦርቶዶክሳዊ ምስጢር ኢትዮጵያዊ ባህልና ትውፊት የሌለውን
ይህን የመናፍቅ ሥርዓት ስንፈፅመው ኖረናል። ቤተ
ክርስቲያናችን ጌታችን በበረት እንደተወለደ በግርግም እንደተኛ
በጨርቅ ተጠቅልሎ ከከብቶች ትንፋሽ ሙቀትን እንዳገኘ ቦታው
በብርኃን ተሞልቶ መላዕክት ከሰወች ጋር በእንድነት እንደዘመሩ
እንጂ የጽድ ዛፍ በአካባቢው እንደነበር በዛስርም የሆነ ታሪክ
እንደተፈፀመ አታስተምርም። እርግጥነው የገና ዛፍ ቤት
ሊያደምቅ ሲያዩትም ሊያምር ይችላል ነገር ግን የጌታን ልደት
የሚያወሳ አንዳች ነገር አናገኝበትም ይልቅ ሳናውቀው
የግኖስቲኮችን የቆየ ምንፍቅና ቀጣይነት እንዲኖረው እንዳይጠፋ
እናደርጋለን እንጂ ።ስለዚህ ማንኛወንም ነገር ስናደርግ ለምን
እንደሆነ ምክንያቱን ቅድሚያ ማወቅ እንዳለብን ከዚህ እንረዳለን
ለምን ቢሉ አለማወቅ ከተጠያቂነት ስለማያድን በዘልማድ የሌላ
እምነት ሥርዓት ስንፈፅም ቆይተን በኋላ ስንጠየቅ እንዳናፍር
ነው።ስለሆነም በጌታችን ልደት ቀን ይህን ከማድረግ ተቆጥበን
ምስጢር ያለውና ሃይማኖታዊ ይዘቱን ሳይለቅ ባገኘናት ነገር
የበረት ግርግም ሰርተን የስነ ልደቱን ስዕል በመሀከል
በማስቀመጥ የሚበራውን ማድመቂያ በመለኮታዊው ብርሃን
መስለን ባማረ መልኩ የራሳችን የሆነ ትርጉም ያለው ልዩ ነገር
አዘጋጅተን ብርሃነ ልደቱን እያሰብን ማክበር እንችላለን ።
ሌሎች ይህን ያውቁ ዘንድ shear ያድርጉት አምላካችን መዋዕለ ጾሙን በሰላም አስፈጽሞ ለብርሃነ ልደቱ በጤና ያድርሰን።

ይ ቀ ላ ቀ ሉ
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEzwE8Rx0_ELfmMHsg
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በእንተ ልደቱ ለክርቶስ
ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል ኦ.ዘኁልቁ 24፤17
በዘመኑ መጨረሻ ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል እንዳለ ከያዕቆብ ወገን ከምትሆን
ከድንግል ማርያም እንደ ህዝቅኤል ቤተመቅደስ ሳይከፈት ገብቶ ሳይከፈት
ይወጣ ዘንድ ኮከብ የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስ በማኅፀነ ድንግል አደረ፡፡ በደስታ
ሲጠበቅ የነበረው ጊዜው ደርሶ አምላክ በቀጠሮ ሥጋ ለብሶ እነሆ ዛሬ ተወደለ፡፡
ለዓለም ተገለጠ፡፡ ቀድሞ በአዳም ምክንያት የሰው ልጅ ሁሉ በሞተ ሥጋ ላይ
ሞተ ነፍስ በርደተ መቃብር ርደተ ገሃነብ ተፈርዶበት በጨለማ ይኖር ነበር፡፡
የዲያብሎስ ቁራኝነት ያስጨነቃቸው ከአዳም ጀምሮ ያሉ ትውልድ ሁሉ “አቤቱ
እጅህን ከሰማይ ልከህ አድነን” ይሉ ነበር፡፡ እነ ኢሳያስም “ሰማያትን ቀደህ
ብትወርድ ምነው” እያሉ ይማፀኑት ነበር፡፡
ከሞት ቁራኝነት ነፃ የምንወጣበትን የምስራች ዜና በቅዱስ ገብርኤል ብስራት
እነሆ ትፀንሻለሽ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ… ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን
ዙፋን ይሰጠዋል፡፡ ይህንን ቃል ያመነች ብፅዕት ናት፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ያለ
ዘርዐ ብእሲ /ያለወንድ ዘር/ አማናዊ ቃል በሥጋ ልጅ አደረ በድንግል ማኅፀን
ተወሰነ፡፡
በዚያም ወራት ይላል ወንጌል /ሉቃ 2፤1-20/ አገሩ ሁሉ ይፃፍ ዘንድ
ከአውግስጦስ ቄሳር ትእዛዝ ወጣ፡፡ የግዛቱን ስፋት የህዝቡን ብዛት ያውቅ ዘንድ
ሁሉም በየወገኑ እንዲፃፍ እንዲቆጠር ከያሉት ከተማ ወደየወገናቸው ወጡ፡፡ ጌታ
በወንጌሉ የናንተስ የራስ ፀጉራቹ ሳይቀር የተቆጠረ ነው፡፡ ሰማያዊ አባታችሁ
ሳያውቅ ከእናንተ አንድም አይወድቅም ብሎ እንደተናገረ፡ እርሱ ግን ሊቆጠር
ከዳዊት ወገን ስለሆነ ወደ ይሁዳ ምድር ወረደ፡፡ ይሄ የአውግስጦስ ቄሣር
ትእዛዝ ምክንያት ሆኖት ከናዝሬት አገር ከገሊላ እንዲወጡና ትንቢት
ወደተነገረበት ቤተልሔም ወደምትባል የዳዊት ከተማ ወደ ይሁዳ ምድር
እንዲሄዱ ሆነ፡፡
ይህ ሁሉ ድንገት የሆነ አይደለም የቃል ኪዳኑ ጊዜው ሲደርስ በፈቃደ
እግዚአብሔር ትንቢቱ እንዲፈፀም ይሄ አዋጅ ወጣ እንጂ፡፡ ብዙ ህዝብ ወደዚህች
ከተማ መጥቶ ነበርና ከእንግዳው ብዛት የተነሳ ዮሴፍና ድንግል ማርያም ማደሪያ
አጡ፡፡
በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ቀን ደረሰ፡፡ ዳዊትና ሰለሞን የነበሩበት ቤተመንግስት
ቦታው ፈርሶ የከብቶች ማደሪያ /ግርግም/ ሆኗል ፤ወደ እርሷም ገቡ፡፡ ቅዱስ
ገብርኤል ለንፅህት ሲያበስራት እግዚአብጠር አምላክ ያባቱን ዙፋን ይሰጠዋል
ብሏት ነበርና፡፡ያ የአባቱ ዙፋን ግርግም ሆኖ ተሰጠው፡፡ በቤተ መንግስት
በንግስና ስፍራ ይወለዳል ሲባል ወደከብቶች ማደሪያ ገብቶ በበረት ተወለደ፡፡
ለንጉስ እንዲገባ በወርቅ የከበረ በአልማዝ ያጌጠ ይለብሳል ሲባል በጨርቅ
ተጠቀለለ፡፡ በዳዊት ፊት ይቆሙ የነበሩ መኳንንቶች ዛሬ የሉም በምትኩ ትጉሃን
እረኞች ቆሙ እንጂ፡፡ መላኩም እረኞችን እንዲህ አላቸው “እነሆ ዛሬ በዳዊት
አገር መድህን /መዳኛ/ እርሱም ክርስቶስ የተባረከ ጌታ ተወልዶላችኋልና፡፡
ይህም ምልክት ይሁንላችሁ ህፃኑ አውራ ጣቶቹን ታስሮ በመጠቅለያ ተጠቅልሎ
በበረት ተኝቶ ታገኙታላችሁ፡፡” /በ1983 ዓ.ም በን.ነ. ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ፈቀድ
የታተመ የአዲስ ኪዳን መፅሐፍ ቅዳስ ሉቃ 2፤7-13 ያለውን ይመልከቱ/ ይህ
የልደቱ ታሪክ የመስቀሉን ታሪክ የሚያሳይ ብርሃን /መነፅር ነው ምክንያቱም
በልደቱ የተደረጉት ታሪኮች በጠቅላላ በስቅለቱ የሚደረገውን ስለሚያሳዩ ነው፡፡
ይኸውም መድህን አዳኝ ተወልዶላችኋል አለን በስቅለቱ መቶ ቤዛ ሆኖ
የሚያድን ነውና፡፡ ህፃኑ አውራ ጣቱን ታስሮ በጨርቅ ተጠቅልሎ በግርግም /
በበረት/ ተኝቶ ታገኙታለችሁ ይላል፡፡ ምሳሌውም * አውራጣቱን መታሰሩ ጌታ
እንደ ወንበዴ በአይሁድ እጅ የመታሰሩ ምሳሌ ነው፡፡* ያቺ የለበሳት ጨርቅ
የጲላጦስ ወታደሮች ጌታን ወደቀራኒዮ ሲወስዱት አነገሰን ብለው እያፌዙ
ያለበሱት ልብስ ምሳሌ ነበረች፡፡ * ያቺ ግርግም የከብቶች ገለባ መቃሚያ ናት፡፡
ከድንጋይ የተሰራች የመቃብሩ ምሳሌ ናት፡፡ * በግርግም መተኛቱ ሞቱን
የምታመለክት ናት፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ጌታ በተወለደ ጊዜ ሰማያዊያን
መላእክት “በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና በምድርም ሰላም ፍቅር ለሰው
ልጆች ሆነ” ብለው ሰውና አምላክን ያስታረቀበት የፍቅሩን ፍፃሜ የገለፀበት
የስቅለቱን መዝሙር በልደቱ ዘምረዋል፡፡ ስቅለቱና ልደቱ አተኩሮ ለሚያየው ሰው
እጅግ ተመሳሳይ ናቸው ፡፡ መፅሐፍ “እንደበግ ሊታረድ መጣ” ይላል ያ “መጣ”
የሚለው ቃል የተፈፀመው በእለተ ልደት ነው፡፡ ጌታ ሆይ አንተ ሊዳስሱት ሊኩት
የማይቻል እሳት ስትሆን በሚያስደንቅ ሚስጥር ትንሹአ ገሊላዊት ብላቴና
አቀፈችህ፡፡
ዮም ፍሰሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርቶስ !!!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEzwE8Rx0_ELfmMHsg