✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.2K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
📊 † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን †
✞ ኅዳር ጽዮን ✞
✞ እንኳን ለእመቤታችን ለጽዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም
በጤና አደረሳችሁ አደረሰን በረከቷ ረድኤቷ አማላጅነቷ ጣዕሟ ፍቅሯ ባለንበት ቦታ
ሁሉ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን ፡፡ ✞
በቅዱሳት መጻሕፍት ጽዮን የሚለው ቃል ተደጋግሞ በነቢያቱ ተነግሯል፡፡ ሆኖም
የጽዮን ትርጉም እንደተነገረበት ዐውደ ትንቢት እንደተሰበከበት መዋዕለ ትምህርት
ምስጢሩ ይለያያል፡፡
በየዓመቱ ኅዳር ፳፩ን የምናከብርበት ምክንያቶች ግን በጥቂቱ የሚከተሉት ናቸው፡-
1ኛ. የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌና ጥላ የምትሆን ታቦተ
ጽዮን ዳጎንን ድል ያደረገችበትን ታሪክ ለማስታወስ /፩ኛ ሳሙ.፭፡፩-፲፪/፤
2ኛ. ይህቺ ታቦት ጾዮን ቀዳማዊ ምንሊክ ከእስራኤል ወደ ኢትዮጵያ ይዟት
መጥቶ አክሱም የገባበትና ንግስተ ሳባ ታላቅ በዓልን አድርጋ የተቀበችበትን ቀን
ለማሰብ፤
3ኛ. ክርስትናው ሲስፋፋ አብርሃና አጽብሃ በዚህችው የታቦተ ጽዮን መዲና ከተማ
፲፪ ቤተ መቅደስ ያለው ቤተ ክርስቲያን አሳንጸው ከጨረሱ በኋላ ቅዳሴ ቤቱ
ያከበሩበት ዕለት ስለሆነ፤
4ኛ. በ፱ኛው መቶ ክ/ዘ. ዮዲት ጕዲት ክርስትናን ለማጥፋት በተነሣች ጊዜ
በእርሷ ምክንያት ታቦተ ጽዮን ወደ ዝዋይ ሐይቅ መጥታ፣ የሰላሙ ዘመን ሲመጣ
ግን የአክሱም ሊቃውንት በዚሁ ዕለት ወደ አክሱም መልሰው ስላስገቧት፡፡
በመኾኑም በእነዚህ ተደራራቢ ታሪኮች ምክንያት በየዓመቱ ኅዳር ጽዮን በደመቀ
ሁኔታ እናከብራለን፡፡ ታቦተ ጽዮን ዳጎንን ሰባብራ እንደጣለችው እመቤታችን
ቅድስት ድንግል ማርያምም ልጇ ወዳጇ ኃጢአታችንን ያርቅልን ዘንድ
በአማላጅነቷ በቃል ኪዳኗ ትርዳን፤
የቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እና ምልጃ አክሊልና ጉልላት በሆነው በእናታችን በወላዲተ
አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎት ሁላችንንም ይማረን አሜን።
እግዚአብሔር አምላክ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤትና
በረከት ያሳትፈን፡፡ የእግዚአብሔር አብ ጸጋ የእግዚአብሔር ወልድ ቸርነት
የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት በእኛ ላይ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኑር
አሜን!!

👇👇👇👇👇👇👇👇

አሜን አሜን አሜን [6]
‎├ hani
‎├ ይ τ α 🎀 φ σ ι
‎├ S @mî
‎├ Mule Xohollic
‎├ ደጉ ሳምራዊ
‎└ Fikirte Girme

👥 6 people have voted so far
ጥያቄና መልስ👆
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ✞
✞ ✞ እንኳን ለሊቀ መልአኩ ለቅዱስ ዑራኤል ክብረ በዓል በሰላም በጤና
አደረሳችሁ አደረሰን አሜን፡፡ ✞ ✞
በፍጹም መጠበቅን ጠብቆ ለዚህ ያደረሰን አምላካችን ክብርና ምስጋን
አምልኮትና ውዳሴ ይድረሰውና ይህን ታላቅ መልአክ በችሎታችን መጠን
እንድናመሰግን እግዚአብሔር ይርዳን፤ አምላክ ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን፤
ምስጢሩን ይግለጥልን አሜን፡፡
“ዑራኤል የተባለ መልአክ ሊረዳኝ መጣ፡፡” መ/ዕዝ. ሱቱ. 2፡1
በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤
እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። በተኵላና በእባብ ላይ
ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። በእኔ ተማምኖአልና
አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ። ይጠራኛል
እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ
አከብረውማለሁ። ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ። መዝ.
90/91/፡11-16
አፈቅሮ ፈድፋደ፡- ዑራኤል ሆይ፣ ከመልኮች ሁሉ ይልቅ ያንተን መልክአ ጸሎት
እወዳለሁ፡፡ የመልክህ ስነ ጸዳል በደመ ወልድ እግዚአብሔር የታተመ ነውና፡፡
ዑራኤል ሆይ፣ እግዚአብሔር ሀይሉን የሚገልጽብን መልአከ ብርሃናት አንተ ነህ፡፡
በዐዕለተ ሥቅለት በደመ ወልድ ዓለምን ለመቀደስ ከሁሉ ይልቅ አንተ
ተሰይመሃልና፡፡ ስለክብርህ የሰማይ መላእክት አደነቁ፡፡
ለተፈጥሮትከ፡-
ዑራኤል ሆይ፡- ያለ መናገር በጥንት አርምሞ ከነፋስና ከእሳት ለተፈጠረ
ተፈጥሮህ ሰላም እላለሁ፡፡ ዑራኤል ሆይ የተፈጥሮና የይቅርታና የቸርነት ክቡር
መልአክ ነህና ስለኛ ስለሰው ልጆች ወደ ልዑል እግዚአብሔር ማልድ
አማላጅነትህ ዘወትር ከጥፋት ያድናልና፡፡
ለዝክረ ስምከ፡-
ዑራኤል ሆይ፡- ከማርና ከወተት ይልቅ ለሚጥመው ስም አጠራርህ ሰላም
እላለሁ፡፡
ዑራኤል ሆይ፡- ክፍልህ /ክንፍህ/ በደመ ወልድ እግዚአብሔር የተከበረ /
የታለለ/ ነውና፡፡ ለዓለሙ ሁሉ መድሃኒት ትሆን ዘንድ ግሩም የሚሆን
የእግዚአብሔር ሥልጣን በክብር ከፍ ከፍ አደረገ፡፡ (መልክአ ዑራኤል)
“የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።”
መዝ.33/34/፡7 የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ዑራኤል ረድኤቱ በረከቱ ፍጹም
አማላጅነቱ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

#join 👉 @embtee
@Embtee

ይላኩልን👉 @maryamn123bot
#join @embtee @embtee

❤️❤️በምን በምን እንመስላት ድንግል ማርያምን "፪"
ምሳሌ የላትም የላትም ክብራን የሚመስል "፪"
የሙሴ ጽላት ነሽ የምሕረት ቃል ኪዳን
የያዕቆብ መሰላል የአብርሃም ድንኳን
የብርሃን መውጫ የኖኅ ድንቅ መርከብ
የመላእከት እኅት የርህሩሃን እርግብ "፪"
………..አዝ……
የሰሎሞን አክሊል የአሮን በትር
የዕዝራ መሰንቆ የጌዴዎን ፀምር
ድንግል እናቴ ናት የጽድቃኖች በር
ሆና የተገኘች የአምላክ ማኅደር፡"፪"
………..አዝ……
የቅዱሳን እናት የአርያም ንግሥት
ስለ ተሸከመች መለኮት እሳት
በሥጋችን ፈቃድ ወድቀን እንዳንጠፋ
አማልዳ ታስምረን ከዚህ ዓለም ጣጣ "፪"
………..አዝ……
ከማር ይጣፍጣል የድንግል መዓዛ
አምላክን አቅፋለች በሁለት እጇ ይዛ
ዓለሙን የዳነ በልጅሽ ነውና
እናታችን ጽዮን ይድረስሽ ምሥጋና "፪"


ሼር እንዳይረሳ👉 #join @embtee @embtee
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ✞
እንኳን ለሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሃዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም
በጤና አደረሳችሁ አደረሰን አሜን፡፡ ሰማዕቱ ባለንበት ጽናትና ብርታቱን ያድለን።
👉 @embtee
† ቅዱስ ጊዮርጊስ †
† “እኔ የክርስቶስ ወታደር ጊዮርጊስ መጣሁባችሁ” ሲላቸው ደንግጠው
ይሸሹ ነበር። †
† † ጊዮርጊስ ማለት ኮከብ፣ ብሩህ፣ ሐረገወይን፣ ፀሐይ ማለት
ነው። ቶማስስ ዘልዳ እንዲለው ሀገሩ ልዳ ነው። አባቱ ዞሮንቶስ (እንስጣስዮስ)
በልዳ መስፍንነት ተሹሞ ይኖር ነበር። እናቱ ትዎብስታ (አቅሌስያ) ትባላለች።
ማርታ ድስያ የሚባሉ እህቶች ነበሩት።
† † አስር አመት ሲሆነው አባቱ ሞቶ ሞቶ ሌላ መስፍን ተሾመ። ደግ
ክርስታናዊ ነበርና ወስዶ እያስተማረ አሳደገው። እርሱም ፈረስ መጋለብ ቀስት
መወርወር ለመደ። ጦር ሜዳ ወጥቶ ከጠላቶቹ መሀል ገብቶ “እኔ የክርስቶስ
ወታደር ጊዮርጊስ መጣሁባችሁ” ሲላቸው ደንግጠው ይሸሹ ነበር።
† † ጽኑ የእምነት አርበኛ በመኳንንቱ በሹማምንቱ በነገስታቱ ፊት
የማይፈራ ድንቅ ወጣትም ነበር። ሃያ ሲሞላው መስፍኑ የ 15 ዓመት ቆንጆ ልጅ
👉 @embtee
ነበረችውና እሷን ድሮለት ሀብቴን ወርሶ ይኑር ብሎ ድግስ ሲያስደግስ ዳስ
ሲያስጥለ ጌታ ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዚህ አላጨውምና የመስፍኑን ነፍስ ወሰደ።
እርሱም ሀዘኑን ጨርሶ ወደ ቤሩት ሄደ። ቤሩት በኢያርኮ አቅራቢያ ያለች ሀገር
ናት። በዚያ በቤሩት ሰዎች እግዚአብሔርን የማያውቁ ለዴጎን የተንበረከኩ ናቸው።
† † ቤሩታዊቷንም የሹም ልጅ ለዚሁ ዘንዶ ግብር ሊገብሩለት
ከግንድ ወስዶ አሰሩለት። ቅዱስ ጊዮርጊስም በዚያ ሲያልፍ የልጅቱን የጩኸት
ድምጽ ሰማ። እሱም ምን ሆነሽ ነው? አላት። ለደራጎን ተሰጥቼ ነው አለችው።
አምላካችሁ ወዴት አለ አላት ምግቡን ሊፈልግ ሄዷል አለችው። ይህን እያነጋገራት
እያለ ደራጎኑ ምድሪቱን እያነዋወጠ መጣ። ሂድ ይበለሃል ስትለው፤ እኔማ ምን
አለኝ ከኔ ጋር ያለው ግን ከሱ ይበልጣል አላት። ሊበላው ሲቀርብ ስመ
እግዚአብሔር ጠርቶ ቢያማትብበት በላዩ ያደረው ሰይጣን እንደ ጉም ተኖ
እንደትቢያ በኖ ጠፋ፤ ሃይሉም ደከመ። ቤሩታዊቷ አንገቷን በታሰረችበት ገመድ
አስሮት እሷ እየጎተተች እሱ በፈረስ ሆኖ ከተማ ደረሰ። ሕዝቡን ሊያስፈጅ ነው
ብለው ይሸሹ ጀመር። አጽናንቶ መለሳቸው። ንጉሱ ዱድያኖስ ግን ተነሳስቶበት
ክርስቶስን ካድ ባለው ጊዜ አምላኬ ክርስቶስን አልክድም በማለቱ ተቆጥቶት
ጥጋውን በመቃጥን አስተፍትፎታል፤ ረጅም ችንካሮች ያለበት የብረት ጫማ
አጫምቶታል፤በችንካር አስቸንክሮታል፤ በፈላ ውሃ ውስጥ አስጨምሮታል።
† † አጥንቱን አስከስክሶታል። መሄድ እስኪያቅተው ድረስ፤ መርዝም
በጥብጦ አጠጥቶታል። በመንኩራኩር አስፈጭቶት ከጥልቅ ጉድጓድ ጥሎታል።
ብዙውን ጊዜ በመንኩራኩር ተፈጭቷል፤ በኋላም በደብረ ይድራስ ላይ አጥንቱን
በትኗል። መከራ ፈተና አብዝቶበታል። ፯ ጊዜ ሞቶ ፯ ጊዜ ተነስቷል።
† † አቤት የቅዱሳን መከራቸ፤ ለዚህ እኮ ነው ቅዱስ ጳውሎስ
“እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ
👉 @embtee
ቃል አገኙ፥ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፥ የእሳትን ኃይል አጠፉ፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፥
ከድካማቸው በረቱ፥ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ። ሴቶች
ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን
ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤ ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና
በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥
👉 @embtee
ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራን
እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ዓለም
አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ።
እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል
👉 @embtee
አላገኙም፥ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ እግዚአብሔር ስለ እኛ አንዳች የሚበልጥ
ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና። † † (ዕብ.፲፩፡፴፫-፵) 11፡33-40
† † ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን
የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል። ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን
ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? የሰው ልጅ ከመላእክቱ
👉 @embtee
ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው
ያስረክበዋል። † † (ማቴ.16፡25-27
† † እኔን የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ መስቀሌንም ተሸክሞ /መከራዬን
ሳይሰለች/ ዕለት ዕለት ይከተለኝ፡፡ † † ማቴ 10፡38-42 እንዲል
ወንጌል
👉 @embtee
† † ስለ ጽድቅ የሚራቡና የሚጠሙ፣ እንዲሁም የሚሰደዱ ብጹዓን
ይጠግባሉና፣ መጽናናትንም ያገኛሉና… ጌታ በተራራ ስብከቱ ከተናገራቸው፣
ካስተማራቸው የሕይወት ምግብ የሆነ ቃሉ ማቴ.5፡1-ፍጻሜ
† † ጊዮርጊስ ሆይ ጨካኝ ቁጡ በሆነው በዱድያኖስ አደባባይ ልዩ ልዩ
ተዓምራትህን እንደማድረግህ በጠዋት በማታ በከንቱ ነገር የሚነሳሱብኝ ጠላቶቼ
ሁሉ እንደ አመድ በነው እንደ ጢስ ተነው ይጥፉ፡፡
👉 @embtee
ጊዮርጊ ሆይ ሰማዕታት ሁሉ አለቃ እንደመሆንህ ቀድሞ ሰብዓ
ነገስታትን እንደደመሰስካቸው ነበልባላዊ በምትሆን ጸሎትህ ጠላቶቼን
ደምስሳቸው፡፡
ተዓምረኛው ሰማዕት ሆይ ቀድሞ የቢፋሞንን ልጅ ከሰዕበተ ሃጢአት ሰውነቱን
👉 @embtee
እንድቀደስከው መንግስተ ሰማያትን ለመውረስ እበቃ ዘንድ ሰውነቴን በፍጹም
መቀደስ ከሃጢአት ርኩሰት ንጹህ አድርግልኝ፡፡
ተዓምረኛው ሰማዕት ሆይ ሙታንን የማስነሳት ሥልጣን ተሰጥቶሃልና አቤቱ
ቤሩታዊትን ከአፈ ዘንዶ እንዳዳንካት እኔን ከእለተ እኪት ከዘመነ መንሱት
በጸሎትህ አድነኝ፡፡
አቤቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ሆይ ማረን፤አቤቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ
@embtee
አምላክ ሆይ ራራልን፤ አቤቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ሆይ ይቅር በለን፡
እግዚአብሔር አምላካችን ሰማዕታትን በደም ቅዱሳንን በገዳም ሐዋርያትን
በአጽናፍ ዓለም መላዕክትን በአጽራርያም እንዳጸናቸው እኛ ሁላችንንም
በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችን በቅድስት ቤተክርስቲያን በበጎ ምግባር በጾም
በጸሎትና በትሩፋት ያጽናን አሜን አሜን አሜን!!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ። ይቆየን

አንብቦ ዝም አይባልም ሼር
#join 👇
@embtee
@embtee
Forwarded from Deleted Account
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📊 ጥያቄ
ከሚከተሉት ውስጥ የማይገባ የክርስትና ስም/
ለሰው ሊሰየም የማይገባ ስም የትኛው ነው??

ሀ) አማኑኤል [10]
‎├ S @mî
‎├ ይ τ α 🎀 φ σ ι
‎├ ㄱㄹ붸 ㄱ차벺ㅌ
‎├ 79697 dreamer
‎├ Joseph
‎├ ሀኒቾ
‎├ sol D.
‎├ Hermela Seifu
‎├ Asen Konjo
‎└ Serka Serka

ለ)ዘአማኑኤል [0]

ሐ/ ሣህለ ሥላሴ [2]
‎├ Kiya Ya T.afe
‎└ Mekdi ymariyam

መ/ ዘሚካኤል [3]
‎├ Bãki bël Jr.★★
‎├ Redite H.gebreal
‎└ Aseki Ar

ሠ/ ሁሉም [2]
‎├ ferehiwot Yekirkos
‎└ ሳንጂዬ

👥 17 people have voted so far
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ✞
✞ ✞ እንኳን ጻድቁ አባታችን ለአቡነ ተክለሐይማኖት
ታላቅ ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን ! ✞ ✞
ህዳር 24 በዚህች ቀን ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ
ሃይማኖት ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ እንደ አንዱ ሁነው መንበረ ጸባዎትን ያጠኑበት
ታላቅ ዓመታዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም በጤና በፍቅር እንኳን አደረሳችሁ
አደረሰን
የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሐይማኖት ረድኤት በረከታቸው ምልጃና ጸሎታቸው
ከመላው ህዝበ ክርስቲያን ጋር ይሁን አሜን! እለቱ ካህናተ ሰማይ ተብሎ በቤተ
ክርስቲያናችን ይከብራል እኛንም ከጻድቁ ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡
👇👇👇👇👇👇
#join @embtee👈
@embtee👈
#share
Forwarded from Deleted Account
ልብ ብለህ አስተውል!!!
☞ አትመኝ፦ እንደ አዳም የዲያብሎስ ባሪያ ትሆናለህ፡፡ ዘፍጥ 3÷1-8
☞ አትቅና፦ እንደ ቃየል ወንድምህን ትገላለህ፡፡ ዘፍጥ 4÷1-8
☞ አትስከር፦ አዕምሮ አሳጥቶ የማይገባ ሥራ ትሠራለህ፡፡ ዘፍጥ 19÷30-38
☞ ዓለምን አትመልከት፦ እንደ ሎጥ ሚስት የጨው ዐምድ ሆነህ ትቀራለህ፡፡
ዘፍጥ 19÷22-23
☞ በአባትህ አትሳቅ፦ እንደ ካም ትረገማለህ፡፡ ዘፍጥ 9÷20
☞ እልከኛ አትሁን፦ እንደ ፈርዖን ትሰጥማለህ፡፡ ዘፀ 14÷28
☞ በሐሰት አትመስክር፦ እንደ ሐማ ባዘጋጀኸው ጉድጓድ ትገባለህ፡፡ መጽ.አስቴ
7÷1
☞ ትዕቢተኛ አትሁን፦ እንደ ሰናክሬም ትወድቃለህ፡፡ 2ነገ 19÷35
☞ ክፉ ባልንጀራን አትያዝ፦ እንደ ሶምሶን በጠላት እጅ ትወድቃለህ፡፡ መጽ.መሳ
16÷15
☞ አትዘሙት፦ እንደ ሰሎሞን አምላክህን አስረስቶ ጣዖትን እንድታመልክ
ያደርግሃል፡፡ 1ነገ 11÷1-8
☞ ሥልጣንን አትውደድ፦ እንደ አቤሴሎም በአባትህ ላይ ትነሣለህ፡፡ 2ነገ ሳሙ
15÷13-17
☞ ገንዘብን አትውደድ፦ እንደ ይሁዳ ጌታህን ያስክድሃል፡፡ ማቴ 26÷14÷16
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!
Forwarded from Deleted Account
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ✞
† † እንኳን ለታላቁ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሪዎስ አመታዊ ክብረ በዓል
በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን!!! † †
ህዳር 25 በዚህች ቀን..
ቅዱስ መርቆሪዎስ በሰማዕትነት አረፈ፤ አገሩ ሮም ነው፤ በወጣትነቱ ከሃዲው
ንጉስ ኡልያኖስ ላቆመው ጣኦት አልሰግድም ብሎ የሰው ልጅ ሊሸከመው
የማይችለውን መከራ ተቀበለ በመጨረሻም ህዳር 25 በዛሬዋ ቀን አንገቱን
ቆርጠው ገደሉት ደም ውኃና ወተት ከአንገቱ ፈሰሰ። ይህ ሰማዕት በአገራችን
በስሙ በርካታ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት አሉት በተለይም ቅዱስ ላሊበላ
ካነጻቸው 11 ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አንዱን ቤተ መርቆሪዎስ ብሎ
ሰይሞለታል፤ በዚህ በሰሜን ሸዋ ደግሞ የሚገርም ገዳም አለው፤ ካህናት
በማህሌት ወረብ ሲያቀርቡ ስዕሉ ያሸበሽባል ይዘላል ፤ ይህንንም አይቶ
ማረጋገጥ ይቻላል፤ በመዲናችን አዲስ አበባ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን
ውስጥ ታቦቱ አለ ዛሬ በደማቁ ተከብሮ ይውላል። መርቆሪዎስ ከሞተ በኃላ ፈረሱ
ለሰባት ዓመት ወንጌልን አስተምሯል፤በኃላም አንገቱን ቆርጠው ገድለውታል
እንዴት ብሎ የሚገረም የበልአምን አህያ ይጠይቃት፤ እኛስ እስመ አልቦ ነገር
ዘይሳኣኖ ለእግዚያብሔር ብለን እንመልሳለን፤ ዘኁልቁ 22፤28 ቅዱስ ጴጥሮስም
እንዲህ አለ ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነብዩን እብድነት አገደ
ይላል 2ጴጥ 2፤16። ከሰማዕቱ በረከት ያሳትፈን።
👉የእመቤታችን የድንግል ማርያም የአስራት ልጆች👈:
👉#join @embtee

ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ እነሆ!!
1: ስለ ሥላሴ የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት:-
ዘፍ 1:26 ዘፍ 3:22
ዘፍ 11:18 ዘፍ 18:1-2
ኢሳ 48:26 ማቴ 3:16-17
ማቴ 28:19 ሉቃ 1:35
ዮሐ 7:28-29 ዮሐ 14:25-26
ሐዋ 3:14 1ኛ ቆሮ 12:4-7
2ኛ ቆሮ 13:14 ኤፌ 4:4-7
2: ስለ እመቤታችን ቅድስናዋ ፣ ክብሯ ፣ ድንግልናዋና አማላጅነቷ:-
መዝ 9:11 መዝ 13:10
መዝ 44:9 መዝ 86:5
መዝ 131:13 መዝ 44:2
መኃ 4:12 ኢሳ 7:14
ኢሳ 49:23 ኢሳ 60:14
ማቴ 1:23 ሉቃ 1:28
ሉቃ 1:42 ዮሐ 2:1-11
ዮሐ 19:16 ሮሜ 11:26-27
2ኛ ቆሮ 11:2 ራዕ 12:16
3: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈራጅ እንጂ አማላጅ አይደለም፡-
ዘፍ 3:22 1ኛ ሳሙ 16:1
ኢሳ 9:6 ዳን 7:14
ሆሴ 13:4 ዘካ 9:9-10
ሚክ 5:2 ሉቃ 1:32-33
ዮሐ 10:30 ሉቃ 2:12
ዮሐ 14:7 ሮሜ 9:5
ቆላ 2:9-10 ቲቶ 2:11-13
ዕብ 1:3-4 ዕብ 1:10-11
1ኛ ጴጥ 3:23 1ኛ ዮሐ 2:23
ራእ 3:22 ራእ 22:12-13
4: ስለ ታቦትና ጽላት
ዘፀ 24:12 ዘፀ 25:10
ዘፀ 25:21 ዘፀ 26:34
ዘፀ 31:18 ዘፀ 32:15
ዘፀ 34:1 ዘፀ 34:28
ዘፀ 37:1 ዘፀ 40:20
መኃ 7:89 ኢያ 3:3
ኢያ 7:6 2ኛ ቆሮ 6:16
5: ስለ ጾም የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ:-
ዘፀ 34:28 ዘፀ 9:9
ሳሙ 20:26 1ሳሙ 7:6
1ሳሙ 31:13 2ኛ ሳሙ 1:12
2ኛ ሳሙ12:16 ዕዝ 8:21
ዕዝ 68:10 ዕዝ 108:24
ኢሳ 48:3 ኤር 36:9
ዳን 9:3 ዳን 20:2-3
ኢዩኤ 2:14 ኢዩኤ 2:12
ዮና 3:5 ማቴ 4:2
ማቴ 6:16:18 ማቴ 9:14-15
ማቴ 17:21 ማር 2:18
ማር 9:29 ሉቃ 2:37
ሉቃ 18:12 የሐ.ስራ 13:3 ሐዋ 14:23 2ኛ ቆሮ 11:17
6: ስለ መስቀል በመጽሐፍ ቅዱስ:-
ማቴ 10:38 ማቴ 16:20
ማር 8:34 ሐዋ 5:30
1ኛ ቆሮ 1:18 ገላ 3:13
ገላ 6:13 ፊል 2:8
ፊል 3:18
7: ጥምቀትን በተመለከተ:-
ሕዝ 36:25 ማቴ 3:5-6
ማቴ 26:19-20 ማር 1:4-5
ማር 16:16 ሉቃ 3:21
ዮሐ 3:5 ዮሐ 3:22
ኤፌ 4:5 ገላ 3:26-27
ሐዋ 19:4 ሐዋ 18:8
ሐዋ 13:24 ሐዋ 10:47 የሐዋ 9:18 1ኛ ቆሮ 1:16
1ኛ ቆሮ 10 :2 1ኛ ቆሮ 12:13
8:ስእለትን በተመለከተ:-
ዘኁ 28:20 ዘኁ 21:2
ዘፀ 23:21 መሳ 11:30
መዝ 49:14 መዝ 75:11
1ኛ ሳሙ 1:11 መክ 5:4-5
ዮና 2:10 ናሆ 1:15
ሐዋ 18:18
9: ጻድቃን ሰማዕታት ያማልዳሉ:-
ዘፍ 18:17-18 ዘፍ 18:23:24
ዘፍ 20:7 ዘፍ 33:3
ዘፍ 42:6 1ኛ ሳሙ 28 :14
2ኛ ሳሙ 1:2 2ኛ ነገ 1:13
2ኛ ነገ 2:15 2ኛ ነገ 4:9
2ኛ ነገ 4:32-35 መዝ 88:34
ማቴ 18:18 ዮሐ 20:23
ሐዋ 10:25 ሐዋ 16 :29
1ቆሮ 6:1-2 ፊሊ 4:6
1ኛጢሞ 5:17 ያዕ 5:14
ራእ 14:13
10: መላእክት ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት ይቆማሉ:-
መዝ 148:2 ኢሳ 6:3
ማቴ 4:12 ማቴ 18:10
ማቴ 25:31 ማር 8:38
ራእ 1:11 ሉቃ 1:19
11: መላእክት ጸሎታችንን ወደ እግዚአብሔር ያደርሳሉ:-
ጦቢ 12:15 ሉቃ 15:10
የሐዋ 10:4 ኢዮ 25:3
ኤር 33:22 ዳን 7:10
ሄኖ 10:1 ራእ 5:11
12:ለመላእክት የአክብሮት ስግደት ይገባል:-
ዘፍ 19:1 ዘኁ 22:31
ኢያ 5:14 ዳን 8:16-17
13:መላእክት አብሣሪያን ናቸው:-
ዘፍ 16:11 ሉቃ 1:13
ሉቃ 1:19 ሉቃ 1:30-31
ሉቃ 2:10-11
14:መላእክት በአደጋ ጊዜ ፈጥነው ይደረሳሉ:-
ዘፍ 22:11-12 መዝ 90:11-12
ዳን 6:22 ዳን 10:13
ማቴ 2:13 ሐዋ 5:19-20
ሐዋ 12:7
15: ፀበል መርጨት ያስፈልጋል:-
ዘኁ 19:20
#join👉 @embtee @embtee