✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.21K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
(纟田山立):
#share #join @embtee
ውዳሴ ማርያም ዘቅዳሜ
ቅዳሜ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም
ምስጋና።
1. ንጽሕት ነሽ ብርህ ትም ነሽ። ጌታን በመካከል እጅ የያዝሽው ሆይ በሁሉ
የተቀደሽ ነሽ። ፍጥረት ሁሉ ቅድስት ሆይ ለምኝልም ብለው እየጮኹ ካንቺ ጋር
ደስ ይላቸዋል።
2. ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ። ባለሟልነትን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ።
እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ። ግርማ ያለሽ ድንግል ሆይ
ገናንነትሽን እናመሰግናለን እናደንቃለን። እንደ መልአኩ ገብርኤልም ምስጋና
እናቀርብልሻለን የባሕርያችን መዳን በማህጸንሽ ፍሬ ተገኝቷልና። ቅድስት ሆይ
ለምኝልን።
3. እንደ ሠርግ ቤት ጉድፍ የሌለብሽ ነሽ መንፈስ ቅዱስ አድሮብሻልና የልዑል
ኃይልም ጸልሎሻልና። ማርያም ሆይ ለዘለዓለም የሚኖር መጥቶ ከኃጢያት ያዳነን
የአብ ልጅ ቃልን በውነት ወለድሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
4. ከዳዊት ሥር የተገኘሽ ባሕርይ (ዘር) አንቺ ነሽ። መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስን በሥጋ ወልደሽልናልና። ከአብ የተወለደ ከዓለም በፊት የነበረ አንዱ
ቃል ራሱን (ባሕርዩን) ሰወረ። ካንቺም የተገዥን (ሰውን) አርአያ ነሣ።ቅድስት ሆይ
ለምኝልን።
5. አምላክን ያለርኩሰት የወለድሽው ሆይ የምድር ሁለተኛ ፀሐይ ካንቺ
ወጥቶልናልና። እንደነቢያት ትንቢትም ያለዘርና ያለመለወጥ ወለድሽው። ቅድስት
ሆይ ለምኝልን።
6. ከተለዩ የተለየች የተባልሽ የኪዳን ጽላት ያለብሽ የተሰወረ መና ያለበት
የወርቅ መሶብ ያለብሽ ደብተራ ድንኳን አንቺ ነሽ። ይኸውም መና የተባለው
መጥቶ በድንግል ማርያም ያደረው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። የአብ ቃል በርስዋ
ሰው ሆነ መጥቶ ያዳነን የባሕርይ ንጉሥን በዓለም ውስጥ የወደችው የሚናገር
በግ የክርስቶስ እናቱ ገነት ደስ ይላታል ለዘላለም የሚኖር የአብ ልጅ እርሱ
መጥቶ ከኃጢአት አድኖናልና።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
7. የንጉስ ክርስቶስ እናቱ ተባልሽ እርሱን ከወለድሽ በኋላም በድንግልና ኖርሽ።
ድንቅ በሆነ ምሥጢር (ተዋህዶ) አማኑኤልን ወለድሽው ስለዚህም ባለመለወጥ
አጸናሽ።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
8. እግዚአብሔር በላይዋ ተቀምጦባት ያዕቆብ ያያት መሰላል አንቺ ነሽ። በሁሉ
በኩል የማይመረመር እርሱን ተፈትሖ በሌለበት ማህፀንሽ ተሸክመሽዋልና።
እኛን ስለማዳን ካንቺ ሰው በሆነ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ አማላጅ
ሆንሽን።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
9. የተባረክሽ ንጽህት የሆንሽ አዳራሽ ሆይ እንሆ ጌታ የፈጠረውን ዓለም ሁሉ
በይቅርታው ብዛት ያድን ዘንድ ካንቺ ወጣ (ተወለደ) ፈጽመን እናመስግነው።
ቸርና ሰውን ወዳጅ ነውና።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
10. ያለርኩሰት ድንግል የሆንሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ። የዓለም ሁሉ
ምክበርያ ጽዋ ነሽ። የማትጠፊ ፋና ነሽ የማትፈርሽ መቅደስ ነሽ። የቅዱሳን
መደገፊያቸው (መጠጊያቸው) የማትለወጪ የሃይማኖት በትር ነሽ። ቸር አዳኛችን
ወደ ሆነ ልጅሽ ለምኝልን ፈጽሞ ይቅር ይለን ይምረን ዘንድ ኃጢአታችንንም
ያስተሠርይልን ዘንድ።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
ወስብሓት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን
አ አ ን
ሜ ሜ ሜ
ን ን ን

አንብበው ዝም ማለት አይቻልም share
share share ያድርጉ @embtee
#join & #share👉 @embtee


👇ስዐለ አድዐኖ ለመላክ

👇መዝሙሮች ለመላክ

👇በ voice መዝሙርን ለ አምላካችን ለመዘመር👇

👇የተለያዩ መፀሀፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶች

👇ትምህርተ ወንጌል ስብከት

👇የተለያዩ ሀሳቦችን


ለመላክ👇👇👇👇👇👇



👇👇👇👇👇👇👇👇just contact us
ይላኩልን👇
@maryamn123bot
@maryamn123bot
@maryamn123bot
4 ቀን ቀረረረረ


ሕዳር ጽዮን!!
(ዉል ዉል አለኝ ደጅሽ፣ ዉል ዉል አለኝ ደጅሽ!!)
“በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀምጠን፡ ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን”
“ዉስተ አፍላገ ባቢሎን ህየ ነበርነ ወበከይነ ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን”
መዝሙር 137-1
ህዳር 21፣ ታቦተ ጽዮን የምትከብርበት ታላቅ ክብረ በኣል
ታላቅ የምስራች ይህን ታላቅ በአል ለማክበር የምትናፍቁና ሀሙስ ቀን በመዋሉ
በስራ ምክንያት ማክበር አንችልም ብላችሁ ለነበረ
የዘንድሮ 2010 ዓ.ም ህዳር ማርያም የምትዉልበት ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ
የመዉሊድ በአል በሙስሊሙ ህብረተሰብ ዘንድ የሚከበርበት ቀን በመሆኑ
እንዲሁም የስራ ቀን እንዳይሆን የጊዜ ቀመር ሰሌዳዉ(ካላንደር) ስለሚዘጋዉ
በዚህ ታላቅ የበረከት ቀን በአዲስ አለም ማርያም ከዋዜማዉ ቀን ጀምሮ ማንም
ሳይቀር በደስታ በረከት የምንሰበስብበት እለት እንዲሆን ሁላችሁም
ተጠርታችኋል ፡፡
ማንም እንዳይቀር!!
ርእሰ አድባረት ወገዳማት ዳግሚት ጽዮን አዲስ አለም ማርያም በምእራብ ሸዋ
ሀገረ ስብከት ስር የምትገኝ ስትሆን ከአዲስ አበባ በአንቦ መስመር አቅጣጫ
42 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡ ደርሶ መልስ ትራንስፖርት 18+ 18
በጥቅሉ 36ብር የሚፈጅ ሲሆን የትራነስፖርት አማራጮች በሰፊዉ የሚገኙ
እንደሆነና ከዋናው አውቶብስ ተራ እና ከአስኮ መናህሪያ ማግኘት የምትችሉ
መሆኑን እያሳሰብኩ ከመኪና መንገድ ወደ ጸበሉ እና ወደ ቤተክርስቲያኒቱ
ለመድረስ የ15 ደቂቃ ብቻ የእግር ጉዞ የሚያስኬድ መሆኑንም ማስታወስ
እወዳለሁ፡፡


Share #share ማድረግ እንዳይረሳ በ ማርያም

#join #join 👇
👉👉 @embtee
@embtee
@embtee

ለበለጠ መረጃ ይጠይቁን👇👇👇

Inbox 👉 @maryamn123bot
ደጓ እናቴ ማርያም:
#join & #share👉 @embtee


👇ስዐለ አድዐኖ ለመላክ

👇መዝሙሮች ለመላክ

👇በ voice መዝሙርን ለ አምላካችን ለመዘመር👇

👇የተለያዩ መፀሀፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶች

👇ትምህርተ ወንጌል ስብከት

👇የተለያዩ ሀሳቦችን


ለመላክ👇👇👇👇👇👇



👇👇👇👇👇👇👇👇just contact us
ይላኩልን👇
@maryamn123bot
@maryamn123bot
@maryamn123bot
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ✞
✞ ✞ እንኳን ጻድቁ አባታችን ለአቡነ ተክለሐይማኖት
ታላቅ ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን ! ✞ ✞
ህዳር 24 በዚህች ቀን ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ
ሃይማኖት ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ እንደ አንዱ ሁነው መንበረ ጸባዎትን ያጠኑበት
ታላቅ ዓመታዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም በጤና በፍቅር እንኳን አደረሳችሁ
አደረሰን
የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሐይማኖት ረድኤት በረከታቸው ምልጃና ጸሎታቸው
ከመላው ህዝበ ክርስቲያን ጋር ይሁን አሜን! እለቱ ካህናተ ሰማይ ተብሎ በቤተ
ክርስቲያናችን ይከብራል እኛንም ከጻድቁ ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡
👇👇👇👇👇👇
#join @embtee👈
@embtee👈
#share
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ✞
✞ ✞ እንኳን ለመድኃኒዓለም ወርኃዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም በጤና
አደርሳችሁ አደረሰን ! መድሐኒዓለም ክርሰቶስ በምህረቱ በቸርነቱ ይጎብኘን
አሜን !!! ✞ ✞
ጌታችን አምላካችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ህይወታችን ነው ፣
ሰላማችንና እረፍታችን እርሱ ነው ፤ የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ የጥበባት ሁሉ
ምንጭ እርሱ ነው ፤ መጀመሪያ የሌለው አልፋ መጨረሻም የሌለው ኦሜጋ እርሱ
ነው ፤ እርሱ ሁሉን የሚወድ ነው ፤ እርሱ የአለም መድሃኒት ነው!!!!
እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት ነፍሱን
ስለ ወዳጆቹ ከማኖር ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለውም እኔ ያዘዝኋችሁን
ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም
ባረያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቀውምና ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ ከአባቴ
የሰማሁትን ሁሉ ለ እናንተ አሳውቄአችኋለሁና እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ
አልመረጣችሁኝም አብም በስሜ የምትለምኑትን እንዲሰጣችሁ ልትሄዱና ፍሬ
ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ይህንን
አዘዝኋችሁ ዮኀ . 15: 12 - 17 ✞ ✞

#join #share
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEzwE8Rx0_ELfmMHsg
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የማያቋርጠው የእመቤታችን ትሕትና
እመቤታችን በቃናው ሰርግ ቤት የተገኘችበት ምክንያት የገሊላ አውራጃ ሰው
በመሆንዋ ነበር። ቅዱስ ገብርኤል ወደ እርሷ የተላከውም <ናዝሬት ወደምትባል
ወደ ገሊላ ከተማ> መሆኑ ይታወሳል። (ሉቃ. ፩፥፳፮) እርስዋም የሀገር ሰው
በመሆንዋና በደግነትዋ በዚህ ሰርግ ቤት ተገኝታለች። ወደ ሰርግ ቤት
በመምጣትዋ የምናስተውለው ትልቅ ቁምነገር የእመቤታችንን ትህትና ነው።
እመቤታችን ከፍጥረት ሁሉ ተለይታ ፈጣሪዋን ለመውለድ የተመረጠችበት
አንዱና ዋነኛው ምክንያት ትህትናዋ ነው። <<ወደ ትሑትና መንፈሱም ወደተሰበረ
ሰው እመለከታለው>> በማለት የተናገረው ልዑል እግዚአብሔር እመቤታችንን
ከሌሎች በላይ ሆና ያገኘበት አንዱና ዋነኛው ምክንያት ትህትናዋ ነበር።
እርስዋም ስትጸልይ <<የባርያዪቱን መዋረድ አይቷልና>> ብላ ከአንስተ ዓለም
ለይቶ የመረጣት አምላክ በእርስዋ ላይ ምን እንዳየ ትናገራለች። (ኢሳ ፶፯፥፲፭ ፤
ሉቃ. ፩፥፵፰) ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግም የእመቤታችንን ትህትና ከሌሎች እንደ
አብርሃም ፣ እንደ ሙሴ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ካሉ ትሑታን አበው ጋር ካስተያየ
በኋላ <<ነገር ግን በምድር ላይ እንደ ማርያም እራሱን ዝቅ ያደረገ ሰው የለም ፤
በዚህም ምክንያት እንደ እርስዋ የከበረ ማንም አለመኖሩን በግልጥ የሚታይ
ነገር ነው>> ብሏል። (on the mother of God ; Homily 1 st. Jacob of
serug)
እመቤታችን የአምላክ እናት ሆና ፈጽሞ ያልተለወጠና የማያቋርጥ ትህትና
ነበራት። ከሰው ልጆች ሁሉ እንደ እመቤታችን ያለ ትሕትና ያለውም የለም።
ከፍጥረታት ሁሉ በላይ የሚያደርጋትን አምላክን የመውለድን ክብር መሸከም
የቻለችበትን ታላቅ ትሕትና ነበራት። ትዕቢት ብዙ ፍጹማንን ሳይቀር የጣለ እስከ
ሕይወት ፍፃሜ ድረስ የማይለቅ ፈተና ነው። ወደ ሰማይ በቅድስና መሰላል
የወጡ ብዙ ቅዱሳን ጥቂት ሲቀራቸው የወደቁት በትዕቢት ነው። ክብሩና ጸጋው
ሲጨመር ጠባዩ የመይለወጥ ሰው የለም። አንድ አባት እንዲያውም <ጸጋንና
ክብርን አትስጠኝ ጸጋና ክብርን ከሠጠኸኝ ደግሞ መሸከም የምችልበት ትህትና
ስጠኝ> ብሎ እስከ መለመን ደርሷል።
እመቤታችን ግን ማንም ያልደረሰበትና ሊደርስበትም የማይቻለውን የእናትነት
ክብርን ይዛ በመላእክት አንደበት ተመስግና ለቅጽበት እንኳን አልተመካችም።
ቅዱስ ኤፍሬም <በትህትና የተናገርሽ ተራራ ሆይ > ብሎ ያመሰገናት ይህች
ድንግል እንደ ተራራ ከፍ ያለች ስትሆን ራስዋን እንደ ሸለቆ ዝቅ አድርጋ
<<እንዲህ ያለ የምስጋና እጅ መንሻ እንደምን ይደረግልኛል?>> ብላ በልብዋ
አሰበች። በዚህ የእናታችን ትሕትና እጅግ እንደነቃለን ፤ <ድንግል ሆይ እንዲህ
ያለ የምስጋና እጅ መንሻ እንደምን አይደረግልሽም የተመረጥሽው የሰማይና
ምድርን ፈጣሪ ልትወልጂ አይደለም ወይ? እሳተ መለኮትን ተሸክመሽ ፣ ሰማይና
ምድር የማይችሉትን ችለሽ እንዲህ ያለ የምስጋና እጅ መንሻ እንደምን
አይደረግልሽም?> እያልንም እናመሰግናታለን።
አምላክን ከጸነሰችበት ሰዓት ጀምሮ እመቤታችን ከፍጥረት ሁሉ በላይ
የሚያደርጋትን ክብር ተጎናጽፍ እያለ ለቅጽበት አልታበየችም። በሦስት መንገድ
ማለትም በሃሳብዋም ፣ በንግግርዋም ፣ በሥራዋም ትህትናዋን አሳይታናለች።
ሰማያዊ መልአክ አደግድጎ እያመሰገናት <እንዲህ ያለውን የምስጋና እጅ መንሻ
እንደምን ይቀበሉታል?> ብላ በልብዋ በማሰብ በሃሳብዋ ትሁት እንደሆነች
አሳይታናለች። በንግግርዋ ደግሞ ከመጽነስዋ በፊትም ከጸነሰች በኋላም ራስዋን
<እንሆኝ የጌታ ባሪያ> <የባርያይቱን መዋረድ አይቷልና> በማለት በትህትና
ጠርታለች።
ቅዱስ ያሬድ <እንዘ አመቱ እሞ ረሰያ> እንዳለ እግዚአብሔር ባርያው ስትሆን
እናቱ አደረጋት ፤ እርስዋም ደግሞ እናቱ ስትሆን ራስዋን ባሪያ አደረገች።
በተግባር ደግሞ ትህትናዋን ያሳየችን ከመልአኩ ብሥራት በኋላ ባደረገችው ጉዞ
ነው። እንደጸነሰች በእመቤት ደንብ ልቀመጥ ሳትል ወደ ተራራማው ወደ ኤፍሬም
ሀገር ኤልሳቤጥን ለመጠየቅ ተፋጥናለች። የአምላክ እናት ሆና እያለ የነቢዩን
እናት ኤልሳቤጥን ተሳልማለች። በስተርጅና የጸነሰችውን ኤልሳቤጥን
ስትንከባከብ ሦስት ወራት ቆይታለች። (ሉቃ.፩፥፶፮)
አሁን ደግሞ በታላቅ ትህትናዋ በሰርግ ቤት አስቀድማ ተገኘች። መገኘትዋ ብቻ
ሳይሆን ሰርግ እንደተጠራ እንግዳ በክብር ወንበር ተቀምጣ መደሰትን
አልመረጠችም። የሰርግ ቤቱ ወይን ጠጅ ማለቅ ከደጋሾቹ ቀድሞ ያስጨነቀው
እርስዋን ነበር። በማያቆም ትሕትናዋ የምትደነቀው እመቤታችን በቃና ሰርግ
ቤትም ውሎዋ ከክብር እንግዶች ጋር ሳይሆን ከአገልጋዮቹ ጋር ነበር።
ከቃና ዘገሊላ ፬ ዕትም መጽሐፍ በጥቂቱ የተወሰደ

#Share👇👆

https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEzwE8Rx0_ELfmMHsg
ውድ እህት ወንድሞቼ በክርስቶስ ስም ሼር በማድረግ ላላወቁ እናሳውቅ
"እግዚአብሔር"
እግዚ=>ጌታ
አብ=>አባት
ሔር=>ቸር አፅናኝ፡ መንፈስ
እግዚአ=>ጌታ ገዥ
ብሔር=>አለም
እያንዳንዳቸው ፊደላት የራሱ የሆነ ትርጉም አላቸው፤እኛም ስንፅፍቸው የስሙ ስያሜ ሙሉ ትርጉም እንዲኖረው በጥንቃቄ ቢሆን በረከቱ ለኛ ነው።
👉🏻ስህተት የሆኑ አፃፃፉች፦
=>እ/ር
=>እግ/ር
=>እግዜር
=>እግዛቤር
=>እግዚሀብሔር
=>እግዛሃብሔር
ወንድሞች እህቶች ይህ ስህተት እንደሆነ አውቀን በረከቱን ለማግኘት፦
📝👉🏻እግዚአብሔርተብሎ መፃፍ ይኖርበታል፤
E/r
Eg/r
Egzi
EGZI
Egzaber
Egzhabher
👀👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻
EGZIABHER
Egziabher
ብለን የፈጣሪን ስም አስተካክለን መፃፍ ክርስቲያናዊ ግዴታችን ነው ።

"በእኔ ተማምኗልና አስጥለዋለሁ፥ስሜንም አውቋልና እጋርደዋለሁ፤ [መዝ.61:14]
ስለ ቃሉ የቃሉ ባለቤት ልኡል ሀያል ቅዱስ እግዚአብሔር ይመስገን!

አሜን ማለት፦ይሁንልን ይደረግልን……ማለት ነው።
👉🏻ስህተት የሆኑ አፃፃፉች፦
=>አመነ
=>አሚን
=>አመን
=>አሜን አሜን ሁለቴ(2) አሜን ማለት "የስላሴዎችን አንድነትና ሶስትነት"አይወክልም፤(ትርጉም አልባ ነው)
በረከቱን ለማግኘት፦
📝👉🏻አሜን
📝👉🏻አሜን አሜን አሜን
📝👉🏻አሜን ፫
📝👉🏻አሜን(3)
📝👉🏻ተብሎ መፃፍ አለበት ።

Be English Words Lemetsaf ከፈለግን ፦

AMIN
Amin
Amin Amin Amin
Amennnn
Aman
👆🏻እንዲህ አይነት አፃፃፍ ስህተት ሲሆን ፦ 👇🏻👀
AMEN
AMEN AMEN AMEN
Amen
Amen Amen Amen
Amen (3)

Be Englizegnaw Fidel Sntsef Endezih👆🏻 Aderegn Bntsef Bereketu ለእኛ ነው ።

የእስራኤል አምላክ ልኡል እግዚአብሔር ለሁላችንም ማስተዋሉን ያድለን! አሜን

ወስብሐት ለ እግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር ይቆየን።
#Share ለሁሉም ይድረስ💠

#JOIN👇
🔰🔰🔰🔰🔰
♥️ @embtee ♥️
♥️ @embtee ♥️
♥️ @embtee ♥️
♥️ @embtee ♥️
♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️
🔆ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ለማወቅ ትክክለኛው ቻናል🔅
👇
ለመቀላቀል ከስር ሰማያዊውን ይጫኑ
⚠️JOIN OUR⚠️
CHANNEL & GROUP

♻️ 📖 ገና እንዘምራለን
🔺የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇
👉 @mezmurat123 👈
👉 @mezmurat123 👈
👉 @mezmurat123 👈
👉 @mezmurat123 👈
👉 @mezmurat123 👈
👆👆👆👆👆👆

♻️ 📖 ደጓ እናቴ ማርያም
♦️የእመቤታችን አስራት ልጆች መሰባሰቢያ፣ መማሪያ ድንቅ ቻናል
✔️ @embtee
✔️ @embtee
✔️ @embtee
✔️ @embtee

♻️ 📖 ️የ እመብርሀን ልጆቸ
🔺ኦኦርቶዶክስ ተዋህዶ እናቴ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 https://tttttt.me/joinchat/EmxkTg3kSPqonu9_bhCMsg
https://tttttt.me/joinchat/EmxkTg3kSPqonu9_bhCMsg
https://tttttt.me/joinchat/EmxkTg3kSPqonu9_bhCMsg
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

💢እስከ አሁን እነዚህን ድንቅ ድንቅ ቻናሎች ያላዩ ወዳጆች አሏችሁ
አሁኑኑ ለአምስት ወዳጆቻችሁ ብቻ ላኩላቸው
እናመሰግናለን።
⚠️ለሌሎች እንዲደርስ📩#Share እንዳይረሳ

🔰ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር።🔰
✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️
🔸ጥምቀተ_ባሕር🔸

ጥምቀተ ባሕር ዮርዳኖስ ነያ /2ጊዜ/
ሀሌ ሉያ /4ጊዜ/
🔆አዝ
ጌታችን ሲጠመቅ ባሕር ምን አለች
አልችለውም ብላ ወደ ኋላ ሸሸች
ብርሃነ መለኮት በወንዙ ሲሞላ
ዮርዳኖስም ሸሸ ሄደ ወደ ኋላ
🔆አዝ
አብ በመጣ ጊዜ ደመናውን ጭኖ
መንፈስ ቅዱስ ታየ በርግብ አምሳል ሆኖ
ለልጁ ምስክር ሊሆን ፈለገና
ቃሉን ተናገረ ሆኖ በደመና
🔆አዝ
ጌታችን ሲጠመቅ በ30 ዓመት
ባሕር ኮበለለች ግዑዟ ፍጥረት
ሰማይ ተከፈተ ሆነልን ፀአዳ
ምሥጢረ ሥላሴ ታየ የዛን ለታ
🔆አዝ
እልል በይ ዮርዳኖስ የጥምቀት መገኛ
የጽድቅ መሰላል የድኅነታችን መገኛ
ቀላያት አብርህት ብዙዎች እያሉ
እንደምን ተመረጥሽ ዮርዳኖስ ከሁሉ
👇 👇
🔻🔻🔻🔻🔻🔻
🗯 @Zemaryan 🗯
🗯 @Zemaryan 🗯
🗯 @Zemaryan 🗯
🗯 @Zemaryan 🗯
🗯 @Zemaryan 🗯
🗯 @Zemaryan 🗯
🔺🔺🔺🔺🔺🔺
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን።
መዝሙረ ዳዊት ፻፶፥፮

ለሌሎች እናካፍል #Share_በማድረግ
~ አዋጅ! አዋጅ! አዋጅ !
የመሰከረም 4ቱ ሰላማዊ ሰልፍ
ዝርዝር መርሃ ግብር ወጥቷል
*★★★*

★ ★ ይህን መልእክት በየፔጁ #SHARE አድርጉታ ?።

★ ወደ ቀደመ ኦርቶዶክሳዊ ማንነታችን በቶሎ እንመለስ።

#ETHIOPIA | ~ ኦርቶዶክስ ሀገር መሆኗን ለዓለሙ ሁሉ የምታሳውቅበት ዕለት መጥቷል። አንተ የተኛህ ሁሉ ንቃ።

• ሰልፉ ከኦሮሚያ ቤተ ክህነት ጉዳይ ጋር ምንም የሚያይዘው ጉዳይ የለም። የኦሮሚያ ቤተ ክህነት የሚባለው አጀንዳ የሚፈታው በተጀመረበት በቅድስ ሲኖዶስና በራሷ በቤተክርስቲያኒቱ ልጆች ነው። ይህን በተመለከተ የሚጻፍ መፈክርም ሆነ ባነር መኖር የለበትም። እንዲህ ዓይነት ባነር ጽፈው የሚወጡ ካሉ እነጃዋር የሚልኳቸውና የሰልፉን መንፈስ ለፖለቲካቸው ማራገቢያ የሚያውሉ ሰዎች ሴራ ነውና ወዲያውኑ እንደታዩ ለሕግ አስከባሪዎች በመጠቆም ማስረከብ ይገባል። በመስከረም 4 ቱ ዓለም አቀፍ ሰልፍ ኦሮሞ፣ ዐማራ፣ ትግሬ፣ ደቡብ፣ ነጭ፣ ጥቁር የለም። እስላም ጴንጤ፣ ካቶሊክ የለም። ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን የሚወዱ ሁሉ አደባባይ ይወጣሉ። በደሏን፣ ችግሯን፣ ብሶቷን አብረው ያሰማሉ። መሆን ያለበት ይኼ ነው። ይሠመርበት።

የአባቶቼን ርስት አልሰጥህም፡፡
*** እንደ አምለከ አበው መድኀኔ ዓለም ፈቃድ #ለመስከረም_፬/ ፳፻፲፪ ዓ.ም. #የሚካሄደውን_ሰልፍ_በተመለከተ_የወጣ_መርሐ_ግብር_

••
ሰልፉ በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገራት መስከረም ፬ በአደባባዮች ይካሄዳል፡፡ በዕለቱም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በሰልፉ ላይ ይገኛሉ፡፡

•••
የሰልፉ አስተባባሪዎች ሁሉም ምዕመን በኀላፊነት የሚያስተባብሩት ሲሆን፤ በግንባር ቀደምትነት ግን
• የሰ/ት/ቤቶች አንድነት፤

• የመንፈሳዊ ኰሌጅ ተማሪዎችና ምሩቃን፤

• በሰ/ት/ቤቶችማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን፤

• የወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት፤

• የሠለስቱ ምዕት ማኅበራት ኅብረት፤

• የአእላፋት ድምፅ የካህናትና ምእመናን ተናሥኦት ኅብረት፤

• የጽዋ ማኅበራት ሙሴና ደርገ ሙሴዎች ናቸው፡፡

የሰልፉ ይህን መስሎ ይካሄዳል።

• መስከረም 4 ጠዋት 2.30-3፡30 ሰዓት ሁሉም የአዲስ አበባ ነዋሪ ነጭ ልብሱን ለብሶ ሌሊት ቅዳሴ ያስቀድሷል። ቅዳሴው እንዳበቃ ከየአብያተ ክርስቲያናቱ እስከ ተመደበላቸው መሰባሰቢያ ቤተ ክርስቲያን ድረስ በሚከተለው ሁናቴ ጉዞ ወደ መስቀል አደባባይ ይሆናል።

★ ለምሳሌ ከሰሜን አቅጣጫ የሚመጡ የተዋሕዶ ልጆች በሙሉ መገናኛቸው ገነተ ጽጌ ላይ ይሆናል። የደቡቦቹም፣ የምሥራቆቹም፣ የምዕራቦቹም እንዲሁ የመገናኛ ስፍራ ይነገራል።

★ ሰልፉ መንግሥትን ለመለመን፣ እግሩ ስር ለመደፋት አይደለም። ሰልፉ ዝም ስላልን ለናቁን፣ ቁጥራቸውም ትንሽ ነው ብለው ለተገዳደሩን ተዉን ትንሽ አይደለንም። ከመቻቻል ወደ መከባበር እንሸጋገር ለማለትና በዚያውም በኢትዮጵያ አየር ላይ የነገሰውንና ደም አፍሳሽ ዲያብሎስን በመስቀሉ፣ በዕጣኑ ማዕጠንት፣ በዝማሬ፣ በምህላ ለማስታገስ፣ ለማሰርም ጭምር ነው።

የሰልፉ ሥዕል ይህን ይመስላል።

• ባለ መለከቶችና ባለ ጥሩንባዎች ድምፅ እያሰሙ ባንዲራን እያውለበለቡ ከፊት ይመራሉ፤

• በመከተልም የበገና ዝማሬ የሚያቀርቡ በገናቸውን እየደረደሩ፣ ተው ስማኝ ሀገሬ፣ እርግብና ዋኔ፣ ኪራላይሶ፣ ስማነ አምላክነ ወመድኃኒነ እያሉ ይከተላሉ፡፡

• ማዕጠንት የያዙ ካህናት እያጠኑ፣ በመስቀላቸውም እየባረኩ፣ አቡነ ዘበሰማያት፣ ጸሎተ ኪዳን፣ ጸሎተ ማርያም፣ መልክአ ማርያምና መልክአ ኢየሱስ፣ ዳዊቱንም ፍካሬ ዘጻድቃንን እየጸለዩ ይመራሉ፤

• የየሰንበት ትምህርት ቤት መለያ ልብስ(ዩኒፎርም)ና ጥንግ ድርብ የለበሱ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና ተማሪዎች በዝማሬ ጭምር አባቶችን ይከተላሉ፤ /የሰ/ትቤቶች አመራር ያስተባብራሉ/

• የጽዋ ማኅበራት በነጭ ልብስ (በማኅበራቸው መለያ ልብስ) ይከተላሉ /የየማኅበሩ ሙሴና ደርገ ሙሴ ያስተባብራሉ/

• ጥንግ ድርብ የለበሱ መዘምራን ማኅሌታውያን ይከተላሉ /አጋፊሪና መጨኔ ያስተባብራሉ/

• መስቀል የያዙ ዲያቆናትና ካህናት፤ ልብሰ ተክህኖ የለበሱ፥ ጥላና ድባብ የያዙ ካህናት ይከተላሉ፤ /ሊቀ ዲያቆንና ቄሰ ገበዝ ያስተባብራሉ/

• ምዕመናን ነጭ ልብስ፣ ነጠላ (ቲሸርት) በመልበስ ይከተላሉ፡፡ /የሰባካ ጕባኤ አባላት ያስተባብራሉ/


• በተመደበልን ቤተ ክርስቲያን ከተገኘን በኋላ ጠዋት ከ3፡30-4፡30 በሊቃነ ጳጳሳት እየተመራን ወደ መስቀል አደባበይ ጕዞ ይካሄዳል፤

• ከረፋዱ 4፡30-7፡30 በመስቀል አደባባይ ሰልፉ ይካሄዳል፡፡

• የመንፈሳዊ ኰሌጅ ተማሪዎችና ምሩቃን ጥቋቁሩን ቀሚሳቸውን እንደለበሱ /አስተባባሪዎሆነው ያስተባብራሉ/

• የማኅበረ ቅዱሳን አባላትና ተማሪዎችም /የተመደቡላቸው አስተባባሪዎች ያስተባብራሉ፡፡/

★ ስለ ጽዮን ዝም አንልም።

#ልዩ_ማስታወሻ፤ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና ምእመናን ተቃውሟቸውን በድጋሚ መስከረም 16 በደመራ ዕለት በትርዒቶቻቸው እንደ የሁኔታው ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ ተቃውሞው ሁሉ ግን በዝማሬ፣ በምስጋና እንጂ ፉጨት፣ ግርግር፣ የለውም። ስንዱዋ እመቤት የሥርዓት ሁሉ ምንጭ ናትና ልጆቿ ምን ያህል ሥርዓት እንዳላቸው በዐይናቸው ይመለከቱታል።

• ተጨማሪ የሰልፉን ማብራሪያዎች በተመለከተ ነገ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ይሰጣልና ይጠብቁ፡፡

•••
¶ድልና ትንሣኤ ለኢትዮጵያ ሀገሬና ለተዋሕዶ ሃይማኖታችን ! ውድቀትና ጥፋት፤ ለሁለቱም ጠላቶች። አራት ነጥብ።

•••
" እኔ ግን እላለሁ! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት፣ ቅድስት፣ ርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜ ትርሳኝ። ትክዳኝም። ባላስብሽና ባልሟገትልሽ ባልሞትልሽም ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ። ሳለጎበድድና ሳለከዳሽ እንድኖርም አምላክሽ ይርዳኝ። ይህን ባላደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ።

"ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው፤ አሁንም እየሆነ ባለው እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ።" አሜን !

"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "
•••

ሻሎም ! ሰላም !

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ጳጉሜን 4/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
​​#ሕዳር_ሚካኤል !

#እንኳን_ለመላእክት_አለቃ_ለቅዱስ_ሚካኤል #በዓለ_ሲመት_በሠላም_አደረሰን !

በዓለ ሲመቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል (ሕዳር 12)
(አንብባችሁ ስትጨርሱ ለሌሎችም ታሪኩን እንዲያዉቁ #SHARE_SHARE_SHARE
ብታደርጉ ብዙ አተረፋችሁ፡፡)

ቤተ ክርስቲያን ልጆቹዋ የመላእክትን ተራዳኢነት አውቀው እንዲጠቀሙና የመንግሥቱ ወራሾች ለመሆን እንዲበቁ ስትል ለቅዱሳን መላእክት የመታሰቢያ ቀን በመስጠት በእነርሱ የምናገኛቸውን እርዳታዎች እንዲታወሱ ታደርጋለች፡፡

በዚህም መሠረት በህዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡

እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል። ይህን ሁለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በተሰኘው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡

የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው ፡፡ ይህም እንደሆነ እንድንረዳ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለውን እስራኤል ዘሥጋን ሲራዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት “… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ የያዘ ሰው በፊቱ ቆመ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት
አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ” (ኢያ.5፡13) ይለናል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነፃ ሲያወጣቸው ይመራቸው የነበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ሹመቱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይም በመሆኑ ስለ እነርሱ ዲያብሎስ ይዋጋው፣ በጸሎትም ይራዳቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ኃጢአት ሠርተው ሲያገኛቸው ለእግዚአብሔር አድልቶ ኃጢአተኞችን ስለሚቀጣ እግዚአብሔር ሕዝቡን “በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት” (ዘጸ.23፡21) ብሎ አስጠንቅቋቸው ነበር፡፡

ይህም ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙን ያስረዳናል፡፡ ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱት ጥቅሶች ሕዝበ እስራኤልን ይራዳቸው የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ አያረጋግጥም የሚል ካለ “መልአክ” የተባለው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ነቢዩ ዳንኤል በተላከ ጊዜ ገልጦልን እናገኛለን፡- ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ቅዱስ ሚካኤል ስለመሾሙ ሲመሰክር “በእውነት በመጽሐፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ ማንም
የለም”(ዳን.10፡21) ብሎአል፡፡

ስለዚህም ለኢያሱ የተገለጠውና እስራኤላውያንንም የመራው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን እንረዳለን፡፡

@christian930 💚
@christian930 💛
@christian930

የቅዱስ ሚካኤል አለቅነት በሐዲስ ኪዳንም አንደሚቀጥል ይህ ነቢይ በትንቢቱ “በዚያ ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ ሚካኤል ይነሣል..” (ዳን.12፡1) በማለት ተናግሮለታል ፡፡

ስለዚህም ቅዱስ ሚካኤል እኛን ከሰይጣን አሽክላና ወጥመድ ይጠብቀንና በጸሎቱ በእግዚአብሔር ፊት ይቆምልን ዘንድ በእኛም ላይ ሹም ነው። ምክንያቱም እኛ የእግዚአብሔር ሕዝቦችና የርስቱ ወራሾች ነንና፡፡

እግዚአብሔር ነቢዩ ሙሴን የሕዝቡ መሪ አድርጎ መሾሙ እጅግ ትሑትና ስለመንጎቹ ነፍሱን እንኳ አሳልፎ እስከመስጠት ደርሶ ስለሚወዳቸው ነበር፡፡ (ዘኁል.12፡3፤ዘጸአ.32፡32)በሕዝቡም ላይ እርሱን መሾሙ እንዲሠለጥንባቸው ወይም እንዲገዛቸው ሳይሆን በትምህርቱና በጸሎቱ እነርሱን እንዲያግዛቸው ነው፡፡ እንዲህም ስለሆነ ቅዱስ እስጢፋኖስ ስለሙሴ ሲመሰክር “እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው”አለ፡፡ (የሐዋ.7፡35)

እንዲሁ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እጅግ ትሑትና ለሠራዊቱ ተቆርቋሪ የሆነ መልአክ በመሆኑ በመላእክትና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ተሾመ፡፡ በመላእክትና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙ ልክ እንደ ሙሴ በእነርሱ ላይ ሊሠለጥንባቸው ወይም ሊገዛቸው ሳይሆን መላእክትን ሊመራ ፣ እኛን ደግሞ ከሰይጣን ጥቃት ሊጠብቀንና በጸሎቱ ሊራዳን ነው (ይሁዳ.12) ፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን መላእክት እኛን እንደሚጠብቁና እንደሚራዱ እንዲሁም ስለእኛ በፊቱ አንደሚቆሙ ሲያስተምረን “ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ስንኳ እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ሁል ጊዜ በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁ” (ማቴ.18፡10) ብሎናል፡፡

እኛን ይጠብቁ ዘንድ የተሰጡን ቅዱሳን መላእክት ስለእኛ እንዲህ የሚቆረቆሩና ስለመዳናችን የሚተጉ ከሆነ በቅድስናው ልቆ የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመው ቅዱስ ሚካኤል እንዴት ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ይበልጥ አይቆም? (ሉቃ.13፡6-9) እንዴትስ በተሰጠው ሥልጣንና ኃይል አይረዳን? (መዝ.33፡7) እርሱ “ስለሕዝብህ ልጆች የሚቆመው” መባሉም እኛን በጸሎቱና በተራዳኢነቱ የጽድቅ ሕይወታችንን በሚገባ እንድናከናውን እንደሚራዳን የሚያሳይ ኃይለ ቃል ነው፡፡

የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ጸሎቱና በረከቱ በእኛ ላይ ለዘለዓለሙ ይደርብን አሜን፡፡
@zemaryan
Forwarded from ✿✟ የ҈ ዳ҈ ዊ҈ ት҈ ዜ҈ ማ҈ ✟✿ (🩸ყเƭαყαℓ🩸🕊 የ҈ ተ҈ ዋ҈ ህ҈ ዶ҈ ል⃝ጅ🕊 📸 Cinematographer 🎞})
በእግዚአብሔር እረዳትነት ሀይማኖቴን አሳልፌ አልሰጥም የሀገሬ ሰው ካሁን ቀደም የበደልሁ አይመስለኝም ጉልበት ያለህ በፀሎት ጉልበት የሌለህም ለልጅ ለሚስትህ ለሀይማኖትህ ስትል በሀዘን እርዳኝ ወስልተህ የቀረህ ግን ኃላ ትጣላኛለህ አልተውህም ማ  ር  ያ  ም  ን  ለዚህ ከዚህ አማላጅ የለኝም ዘመቻዬ  (የካቲት 5) ነው በእለተ እሁድ ከጥዋቱ 1 ሰአት መስቀል አደባባይ ከትመህ ጠብቀኝ


#share #ሼር

@zemaryan
@zemaryan
@zemaryan
ሰበር መረጃ
===========
ሕገወጡ ቡድን (የቀድሞ 3 ጳጳሳት እና 25 ሕገ ወጥ ተሿሚዎች) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት እና ቢሮዎች እንዳይገቡ ፍርድ ቤት አግዷል።

“እስከ ትበጽህ ለሞት ተበዓስ በእንተ ጽድቅ እስመ እግዚአብሔር አምላክከ ይትበአስ
በእንቲአከ”

“እስክትሞት ለእውነት ታገል። እግዚአብሔር ላንተ ይታገልለሀልና”

           ሲራክ 4 ፡ 2

ምዕመናን መረጃ ይደርሳቸውና ይነቁ ዘንድ ይሄን ሊንክ ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ አድርሱ ቀላል የሚመስል ግን ብዙ ጥቅም አለው አድርጉት።

በዚ ግዜ ለዚያልሆንን መቼ ልንታዘዝ ነው። 

#share #share #share 

ማህበረ ቅዱሳን
https://tttttt.me/mahbere_kidusan
CASTING CALL

በትወና ለመሳተፍ ኦዲሽን መውሰድ ምትፈልጉ 7 ሴት እንፈልጋለን

ምዝገባ ጀምረናል

አዲስ በምንሰራው ፊልማችን ላይ ለመሳተፍ ከላይ የተገለፀውን መስፈርት የምታሟሉ ብቻ
● ሙሉ ስም
● እድሜ (የትውልድ አመተ ምህረት)
● ቁመት
●  ክብደት
● ስልክ ቁጥር
• telegram user
● 3 ፎቶግራፍ (በፕሮፌሽናል ካሜራ የተነሳ እንዲሁም
● Instagram username (አካውንት ላለው)
● በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የተወናችሁበት ስራ ካለ ሊንኩን አያይዛችሁ መላክ ይጠበቅባችኋል።
መረጃዎቹን ለመላክ
@Ethioquationary123bot
በቴሌግራም @Ethioquationary123bot
በመላክ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን

ማሳሰቢያ :- ከተጠቀሰው ውጪ (መስፈርቱን የማታሟሉ ሰዎች) ሌላ የሚወጣ ማስታወቂያ ስለሚኖር በትእግስት ጠብቁ በተጨማሪ በተመሳሳይ ሰአት ብዙ ሰዎች ስለሚልኩ ለሁሉም ሰው ለመመለስ ስለምንቸገር ከላይ የተቀሰውን ግላዊ መረጃችሁን እና ፎቶግራፍ ብቻ ላኩልን ከተጠቀሰው ውጪ የሚልክ ሰው ውድቅ ይደረጋል።
ለሚኖሩ ተጨማሪ ማብራሪያዎች የቴሌግራም የፊልም ካስቲንግ ቻናላችንን ይቀላቀሉ



Share share #share