✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.2K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
#join & #share👉 @embtee


👇ስዐለ አድዐኖ ለመላክ

👇መዝሙሮች ለመላክ

👇በ voice መዝሙርን ለ አምላካችን ለመዘመር👇

👇የተለያዩ መፀሀፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶች

👇ትምህርተ ወንጌል ስብከት

👇የተለያዩ ሀሳቦችን


ለመላክ👇👇👇👇👇👇



👇👇👇👇👇👇👇👇just contact us
ይላኩልን👇
@maryamn123bot
@maryamn123bot
@maryamn123bot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📊 + ድንግል እመቤቴ ኪዳነ ምሕረት ሆይ +
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ኪዳነ ምህረት ወርሃዊ የመታሰቢያ ክብረ በዓል
በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን
ከገነት በተሰደደ ጊዜ የአዳም ተስፋው አንቺ ነሽ በግፍ የተገደለው የአቤል
የውሃቱ አንቺ ነሽ::የሴት ቸርነት አንቺ ነሽ የሄኖክም ስራዎቹ ከክፉ ጥፋት
የዳነባት የኖህ መርከብ የሴም ቡራኬው እድል ፈንታውም አንቺ ነሽ ::የአብርሃም
የይስሃቅ መአዛ የያእቆብም መሰላል አንቺ ነሽ ::ዮሴፍንም የምታረጋጊው አንቺ
ነሽ የሙሴ ጽላት ጳጦስ የተባለች የሲና ዕጽ በካህን አሮን ልብስ የነበረች ጽናጽል
ዳግመኛም የበቀለችና ያበበች ያፈራችም በትር አንቺ ነሽ:: የእያሱ የምስክር
ሃውልት የጌድዮን ጸምር የሳሙኤል ሽቱ ሙዳይና የዘይት ቀንድ አንቺ ነሽ
::የተመካባት የእሴይ ስር የአሚናዳብም ሰረገላ የዳዊት መሰንቆ የሶሎሞንም
አክሊል አንቺ ነሽ::የታጠረች ተክል የፀናች የውሃ ጉድጓድ አንቺ ነሽ::የኤልያስ
የወርቅ ሞሶብ የኤልሳ ጋን አንቺ ነሸ:: ኢሳያስ ጽንስ ከድንግልና ጋር የተናገረልሽ
ዳንኤልም ያለ ሩካቤ መውለድን የተናገረልሽ አንቺ ነሽ:: ፋራን የምትባል
የእንባቆም ተራራ የተዘጋች የህዝቅኤል ምስራቅ የቤቴልሔም ህግ መውጫ
ኤፍራታ የምትባል ምድር አንቺ ነሽ::የሲሎንዲስ እጸ ህይወት የናሆምም ቁስል
የምታድን የዘካርያስ ደስታው የሚልኪያስ እጽህት አዳራሽ አንቺ ነሽ:: ድንግል
ሆይ የነቢያት ትንቢትና ምሳሌ የሃዋርያት ሞገሳቸው የሰማእታት እናታቸው
የመላእክትም እህታቸው አንቺ ነሽ::በመዐልትና በሌሊት በበሮቿ ደጅ የሚጠኑ
የወራዙትና የደናግል የመነኮሳትም መመኪያቸው አንቺ ነሽ:: እመቤቴ ማሪያም
ሆይ እኔን ያጥያተኛዋን ባሪያሽን በደሌን በዘርፋፋው ቀሚስሽ ሸፍነሽ በበደሌ
ብዛት ከእጁ እንዳያወጣኝ ከአባቶቼ አምላክ ከልጅሽ ከወዳጅሽ ከመድሐኒአለም
ዘንድ አማልጅኝ::

አሜን አሜን አሜን

አሜን አሜን አሜን [7]
‎├ ይ τ α 🎀 φ σ ι
‎├ Gashahun Tashome
‎├ Li X Frïsky😷(Ayo&teo)fan😍
‎├ bebi bebi
‎├ Abenet Akalu
‎├ ferehiwot Yekirkos
‎└ Fikirte Girme

👥 7 people have voted so far
✞ ✞በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን! ✞
✞ ✞
† † እስጢፋኖስም ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ
ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ።† †(የሐዋ.ሥራ ፯፡፶፱-፷)
እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖ ወርሃዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም
በጤና አደረሳችሁ አደረሰን!!!
† † ሰው ግን ዓለምን ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢጎዳ ምን ይረባዋል/ምን
ይጠቅመዋል?† † ማቴ.፲፮፡፳፮
የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው። መዝ. 115/116፡15
† †እኔን የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ መስቀሌንም ተሸክሞ /መከራዬን
ሳይሰለች/ ዕለት ዕለት ይከተለኝ † †፡፡ ማቴ ፲፡፴፰-፵፪
† † ስለ ጽድቅ የሚራቡና የሚጠሙ፣ እንዲሁም የሚሰደዱ ብጹዓን
ይጠግባሉና፣ መጽናናትንም ያገኛሉና…† †
ጌታ በተራራ ስብከቱ ከተናገራቸው፣ ካስተማራቸው የሕይወት ምግብ የሆነ ቃሉ
ማቴ.፭፡፩-ፍጻሜ ቅዱስ እስጢፋኖስ በፍርድ አደባባይ ሲቆምና ሲከሠስ እውነቱን
መናገሩ ሕይወቱን እንደሚያስከፍለው እያውቀ፡፡ እውነቱን መናገር አልፈራም፡፡
አያችሁ ቅዱስ እስጢፋኖስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ነበር ያስተዋለው፡፡ ውጤቱ
ምንም ይሁን፡፡ እግዚአብሔር በእውነት የተሞላን እንድንሆን ይፈልጋል፡፡
የክርስቶስ ምስክር ሆነው የተሰዉት ቅዱሳን የክብር አክሊል የተቀዳጁት
ለእውነት ስለሞቱ ነው፡፡ ነገር ግን በመንፈስ ሕያዋን ናቸው፡፡ በዘላለማዊ
ደስታም ከእግዚአብሔር ጋር ኖረዋል፡፡ እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ
በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር የነፃ ወጪዎች
ከተባለችው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያም ሰዎች ከኪልቅያና ከእስያም
ከነበሩት አንዳንዶቹ ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር፤ ይናገርበት
የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም። በዚያን ጊዜ። በሙሴ
ላይ በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን
አስነሡ። ሕዝቡንና ሽማግሌዎችንም ጻፎችንም አናደዱ፥ ቀርበውም ያዙት ወደ
ሸንጎም አመጡትና። ይህ ሰው በዚህ በተቀደሰው ስፍራ በሕግም ላይ የስድብን
ነገር ለመናገር አይተውም፤ ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል
ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል ሲል ሰምተነዋልና የሚሉ የሐሰት
ምስክሮችን አቆሙ። በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኵር ብለው ሲመለከቱት እንደ
መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት። ፮፡፰-፲፭) “ይህ እንዴት ያለ ይቅርታ ነው? ልክ ጌታ
በዚያ በመከራ ሰዓት ብዙ መከራ ሲያጸኑበት አባት ሆይ የሚያደርጉት አያቁምና
የቅር በላቸው ብሎ የፍቅር አምላክ ይቅርታ እንዳደረገላቸው ሁላ የጌታው ተከታይ
የሆነው፤ እስጢፋኖስም።” “ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ
ይወግሩት ነበር። ተንበርክኮም። ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ
በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ። ሳውልም በእርሱ መገደል
ተስማምቶ ነበር።” (የሐዋ.ሥራ ፯፡፶፱-፷) የሰማዕቱ በረከት ይደርብን እስከ ሞት
ድረስ ለአምላካችን እንድንታመን እርሱ ይርዳን፡፡ እስከ መጨረሻ ድረስ የታመንህ
ሁን የህይወት አክሊል እሰጣሃለሁ ራዕይ 2፡10 ለዚህ ነው እኮ ቅ/ጳውሎስ
“እሩጫዬን ጨርሻለሁ ሃይማኖቴን ጠብቄያለሁ ከእንግዲህ የሕይወት አክሊል
ይጠብቀኛል” ያለው ፪ጢሞ.፬፡፮-፯
የእግዚአብሔር፣ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት
ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው
መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው
ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ይቆየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ። ይቆየን
4 ቀን ቀረረረረ


ሕዳር ጽዮን!!
(ዉል ዉል አለኝ ደጅሽ፣ ዉል ዉል አለኝ ደጅሽ!!)
“በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀምጠን፡ ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን”
“ዉስተ አፍላገ ባቢሎን ህየ ነበርነ ወበከይነ ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን”
መዝሙር 137-1
ህዳር 21፣ ታቦተ ጽዮን የምትከብርበት ታላቅ ክብረ በኣል
ታላቅ የምስራች ይህን ታላቅ በአል ለማክበር የምትናፍቁና ሀሙስ ቀን በመዋሉ
በስራ ምክንያት ማክበር አንችልም ብላችሁ ለነበረ
የዘንድሮ 2010 ዓ.ም ህዳር ማርያም የምትዉልበት ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ
የመዉሊድ በአል በሙስሊሙ ህብረተሰብ ዘንድ የሚከበርበት ቀን በመሆኑ
እንዲሁም የስራ ቀን እንዳይሆን የጊዜ ቀመር ሰሌዳዉ(ካላንደር) ስለሚዘጋዉ
በዚህ ታላቅ የበረከት ቀን በአዲስ አለም ማርያም ከዋዜማዉ ቀን ጀምሮ ማንም
ሳይቀር በደስታ በረከት የምንሰበስብበት እለት እንዲሆን ሁላችሁም
ተጠርታችኋል ፡፡
ማንም እንዳይቀር!!
ርእሰ አድባረት ወገዳማት ዳግሚት ጽዮን አዲስ አለም ማርያም በምእራብ ሸዋ
ሀገረ ስብከት ስር የምትገኝ ስትሆን ከአዲስ አበባ በአንቦ መስመር አቅጣጫ
42 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡ ደርሶ መልስ ትራንስፖርት 18+ 18
በጥቅሉ 36ብር የሚፈጅ ሲሆን የትራነስፖርት አማራጮች በሰፊዉ የሚገኙ
እንደሆነና ከዋናው አውቶብስ ተራ እና ከአስኮ መናህሪያ ማግኘት የምትችሉ
መሆኑን እያሳሰብኩ ከመኪና መንገድ ወደ ጸበሉ እና ወደ ቤተክርስቲያኒቱ
ለመድረስ የ15 ደቂቃ ብቻ የእግር ጉዞ የሚያስኬድ መሆኑንም ማስታወስ
እወዳለሁ፡፡


Share #share ማድረግ እንዳይረሳ በ ማርያም

#join #join 👇
👉👉 @embtee
@embtee
@embtee

ለበለጠ መረጃ ይጠይቁን👇👇👇

Inbox 👉 @maryamn123bot
Forwarded from Miki
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለ ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ወርሃዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም
በጤና አደረሳችሁ አደረሰን ! ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል በአማላጅነቱ
በጸሎቱ ለታመኑበት ፈጥኖ የሚደርስ በብለይ እና በሐዲስ ኪዳን በልዪልዩ
ተልኮዎቹ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ፈቃድ በመፈጸም የጸና ሰለሆነ ጥበብ
በመግለጽ በማጽናት በማብሰር ከመከራ በማዳን ከእሳት ወላፈን በመታደግ
ከአንበሳ መንጋጋ በማትረፍ እና ትዕቢተኞችን በመቅጣት በመገሰጽ እውነተኛ
ታዳጊ መልአክ ነው ።ሰለስቱ ደቂቅን እንደታደጋቸው እንደተራዳቸው ዛሬም
በጸሎቱ ለሚታመኑ ዝክሩን ለሚያደርጉ ድረሳኑን የሚደግሙትን በጸሎት
በመዝሙር በቅዳሴ በልዮ ልዮ መንፈሳዊ ክብረ በዓሉን ብናከብር አማላጅነቱን
የተሰጠውን ጸጋ ብንመሰክር በበደላችን ምክንያት ከተግባረ ጽድቅ ለተሰደድን
ስደተኞች ከባሕረ እሳት ለሰጠምን ኃጥያተኞች የምናመልከው የአባቶቻችን
አምላክ መልአኩን ልኮ የእሳቱን ባሕር እንዲያሻግረን የሊቀ መላእክትየቅዱስ
ገብርኤል አማላጅነቱ የሰለሰቱ ደቂቅ በረከታቸው ይደርብን አሜን!
እንኳን ለእናታችን ጽዮን ማርያም ዓመታዊ በዓል አደረሰን
__የታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት______
ኢትዮጵያ ከአርባ ሁለት ጊዜ በላይ ስሟ ተደጋግሞ የተጠቀሰው ሀገረ
እግዚአብሔር ቅድስት ኢትዮጵያ የተወደደችለመሆኗ ነቢያቱ መስክረዋል፡፡
ከነቢያት አንዱ አሞፅም፤ «የእስራኤል ልጆች ሆይ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች
አይደላችሁምን ?» ብሎ እግዚአብሔር መናገሩን ጽፏል /9÷7/፡፡ ከሁሉም ከፍ
ባለመልኩ ነቢዩ ቅዱስዳዊት፤ «ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር
ትዘረጋለች» ብሎ ሕዝበ ኢትዮጵያ እደ ሕሊናውን እና እደልቡናውን ዘወትር
በአምልኮተ እግዚአብሔር፣ በጾምና በጸሎት፣ በምጽዋትና በትሩፋት፣ ዘርግቶ
በሃይማኖት ጸንቶ፣ ምግባር ቀንቶ የሚኖር ሕዝብ በመሆኑ፤ ሕዝበ እግዚአብሔር
ምድሪቱ ሀገረ እግዚአብሔር ተብለዋል፤/መዝ.68÷31/፡፡ለታቦተ ጽዮን ወደ
ኢትዮጵያ መምጣት ዋናው ምክንያት በእስራኤል እና በኢትዮጵያ መካከል
የነበረውየሠመረ ግንኙነት ነው፡፡ ይኽም በመሆኑ የንግሥት ሳባ እና የንጉሥ
ሰሎሞን ግንኙነት ሰፊውን ታሪክ ይዞይገኛል፡፡የንግሥተ ሳባ ዕቃ ግምጃ ቤት
የነበረው ታምሪን ወደ ኢየሩሳሌም ሔዶ ንጉሥ ሰሎሞን ያሠራውን ቤተ መቅደስ
ዓይቶ፣ የሰሎሞንን ጥበባዊ ዝና ሰምቶ በፍጹም መደነቅ ወደ ሀገሩ ተመለሰ፡፡
ያየውንና የሰማውንለንግሥቲቱ አጫወታት፡፡ እሷም የሰማችውን ለማየት ወደ
ኢየሩሳሌም ሔዳ የሰሎሞንን መንፈሳዊና ሥጋዊ ጥበብ ተመልክታ
እግዚብሔርን አመስግና ተመለሰች፡፡ከንጉሥ ሰሎሞን ምኒልክን ፀንሳ
ከኢየሩሳሌም ተነሥታ ባሕረ ኤርትራን ተሻግራ፣ ሐማሴን አውራጃ ስትደርስ
አሥመራ ከተማ በሚገኘው ማይበላ ከተባለው ቦታ ወንድ ልጅ ወለደች፡፡
የሕፃኑንም ስም የንጉሥ ልጅ ስትል «እብነ መለክ» አለችው፡፡ ይኽ ስም በዘመን
ሒደት ምኒልክ ተብሎ ተለወጠ፡፡ምኒልክ ተወልዶ በአእምሮ እያደገ ሲሔድ አባቴ
ማን ነው ? አድራሻውስ ወዴት ነው ? እያለ ጥያቄ ቢያበዛባት በሃያ ሁለት ዓመቱ
ወደ ኢየሩሳሌም ላከችው፡፡ ምኒልክም አባቱ ንጉሥ ሰሎሞንን አግኝቶ ሕገ
ኦሪትንና የዕብራይስጥ ቋንቋ ሲያጠና ከቆየ በኋላ፤ ዐሥራ ሁለት ሺሕ
እስራኤላውያንን አስከትሎ ከምድረ እስራኤል ወደኢትዮጵያ ጉዞውን አቀና፡፡
ከቀዳማዊ ምኒልክ ጋር ለጉዞ የተነሡ ዕብራውያን ከቤተሰቦቻቸው መለየታቸው
ሳያሳዝናቸው ከታቦተ ጽዮን መለየታቸው እጅግ ከበዳቸው፡፡ ወዲያው በፈቃደ
እግዚአብሔር ታቦተ ጽዮንን ከመንበሯ አንሥተው በሊቀመላእክት በቅዱስ
ሚካኤል መሪነት ወደ ኢትዮጵያ ገቡ፡፡ቀዳማዊ ምኒልክ እና እስራኤላውያን ታቦተ
ጽዮንን ይዘው አክሱም የደረሱት ኅዳር 21 ቀን ነበር፡፡ ንግሥተ ሳባም የታቦተ
ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት በጣም ስላስደሰታት በክብር ተቀበለቻቸው፡፡
«ወአንበርዋ ውስተ ሕፅነ ደብረ ሀገረ ማክዳ» እንዲል በአክሱም ከተማ መካከል
ደብረ ማክዳ /ዛሬ ቤተ ጊዮርጊስ ከሚባለው/ ላይ ደብተራ ኦሪት ሠርተው
አስቀመጧት፡፡አሁን ያለው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በዘመናዊ ዐቅድ የታነፀው
የአክሱም ጽዮን ገዳም ቅዳሴ ቤቱ ጥር 30 ቀን1957 ዓ.ም ግርማዊ ንጉሠ
ነገሥት ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ፣ ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ /የታላቋ
ብሪታንያ ንግሥት/ እና ልዑል ፊልፕ ከክብር ባለሟሎቻቸው ጋር በተገኙበት
ተከብሯል፡፡ኅዳር ጽዮን በአክሱም አክሱም ማርያም ጽዮን በኢትዮጵያ ውስጥ
ለሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ መሠረታቸው ስትሆን ከተማዋም የኢትዮጵያ
ሥልጣኔ መነሻ ናት፡፡ አክሱም በሕገ ልቡና የጸናች፣ ሕገ ኦሪትን የፈጸመች፣
በሕገወንጌል ያመነች ናት፡፡ ለዚህም ነው «ሕግ ይወጽእ እምጽዮን፤ ከጽዮን ሕግ
ይወጣል» የሚለው ጥቅስ የሚነገረው፡፡ በዓለ ልደትን በላሊበላ፣ ጥምቀትን
በጎንደር፣ ኅዳር ጽዮንን በአክሱም ጽዮን ሲያከብሩት ልዩ የሆነ ሥርዓት
ስለሚቀርብባቸው ምእመናን መንፈሳዊ ደስታ ይሰማቸዋል፡፡ኅዳር 21 ቀን
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል ነው ብለን በተለየ
መልኩየምናከብርበት ምክንያት፡-
1. በብሉይ ኪዳን ታቦተ ጽዮን የፈጸመችውን ልዩ ልዩ ገቢረ ተአምራትን ለማሰብ
2. ቀዳማዊ ምኒልክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር ሊቀ
ካህናቱን አዛርያስንና ታቦተጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበት ዕለት በመሆኑ
3. በሦስት መቶ ሠላሳ ዓመተ ምሕረት በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት
ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ይሁን ተብሎ ዐዋጅ የታወጀበት
4. ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ምሳሌ ራእይ ያየበት
5. ነቢዩ ሕዝቅኤል በተቆለፈች ቤተ መቅደስ
6. ዕዝራ በቅድስት ሀገር ምሳሌ ራእይ ያየበት
7. አብርሃና አጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል
ቤተመቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴቤቱ የተከበረበት
8. በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያናትን ስታቃጥል
ታቦተ ጸዮንን ይዘው ወደዝዋይ ሐይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር
አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት
ዕለትበመሆኑ በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ
በዓል እናከብራለን፡፡ ይኽ ሲባል ግን በዓሉ የሚከበረው በአክሱም ጽዮን ማርያም
ብቻ ነው ማለት ሳይሆን፤ ታቦተ እግዝእትነ ማርያም ባለችበት ቦታ ሁሉ መከበሩን
ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ ከዚሁ ጋርም የመመኪያችን ዘውድ፣ የመዳናችን
ምክንያት፣የንጽሕናችን መሠረት ስለሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል
ማርያም ያልተነበየ ነቢይ፣ ያልሰበከ ሐዋርያ፣ያልተቀኘ ባለቅኔ ከቶ የለም፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወረደ፣ በቤዛነቱ ዓለምን አዳነ፣ ዳግመኛም
በክበበ ትስብእት፣ በግርማ መለኮት ለፍርድ ይመለሳል ብንል ከቅድስት ድንግል
ማርያም በነሣው ሥጋ በመሆኑ ያለ ወላዲተ አምላክ ምስጢረ ሥጋዌን፣ ነገረ
ድኅነትን፣ ነገረ ምጽአትን ማሰብ ከቶ የማይቻል ነው፡፡ «ዕግትዋ ለጽዮን፤ ጽዮንን
ክበቧት» እንዳለ ነቢዩ፤ ዐሥርቱ ቃላት የተጻፈባትን የእስራኤል አምባና
መጠጊያየሆነችውን ታቦተ ጽዮንን ሌዋውያን ከበዋት ውዳሴ ያቀርቡላት
እንደነበረው፤ ዛሬም እመቤታችን ቅድስትድንግል ማርያምን ካህናትና ምእመናን
ከሩቅ እና ከቅርብ ተሰብስበው በማኅሌት፣ በዝማሬ፣ በቅዳሴና
በውዳሴያከብሯታል፡፡በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቃል ኪዳኑ
ታቦት መካከል ጥልቅ የሆነ ምስጢራዊ ትምህርትአለ፡፡ /ዘፀ. 25÷9-20/፡፡
ይህቺ የቃል ኪዳን ታቦት በደብተራ ኦሪት በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ
የኖረች፣የዮርዳኖስን ባሕር የከፈለች /ኢያ. 3÷14-17/፤ ቅጽረ ኢያሪኮን
ያፈረሰች /ኢያ 6÷1-21/፤ ዳጎን የተባለ የፍልስጥኤማውያንን ጣዖት
የቆራረጠች /1ሳሙ 5÷1-5/፤ በድፍረት ሊነካ የሞከረውን ኦዛን
የቀሰፈች/1ሳሙ 6÷6/፤ በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀምጣ ቤቱን በበረከት
የመላች /2ሳሙ 6÷12/፣ ዳዊትየዘመረላት /2ሳሙ 6÷14/፤ ጠቢቡ ሰሎሞን
በቤተ መቅደስ በክብር ያኖራት /1ነገ 8÷1/፤ የእግዚአብሔርየክብር መገለጫ
ናት፡፡በታቦተ ጽዮን እና በዘመነ ሐዲስ በተገለጠችው በቅድስት ድንግል ማርያም
መካከል ያለውን ረቂቅ እና ድንቅ ምስጢራዊ ንጽጽር አስመልክቶ ሦርያዊው ሊቅ
ቅዱስ ኤፍሬም፤ «ታቦት በወርቅ ልቡጥ እምኩለሔ ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ፤
ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸ በውስጥ በአፍአ በወርቅ የተለበጠ እመቤታችን
ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሐ ጠባይዕ ሳያድፍባትና የቅድስና ባሕርይ
ሳይጎድፍባት በማየት፣ በመስማት፣ በመዳሰሰ፣ በማሽተት አንዳችም እድፍ
ጉድፍ ሳያገኛት በንጽሕናና በቅድስና ጸንታ በኃጢአት ሳትለወጥ ኖራለች፡፡ ጠቢቡ
ሰሎሞንም፤ «አልብኪ ነ
ውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ፤ ምክንያታዊ ነውር ኃጢአት
የሌለብሽ የኃጢአት ሸታ ያልደረሰብሽ ንጽሕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና
ክብርት በልዕልና አንቺ ነሽ» /መኃ 4÷7/ ሲል ተናግሯል፡፡ ታቦተ ጽዮን በከበረ
ወርቅ እንደተሸለመች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በንጽሐ ሥጋ፣
በንጽሐ ነፍስ እና በንጽሐ ልቡና የተሸለመች ያጌጠች መሆኗን ያጠይቃል፡፡ታቦተ
ጽዮን የቃለ እግዚአብሔር ማደሪያ እንደሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያምም
ለአካላዊ ቃል ለእግዚአብሔር ወልድ ማደሪያ ሆናለች፡፡ ይኽንንም ቅዱስ
ኤፍሬም ሲያስረዳ፤ «ኮንኪ ታቦቶ ለፈጣሬ ሰማያት ወምድር ፆርኪዮ በከርስኪ
ተሰዓተ አውርኃ አንቲ ማእምንት ለዘኢያገምርዎ ሰማያት ወምድር፤
ድንግልማርያም ሆይ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ አምላክ ለእርሱ ማደሪያ ሆንሽ
ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀንሸቻልሽው ተሸከምሽው ሰማይና ምድር
የማይወስኑትን ለመወሰን የታመንሽ አንቺ ነሽ» ብሎ ተቀኝቶላታል፡፡ስለሆነም
ከብሉይ ኪዳን እስከ ሐዲስ ኪዳን እግዚአብሔር ራሱን የገለጠበትን የቸርነት
በዓል እግዚአብሔር በፈቀደልን ቦታ ሆነን ስናከብር ከእኛ የሚጠበቀውን በጎ
ነገር እያሰብን በተግባርም እየገለጥን ከበዓሉ ረድኤትና በረከት ተሳታፊ እንሆን
ዘንድ የእግዚአብሔር ቸርነት የእናቱ የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት
አይለየን፡፡የቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እና ምልጃ አክሊልና ጉልላት በሆነው በእናታችን
በወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎት ሁላችንንም ይማረን፡፡
•✙•ወስብሐት ለእግዚአብሔር
•✙•ወለ ወላዲቱ ድንግል
•✙•ወለ መስቀሉ ክቡር
ደጓ እናቴ ማርያም:
#join & #share👉 @embtee


👇ስዐለ አድዐኖ ለመላክ

👇መዝሙሮች ለመላክ

👇በ voice መዝሙርን ለ አምላካችን ለመዘመር👇

👇የተለያዩ መፀሀፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶች

👇ትምህርተ ወንጌል ስብከት

👇የተለያዩ ሀሳቦችን


ለመላክ👇👇👇👇👇👇



👇👇👇👇👇👇👇👇just contact us
ይላኩልን👇
@maryamn123bot
@maryamn123bot
@maryamn123bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
ቅዱሳን ስዕላት.pdf
1.6 MB
👆👆👆
ቅዱሳት ስዕላት
@And_Haymanot
👉መንፈሳዊ ስዕልና መጽሐፍ ቅዱስ
👉ስዕልና ጣዖት
👉ስዕልና የፕሮቴስታንት መንትያ አቋም
👉በስዕል ፊት ጸሎት ማድረግና መስገድ
👉ስዕልና ክርስትና
ሁሉንም በዚህ pdf አዘጋጅተናል
ይጠቀሙት(ለሌሎችም share)
@And_Haymanot
@And_Haymanot
“ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል
መሠረታት።” መዝ. 86/87፥5
እንኳን ለእመቤታችን ለጽዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳቹ
በምን በምን እንመስላት ድንግል ማርያምን "፪"
ምሳሌ የላትም የላትም ክብራን የሚመስል "፪"
የሙሴ ጽላት ነሽ የምሕረት ቃል ኪዳን
የያዕቆብ መሰላል የአብርሃም ድንኳን
የብርሃን መውጫ የኖኅ ድንቅ መርከብ
የመላእከት እኅት የርህሩሃን እርግብ "፪"
………..አዝ……
የሰሎሞን አክሊል የአሮን በትር
የዕዝራ መሰንቆ የጌዴዎን ፀምር
ድንግል እናቴ ናት የጽድቃኖች በር
ሆና የተገኘች የአምላክ ማኅደር፡"፪"
………..አዝ……
የቅዱሳን እናት የአርያም ንግሥት
ስለ ተሸከመች መለኮት እሳት
በሥጋችን ፈቃድ ወድቀን እንዳንጠፋ
አማልዳ ታስምረን ከዚህ ዓለም ጣጣ "፪"
………..አዝ……
ከማር ይጣፍጣል የድንግል መዓዛ
አምላክን አቅፋለች በሁለት እጇ ይዛ
ዓለሙን የዳነ በልጅሽ ነውና
እናታችን ጽዮን ይድረስሽ ምሥጋና "፪"
ንፅህተ ንፁሐን

ንፅህተ ንፁሐን ከዊና ከመታቦት ዘዶር ዘሲና
ውስተ ቤተ መቅደስ ነበረት በድንግልና ነበረት
ሲሳያ ህብስተ መና ወስቴ ሀኒ ስቴ ፅሙና

ስታድጊ በቤተመቅደስ
በቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈስ
አጊጠሽ በትህትና
ተውበሽ በቅድስና
ምግብሽ የሰማይ መና
ከምድር አደለምና
አካላዊ ቃል መርጦሻል
ትውልዱ ብፅዕት ይሉሻል

መልዐኩ ፋኑኤል ወርዶ
በክንፉ ለብቻሽ ጋርዶ
መገበሽ ህብስተ መና
አቅርቦ ስግደት ምስጋና
ምግብሽ የሰማይ መና
ከምድር አደለምና
አካላዊ ቃል መርጦሻል
ትውልዱ ብፅዕት ይሉሻል

ሐርና ወርቁ ተስማምቶ
አጌጠ በእጅሽ ተሰርቶ
በመቅደስ ያለው ማህሌት
አስናቀሽ የአባትሽን ቤት
ምግብሽ የሰማይ መና
ከምድር አደለምና
አካላዊ ቃል መርጦሻል
ትውልዱ ብፅዕት ይሉሻል
👇👇👇👇👇
👉ይላኩልን @maryamn123bot