ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#እንኳን ለበዓለ ዕርገቱ በሰላም #አደረሳችሁ

"፤ እስከ #ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ #ባረካቸው። ሲባርካቸውም #ከእነርሱ ተለየ ወደ #ሰማይም #ዐረገ።"
(የሉቃስ ወንጌል 24÷50-51)

"አምላክ በእልልታ፥ #እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ። #ዘምሩ፥ ለአምላካችን #ዘምሩ#ዘምሩ፥ ለንጉሣችን #ዘምሩ "
#መዝ 46÷5 -6

#እየባረካቸው ወደላይ አቀና(2)
መዳኃኔ ዓለም (2) ዐረገ በክብር ደመና (×2)
*********
#ተሰብስበው ሳሉ ሁሉም በአንድነት
በመካከል ቆሞ ሥግው መለኮት
ባረካቸው ፤ ቀደሳቸው (2)
ዐረገ በዓይን እየታያቸው
አዝ >> >> >>
#እንዲልክላቸው አጽኙን መንፈስ
ከላይ ከአርያም ከአባቱ ሲደርስ
ኃይል ሆናቸው ፤ አጸናቸው (2)
በቃሉ አንድ አደረጋቸው
አዝ >> >> >>
#በአንድነት ሆነው ኢየሩሳሌም
ተስፋ ሲጠብቁ ከላይ ከአርያም
መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል(2)
ወረደ በምህረት ወሣህል
አዝ >> >> >>
#መላእክት በሰማይ እልል እልል አሉ
ዕርገቱን አጅበው ምስጉን ነህ እያሉ
የሰማይ ደጀ ተከፈቱ (2)
ዘመሩ ሊቀ መላእክቱ
አዝ >> >> >>
#እልልል.....#እልልል.... #እልልል.....👏👏👏👏
መዝ 46(47)÷5-6 ሉቃ 24 ÷50
ሐዋ 1÷8-9

#ግንቦት ፲ ቀን ፳ ፻ ፲ ዓ.ም
#እንኳን ለበዓለ ዕርገቱ በሰላም #አደረሳችሁ

"፤ እስከ #ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ #ባረካቸው። ሲባርካቸውም #ከእነርሱ ተለየ ወደ #ሰማይም #ዐረገ።"
(የሉቃስ ወንጌል 24÷50-51)

"አምላክ በእልልታ፥ #እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ። #ዘምሩ፥ ለአምላካችን #ዘምሩ#ዘምሩ፥ ለንጉሣችን #ዘምሩ "
#መዝ 46÷5 -6

#እየባረካቸው ወደላይ አቀና(2)
መዳኃኔ ዓለም (2) ዐረገ በክብር ደመና (×2)
*********
#ተሰብስበው ሳሉ ሁሉም በአንድነት
በመካከል ቆሞ ሥግው መለኮት
ባረካቸው ፤ ቀደሳቸው (2)
ዐረገ በዓይን እየታያቸው
አዝ >> >> >>
#እንዲልክላቸው አጽኙን መንፈስ
ከላይ ከአርያም ከአባቱ ሲደርስ
ኃይል ሆናቸው ፤ አጸናቸው (2)
በቃሉ አንድ አደረጋቸው
አዝ >> >> >>
#በአንድነት ሆነው ኢየሩሳሌም
ተስፋ ሲጠብቁ ከላይ ከአርያም
መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል(2)
ወረደ በምህረት ወሣህል
አዝ >> >> >>
#መላእክት በሰማይ እልል እልል አሉ
ዕርገቱን አጅበው ምስጉን ነህ እያሉ
የሰማይ ደጀ ተከፈቱ (2)
ዘመሩ ሊቀ መላእክቱ
አዝ >> >> >>
#እልልል.....#እልልል.... #እልልል.....👏👏👏👏
መዝ 46(47)÷5-6 ሉቃ 24 ÷50
ሐዋ 1÷8-9

#ግንቦት 28 ቀን 2011 ዓ.ም
#አባቴ_ነውና_አዎን አውቀዋለሁ !
______

#ያለ_ተክለ_ሃይማኖት_ጸሎትና_ረድኤት
#ለኢትዮጵያ_ሰዎች_የመዳን_ተስፋ_የላቸውም

ሰይፍ አርእድ በተባለ በነዋየ ክርስቶስ መንግሥት ደግሞ ከንጉሥ ሠራዊት አንዱ ወደ ዋሊ ገዳም ሄደ ።ሁለት መነኮሳት አግኝቶ እጅ ነሳቸው ፤ ከወዴት ነህ? አሉት? ከሸዋ ክፍለ ሀገር ከዚያው ግራርያ ከምትባል አውራጃ ነኝ አላቸው። ተክለ ሃይማኖት የሚሉትን ታውቀዋለህ ? አሉት። #አባቴ_ነውና_አዎን_አውቀዋለሁ አላቸው።

#ወደ_መቃብሩ_ደርስሃል ? አሉት። አዎን ደርሻለሁ አላቸው። እነዚያም መነኮሳት ተነስሀው ሰገዱለት የእግሮቹንም ትቢያ ይልሱ እጆቹንም ይስሙ ጀመሩ። ጭፍራውም ጌቶቼ ይህንን ስለምን አደረጋችሁ?? አላቸው ። እኛ እናውቃለን አሉት። ዳግመኛም በተክለ ሃይማኖት የመቃብር ቦታ ሥጋ ወደሙን ተቀበልክን? አሉት። አልተቀበልኩም አላቸው። ከቅዱሱ መቃብር ዘንድ ቁርባን ያልተቀበልክ #እቡዘ_ልብ_ለምን_ሆንክ ? የተክለ ሃይማኖት አጽም ካረፈበት ቦታ ቁርባንን የተቀበለ ሁሉ ሲዖልን ዐያይም ሲል ከጌታ አንደበት በእውነት ሰማን ብለን በእውነት እንነግርሃለን አሉት።

#በውስጧም የሚቀበር ለዘለዓለም እንዳይጎዳም እኛም መንፈስ ቅዱስ በየሰዓቱ ይልቁንም በቁርባን ጊዜ እየወረደ በውስጧም መሥዋት ለሚያቀርቡ መዐዛ ያለውን ሽቱ ሲቀባቸው ዘወትር እናያለን ፤እንደ ብርሃን ደመና በላይዋ የረበበ ነው እንጂ ለሊትና ቀን ከእርሷ መንፈስ ቅዱስ አይርቅም።
እንዲሁ ዘወትር ይኖራል።በእርሷም የተቀመጠ የቆመ በውስጧም የተቀበረ በረድኤቷም የተጠጋ የተመሰገነ ነው። #ያለ_ተክለ_ሃይማኖት_ጸሎትና_ረድኤት_ለኢትዮጵያ_ሰዎች_የመዳን_ተስፋ_የላቸውም ። አሉት
ሌላም የተሰወረ ምሥጢር ነገሩትሌላውን ግን ልንጽፈው አንችልም መጽሐፍ የምንገልጠውም የምንሰውረውም ነገር አለ እንዳለ ይንንም ብለውት ከእርሱ ተሰወሩ።

" #አዎን_ለምንፍገመገም_ለኛ_ለኢትዮጵያውያን ያላንተ ረዳት የለንምና #ምልጃህ አትለየን " #አሜን!

#ገድለ_ተክለ_ሃይማኖት ምዕራፍ 50/60

አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ጥንተ ጽሕፈቱ #ግንቦት 11/2014ዓ.ም