ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
ስለ ጥያቄዎ ከልብ እናመሰግናለን የሕይወትን ቃል ያሰማልን
#የናሆም መድኃኒት ፣ የኢያሱ የምስክርነት ሃውልት ፣ የኤልያስ የወርቅ መሶብ ፣የነቢያት ትንቢትና ምሳሌ የሆነች እመቤታችንን የመሰሏትን ነገሮች (ምሳሌዎቿን) መጨረስ አይቻልም ነገር ግን ጥቂቶቹን ከመጠነኛ ማብራሪያ ጋር እነሆ

#የአዳም_ተስፋ_ሔዋን ዘፍ 2፥24
እጸ በለስን ከበሉ በኃላ አዳም አንቺ ነሽ ያሳሳትሽኝ ብሎ ሔዋንን ተጣልቶ አባሯት ነበር መላእከ እግዚአብሔር ተገልጾ ዳግመኛም የምትድነው በእርሷ ነውና ሄደህ ፈልገህ አምጣት ብሎታል ፈልጎም አምጥቷታል። ከዚህ በኃላ ዳግሚት ሔዋን እመቤታችን ተስፋ ሆና እንደምትሰጠው አውቆ አባታችን አዳም ሚስቱ ሔዋንን ሕይወቴ ነሽ ብሎ በአንጻር በምሳሌ ይጠራት ነበር። ስለዚህ ዳግሚት ሔዋን እመቤታችን በቀዳማዊት ሔዋን በአዳም ሚስት ትመሰላለች ምሳሌ ከሚመሰልለት ዋና ነገር እንደሚያንስ ሁሉ ምሳሌዋ ቀዳሚት ሔዋንም(የአዳም ሚስት)ከዳግሚቱ ሔዋን(ከእመቤታችን) በእጅጉ ታንሳለች ።

-ቀዳሚት ሔዋን የዲቢሎስን የሐሰት ቃል ሰማች
- #ዳግሚት_ሔዋን የመላእኩ የእውነት ቃል አደመጠች
-ቀዳሚት ሔዋን የሞት ፍሬ በላች
- #ዳግሚት_ሔዋን ኤፍራታ ግን የሕይወት ፍሬ አፈራች
-ቀዳሚት ሔዋን እንደ ስሞ የሕያዋን እናት መሆን ተሳናት
- #ዳግሚት_ሔዋን የሕያዋን ሁሉ ሕያው እናት መሆን ተቻላት
-ቀዳሚት ሔዋን በአዳም ምክንያት በዘር ጸነሰች
- #ዳግሚት_ሔዋን በመንፈስ ቅድስ ምክንያት ያለ ዘር ጸነሰች
-ቀዳሚት ሔዋን እንደ ተፈጥሮ ድንግልናዋን አጥታ ጸነሰች
- #ዳግሚት_ሔዋን በድንግና ጸነሰ
-ቀዳሚት ሔዋን በሕማምና በምጥ ወለደች
- #ዳግሚት_ሔዋን ያ ሕማምና ያለ ምጥ ወለደች
-ቀዳሚት ሔዋን ታላቅና ታናሽ የሆኑ እርስ በእርስ የሚገዳደሉ ሞችና ገዳይ ልጆችን ወለደች
- #ዳግሚት_ሔዋን ግን ቀዳሚ ተከታይ የሌለው አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ በድንግልና ወለደች

#የአቤል የዋህት ዘፍ 4÷8
ወንድሙ ቃየን ና ውኃ እንጠጣ ብሎ በድንጋይ ጭኖ የገደለው አቤል እጅግ የዋሕ በመሆኑ ነው ። ይህ የአቤል የዋህነት የእመቤታችን ምሳሌ ናት ። የአቤል ልቡና የዋህት ፣ቅን ፣ደግ እንደሆነች እመቤታችንም እንኳን ለሰው ለተጠማ ጥቁር ውሻ የምትራራ እርርይተ ልቡና ነችና የአቤል የዋህት (ደግነቱ ፣ቅንነቱ) ትባላለች። ለቅኖች ደግሞ ምሥጋና ይገባልና በሰማይ በማሕበረ መላእክት በምድር በደቂቀ አዳም ሁሉ ለዘለዓለሙ ትመሰገናለች።መዝ32(33)፥1

#የጌዲዮን ጸምር መጻ መሳ(6)(7)

#የኤልሳዕ_አዲስ_ማሰሮ 2ነገ 2፥20
የፀነሱ ሴቶች ሲጠጡት የሚያሶርዳቸው ወላድ ወንዶችን በጠጡት ጊዜ የሚያኮላሻቸውን የተመረዘውን ማየ ግብጽ (የግብጽን ውኃ) ኤልሳዕ የፈወሰላቸው ጨው የተጨመረባት አዲስ ማሰሮ በመጠቀም ነበር :: ጨው የጨመረበትን ማሰሮ የተመረዘውን ውኃ ቀድቶ ከጨመረበት በኃላ መልሶ ወደ ወንዙ ቢያፈሰው ወንዙ እንደ ቀድሞ ደህነኛ ውኃ ሆነ አዲሷ ማሰሮ የእመቤታችን በውጧ የጨመረው ጨው የልጇ የክርስቶስ ምሳሌ ነው :: ስለዚህ እመቤታችን አልጫው ዓለም የጣፈጠባት፤ የመጣፈጣችን ምክንያት የሆነች ጨው ክርስቶስ የተገኘባት አዲስ ማሰሮ ነች ::


#የሙሴ ጽላት ዘጸአት 24፥12
ታቦት ማደሪያ ሲሆን ጽላት ደግሞ ሰሌዳ መጻፊያ የፊደሉ ቅርጽ ማረፊያ ወይም ያረወበት ማለት ነው ። እመቤታችን ታዲያ የአምላክ ማደሪያ ማህደረ መለኮት በመሆኗ ታቦት የፊደል ክርቶስ መቀረጫ ጽሌ በመሆኗ ደግሞ ጽላት እየተባለች በሁለቱም በማስተባበር ትጠራበታለች ። በጽላት አስርቱ ትዕዛዛቶ እንደተቀረጸ በእመቤታችንም የሕይወት ፊደል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተቀርጾባታልና ይልቁኑ እርሷ በንጽሕና የተጻፈች ፊደል ናት ማ ር ያ ም!

#ሙሴ ያያት የሲና ዕፀ ጳጦስ ዘጽ3፥2
አመልማል ከነበልባል ነበልባልም ከአመልማል ተዋሕደው በአንድነት ሆነው ሙሴ በደብረ ሲና ተመልከቶ ነበር የሚገርመው አመልማሉ ዘነበልባሉ አይቃጠልም ነበር ነበልባሉም በአመልማሉ አይጠፋም ነበር :: ምነው እንዴት ቢሉ ምሥጢረ ተዋሕዶ ነውና አመልማል የሥጋ ፤ነበልባል ደግሞ የመለኮት አምሳል ነው :: ነበልባሉ አመልማሉን እንዳላቃጠለው ነበልባል የሚባል መለኮትም በድንግል ማርያም ማህፀን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሶም ነፍስ ነስቶ 9ወር ከ5 ቀን ሲቆይ ድንግል ማርያምን አላቃጠላትም ስለዚህ ሙሴ ነበልባል ታቅፋ ያያት አመልማል የእመቤታችን ምሳሌ ናት:: (ማርያም ተአቢይ እምኩሉ ፍጥረት ሕያዋያ አሳተ መለኮት) ማርያም ትበልጣለች ከሁሉም ፍጥረት ስለ ያዘች እሳተ መለኮት እያልንም እንዘምርላት ዘንድ ተገባት።

#የአብርሃም_ድንኳን ዘፍ 13÷1-18
በአብርሃም ድንኳን ቅድስት ሥላሴ ተስተናግደዋል በእመቤታችንም በቅድስት ድንግል ማርያም ሥላሴ በጉልዕ ተገልጠዋል :: ከእመቤታችን መገኘት በፊት የሥላሴ ምሥጢር በጎላ በተረዳ ነገር አይታወቅም ነበር የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በፍጥረቱ ዘንድ በእጅጉ የጎላውና የተረዳው በድንግል ማርያም ምክንያት ነው:: እንደ እመቤታችን እንደ ማርያም የአብ ማረፊያ የሆነ ማነው ? እንደ እመቤታችን እንደ ማርያም የወልድ ማደሪያ የሆነ ማነው ? እንደ እመቤታችን እንደ ማርያም የመንፈስ ቅዱስ ንጽሕ አዳራሽ የሆነስ ማነው? /እንዲል ተአምረ ማርያም መቅድም/

#በጉ_የተያዘበት_ዕፀ_ሳቤቅ ዘፍ 22፥13
አብርሃም የእምነቱ ጽናት እንዲገለጥ አንድ ልጅህን ሰዋልኝ የሚል ጥያቄ ከእግዚአብሔር ቀረበለት በእስተ እርጅናዬ ያገነውት የምወደው አንድ ልጄን አልሰዋልህም ሳይል የምትነሳኝ ከሆነ ለምን ሰጠህኝ ብሎም ሳያማርር እሺ በጄ ብሎ ልጁ ይስሐቅን የመሰዋይቱን እንጨት አሸክሞ እራሱ ደግሞ ቢላዋን ይዞ ወደ ሞሪያም ተራራ ወጣ ይስሐቅም አባቴ የመሰዋቱን እንጨት እኔ ይዣለሁ መሰዊያውንም ቢላዋ አንተ ይዘሃል መሰዋይቱ ግን አይታየኝም የታለ? አለው አብርሃምም እርሱን #እግዚአብሔር ያዘጋጃል አለው የልጁ የይስሐቅ አሳዛኝ የልጅነት ንግግር ሳያባባው ምሰዋይት አድርጎ ያቀርበው ዘንድ ቆረጠ ለእግዚአብሔር በፍጹም ታምኟልና ከፍቅረ ልጅ ይልቅ ፍቅረ እግዚአብሔር አገብሮታልና። በደረሱ ጊዜም ልጄ ይስሐቅ ሆይ መሰዋይቱ አንተ ነህ እግዚአብሔር አንተን እሰዋለት ዘንድ ወዷል አለው ይስሐቅም አንተ ጨካኝ አባት ሳይል በእሺታ በመሰዊያው ላይ ወጣ አባቴ ዐይን ዐይኔን እያየህ ስቁለጨለጭብህ አዝነህ ትተወኝና ከፈጣሪ እንዳትጣላ በጀርባዬ ገልብጠህ ሰዋኝ አለው እዳለውም አድርጎ ሊሰዋው ሲዘጋጅ አብርሃም አብርሃም በልጅህ ላይ አዳች እንዳታደርግ ተባለ ዞር ሲልም ቀንዶቹ በእጸ ሳቤቅ የተያዘ በግ አየና በይስሐቅ ፈንታ እርሱን መሰዋት አቀረበ:: በዚህም የእግዚአብሔር ቸርነት የአብርሃም እምነት የይስሐቅም ፍጽም ታዛዢነት ተገለጠ።
#አብርሃም የእግዚአብሔር አብ
#ይስሐቅ የአዳም
#በጉ የእግዚአብሔር ወልድ(የኢየሱስ ክርስቶስ )
#በጎን በቀንዱ በኩል አስራ የያዘችሁ እፀ ሳቤቅ የእመቤታችን ምሳሌ ናቸው።

ሥልጣን ኃይል ብርታት በመጻሕፍ ቅዱስ አገላለጽ " ቀንድ " ተብሎ ይገለጻል ። “ሐናም ስትጸልይ እንዲህ አለች፦ ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፥ ቀንዴ በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህ ደስ ብሎኛል።” 1ኛ ሳሙኤል 2፥1
“ቀንዴ አንድ ቀንድ እንዳለው ከፍ ከፍ ይላል፤ ሽምግልናዬም በዘይት ይለመልማል።” መዝ 92፥10

ቀንድ በከብቶች ሕይወት ውስጥ ሰፊ ሚና አለው ከብቶች የቀንድ ከብት እና የጋማ ከብት ተብለው ለሁለት ይከፈላሉ ታዲያ የቀንድ ከብቶች እራሳቸውን ከጥቃት