Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Eyob kinfe)
"ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት" የዘወትር ጸሎታችን ነው።አስቀድሞ በማኅፀነ #ድንግል ሥጋችንን ቃል ስለተዋሐደው በባሕርይ አምላክነት (በፈጣሪነት) ዐርጓል (ከፍ ከፍ ብሏል)።ሆኖም ግን እስከ ትንሣኤ ድረስ የትሕትናን ሥራ ከልዕልና ጋር ሲሠራ ቆይቷል።ከትንሣኤ በኋላ እስከ ዐርባ ቀን ድረስ ምሥጢረ መንግሥተ ሰማያትን ለቅዱሳን #ሐዋርያት ሲያስተምር ቆይቶ በአርባኛው ቀን በግርማና በስብሐት ወደ ሰማይ ዐረገ፤በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ።
አካላዊ ቃል ከድንግል #ማርያም ነሥቶ የተዋሐደው ሥጋ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ የሆነው ማለትም ምልዐትን፣ ስፋትን ፣ርቀትን የአብ ልጅነትን ገንዘብ ያደረገው ቃል ሥጋን በተዋሐደበት (ጌታ በተፀነሰበት) ቅጽበት ነው።ዳግመኛ በትሕትና ሥራ ላይገለጥ ከብሮ የታየበት በዓሉ ደግሞ ዕርገት ነው።
"ታስበው ዘንድ ሰው ምንድነው" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ባለ ክብር ሰውነታችንን ያከብር ዘንድ በእውነት እኛ ምንድነን?ዛሬ የእኛ ሰውነት በቅዱሳን በመላእክት ታጅቦ ወደ ሰማይ ወጣ።ድል ነሥቶ በአብ ቀኝ ተቀመጠ።
"በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ" ስንል ክርስቶስ ከአባቱ ቀኝ ተለይቶ ኖሮ ኋላ
ወደ አባቱ ቀኝ የሄደ አይደለም።ሰው የሆነበትን ዓላማ ፈጽሞ ሰይጣንን አሥሮ ሰውን ነፃ አውጥቶ በድል ነሺነት በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ ማለታችን ነው።
#ዕርገትን ስናስብ
#የእግዚአብሔርን ውለታ እናስባለን (እኛን ያከበረበትን ክብር)
#ያዘጋጀልንን መንግሥተ ሰማያት እናስባለን።ተስፋችን ይለመልማል።
“ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።”(ዮሐ 14፥3) "ሄጄም" ሲል ዕርገቱን ተናገረ።
#የዳግም ምጽአትን ፍርድን በማሰብ ራሳችንን እናዘጋጃለን።
“የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው #ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው።”(ሐዋ 1፥11)
#በመንግሥተ ሰማያት የሚኖረንን ዕርገታዊ ሕይወት እናስባለን።
በክብር ላይ ክብር፣በጸጋ ላይ ጸጋ፣በጣዕም ላይ ጣዕም፣በመዓዛ ላይ መዓዛ በማያቋርጥ ከፍ ማለት መኖራችንን ተስፋ እናደርጋለን።
"የሙታንን መነሣት የሚመጣውንም ሕይወት ተስፋ እናደርጋለን" "የሚመጣው ሕይወት" ምንድንነው?ከትንሣኤ በኋላ የሚኖረን የማያቋርጥ ሱታፌ #አምላክ (#እግዚአብሔርን መምሰል) ነው እንጂ!!!
ከበዓለ ዕርገቱ ረድኤት በረከት ያሳትፈን!!
#ኢዮብ ክንፈ
ግንቦት 21/2017 ዓ.ም