ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
የዛሬው ባለ ታሪክ ደግሞ ሌንጌኖስ ይባላል
ዘመነ መስቀልን በማገናዘብ የተመረጠ ወቅታዊ ታሪክ ነው።


#ከዮናናውያን ወገን ሲሆን የሮማ ወታደር ነው፡፡ ጲላጦስ ጌታችንን እንዲሰቅሉት ለአይሁድ አሳልፎ ሲሰጠው ይህ ለንጊኖስ ከጲላጦስ ጭፍሮች ውስጥ አንዱ ስለነበር የጌታችንን ሥቃይ አይቶ በክፉ ግብራቸው ላለመተባበር ብሎ ከአካባቢው ሸሽቶ ሄደ፡፡ በዕለተ አርብ ግን ሮማውያን በጌታችን መከራ ያልተባበረውን ሁሉ እንደ ንጉሥ ጠላት ስላዩት መድኃኔዓለም ክርስቶስ በመጨረሻዋ ሰዓት ‹‹ተፈጸመ›› ካለ በኋላ ለንጊኖስ ወደ ቀራንዮ ተራራ ወጣ፡፡ በሁለት ወንበዴዎች መካከልም ተገርፎ የተሰቀለውን አይቶ ልቡ በአዘን ተመላ በሀገራቸው የተገረፈ እንደማይሰቀል የሚሰቀልም እንደማይገረፍ ያውቅ ነበርና የክርቶስን የተሰቀለ ገላ ሲያይ የግርፋቱን ሰንበር አስተዋለ ያለ ሕግም በግፍ ገርፈው እንደሰቀሉት አወቀ ። ሮማውያኑም የሁለቱን ሽፍቶች አጥንቶች ሲሰብሩ ሌንጌሎስም አልተባበረንም ብለው ይቃወሙኛል ንጽህ እንደሆነና በግፍ እንደተሰቀለ ባውቅም እኔም አንዳች ነገር ማድረግ አለብኝ ብሎ ሀሰበ አስቦም አልቀረ ለንጊኖስ ያላመነበትን ነገር አደረገ ደግሞ ከሞተ መቼም አልጎዳውም ብሎ አስቦ የጌታችንን በጦር ጎኑን ወጋው፡፡ በዚያም ጊዜ አንድ ዐይኑ ዕውር ነበርና ከጌታችን ከግራ ጎኑ ውኃና ደም ሲወጣ የታወረች ዐይኑን ቢነካው ዐይኑ በራችለት፡፡ ሆኖም ግን ዐይነ ልቡናው በሰራው ሥራ በተራዋ በጸጸት ታወረችበት ።


#ውድ የመርሐ ግብር ታዳሚዎቻችን እርሶ ሮማዊውን ወታደር ሌንጌኖስን ቢሆኑ ምን ያደርጉ ነበር?
👉እኔ ሥራዬ ነው የሰራሁት ጥፋት የለብኝም ይላሉ? ወይስ
👉ንጽሕናው ከገባኝ ሥራዬን እንኳ እለቅ ነበር ይላሉ? ወይስ ደግሞ
👉ከሰዎች ከምለይ ሰዎችም ከሚያገሉኝ የማላምንበትንም ነገር ቢሆን ሰርቼ ጌታዬን እወጋዋለው ይላሉ?

👩‍🚀ሮማዊው ወታደር ምክሮቻችሁን ይጠብቃል👨‍🚀

እርሶ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE

ዓውደ ምሕረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit